💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
«ማንኛውም ትዳርን ያሰበ አስተዋይ የሆነ ሰው ሁሉ ከመልካም ቤተሰቦች የተገኘችን መልካም ሴት ለትዳሩ ሊመርጥ ይገባዋል።

📔ኢብኑል ጀውዚይ/ሶይዱል ኻጢር- 493
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan
በነገራችን ላይ በሚድያ ትዳር ጉዳይ እንጥፍጥፍ አድርጎ ወንዶችን ብቻ የጥፋት ባለቤት ማድረግ ተገቢ አይደልም።አንዳንድ እህቶችም እኮ በትዳር ላይ ትዳር ፈላጊዎች ናቸው።

አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
ለደስተኛ የትዳር ህይወት ────────── ↳ክፍል ⑤↲   ⤿⤿⤿⤿⤿⤿⤿           ❶↺አንዳንዴ ዝምታ ከንግግር ይልቃል፣ ጥቂት በማይባሉ ክስተቶች ላይ  ዝምታ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ሆኖ የምናገኝበት ጊዜ አለና ዝም ማለትን አንዘንጋ!! ❷↺እርስበርስ መከባበር። በተለይም ልጆች፣ ዘመዶች እና ሌሎችም ሰዎች ባሉበት፤ ምክንያቱም መከባበር ለመዋደድ እና ለመቀራረብ ሰበብ ነውና።  ❸↺የምክር  አሰጣጥ…
ለደስተኛ የትዳር ህይወት
∼∼∼∼∼∼∼∼∼∼

ክፍል ⑥↲
    ⇀⇀⇀⇀

➊↷ተፈጥሮአዊ የሆኑ ባህርያትን መቀበል።
በተፈጥሮ ካሉ ባህሪ የሚመነጭ ስህተትን በተለምዶ እና ሰው ሰራሽ  ከሆነ ባህሪ የሚመነጭን ስህተትን እኩል የሆነን ፍርድ አለመስጠት።


❷↷እራስን ከፍ ከፍ ከማድረግ ነፍስያን ከማዋደድ ከማዳነቅ  መቆጠብ።

❸↷ከኩራት ከጉራ የበላይ ነኝ ብሎ ከማሰብ እርቆ በተቃራኒው እራስን ማስተናነስ።
ምንም እንኳን በእውቀት፣ በሐብት፣ በደረጃ ከፍ
ያልን ብንሆንም እንኳ ያለነው በትዳር ጎጆ ጥላ ስር እንደሆነ መገንዘብ አለብን።


❹↷ያማሩ ደስ የሚያሰኙ ስያሜዎችን መጠቀም። በምንጠራራበት ወቅት ውዴታን ሊገልፅ የሚችልን  ጥሪ ማቆላመጥም ሊሆን ይችላል መጠቀም።

❺↷ፈገግታ እና  ፈታ ያለ ፊት በትዳር ህይወት ውስጥ ትልቅ ሚስጥር አላቸው።

❻↷ ርህራሄ እና መተዛዘን የትዳር ህይወት የተስተካከለ እንዲሆን ከሚያደርጉ ቁልፍ ሚስጥሮች አንዱ ነው።
ለዚህም ከፍ ያለው ጌታ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፦ "መዋደድን እና መተዛዘንን በመሐከላችሁ አደረገ።"

➐↷የትዳር ህይወትን የመኗኗሪያ ዘዴዎችን እና አደቦችን መማር በተቃራኒው በዚህ ዙሪያ ያሉብንን አለማወቅን ማስወገድ ወይም መቀነስ።

➑↷ትውስታዎችን ማደስበትዳር ህይወት ውስጥ ጥሩ ጥሩ ጊዜያቶችን ትውስታዎችን አስቀምጦለፍ ምንኛ ህይወትን  ያማረ ያደርገዋል!

➒↷እራስን ከአዛዥነት ባህሪ ማላቀቅ እና ሐሳብ የማመንጨትን ባህሪ መላበስ።
ምክንያቱም ነፍስ በተፈጥሮዋ ተደጋጋሚ የሆነ ትዕዛዝን ትሰለቻለች ነገር ግን ሐሳብን በማቅረብ ዘዴ እና አማራጮችን በመስጠት ሲሆን ግን የተፈለገውን ግብ መምታት ይቻላል።

❿↷ትርፍ ጊዜያችንን በሚጠቅሙ እና ፋኢዳ  ባላው ነገሮችመዝጋት።የጊዜ አጠቃቀም ዘዴን መማር።ክፍት (ትርፍ)ጊዜ መሰላቸትን፣ መጥፎ እና አላስፈላጊ ስሜቶችን ይወልዳልና።
    
منقول
📝ይቀጥላል......

http://t.me/https_Asselefya1
”لِقاءُ النَّاسِ ليسَ يُفيدُ شَيئًا
سِوى الهَذَيانِ مِنْ قِيلٍ وَقــالِ

فأَقلِلْ مِنْ لِـــقاءِ النَّاسِ إلّا
لأَخذِ العِلمِ أو إصلاحِ حــالِ“
.
«#التغافل سر الوئام بين الزوجين»

🍃إن اكرم الاخلاق في البيت الكرم والتغافل. فإذا رأى خطأ غض الطرف عنه، فان سيد قومه المتغافل ليس بالغافل وانما المتغافل.
وفي حديث ام زرع أن عائشة رضي الله عنها لما ذكرت النسوة الإحدى عشر ذكرت أن امرأة اثنت على زوجها فقالت إن زوجي إذا دخل...

استمع للشيخ أ.د.#عبدالسلام_محمد_الشويعر
-حفظه الله-

🍃
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
⭞ኢስቲሀዷ «የበሽታ ደም» 【ክፍል  ⓵⓼】 ∼∼∼∼∼∼ ☞ከላይ ያሉትን ሁለቱን ሁኔታዎች ካላሟላች ደግሞ አብዛኛዎቹ ሴቶች የሚያጋጥማቸውን የሀይድ የጊዜ ቆይታ ለራሷ በመውሰድ በሀይድ ታስባቸዋለች፡፡ ለምሳሌ ሀይድ በአብዛኛዎቹ ሴቶች ላይ የሚቆየው ለስድስት ወይም ለሰባት ቀናት ስለሆነ ከረጅሙ የደም ፍሰቷ ዉስጥ ስድስቶቹን ወይም ሰባቶቹን ቀናቶች በሀይድ በማሰብ ትጸዳና ከዚይ በኋላ የሚፈሰውን…
ኢስቲሀዷ «የበሺታ ደም»


【ክፍል ⓵⓽】
∼∼∼∼∼∼

ኢስቲሀዷ ላይ ያለች ሴት ሶላት አሰጋገድ


ለእያንዳንዱ ሶላት ዉዱእ ማድረግ ይኖርባታል፡፡ ለምሳሌ ዙህርንለመስገድየዙህርወቅት ሲገባ ዉዱእታደርጋለች። የዱሃሶላትንለመስገድምስታስብአድስ ዉዱእ ማድረግ ይጠበቅባታል ማለት ነው። ደም እስከፈሰሳት ድረስ ኢስቲንጃእ ማድረግ እንደሚያስፈልጋትም ግልጽ ነው፡፡ ይህ የሻፊዒይና የአህመድ አቋም ነው።

ሸይኽ አልባኒም ይሄን ይመርጣሉ። ለዙህር ሶላት ባደረገችው ዉዱእ ዙህርን፣ የዙህርን ሱንናዎች እንድሁም በጥቅሉ ሌሎች ዉዱእ አፍራሽ ነገራቶች እስካላጋጠሟትና የዐስር ሶላት ወቅት እስከሚገባ ድረስ የትኛውንም አይነት ሶላት መስገድ ይፈቀድላታል የሚሉት ደግሞሀነፊያዎችናቸው።ኢብኑባዝምከዚህአቋምጎን ይሰለፋሉ። ማሊኪያዎች ደግሞ ለእያንዳንዱ ሶላት ዉዱእ ማድረግ እንዳለባት የሚገልጹ ሀዲሶች በሙሉ ደካማዎች፣ እርስበርሳቸው የማይስማሙ፣ ወጥነት የሌላቸው፣ የተምታቱ ሀዲሶችስለሆኑለሁሉም ሶላትበተናጠልዉዱእማድረግ የሚወደድ ተግባር እንጅ ግዴታ አይደለም ይላሉ።

ኢብኑ ዑሰይሚኒም ይሄንን ሃሳብ ይጋራሉ። ለጥንቃቄም ሲባል ቢሆን የመጀመሪያውን አቋም መከተል በጣም አዋጭ ነው።

«قال النبي ﷺلعائشة " مري فطمة بنت ابي حبيش  فلتمسك كل شهر عدد ايام أقرائها، ثم تغتسل  وتحتشي، وتستثفر،  وتنظف ، ثم تطهر عند كل صلاة وتصلي " أخرج أحمد ودارقطني  وإستدل به الألباني  في ثمر المستطاب وقال في الباب  احديث أخری  »


ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ ዙህርን በማዘግየትና ዐስርን በማፋጠን የሁለቱ ሶላቶች መገናኛ ወቅት ላይ ሰውነቷን ታጥባ ሁለቱንም ሶላቶች በተቀራራቢ ሰአት አስከታትላ መስገድ ትችላለች፡፡ ለመግሪብና ለዒሻእም ተመሳሳይ አፈጻጸምን ትከተላለች፡የሱብሂ ሶላት ግን ከየትኛውም ሶላት ጋር መሰባሰብ ስለማይችል ለብቻው ሰውነቷን ታጥባ ትሰግዳለች፡፡ ይህ የሚወደድ ተግባር እንጅ ግዴታ አይደለም።

«ففي حديث أسماء بنت عميش ،، قال رسول اللهﷺ لفاطمة بنت أبي حبيش .. فإذا رأت صفرة فوق الماء  فلتغتسل للظهر  والعصر غسلا واحدا ،، وتغتسل للمغرب والعشاء  غسلا واحدا وتغتسل للفجر وتتوضأ فيما بين ذالك ""  أخرجه حاكم وصححه شيخ الألباني "»


ሶስተኛው አማራጭ ለእያንዳንዱ ሶላት ለየብቻቸው መላ ሰውነቷን እየታጠበች መስገድም ትችላለች፡፡ ግዴታ ግን አይደለም። ምክንያቱም ፋጢማ ቢንት አቢ ሁበይሽ ከራሷ ተነሳሽነት እንጅ ነብዩ አዘዋት አልፈጸመችውም።

عن عائشة  . أن فاطِمة  بنت أبي حبيش  رضي الله تعالى  عنها سألت النبي ﷺ قالت  إني أستحاضُ  فلا أطهُرُ ،، أفأدعُ الصلاة ؟؟ فقال.. لا إنَّ ذالِكِ عِرقٌ ،، ولكِن دعِي الصلاة  قدر الأيام التي كنتِ تحيضين فيها ،، ثم اغتسلي ، وصلي " فكانت تغتسلُ لِكُلِ صلاةٍ .


በበሽታ ደም የተጠቃች ሴት ዉዱእ ካደረገች በኋላ ሶላት እስከምትሰግድ ድረስ የሚፈሰው ደም በዉዱእዋ ላይ ምንም አይነት ተጽእኖአያሳድርባትም፡፡ ሶላት በምትሰግድበት ወቅት ደሙ ቢንጠባጠብ ራሱ ሶላቷም ላይ ይሁን ዉዱእዋ ላይ የሚኖረው ጉዳት የለም፡፡ የንጽህና መጠበቂያ መጠቀሟ ግዴታ መሆኑን የሚጠቁሙ ትክክለኛ ሀዲሶች ስላሉ አቅም የፈቀደውን መጠቀም ግድ ይላል።

قال النبي ﷺ لفاطمة بنت ابي حبيش " وتوضئي  لكل صلاة  وإن قطر الدم علی الحصير .. رواه ابن ماجه

عن عائشة قالت :إعتكفت مع رسول الله صلىccc الله عليه وسلام  إمرأة  من أزواجه  فكانت  ترى الدم والصفرة  والطست  تحتها  وهي تصلي . رواه البجاري



ኢስቲሀዷ ላይ ያለች ሴት ግንኙነት መፈጸምንየሚከለክላት ምንም አይነት ትክክለኛ እና ግልጽ መረጃስለሌላ መፈጸም የተፈቀደ ነው፡፡ መረጃም ተገኝቶለታል፡፡

سئل سعيد بن جبير : اتجامع المستحاضة ?  فقال الصلاة  أعظم من الجماع''   رواه الدارمي

عن عكرمة قال  كانت  أم حبيبة  تستحاض فكان  زوجها  يغشاها. صحيح سنن أبي داود


በማህጸን ቁስለት ወይም በህክምና ምክንያት የሚፈስ ደም ከሀይድም ይሁን ከኢስቲሀዷ አይመደብም፡፡ ስለዚህ ይህ ደም እንደማንኛውም ዉዱእ አፍራሽ ነገር ብቻ ነው የሚቆጠረው፡፡ በርግጥ ሸይኽ ዑሰይሚን የዚህ አይነት የደም ፍሰት ያጋጠማት ልክ ኢስቲሀዷ ላይ እንዳለች ሴት ለእያንዳንዱ ሶላት ዉዱእ ማድረግ ይጠበቅባታል የሚል እይታ አላቸው፡፡

«ኢንሻ አላህ ይቀጥላል ๏๏๏๏

    •━━━ ✽ • ✽ ━━━•
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1