💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
🥀ይቀመጥ🥀

ዉሰዱ ኡሙ ዑሰይሚኖችዬ

~
26-العبودية - لشيخ الإسلام ابن تيمية
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም
አዲስ ተከታታይ ትምህርት


📚 العبودية لشيخ الإسلام ابن تيمية

ክፍል 26

ፉሪ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ

🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም

𝐓𝐞«t.me/SheikhMuhammedZainAdam
🛑👉ይድረስ ለቻናል እና ለግሩፕ ባለቤቶች
~~

ዲንን ማሰራጨት ትልቅ አጅር አለው ዲናችንን ከምናሰራጭባቸው ከምንማርባቸው መንገዶች አንዱ ማህበራዊ ሚዲያ ነው !! ከነዝህ ማህበራዊ ሚዲያዎች ደግሞ በርካታ ዱዓት ኡስታዞች መሻይኾች በተለያዩ ግሩፖች እና ቻናሎች ትምህርቶቻቸው ይሰራጫል አልሀምዱሊላህ ይህ ትልቅ ስራ ነው !!

ነገር ግን ብዙዎቻችን ቻናሎቻችንን የራሳችንን የግል ጉዳያችንን ብቻ መናገሪያ እና መለፍለፊያ አድርገነዋል የተከፈተበት አለማ ግን ይህ አልነበረም !! እንደውም ከዝህ አልፎ አንዳንዱማ #ጭልጥ ያለ ምቀኝነት ውስጥም የሚገባ አለ የሱ ቻናል ሊንክ በየ ቻናሎች ስላልዞረለት ስለዝህ የማንንም ኡስታዝ ድምፅ ካመጣ ከኡስታዙ ግሩፕ ሰው እንዳይገባ ሊንኩን አንስተው የራሳቸውን ያደርጋሉ !!

ከአመታት በፊት ይህንን ጉዳይ አንስቼው ነበር ግን በቦት በኩል የመጡልኝ የአንዳድ እህቶች ስድብን ብታዩ ሙስሊም ናቸው ግን ? ያስብላል ወሏሂ እኔም ምንም አልገረመኝም ምላሰኛ ሰዎች እንዳሉ ስለማውቅ !! ይገርመኛል እኔ ግን ዝም ካላችሁ ትሞታላችሁ የተባሉ ይመስል ሲለፈልፉ ትንሽም እፍረት የለላቸው አሏሁልሙስተዓን !!

ስለዝህ ረጋ በሉ ባካችሁ የቻናል እና ግሩፕ ቁጥር ከፍ ሲል የናንተ ዝቅ ካለ ምቀኝነት ውስጥ አትግቡ ከፍ ይበልለት ምን ችግር አለው ጥሩ ትምህርቶች ካሉበት ?? አንዳንዱ ደግሞ የራሱን ቻናል ብቻ ከፍ ለማድረግ ሲል የሱን ሊንክ የሱን ፅሁፍ የሱን ድምፅ ሼር የሚያደርጉትን እንጅ የሌሎችን ሼር አያደርግም ይህ ብዙ ወንድሞች እህቶች የተፈተኑበት ትልቅ በሽታ ነው !!

አንዳንዱ ደግሞ ሌላ ሰው የፃፈውን ፅሁፍ ራሱ እንደፃፈው አድርጎ ያመጣል ምን ችግር አለው እሱ እንደፃፈው ቢቀመጥ ?? ነው የራሴ ቻናል ግሩፕ ብለን የምናበላሽ ?? እረ ከዓቅላችን እንሁን ወገን ግሩፕ እና ቻናል እልህ መወጫ ሳይሆን መልካም ነገር ማስተላለፊያ ነው አጠቃቀሙን ካልቻልን ደግሞ ወንጀለኛ ከምንሆን እንዝጋው አለቀ !!

የቁጥር መብዛትና መቀነስ አያሳስበን , የሌሎች ኡስታዞችን ደርስ , ዳዕዋ እናስተላልፍበት ሰውን ቢጠቀምኮ ለኛ ነው ጥቅሙ አጅሩ ኢንሻ አሏህ !! ምቀኝነት ወጥሮን " የሱን ትምህርት አላስተላልፍም የኔን እኮ ሼር አያደርግም " የሚል ሰው ጭንቅላቱ ጤናማ አይመስለኝም ቢታይ ባይ ነኝ !!

እህቶችም አሏህን ፍሩ ስትባሉ እስኪ ስሙ የቀናንባችሁ አይምሰላችሁ ሰው በዝህ ግዜ ሰውን እመክራለሁ ካለ የተቀናበት ይመስለዋል ከሞኝነቱ የተነሳ አንዳንድ እህቶችማ ከነሱ በላይ አዋቂ ያለም አይመስላቸው ግን ባዶ ናቸው ስታያቸው የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ይለያል እንደሚባለው ነው ነገሩ !!

በተለይ በየግሩፑ አድሚን የተደረጋችሁ አሏህን ፍሩ አድሚን የተደረጋችሁት ግሩፑን ለመበጥበጥ አይደለም !! ምቀኝነት ውስጥ አትግቡ አትጣሉ የኔ ብቻ አትበሉ እልህ መጋባቱ ትልቅ ጥፋትን ያስከትላልና !! አንዳንዶቹ ይገርሙኛል አድሚኖች ከተጋጩ እርስ በእርሳቸው አንዷ የላከችውን አንዷ ታጠፋለች አንዷ ስትልክ አንዷ ስታጠፋ ግሩፑ መጫወቻ ሁኖ ቁጭ አሏሁልሙስተዓን!!

አንዳንዱ ደግሞ ቻናል ወይም ግሩፕ ይከፍትና የለለ ራሱን ሰማይ ይሰቅላል እኔ ብቻ ሚዲያውን ልቆጣጠረው ይላል። እረ ስንቱን ጠቅሼ ስንቱን ልተወው : ስለዝህ የቻናል እና የግሩፕ ባለቤቶች ሆይ አላህን እንፍራ ካሰራጨን መልካም ነገርን እናስተላልፍ ካልሆነ ዝም እንበል !!!

ተፃፈበአብዱረሕማን አቡ ዑሰይሚን

•━━━ ✽ • ✽ ━━━••━━━ ✽ •
http://t.me/abuUseyminabdurehman
http://t.me/abuUseyminabdurehman
~በነገራችን ላይ…በዚህ ቻናል ላይ ያገኛችሁትን ማንኛውንም ነገር የኔን ሊንክ አንስታችሁ የራሳችሁን ሊንክ አያይዛችሁ ሼር በማድረጋችሁ ምንም ቅሬታ የለብኝም።

በዚህ ቻናል የምታገኟቸው ማንኛውም ጠቃሚ ነገሮች ወደ ሌላ ሼር በማድረግ ምንዳዬን አስፋችሁልኝ እንጁ አጁሬን አልቀነሳችሁም! እኔ ደሞ ተከታዮቼን ከማብዛት በላይ ምንዳየን ማብዛትን እሻለሁና። የኔን ሊንክ በማንሳት የራሳችሁ ብታደርጉ ሁለቱም የጋራ ጥቅሞቻችን ናቸው። ምክኒያቱም የሚለቀቁትን ነገሮች ሼር ስታደርጉ  የኔም ሳይቀነስ ለናንተም አጅር ይፃፍላችኋል።

ስለዚህ…ኮፒ እያደረጋችሁ ፖስቱ።ምክንያቱም ጠቃሚ መረጃዎችን ኮፒ እያደረጉ ማሰራጨት አንዱ ዒልምን የማሰራጭያ መንገድ ነው። በዚህ ድርጊታችሁ ልትደሰቱ እንጂ ልታፍሩ አይገባም። ደግሞ ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁሉም ኮፒ አድራጊ ነውኮ። ግማሹ ከፌስቡክ ላይ ኮፒ ያደርጋል። ሌላኛው ከኪታብ ላይ ያለውን እንደወረደ ኮፒ አድርጎ ይተረጉማል። ሌላኛው የሰማውን ኮፒ አድርጎ ወደጽሁፍ ይቀይራል። ስለዚህ ሁሉም ኮፒ አድራጊ ነው ቢባል ብዙም አልገነነም።

እናም ኮፒ አድርጋችሁ ስታሰራጩ አጂር እንዳላችሁ አትዘንጉ። ባሰራጫችሁት መልእክት አንድ ሰው አንድትን ዒባዳ ቢፈፅም ከዚያች ዒባዳ እናንተም ድርሻ እንዳላችሁ አትርሱ። በተለያዩ ሚድያዎች ያሠራጫችኋቸው ጽሁፎቻችሁ እስከተነበቡ ድረስ ቋሚ ሰደቃም እንዳስቀመጣችሁ ከግምት ውስጥ አስቀምጡ።

(NB_ይህ የኔ አቋም ነው። ሊንኩ እንድነሳበት ፍቃደኛ ያልሆነን ሰው ግን ማንሳት ከ አደብ አይደለምና ፍቃድን ጠይቁ። በኔ ቻናል ግን አብሽሩ!)
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
~ፈገግ በሉ

ፈገግታ ሱና ነዉ።

ሌባና ሴቶች ዘዴ አያጡም ይላል ያገሬ ሰዉ...የሌባዉ ግን አትሻብኝ
ምላስ ቀጥ ካለ ልብም ቀጥ ይላል!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا يَسْتَقِيمُ إِيمانُ عبدٍ حتى يَسْتَقِيمَ قلبُهُ، ولا يَسْتَقِيمُ قلبُهُ حتى يَسْتَقِيمَ لسانُهُ﴾

“የአንድ ባሪያ ኢማኑ ቀጥ አይልም፤ ልቡ ቀጥ እስኪል ድረስ። ልቡም ቀጥ አይልም ምላሱ ቀጥ እስኪል ድረስ።”

📚 አልባኒ በሶሂህ አተርጊብ ወተርሒብ ውስጥ ሶሂህ ብለውታል: 2865

💸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

🌐https://bit.ly/4ayf0xJ

💬https://bit.ly/486xnrS

🌐https://bit.ly/41zEZkk

🌐https://bit.ly/4arMbTx

🌐https://bit.ly/41tIUPv

🌐https://bit.ly/41yPkNg
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM