💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
እኛማ! አላህ ይድረስልን!

ዘይድ አልያሚ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–
"አንዲት የኢብኑ መስዑድ ንግግር ሃያ አመት ዝም አስብላኛለች። እሷም:
‘ንግግሩ ተግባሩ ጋር የማይገጥም የሆነ ሰው እራሱን ነው የሚወቅሰው’ የምትለዋ ነች።"
[ዑዩኑል አኽባር: 2/179]
Audio
ስለ ድንበር ማለፍ በኡስትዝ ኢብኑ ሙነወር

👇👇👇👇👇👇

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
►◉ወደ ሸር እሚጣሩ ብዙ ናቸው በኢስላም ስም ወደ እሳት በር እሚጣሩ ‼️

►◉ወደ ኸይር እሚጣሩ ግን ጥቂት ናቸው እነሱ ናቸው ኸይር ለእነሱ 《ጡባ እሚባል ጀነት》
አላችው‼️

🎤ሸይኽ ፈውዛን ሃፊዘሁላህ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ዚክር፣ የዘነጋነው ሃብት
~~~~~~~~>
መቼም ሰው ነንና ፈራሽ እንደሆንን እናውቃለን። እንደ ሙስሊም ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ እናምናለን። ስለሆነም የአኺራችን ጉዳይ ያስጨንቀናል። ለዚህም ሲባል በጌታችን ህግ ለመኖር፣ ትእዛዛቱን ለመፈፀም ክልከላውን ለመራቅ፣ ስለ ድክመታችን ተውበት ለማድረግ እንሞክራለን። ሆኖም ግን አንድ በቀላል ጥረት ብዙ ትርፍ የምንሸምትበትን ነገር ስንዘነጋ እንስተዋላለን።
አዎ ስራሽን እየሰራሽ፣ መኪናህን እየሾፈርክ፣ ወረፋ እየጠበቃችሁ፣ በመኪና እየተጓዝክ፣ ሰው እየጠበቅሽ፣ በእግራችን እየተንቀሳቀስን፣… ዚክር ቢደረግ በየእለቱ ስንትና ስንት አጅር በሰበሰብን ነበር። ዚክር ከምናስበው እጅግ የላቀ ፋይዳ አለው። ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
"أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرِ أَعْمَالِكُمْ، وَأَزْكَاهَا عِنْدَ مَلِيكِكُمْ، وَأَرْفَعِهَا فِي دَرَجَاتِكُمْ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ إِنْفَاقِ الذَّهَبِ وَالْوَرِقِ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ أَنْ تَلْقَوْا عَدُوَّكُمْ، فَتَضْرِبُوا أَعْنَاقَهُمْ، وَيَضْرِبُوا أَعْنَاقَكُمْ ".
قَالُوا : بَلَى.
قَالَ : " ذِكْرُ اللَّهِ تَعَالَى".
"ከ(መልካም) ስራዎቻችሁ በላጭ፣
ከንጉሳችሁ ዘንድ የጠራ፣
ደረጃዎቻችሁን ከፍ የሚያደርግ፣
ወርቅና ብር ከመለገስ የሚሻላችሁ፣
ጠላቶቻችሁን አግኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትመቱና አንገቶቻችሁን ከሚመቱ (ከጂሃድ) የሚበልጥባችሁን አልነግራችሁምን?"

√ (ሶሐቦች):– "እንዴታ! (ይንገሩን) የአላህ መልእክተኛ ሆይ" አሉ።
"አሸናፊና የላቀውን አላህ ማውሳት" አሉ።
[ቲርሚዚ ዘግበውታል: 3377]

ትልልቅ ምንዳ ያላቸው አጫጭር ዚክሮች
~~~~~~~~~~~~~~~~~
① ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: سبحان الله وبحمده، في يوم مائة مرة، حُطَّت خطاياه وإن كانت مثل زبد البحر)؛
"በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ’ ያለ ሰው ወንጀሎቹ እንደ ባህር አረፋ ቢሆኑ እንኳን ይረግፉለታል።" [ቡኻሪ]

② እናታችን ጁወይሪያህ ቢንቲል ሓሪሥ ረዲየላ፞ሁ ዐንሃ ባስተላለፈችው በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ሱብሕን ከሰገዱ በኋላ ማለዳ ላይ ከሷ ዘንድ ወጡ። እሷ መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ ዚክር ላይ ነች። እዚያው እንደተቀመጠች ረፋድ ላይ ተመለሱ።
"ካንቺ ከተለየሁ ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተለየሁብሽ ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽም?" አሏት።
"አዎ" አለች።
በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ:–
" لَقَدْ قُلْتُ بَعْدَكِ أَرْبَعَ كَلِمَاتٍ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، لَوْ وُزِنَتْ بِمَا قُلْتِ مُنْذُ الْيَوْمِ لَوَزَنَتْهُنَّ : سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ ".
"በእርግጥም ካንቺ በኋላ አራት ንግግሮችን ሶስት ጊዜ ተናግሬያለሁ። ከንጋት ጀምሮ አንቺ ካልሺው ጋር ቢመዘኑ (እኔ ያልኳቸው) ይመዝናሉ።
ሱብሓነላ፞ሂ ወቢ ሐምዲሁ ዐደደ ኸልቂሁ፣
ወሪዷ ነፍሲሂ፣
ወዚነተ ዐርሺሂ፣
ወሚዳደ ከሊማቲሂ።" [ሙስሊም የዘገቡት]

③ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(كلمتان خفيفَتان على اللسان، ثقيلَتان في الميزان، حبيبَتان إلى الرحمن: سُبحان الله وبحمده، سبحان الله العظيم)؛
"ምላስ ላይ የቀለሉ፣ ሚዛን ላይ የከበዱ እና አረ፞ሕማን ዘንድ የተወደዱ ሁለት ንግግሮች አሉ። ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ፣ ሱብሓነላ፞ሂል ዐዚም።" [ቡኻሪና ሙስሊም]

④ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ከጀነት ድልብ ሃብቶች ውስጥ እንደሆነ የገለፁት የዚክር አይነት
(لا حول ولا قوة إلا بالله)؛
"ላ ሐውለ ወላ ቁወ፞ተ ኢላ፞ ቢላ፞ህ" [ኢብኑ ሒባ፞ን]

⑤ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير - عشر مرات - كان كمَن أعتق أربعة أنفُسٍ مِن ولد إسماعيل)

"አስር ጊዜ ’ላ ኢላሀ ኢለ፞ላ፞ህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ። ወሁወ ዐላ ኩሊ፞ ሸይኢን ቀዲር’ ያለ ሰው ከኢስማዒል ልጆች አራት ነፍሶችን ነፃ እንዳወጣ ነው።" [ሙስሊም]

⑥ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(سيِّد الاستغفار أن تقول: (اللهمَّ أنت ربي، لا إله إلا أنت، خلقتَني وأنا عبدُك، وأنا على عهدك ووعدك ما استطعتُ، أعوذ بك من شرِّ ما صنعتُ، أبوء لك بنعمتك عليَّ، وأبوء لك بذنبي، فاغفر لي، فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت، قال: ومَن قالها من النهار موقنًا بها، فمات من يومه قبل أن يُمسي فهو مِن أهل الجنَّة، ومَن قالها من الليل وهو مُوقن بها، فماتَ قبْل أن يُصبح، فهو مِن أهل الجنَّة)؛
"የኢስቲግፋር ሁሉ አለቃ ‘አላ፞ሁመ፞ አንተ ረቢ፞ ላ ኢላሀ ኢላ፞ አንተ። ኸለቅተኒ። ወአነ ዐብዱከ። ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መ’ስተጦዕቱ። አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ፞ ማ ሶነዕቱ። አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፞። ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ። ፈግፊር ሊ። ፈኢነ፞ሁ ላ የግፊሩ ዙ፞ኑበ ኢላ፞ አንተ’ የሚለው ነው።
በሷ አረጋግጦ በቀኑ ካላት በኋላ ሳያመሽ በእለቱ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው። በሷ አረጋግጦ በሌሊት ካላት በኋላ ሳያነጋ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው።" [ቡኻሪ]

እነዚህ ምሳሌዎች ብቻ ናቸው። ሌሎችም ብዙ አሉ። ከነዚህ በተጓዳኝ ከውዱእ በኋላ፣ ከአዛን በኋላ፣ መስጂድ ስትገባ፣ ከመስጂድ ስትወጣ፣ ከሶላት በኋላ፣ ከምግብ በኋላ፣ ስትተኛ፣ ስትነሳ፣ ወዘተ ያሉትን ብትል ቆጥረህ የማትዘልቀው አክተር አለህ።
በጥቅሉ ጊዜህን መድበህ ዚክርን የህይወትህ አካል አድርገው። ለዚህ ከተቸገርክ እየሰራህ፣ እየተጓዝክ ዚክር ትኩረት እንጂ የረባ ጥረት አይጠይቅህም። መልእክተኛው ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዳሉት "ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አትወገድ።"

ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁሏህ

@IbnuMunewor

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
👉ሴት ልጅ ከሀይዷ ከጠራችና ደሙ ከተቋረጠ በኋላ መታጠብና ኢባዳዋን መቀጠል ይኖርባታል
👉ደሙ ከተቋረጠ በኋላ ለሚወጣው ፈሳሽ ቦታ ልትሰጠው አይገባም።
👉ደሙ ከተቋረጠ በኋላ የሚፈሰው ፈሳሽ ሁክሙ እንደ ሽንት ነው የነካው ሰውነቷም ሆነ ልባሷን በማጠብ እስቲንጃእ በማድረግ በኢባዳዋ መቀጠል አለባት
👉ስለዚህ አንድ ሴት ከሀይድ መጥራቷን ምታረጋግጠው ደሙ በመቋረጡ እንጂ ከዛ በኋላ በሚፈሰው ፈሳሽ እንዳልሆነ ልታውቅ ይገባል

🎙 ج/ الشيخ العلامة الإمام:
محمد بن صالح العثيمين
-رحمه الله تعالى-
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
صفات الزوج الصالح
ሸይኽ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህን)
➧ወንዶች ጥሩ ሚስት እነደሚያስፈልጋቸው ሁሉ ሴቶችም ጥሩ ባል ያሰፈልጋቸዋል፡፡

➧በሁለቱም ወገን ትዳር ሲታሰብ ጥሩ ጓደኛ ወይም የሂይወት አጋር የሚሆን ሰው ማግኘት ዋናውና አሳሳቢው ጉዳይ ነው፡፡

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
4_6023994784316654978.amr
4.8 MB
ሙሓደራ 045
ክፍል 01
ሓቂቀቱል ጀምዕያ
🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ [ሀፊዘሁላህ]

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
4_6021655560443660112.amr
5.5 MB
ሓቂቀቱል ጀምዕያ
🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ [ሀፊዘሁላህ]
👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ወንድሜ ሆይ ለባለቤትህ ኒቃብን ለሞባይልህ ግላስን ማድረግን አትርሳ!!
Forwarded from Ibnu Seid (Channel)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰይድ ቁጥብ በዓለም ዛሬ ባለንበት ዘመን የተክፊሮች መሪ ነው።
🎙ሸይኽ መሓመድ ሰኢድ ረስላን [ሀፊዘሁላህ]
https://t.me/Ibnumohammedseid/1487
▪️عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا ، قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : (( مُرُوا أَوْلَادَكُمْ بِالصَّلَاةِ وَهُمْ أَبْنَاءُ سَبْعِ سِنِينَ، وَاضْرِبُوهُمْ عَلَيْهَا وَهُمْ أَبْنَاءُ عَشْرٍ، وَفَرِّقُوا بَيْنَهُمْ فِي الْمَضَاجِعِ ))

📚 صحيح أبي داود - رقم : (495)
👈🏽 قال الألباني حسن صحيح
▪️የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
“ልጆቻችሁን የሰባት አመት ልጆች ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፡፡ የአስር አመት ልጆች ሲሆኑ ደግሞ (ካልሰገዱ) ግረፏቸው።”
📚 አቡ ዳውድ (በቁጥር 495) ዘግበውታል።
👉 አልባኒ ሐዲሱን ሰሒህ ብለውታል።
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➻ሂጃብ ላለመልበስ የተለያዩ ምክኑቶች ከሚያቀርቡ ሴቶች ጋር የተደረገ ውይይት

➧እርሷ:- እኔ ሂጃብ ባለብስም አሏህን እወዳለሁ ስለዚህ አላህን መውደዴ በቂየ ነው።

➧መልስ:-
"قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ"

➧ "በላቸው አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ አላህ ይወዳችኋልና ኀጢኣቶቻችሁን ይምርላችኋልና።
አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።" 【ዒምራን 31】

➻አላህንማ ብትክክል የምትዎጅ ከሆነ መልእክተኛውን ባግባቡ ትከተይ ነበር

➧እርሷ:- በሙቀትና በፀሃይ ሰአት ሂጃብ ስለሚያስቸግረኝ መልበስ አልፈልግም

➧መልስ:-
"ِّۗ قُلْ نَارُ جَهَنَّمَ أَشَدُّ حَرًّاۚ لَّوْ كَانُوا يَفْقَهُون"
"የጀሃነም እሳት ተኳሳነቱ የበረታ ነው በላቸው የሚያውቁ ቢኾኑ" 【አት–ተውባህ 81】

➻በመገላለጥሽ ምክኒያት ነገ በአኼራ በእሳት ከመቀጣት ዛሬ በአዱኒያ ያለውን ሙቀት ተቋቁመሽ ጀነት መገባት አይሻልሽምን?

➧አርሷ:- አሁን ገና ልጅ ነኝ ትልቅ ስሆን ሂጃብ እለብሳለሁ

➧መልስ:- ሞት ልጅና ትልቅን አይመርጥም ትልቅም ትንሽም ይሞታል
ትልቅ ሳትሆኒ ብትሞችስ?

➧እርሷ:- እባክህ የኛ ማሃበረሰብ ሴቶች ሁሉም ተገላልጠው ነው የሚሄዱት እኔ ብቻየን ሂጃብ ስለብስ ይደብረኛል

➧መልስ:- ወላሂ አሁን ያልሽው በጣም የከፋ የጀሃነም ሰዎች ንግግር ነው። እነርሱ በርግጥ እንዲህ ይላሉ

"بَلْ قَالُوٓا إِنَّا وَجَدْنَآ ءَابَآءَنَا عَلَىٰٓ أُمَّةٍ وَإِنَّا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُّهْتَدُونَ"
➧"ከቶውንም እኛ አባቶቻችንን በሃይማኖት ላይ አገኘናቸው እኛም በፈለጎቻቸው ተመሪዎች ነን አሉ።" 【አዝ–ዙኽሩፍ 22】

➻አርአያሽን የሰፈርሽን ሴቶች ሳይሆን እነዚያን ብርቄየ ሱሃቦች አድርጌ!

እርሷ:- በቃ ካገባሁ በሗላ እሸፈናለሁ

➧መልስ:- ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ "አንድ ባሪያ በሚሰራት ወንጀል ሪዝቅን ይከለከላል" 【አህመድ ዘግበውታል】

➻ጥሩ ባል ከአላህ የሆነ ሪዝቅ ነው በወንጀልሽ ምክኒያት እንዳይከለክልሽ ተጠንቀቂ

➻ግን እመትሸፈኒው ለአላህ ነው ወይንስ ለባል? በዚህ አባባልሽ መሰረት ካገባሽ በሗላ ባልሽ መሸፈንሽን ባይፈልግ እርሱን ላለማጣት ስትይ አትሸፈኒም ማለት ነው?
ስለዚህ አንች ጌታሽን አምላኪ ሳትሆኒ ባል አምላኪ ነሽ ማለት ነው!

➧እርሷ:- እባክህ ዋናው የልብ ንፅህናነው ልቤ ንፁህ ከሆነ ከመሸፈኑ ምን አለኝ

➧መልስ:- ወስጥሽማ በተስተካከለ አካልሽም ይስተካከል ነበር ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ:- "ንቁ በሰውነት ውስጥ ቁራጭ ስጋ አለች እርሷ ከተስተካከለች አካል ሁሉ ይስተካከላል እርሷ ከተበላሸች አካል ሁሉ ይበላሻል ንቁ እርሷ ቀልብ ነች"
በነቢዩ ምስክርነት የውጫውይ ገፅታሽ እንዲህ መበላሽቱ የውስጥሽን መበላሸት ይጠቁማል!

➻ደግሞም ውስጥሽ ቢስተካከል ኑሮ እንዲህ ባልተገላለጥሽ ነበር እንዲህ የተገላለጥሽው ውስጥሽ ስለተበላሸ ነው።

ከተወሰነ ጭማሬ ጋር ከአረበኛ የተዞረ

ኢብኑ ሙሐመድዘይን

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
4_6023994784316654982.amr
4.1 MB
ሓቂቀቱል ጀምዕያ
🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ [ሀፊዘሁላህ]
👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
መልካም ሚስት ባንተ ፍለጋ አይደለም የምትመጣው፡ መልካም ሚስት ጌታውን ለሚፈራ ሰው ብቻ የምትሰጥ የሆነች ውድ የአላህ ስጦታ ነች።

ኢብኑል አረቢ

📚ምንጭ አህካሙል ቁረአን (536-1)
🌹ለብቻሽን ከሆንሽ የጥገና ሰራተኛ ቤትሽ እንዲገባ አትፍቀጂለት ።
የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል «ሴት ካለ መህረም ጉዞ አታደርግም፤ መህረም በሌለበት ወንድ አሷ ዘንድ አይገባም» (ቡኻሪ ዘግበውታል!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➪አቡ ዓብዱራህማን አል ዓምሪ
ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል :-

«በእናቴ ማህፀን ውስጥ ፅንስ ነበርኩኝ ርዝቄ መጥቶ በአፌ ይደረግልኝ ነበር አድጌ ጌታዬን ካወቁሁኝ በኀላ ጥርጣሬ ውስጥ ገባሁ ( በጌታዬ ላይ) ታዲያ ከኔ የባሰ ምን አይነት ሸረኛ ባሪያ አለ »
ሂልየቱል አውሊያ (7/208)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሰላት
Sadat
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህች ነች ሳዑድ አረቢያ

በሸይኽ ሷሊህ አል–ፈውዛን አንደበት

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w