💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
القارئ ناصر القطامي | ومن يهد الله فهو المهتد
💭🌸خدمة تلاوات🎧
•|تلاوة صباحية

﴿وَمَن يَهْدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلْمُهْتَدِ ۖ وَمَن يُضْلِلْ فَلَن تَجِدَ لَهُمْ أَوْلِيَآءَ مِن دُونِهِۦ ۖ وَنَحْشُرُهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَـٰمَةِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمْ عُمْيًا وَبُكْمًا وَصُمًّا ۖ مَّأْوَىـٰهُمْ جَهَنَّمُ ۖ كُلَّمَا خَبَتْ زِدْنَـٰهُمْ سَعِيرًا ۝﴾

🎙القارئ : ناصر القطامي

=
t.me/https_Asselefya1
አንድ አንድ ነገሮች ባሰብነዉ ልክ  አይሄዱልንም፣ሁሉም ነገር ለበጎ
ስለሆነ ሶብር ማድረግ ያስፈልጋል።

=

t.me/https_Asselefya1
31-العبودية - لشيخ الإسلام ابن تيمية
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም
አዲስ ተከታታይ ትምህርት


📚 العبودية لشيخ الإسلام ابن تيمية

ክፍል 31

ፉሪ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ

🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም

𝐓𝐞«t.me/SheikhMuhammedZainAdam
በስደት አለም የቆየዉን ያክል ሰዉ ቆይቶ
በሰላም በሙሉ ጤና ወደ ሀገር መመለስ ትልቅ ነገር ነዉ ከዶዬ የኔ የዋህ እንኳን ደስ አለሺ በጉጉት ስትጠብቄት የነበረችዉ ቀን ዛሬ ደረሰች አልሀምዱሊላህ አላህ በሰላም ከምትወጃቸዉ ቤተሰቦቼሽ ያገናኚሺ! በስደት ቆይታ ካገኘሁሽ ስአት ጀምሮ እስከ አሁኗ ስአት ድረስ ደስ የሚል ጊዜ ነበሩ ያሳለፍናቸዉ የኔ ምርጥ እህት ሀገርም እንገናኛለን ኢንሻ አላህ አላህ በሄድሽበት ሁሉ መልካሙን እመኚልሻለሁ ሰላም ግቢ ብሎ መሸኘት ቀላል ይመስላል ግን ጓደኛ መለየት ይከብዳል በሀቂቃዉ ነገር ግን የአላህ ዉሳኔ ነዉ ሰላም ግቢልኝ እህት አለሜ ከድጃ ቢንት ዳዉድ እወድሻለሁ🥀

አልሐምዱሊላህ!
መንገድሽ ይጠረግ አይኑረው እንቅፋት
ለኔም ዱዓ አርጊልን እንዲበቃኝ ስደት
ከኔ መራቅሽን ምንም ባልወደውም
ላገር መብቃትሽን ፈፅሞ አንጠላውም
በሠላም ተገናኝ ከቤተሠቦችሽ
ዲኑን ተማማሩ ከእህት ወንድሞችሽ
ተውሒድ ሡና ፋፍቶ ቢድዓ እንዲሟሽሽ
ይህ ነው ምኞቴን የሡናዋ እህትሺ

✍️𝑩int 𝑨ragaw
=
t.me/https_Asselefya1
ንግግር የብዙዎች ሲሆን ተግባር ደግሞ ለጀግኖች የሚሰጥ ልዩ ሽልማት ነዉ።

=

t.me/https_Asselefya1
لاتيّأس وأنتَ تعلمُ أنْ الله يَخلُق دوماً نوراً جَديداً بعد كُل ظلام
🫧

«اللَّهُمَّ بِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوتُ وَإِلَيْكَ النُّشُورُ»

أذكَار الصَباح

=
من أفضل الصِّيَّام في شعبانَ صيامُ أيَّام البيض: الثالثَ عشرَ، والرابعَ عشرَ، والخامسَ عشرَ، وهي توافق في سَنَتِنَا هذه ببلدنا الجمعة ويومين بعدها.

📝 الشيخ صالح العصيمي
الخميس ١٢ شعبان ١٤٤٥
=
ስ ለ ሻዕባን ወር አጫጭር ጥቆማዎች 


በሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን

«ሙስሊሞች ሆይ ያለነው በሻዕባን ወር ላይ ነውና በዚህ ወር ዙርያ አንድ ስድስት ነጥቦችን በማውሳት ልንከተለው ስለሚገባን ግዴታችን እናብራራለን።

📍የመጀመርያው ነጥብ
የሻዕባን ወር ከሌሎች ወራት በተለየ ሁኔታ በፆም ይለያልን? አዎን ይለያል ። ምክንያቱም ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] «በዚህ ወር ፆም ያበዛሉ። ከወሩ ጥቂት ቀናት እስኪቀራቸው ወሩን ይፆሙት ነበርና።»
በዚህም ሱና መሰረት የአላህ መልእክተኛን [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] በመከተል በዚህ በሻዕባን ወር ፆም ማብዛት አለብን።

📍ሁለተኛው ነጥብ
የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ፆምን የተመለከተው ነው። ይህንን ቀን ለይቶ መፆምን የሚመለከቱ ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኙና ትክክለኛ ያልሆኑ ደካማ ሀዲሶች ተነግረዋል። በነዚህ ተመርኩዞ ይህንን ዒባዳ መፈፀም ደግሞ አይቻልም። ከነቢዩ ለመተላለፉ ባልተረጋገጠ ማንኛውም ነገር አላህን ማምለክ አይፈቀድም። በመሆኑም የሻዕባን አስራ አምስተኛው ቀንን ለይቶ መፆም የሌለ ነገር ነው። ከመልእክተኛው ለመገኘቱ መረጃ ከሌለ ደግሞ ቢደዐ ነው።

📍ሶስተኛው ነጥብ፤ የሻዕባን ወር አስራ አምስተኛው ቀን ሌሊት ትሩፋትን ይመለከታል።
ልክ ቀኑን መፆም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለው ሁሉ ለሌሊቱም ከሌሎች ሌሊቶች በላጭ ነው ተብለው የተነገሩት ሀዲሶች ከነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለመነገራቸው ትክክለኛ መረጃ የሌላቸው ደካማዎች ናቸው።
ስለሆነም የሻእባን አጋማሽ ሌሊት ልክ እንደ ረቢዕ ወር ሌሊት፣ እንደ ረጀብ ወር ሌሊት እንጂ የተለየ ነገር የለውም። ተነገረ የተባለውም መረጃ ቀድሜ እንደገለፅኩት ደካማዎች ናቸው።

📍አራተኛው ነጥብ
ይህችን የአስራ አምስተኛዋን ሌሊት ለየት አድርጎ ዝግጅት ፈጥሮ ማሳለፍ ቢደዐ ነው። ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለየት አድርገው ያሳዩን፣ ሌሊቱን የሚሰገድ አምልኮትም ዝግጅትም የለምና። ስለዚህ ምሽቷ ልክ እንደ ሌሎች ምሽት ናት። አንድ ሰው ከዚያች ሌሊት በፊትም የለይል ሰላት መስገድ ልምዱ ከነበረ በዚያች ሌሊትም ተነስቶ መስገዱ ልክ እንደበፊቱ ነውና ችግር የለውም። ካልሆነና በፊት የማይሰግድ ከነበረ ዛሬ በሻዕባን "ለይለቱ ኒስፍን" ለየት አድርጎ መስገድ የለበትም። ምክንያቱም ከአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኘ ተግባር ነውና። ከዚህም የከፋው ደግሞ አንዳንዱ ሰው የሆነ ያህል ረከዓ በዚህ ምሽት ይሰገዳል በሚል ለየት ያደርገዋል። ይሁንና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህንን ምሽት ነጥሎ ለየት ማድረግ ስላልተገኘ ይህችን ምሽት በሰላት ልዩ አናደርግም።

📍አምስተኛው ነጥብ
የአላህ ሱብሃነሁ ለነገሮች የሚያደርገው ውሳኔ በሻዕባን አስራ አምስተኛዋ (አጋማሽ) ምሽት ነውን

ምላሹም አይደለም ሲሆን፤ ምሽቷም የመወሰኛይቱ ሌሊት [ለይለቱል ቀድር] አይደለችምና ነው። ምክንያቱም "ለይለቱል ቀድር" በረመዳን ውስጥ የምትገኝ ምሽት ናት። ሃያሉ አላህ እንዳለው፤
”إنا انزلناه“
"እኛ አወረድነው" ማለትም ቁርኣንን ለመጀመርያ ግዜ ያወረድነው ማለቱ ነው። ይህም ሙሉ ምዕራፉ ሲነበብ እንዲህ ይላል፤

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ ﴿١﴾ وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ ﴿٢﴾ لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ ﴿٣﴾ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ ﴿٤﴾ سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ ﴿٥﴾
Al-Qadr☞ القدر:- [1-5]

[እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡ (1)መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? (2)መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡ (3) በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡ (4) እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡(5)]
ይህ ክስተትና ምሽቱም መቼ እንደሆነ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፤

(شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖوَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّـهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّـهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ) البقرة:- 185

[(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡ (185)]

በዚህም መረጃ መሰረት ለይለቱል ቀድር ማለትም ፈጣሪያችን አላህ ለማንኛውም ነገር ሁሉ አመታዊ ውሳኔ የሚሰጥበት ምሽት በረመዳን ወር ውስጥ የምትገኝ አንዲት ሌሊት መሆኗን እንረዳለን። ምክንያቱም ሌሊቷ ቁርኣን የወረደባት ሌሊት ነች ። ቁርኣን ደግሞ የወረደው በረመዳን ወር ነውና የመወሰኛይቱ ምሽትም የምትገኘው በረመዳን እንጂ በሌላ ወር አይደለም። ስለሆነም የሻዕባን አጋማሽ ሌሊት  "ለይለቱል ቀድር" የመወሰኛይቱ ምሽት አይደለችም። በዚያች ሌሊትም ለአመቱ የሚሆን ምንም የሚወሰን ነገር የለም።

📍ስድስተኛው ነጥብ፦
የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ላይ አንዳንዶች ምግብ አዘጋጅተው ለድሆች በሚል የሚያከፋፍሉትና የእናት እራት፣ የአባት እራት ወይም የወላጆች እራት የሚሉት [እንዲሁም ባገራችን የእህል ዘሮችን ባንድ ላይ ሰብስቦ በመቀቀልና ከዚያም መጀመርያ ግቢ ውስጥና ውጪም በመበተን አመቱ የጥጋብ የርጋታ ይሁንልን የሚሉት] ሁሉ ከነቢዩ ያልተላለፈልን ከሰሃቦችም ሪድዋኑላሂ አለይሂም ያልተገኘ መጤ የሆነ ቢድዐ ነው።

👆 እነዚህን ስድስት ነጥቦች ጠቅሼ ብቆጥራቸውም ሌሎች ላብራራቸው የሚገቡ ሆነው ያለፍኳቸው እንዳሉ ግልፅ ነው።  አላህ እኛንም እናንተንም ሱናን የሚያሰራጩ፣ ቢድዐን የሚያስጠነቅቁና ተመርተው የሚመሩ (ቅን ሆነው የሚያቀኑ) ያድርገን። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በጁምዓ ኩጥባቸው ወቅት እንደገለፁት ከምሪቶች ሁሉ በላጩ የሳቸው ምሪት ነውና ቅኑን መንገድ የሚከተሉ፣ በሳቸው አመራርም የሚመሩ ያድርገን። «በማስከተል፤ ከንግግሮች ሁሉ በላጩ የአላህ ኪታብ ነው። ከአመራሮች ሁሉ በላጩም የሙሀመድ ምሪት ነው። መጥፎ ጉዳይ ማለት መጤዎቹ ናቸው። ሁሉም ፈጠራዎች ጥመት ናቸውና።»ብለዋል።


منقول
=
https://t.me/https_Asselefya1
ሁለት ሦስት ቀን ከዚህ አካባቢ ስጠፋ«ምነው ጠፋህ?» ብለው የሚጽፉልኝና የሚደዉሉልኝ ወዳጆች አሉኝ አልሐምዱ ሊላህ።

ምን ገባኝ መሠላችሁ…የኔን የተስፋ መልዕክት ሰንቀው የሚበረቱ፣የአብሽሩ ፊደላቴን ጠብቀው የሚተዳደሩ፣ መልካም ቃላትን ተመግበው የሚኖሩ፣ የሚያድሩ፣ እህትና ወንድሞች እንዳሉኝ።

ሐቂቃ…የምንኖርለት ሰው መኖሩን ማወቃችን በራሱ ትልቅ ደስታ ነው። ለነርሱ ስንል እስከ እስትንፋሳችን ፍፃሜ እንኖራለን ኢንሻአላህ።

አላህ ይርዳኝ።በዱዓችሁ።
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan
ስማ ስማ!!

ليس كل من نظر إليك وابتسم دليل على أنه يحبك.
فبعض الناس حقدهم في إبتسامتهم

ፈገግ ብሎ የተመለከተህ ሰው ሁሉ ይወደኛል ለማለት መረጃ አይሆንም።
ከፊል ሰወች ክፋታቸው በፈገግታ የተሸፈነ ነው።

✍️ኑር

http://t.me/nuredinal_arebi
የገጠር ሙሀደራዎች

~
ድግምት እና ድግምተኞች↷⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19668
t.me/nuredinal_arebi/19668

በአላህ ማመን ⓵↷⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19670
t.me/nuredinal_arebi/19670

√በአላህ ተመኩ ⓶↷⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19672
t.me/nuredinal_arebi/19672

√አስካሪ መጠጥ እና ቁማር↷⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19675
t.me/nuredinal_arebi/19675

√ኒፋቅ እና ሙናፊቆች↷⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19681
t.me/nuredinal_arebi/19681

√የልብ በሽታ እና በሺተኞች↷⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19682
t.me/nuredinal_arebi/19682

√የቀብር አምልኮ↷⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19683
t.me/nuredinal_arebi/19683

√ህዝባችን እና እስልምና↷⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19685
t.me/nuredinal_arebi/19685

√ሞትን ማስታወስ↷⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19691
t.me/nuredinal_arebi/19691

√በአላህ ብቻ መመካት↷ ⇓↶
t.me/nuredinal_arebi/19723
t.me/nuredinal_arebi/19723

=

🎙በኑረድን አል አረቢ አቡ ፋሩቅ