💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
أنقذوا أنفسكم ..أنقذوا بناتكم وزوجاتكم

الشيخ صالح الفوزان حفظه الله ورعاه
~

t.me/https_Asselefya1
Audio
#صوتيات_البدر

▪︎من يفعل مثل هذه الأفعال عنده نقص في ايمانه أو نفاق...

🎙الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله

~ t.me/https_Asselefya1
✍ ትንሽየ መልክት ለዱዓቶች ወንድሞቼ !


☞ አልሀምዱሊላህ ለአሏህ ምስጋና ይገባው ወደ ዲን ወደ ሓቅ የሚጣሩ ትጉ ዳዒዎችን በየዘመኑ የሚቀሰቅስ አምላክ !! ወደ አሏህ ጥሪ ማድረግ ታላቅ ቦታ አለው ከዱንያዊ ብልጭልጭ እንዳለ የበለጠ ነው ነብያችን ﷺ ለዓልይ የኸይበር ቀን ላይ እንዳሉት ።

☞በሀገራችንም ብዙ ዳዒዎች አሉ አልሀምዱሊላህ አሏህ ይጠብቃቸው አሏህ ከነሱ ይመድበን ያረቢ !! እኔ ትንሹ ወንድማችሁ ከናንተ መደዳ ባልሆንም ግን ትንሽየ ሀሳብ ስላለኝ ነው ብዙ ወቀሳዎችን ስለምሰማ ነው የምፅፈው ስህተት ካለኝም ብታርሙኝ ደስ ይለኛል ኢንሻ አሏህ

☞አዋቂ ተቀምጦ ተማሪው መናገር አደብ እንዳልሆነ አውቃለሁ ግን ለዛሬ ፍቀዱልኝ ባረከሏሁ ፊኩም ፈሳዱ እየበዛ ስላለ ነው የምናገረው ወንድሞቼ አሏህ ያግራውንጅ መቼም የሰው ልጅ ይሳሳታል ከስህተቱ መመለስ ግን ትልቅ ነገር ነው ! በተለይ ማንሳት የፈለኩት ስለ ሚዲያ ነው በዝህ ፈተና በበዛበት ዘመን ብዙ ዳዒዎችን ከዱርየ።ሰፈር እያዋለ ያለው ትልቁ ወጥመድ ይህ ሚዲያ ነው በዝህም ምክኒያት ብዙ ዱዓት ራሱን አስንቆ ሌሎች ዱዓትንም አሰድቧል الله المستعان

☞ የሴት ልጅ ፈተና ከባድ እንደሆነ በኪታብ አንብበናል ስለዝህ መተግበሩ ላይ ምነው ከበደንሳ ??? የሴት ልጅ ፈተናን ተጠንቀቁ ተብለን እኛ መጀመሪያ ወዳቂ ከሆንን ምኑ ላይ ተጠነቀቅን እስኪ ???

☞ በሚዲያ በብዙ መንገዶች ከሴቶች ጋር ልንገናኝ እንችላለን በቂርአት ወዘት ... ግን ይህ ለምን ድንበር አሳልፎ እንድንጃጃል አደረገን ምን ታስቦበት ነው ?? እውነት ለመናገር ብዙ እህቶች እንደተበደሉ ሰምቻለሁ ግን እውነት አልመስል እያለኝ ነበር ብዙው በተለይ ከዳዒ ይህ አይጠበቅም አላህን መፍራት አያስፈልግም ትላላችሁ ??

☞ሴቶች ዲን አስተማሪ ነው በሚል ለትዳር ሲመኙና ከኛ ያለው።አፀፋዊ ምልሻ ግን የከፋ ከሆነ በጣም ይገርማል ወሏሂ ከሆነ ትዳሩን አጥብቆ መቀጠል ካልሆነ ወጣ ገባ አለማለት ይሰመርበት !! በሚዲያ ያየናትን ሴት እንዳለ መልከፍ እኮ ይህ የዱዓቶች ስራ አይደለም ወሏሂ ይህ የዱርየ ስራ ነው አድሚናቶችን ሰብስቦ ለብቻ መጀንጀን ምን የሚሉት አካሄድ ነው ወገን ?? እንዴት አሏህን ፍሩ የሚል ይጥፋ ... ??

☞አድሚናቶችስ ሴት አይደሉምን ? ወይስ ለነሱ የተለየ አለው አንዳንዱ ደግሞ ቂርአት አቀራለሁ ብሎ ገብቶ በመጀመሪያው ቀን ድምፁዋን ሲሰማ ቅልጥ ብሎ ቁጭ ይህ ሰው ላቅራ ብሎ ገብቶ ተቀርቶበት ወጣ الله المستعان ያልሆኑ ቃላትን መናገር እና መሳደብ መዝለፍ ማሽሟጠጥ ይህ ከዳዒ አይጠበቅም እኮ

☞ በግል እየገባህ " ማሻ አሏህ " ትላለህ በመጀመሪያው ቀን በሁለተኛ ደግሞ ሌላ ቃል ይከተላል እረ ተው ይቅርብህ ወንድሜ በየግሩፕ እና ቻናል እየገባን አድሚኖችን እና ተሳትፌ ያላቸውን ሰዎች አዛ።ማድረግ ከኛ አይጠበቅም ወሏሂ ያሳፍራል ሲጀመር

☞ለዳዕዋ ጋብዘውህ ከሆነም ዳእዋህን አድርገህ ሹልክ ብለህ ውጣ ከዛ ውጭ ማሽቃበጡና እየየ ማለቱ ጥሩ አይደለም ወሏሂ ። እንዲህ ከሆንም ራስህ ተደፍረህ ሌሎችንም ታስደፍራለህ በግል እየገቡ ሴቶች አዛ ቢያደርጉህ ምንም እነሱን እንዳትወቅስ ችግሩ ከራስህ ነው የስራህን ውጤት ነው ያገኘኸው !!

☞በተለይ በሚዲያ ስታስተምር ከዝህ ነገር ራስን አርቀህ ቆፍጠን ብለህ ኮስተር ብለህ ነው መሆን ያለበት እንጅ እየተለፈሰፈስክ እየሳቅክ በቃላት እያሽሞነሞንክ ከሆነክ እመነኝ 3 ወር ሳታቀራ ነው አደጋ ውስጥ የምትወድቀው !! በሚዲያ ቂርአት ማቅራት ቀላል እንዳይመስላችሁ ፍም ነው ፍም ለዛውም በጣም ከባድ ለቻለበት ቀላል ሲሆን ላልቻለበት ደግሞ ጠልፎ የሚጥል ወጥመድም ጭምር ነው !!

☞ ስለዝህ ወንድሞቼ ሴት እህቶቻችን እንዲያከብሩህ አሏህ እንዲያከብርህ ሰው ዘንድ እንድትከበር " ክብርህ ጠብቅ ትከበር ዘንድ " ይህ ትልቅ አባባል ነው ለተገነዘበው ። እናም እኔ ወንድማችሁ ያየሁትን ጥፋት ነው የተናገርኩት አሏህን እንፍራ ሚዲያን ለጥሩ ነገር እንጠቀምበት እንጅ ሰውን ማጃጃያ አናድርገው ለማለት ነው የበደልነው ሰውም ካለ ይቅርታን እንጠይቅ ነገ አሏህ ፊት መቆም ስላለ ፀፀት የማይጠቅምበት ቀን .... !!

👉 እናንተ ዱዓት ወንድሞቼ ሆይ ፦ በተናገርኩት ስህተት ካለበት እረሙኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ ኢንሻ ኣሏህ , አሏህ ይጠብቃችሁ አሏህ ሰላም ያድርጋችሁ በያላችሁበት!!

✍ አብዱረሕማን አቡ ዑሰይሚን
~~
t.me/abuUseyminabdurehman
t.me/abuUseyminabdurehman
ሴት ልጂ በዲኗ ጠንካራ ከመሆኗ ጋር  አኽላቋ ያማረች ደርበብ ያለች ስትሆን እንዲሁም ራሷን የጠበቀች ስትሆን ደስ ትላለች።
ያዉ ራሳችሁን  ዉበታችሁን ጠብቁ ምናባቱ ለብቻዬ ነኝ ብላችሁ ራሳችሁ አትጣሉአሁን ያልተለመደ ካገቡ በኋላ አይመጣምና ራሳችሁን በየትም ሆናችሁ ጠብቁ ለባል ብቻ አይደለም ዉበት ለራስሺም ዋብ በይ በቃ ሚ ሙሽክላ እ!?

~
https://t.me/https_Asselefya1
11-العبودية - لشيخ الإسلام ابن تيمية
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም
አዲስ ተከታታይ ትምህርት


📚 العبودية لشيخ الإسلام ابن تيمية

➮ ክፍል 11


ፉሪ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ

🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም

𝐓𝐞«t.me/SheikhMuhammedZainAdam
‏قال يحيى بن معاذ :

للتائب فخر لا يُعادله فخر، فرح الله بتوبته .

📚 « صفوة الصفوة ( ٣٤٢/٣) -"
وسيق الذين اتقوا
مزامير الفرقان
ውሀ ምድርን ህያው እንደሚያደርጋት ሁሉ  ቁርአንም ቀልብን ህያው ያደርጋታል።» ኢብኑል ቀይም»

«ከቁርአን ጋር እንኑር»

~

𝐓𝐞« t.me/https_Asselefya1
ኢብኑ ረጀብን አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል፦

አንድ ባሪያ በዱዓ ላይ ችክ እስካለ ድረስ፡የዱዓውን መልስ እስከከጀለና ተስፋ እስካልቆረጠ ድረስ፡እርሱ መልስ ለመሰጠት ቅርብ ላይ ነው።በርን መቆርቆር ያበዛ ሊከፈትለት ይቀርባል።
ጃሚዑ_ል ዒልሚ ወ_ል ሒከም (ገፅ፡404)

አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida