💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ነጭ ልብስ መልበስና ከፈን!

ኢብኑ አባስ "ረዲየሏሁ አንሁ" ባስተላለፉት ሃዲስ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

"ከልብሶቻቹህ ነጭ ልብስን ልበሱ እርሷ ከመልካም ልብሶቻቹህ ነችና በርሷም ሙታኖቻቹህን ገንዙባት!"

📚 صحيح الجامع (1236)
አንድ ነጥብ ለአስተውሎት
~~~~~
በጣም ከምንሸወድባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ በእውቀት የሚበልጡንን መሻይኾች ልንጠቀምባቸው አለመቻላችን ነው። በሃገራችን የመንሃጅ ግንዛቤ በጣም የሳሳ እንደሆነ ማንም የማይክደው ሐቅ ነው። ይሄ ክፍተት ደግሞ ብዙ መሻይኾች ላይ ይጎላል። ለወቅታዊ ኪታቦችና ለኢንተርኔት የቀረበው ወጣት #አንፃራዊ በሆነ መልኩ ትንሽ ሻል የሚልበት ሁኔታ አለ። በንፅፅር ነው እያወራሁ ያለሁት። ትንሽ እውቀት የራሱ ብዙ ድክመት አለበትና የማንክደው ብዙ ጣጣ እያመጣብን ነው። ሌሎችን ችግሮች ለጊዜው ልተውና በተነሳሁበት ጉዳይ ላይ ያለውን ላንሳ። ድርቅና (ዒናድ) ሳይሆን የግንዛቤ ችግር ያለባቸውን መሻይኾች መቅረብ እንጂ መራቅ ለሁሉም አይበጅም። ይሄ ማግበልና መፃፍት ለነሱም፣ ለኛም፣ ለቆምንለት አላማም፣ ለወገናችንም የሚበጅ አይደለም፡፡ እና ተውሒድና ሱናን መውደድ፣ የሱና ዑለማዎችን ማክበር፣ ለደሊል እጅ መስጠት ካሸተትንባቸው ክፍተቶችን ብናይ እንኳ ከመራቅ ይልቅ መቅረባችን ነው የሚያተርፈን።

1ኛ:- ለነሱም ውለታ መዋል ነው። እኛ ችላ ስንላቸው በሌሎች አንጃዎች ይጠለፋሉ። ይሄ ከዚህ ቀደም በስፋት ተከስቷል። እኛ ስንርቃቸው የሌሎች ሲሳይ ሆነዋል። በራሳችን ላይ ጠላት አብዝተናል። ካለፈው ልንማር በቃ ልንል ይገባል፡፡
2ኛ:- ለሰፊው ህዝበ ሙስሊም፦ እነዚህ መሻይኾች ህዝብ ዘንድ የተሻለ ቦታ ስለሚኖራቸው የነሱ መጠንከር ለህዝብ ይተርፏል፡፡ እኛ ባግባቡ ካልቀረብናቸው ግን የሚጠልፏቸው አንጃዎች የሰለፊያን ዳዕዋ በጥላቻና በስጋት እንዲመለከቱ አድርገው ይሞሏቸዋል። ይሄ ደግሞ ዞሮ ዞሮ ዳፋው ለህዝብ ነው የሚተርፈው።
3ኛው:- ጥቅም ለራሳችን ነው፡፡ እኛ ትንሽዬ የመንሃጅ ግንዛቤ አለችን ማለት (ያውም ከኖረ) ከነሱ በእውቀት በለጥን ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ከነጭራሹ እውቀት አለን ማለትም አይደለም። እነሱ ዘንድ መንሃጅ ላይ የግንዛቤ ክፍተት መታየቱ እውቀት የላቸውም ማለት አይደለም፡፡ ለሁለቱም ወገን የሚበጀው መቀራረቡ ነው። እነሱ ዘንድ ያለውን ክፍተት ከቻልን ኪታብ እየገዛንላቸው ፣ ካልሆነ እያዋስናቸው፣ የታላላቅ ዑለማዎችን ንግግር እያሰማናቸው፣ በአደብ እየተከራከርናቸው ለመሙላት መጣር አለብን። በተለይ ኪታብ መስጠት ያለው ዋጋ ቀላል አይደለምና በዚህ ላይ ልንረባረብ ይገባል። የኛን ጅህልና ደግሞ ቁጭ ብሎ በመማር መግፈፍ አለብን። ይህን ስናደርግ ለራሳችንም፣ ለመሻይኾቹም፣ ለወገናችንም ትልቅ ውለታ እንውላለን። ለደዕዋችን መፋፋትም ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ የማወራው ከላይ እንደገለፅኩት ተውሒድና ሱናን መውደድ፣ የሱና ዑለማዎችን ማክበር፣ ለደሊል እራስን ዝቅ ማድረግ፣ ቅንነት ስለሚታይባቸው መሻይኾች ነው። አላማዬ ጥቆማ መስጠት ነው። ሃሳቡን ይበልጥ ልታዳብሩት ትችላላችሁ። አላህ ማስተዋሉን ያድለን። ኣሚን።

https://t.me/IbnuMunewor
የ"ሰለፊያ" ደዕዋ መሰረቶች
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
مُحَاضَرَةٌ جَدِيْدَة
አዲስ ሙሓደራ

←المَوضُوعُ↓
→ ርዕስ↓

[ أُصُولُ الدَّعْوَةِ السَّلَفِيَّةِ ]
[ የ "ሰለፊያ" ደዕዋ መሰረቶች ]

←المحاضرة الأولى↓
→ ክፍል ①

مُحْتَوَيَاتُ المُحَاضَرَةِ
በሙሓደራዉ ዉስጥ የተካተቱ ነጥቦች

الأصل الأول الإهتمام والعناية بطلب العلم الشرعي والتفقه في الدين

①ኛዉ መሰረት→ሸሪዓዊ እዉቀትን በመማርና ዲንን በመገንዘብ ላይ ትኩረት ማድረግ

الأصل الثاني الحرص على التطبيقي العملي للإسلام

②ኛዉ መሰረት→እስልምናን በተግባር ተፈፃሚ በማድረግ ላይ ትኩረት መስጠት

الأصل الثالث الدعوة إلى الله تعالى على بصيرة

③ኛዉ መሰረት→ወደ አሏህ በእዉቀት ላይ ሆኖ መጣራት

الأصل الرابع الإهتمام بعقيدة السلف علما وعملا وتعليما

④ኛዉ መሰረት→የሰለፎችን አቂዳ በመማር በመስራትና በማስተማር ላይ ትኩረት መስጠት

🕌 ደሴ ሸምስያ መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

ክፍል ② ይቀጥላል ኢንሻ አሏህ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
كُن_لها_رجلاً.......................... تَكون_لكَ_أربع_نساء!..............................
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ ክፍል 1⃣5⃣ ↩️
〰〰〰〰〰〰

↪️ ሱናው የጠበቀ የሀይድ ትጥበት
↪️ በሀይድ ትጥበት ጊዜ የሚወደዱ ሱናዎች
ን በተመለከተ

🔻ሼር በማድረግ እህቶቻችን እናንቃ

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
🔺حفظه الله تعالى!!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የሴት ፈተና
Sadat
ገራሚ ምክር በውዱ ወንድማችን

አቡመርየም ሳዳት ከማል ሀፊዞሁሏህ


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💢ድሃ ማነው⁉
➖➖➖➖➖

↪️የአላህ መልክተኛሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ከዕለታት አንድ ቀን ለባልደረቦቻቸው ቁጭ ብለው ሳለ እንድህ በማለት ጠየቁ

“ድሃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?”  በማለት ይጠይቃሉ። 


💧ሰሐቦችም እንድህ በማለት መለሱ፣


“▪️እኛ ጋር ድሀ ማለት ምንም ንብረትና ገንዘብ የሌለው ነው።” በማለት ይመልሳሉ። 


💧የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ አሉ

 â†Şď¸áŠ¨áŠĄáˆ˜á‰´ ደሀ ማለት የትንሳኤ ቀን በብዙ ሰላቶች፤ ዘካዎችና፤ ፆሞች የሚመጣ ሰው ነው፣ግና ይህ ሰው â¤ľď¸

🔹አንድ ወንድሙን ሰድቧል፣ 

🔹ሌላው ላይ ዋሽቷል፣

🔹የአንዱን ገንዘብ ያለአግባብ ወስዷል፣

🔹 የሌላውን ደም አፍስሷል፣

🔹አንዱን መትቷል፣ 

🔹 በሌላው ላይም ድንበር አልፏል፣ 

↪️ያኔም (የትንሳኤ ምርመራ ቀን ) የራሱን ጥሩ ሥራዎች ለበደላቸው በካሳ መልክ አሳልፎ ይሰጣል፣ ጥሩ ሥራው ለመካሻ አልበቃ ይለውና የበደላቸውን ሰዎች ወንጀል((ሐጢአት}} ይሸከማል። ከዚያም ወደ ጀሀነም ይወረወራል።”  በማለት መለሱላቸው። 

{{{ áˆ™áˆľáˆŠáˆ ሐዲሥ ቁ.653}}}

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲ የትዳር ዋና አላማው ምን እንደሆነ ሳንረዳ ትዳር ውስጥ የሚገጥሙ አለመግባባቶች እንዴት መፍታት እንዳለብን ሳንረዳ ዘው ብለን ወደ ትዳር መቀላቀል ይቅርብን!!!

በተለይ እህቴ ወጣም ወረደም የምትጎጂው አንቺ ነሽ እባክሽን ማንነትሽን ለማን አሳልፈሽ መስጠት እንዳለብሽ በጥልቀት አስቢበት ዲንሽን ተማሪ! ማንነትሽን ለማን መስዕዋት ማድረግ እንዳለብሽ በታትኖ ይነግርሻል! በትዳር ዙሪያ የሚሰሙ ሰቆቃዎች ያሳምማሉ!


➽ አንተ ወንድሜ የእህትህን ቀልብ በቀላሉ ሰብረህ ደስተኛ ህይወት የምትኖር ይመስልሃል!..በተለይ ልጅ ከወለዱ በኃላ መለያየት ምነኛ ከባድ ነው!? ትዳር እኮ መስዕዋትነትን ይጠይቃል። ኮሽ ባለ ቁጥር ለፍቺ መራወጥ ምን የሚሉት ተግባር ነው!? ለውሳኔ ከመቸኮልህ በፊት ያኔ ከሷ ጋር ያሳለፍካቸውን ጣፍጭ የህይወት ሂደቶችን አስታውስ! በመካከላቹ ያለውን ክፍተት ለማጥበብ ሰበቦችን አሟጠህ ሳታደርስ ወደ ውሳኔ አትግባ እሷም እንዳንተው ሰው ናት ብዙ ደካማ ጎኖች ሊኖሩባት ይችላሉ ችግሮችን ስታይ በቅንነት በግልፅ ያየህባትን ድክመት ንገራት መልካም በሆኑ ቃላቶች ምከራት ከስህተቷ ትመለስልሃለች።

እኔን ብቻ ስሚኝ አትበላት የሷንም ምክር ስማት በመካከላችሁ ክፍተት ይፈጥራል ብላ የሰጋችበትን ሀሳብ ስታካፍልህ እንድትተው ስትመክርህ ምክሯን ተግባራዊ አድርግላት መቼም የሱና እህቴ በኸይር እንጂ በሌላ አታዝህም! በመካከላችሁ ልጅ እያለ አንተን በቀላሉ መርሳት ይከብዳታል። ላንተ ብላ ብዙ መስዕዋትነት ከፍላ ይሆናል! ንግግርህ ከተግባርህ ተቃራኒ አይሁን! የሱና ሰዎች ለሚስቶቻቸው እጅጉን አዛኞች ናቸው።
ሸይኽ አልባኒ እንዲህ አሉ:- ከሚስቶቻቸው ጋር በጣም ለስላሳዎቹ እና መልካሞቹ አህለሱናዎች ናቸው።
المصدر متفرقات شريط(٨٢٨)

አንተ ወንድሜ ሆይ! ሚስትህ ባንተ ስር ያለች እንቁ አማና ናት!
በመልካም ተኗኗራት እዘንላት ተንከባከባት!!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ ክፍል 1⃣6⃣ ↩️
〰〰〰〰〰〰

↪️ አዛን ከተባለ በኋላ ሀይድ ቢመጣ ያንን ሶላት ቀዷ ታወጣለችን?
↪️ ኢሻ ላይ ከሀይድ ብትጠራ መግሪብ መስገድ አለባትን?
↪️ አሱር ላይ ከሀይድ ብትጠራ ዝሁርን መስገድ ግድ ይላታል?

🔻ሼር በማድረግ እህቶቻችን እናንቃ

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
🔺حفظه الله تعالى!!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💢✅ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሺን አደራ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ #ክፍል_ሁለት↩️
〰〰〰〰〰〰〰

↪️የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ማንኛውም የተሟላ እድልሽ ፣ ክብርሽ የአላህን
ህግጋት አጥብቆ ከመያዝ ጋር ቁርኝት እንዳለው እዎቂ፡፡ ያንች እድል ወይም ዕጣ
አላህን በመታዘዝሽ ወይም ሸሪዓውን በመጠበቅሽ የሚወሰን ይሆናል፡፡

🔷አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከለተውን ተናግሯል፡-

📌إن تَجتَنِبُوا كَبائِرَ ما تُنهَونَ عَنهُ نُكَفِر عَنكُم سَيِّئاتِكُم ونُدخِلكُم مُّدخَلاََ كَرِيمًا
ْ
🔷“ከእርሱ ከተከለከላችሁት ታላላቆቹን (ሃጢያቶች) ብትርቁ (ትናንሾቹን)
ሃጢያቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን፡፡ የተከበረንም ስፍራ (ገነትን)
እናገባችኋለን፡፡” አን ኒሳዕ 31

📌قَد أَفلَحَ مَن زَكَّهَا ۞ وَقَد خَابَ مَن دَسَاهَا

“(ከሃጢያት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡ የሸፈናትም ሰው
በእውነት አፈረ፡፡” አሽ ሸምስ 9-10


↪️✅የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ይህንን አላህ የሰጠሽን ክብር ለመንጠቅና አንቺ
ውርደት ላይ የምትወድቂበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚንቀሳቀሱ የኢስላም ጠላቶች መኖራቸውን እዎቂ፡፡ ከእነዚህ ግንባር ቀደም ጠላቶች መካከል የአላህና የዲኑ ጠላት የሆነው ሰይጣን ነው፡፡

🔷አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-

📌إنَّ الشَّيطَانَ لَكُم عَدُوٌّ فَتَّخِذُوهُ عَدُوًا إِنَّمَا يَدعُو حِزبَهُ لِيَكُونُوا مِن أَصحَابِ السَّعِيرِ

↪️“ሰይጣን ለናንተ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ ጠላት አድርጋችሁ ያዙት፡፡ ተከታዮቹን
የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲሆኑ ብቻ ነው፡፡” ፋጢር 6

↪️የአላህ ጠላቶች ዋና ግብ ሙስሊሟ ሴት በዱንያና በአኼራ ነጃ የምትወጣበትን ስርዓት ለቃ የእነርሱን የተበላሸ ስርዓት እንድትከተል በመሆኑ ማንኛውንም ጥንቃቄ ማድረግ
ይኖርባታል፡፡

↪️✅የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ወደመልካም አቅጣጫ መመራት በአላህ መሆኑን ፤ አላህ ያላቀው እርሱ ብቻ የተላቀ ፤ አላህ ያዋረደው ደግሞ እርሱ ብቻ የተዋረደ መሆኑን ልታረጋግጭ ይገባል፡፡

🔷አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡-

📌وَمَن يُهِنِ اللَّه فَمَا لَهُ مِن مُكرِمٍ إِنَّ اللَّه يَفعَلُ مَا يَشَاء

“አላህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም፡፡ አላህ የሻውን
ይሰራልና፡፡” ሐጅ 18

↪️ስለዚህ ከአላህ ጋር ያለሽን ግንኙነት ማጥበቅና ማጠናከር ፤ ወደአላህ መጠጋት ፤ በዲኑና እና በዱዓ ላይ ጽናት ልታደርጊ ይገባሻል!!


📌✅ከዱአዎች ሁሉ ትልቁ ደአ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

📌اللهم أصلح لي ديني الذي هو عصمة أمري ، وأصلح لي دنياي التي فيها معاشي
، وأصلح لي آخرتي التي فيها معادي ، واجعل الحياة زيادة لي في كل خير واجعل
الموت راحة لي من كل شر"

📚رواه مسلم


“አላህ ሆይ! የነገሬ ሁሉ መጠበቂያ የሆነውን ሐይማኖቴን አብጅልኝ ፤ መኖሪያየ
የሆነችውን ምድረ ዓለም አብጅልኝ ፤ መመለሻየ የሆነችውን የመጨረሻ ዓለም አብጅልኝ ፤ ህይዎቴን ለበጎ ስራ መጨመሪያ አድርግልኝ ፤ ሞቴንም ለእኔ እረፍት አድርግልኝ፡፡”

📚ሙስሊም ዘግበውታል

#ኢንሻአላህ
ይቀጥላል

=
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ ክፍል 1⃣7⃣ ↩️
〰〰〰〰〰〰

↪️ የሀይድና የበሽታ ደም መለያዎች
↪️ የበሽታና የሀይድ ደም በሚዛባ ጊዜ የሴቶች ሁኔታ


🔻ሼር በማድረግ እህቶቻችን እናንቃ

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
🔺حفظه الله تعالى!!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
✅ነፍሱ ከዒባዳ መሰላቸቷን ያስተዋለ፤ኢስቲግፋር ያብዛ። ማንኛውም ሰው ዒባዳን መፈፀም የሚሳነው በሰራው ወንጀል ምክንያት ነው።
أَسْتَغْفِرُ اللَّهَ الْعَظِيمَ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ، وَأَتُوبُ إِلَيْهِ.
https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
አጥጋቢ ረድ ለ አህባሹ ዩኑስ ቅጥፈት ና ጅህልና
أبو البخاري مبارك بن إبراهيم
↪️ የአህባሾች ዉሸትና ቅጥፈት በኢብኑ ተይሚያ ላይ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

ረድ ለቀጣፊው ለጃሂሉ ለአህባሹ ዩኑስ

👉ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ አላህ ወደ ታችኛው ሰማይ የሚወርደው ልክ እኔ እንደምወርደው ነው ብሎ ከሚንበር ወርዶ አሳየ እያሉ ለሚቀጥፋ አህባሾች የተሰጠ አጭር መልስ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Kitabu Tewhid #2
Ibnu Munewor
↪️ ተከታታይ የኪታቡ ተውሒድ ደርስ

ደርስ ክፍል 2⃣
〰〰〰〰

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
🔻حفظه الله تعالى
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
አርበዒን 21ኛ ሐዲሥ
Ibnu Munewor
ደርስ
~~~~

~ አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር
~ በመርከዘ ተውሒድ ላሉ የቁርኣን ሒፍዝ ተማሪዎች እየቀረበ ያለ
~ ሐዲሥ ቁጥር – 21
~ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ pdf መልክ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/1672

ክፍል ሀያን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊክ ይጫኑ⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/Umu_Yusuf_talibetalelm/1006
Audio
▪️አዝካር ወል አዳብ
➖➖➖➖➖➖➖
🔻الأذكار والآداب


↪️ ክፍል 0⃣9⃣ ↩️
〰〰〰〰〰〰

👉ከሶላት በኋላ የሚባሉ ዚክሮችና ትርጉማቸው በአጭሩ

①) ستغفر الله أستغفر الله أستغفر الله

②) اللهم أنت السلام ومنك السلام تباركت يا ذا الجلال والإكرام

③) لا إله إلا الله وحده لا شريك له له الملك وله الحمد وهو على كل شيئ قدير اللهم لا مانع لما أعطيت ولا معطي لما منعت ولا ينفع ذا الجد منك الجد

④) لا إله إلا الله وحده لا شريك له له الملك وله الحمد وهو على كل شيئ قدير لا حول ولا قوة إلا بالله لا إله إلا الله ولا نعبد إلا إياه له النعمة وله الفضل وله الثناء الحسن لا إله إلا الله مخلصين له الدين ولو كره الكافرون

⑤) لا إله إلا الله وحده لا شريك له له الملك وله الحمد يحيي ويميت وهو على كل شيئ قدير


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
🔺حفظه الله تعالى!!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w

ክፍል አንድን ለማገኘት⤵️⤵️⤵️
https://t.me/Umu_Yusuf_talibetalelm/1526