💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
☑️ ወንድማዊ ምክር
〰〰〰〰〰〰〰

🛑👉እድሜህን በጭንቀት፣ በሀዘንና በትካዜ አትጨርስ። በረባ ባረባው በትንሽ በትልቁ እየተብሰለሰልክ ውስጥህን አትጉዳ። ከዛም አልፎ ለስኳር፣ ለደም ግፊትና ለሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች እራስህን አታጋልጥ። የሚያስከፋ የሚያሳዝንና ደስ የማይል ነገር ቢገጥምህ እንኳ ቀልብህ ላይ ቋጥረህ ይዘህ ነፍስህን አታስጨንቅ። ዱንያ አጭር ናት ቢደላህም ቢከፋህ ታልፋለች። ዘውታሪነት ለአላህ እንጂ ለማንም የለም። ስታገኝ አመስጋኝ ስታጣ ታጋሽ ውድ የአላህ ባሪያ ሁን። ከዛ በዘለለ ለዱንያ ብዙም ቦታ አትስጥ። እንደሚታወቀው  ከሀዘን በኋላ ደስታ ከማጣት በኋላ ማግኘት እንዳለ ሆኖ የዱንያ መከራና ስቃይ የፈለገ ቢገዝፍና ቢበረታ በሶብርና በፅናት ትሻገረዋለህ። እጅግ ከከፋም በሞት ትገላገለዋለህ። ነገራቶች ሲስተካከሉልህ፣ ያሰብከው ሲሳካና ህልምህን እውን ሲሆን እንደምትደሰተው ሁሉ ነገራቶች በተቃራኒ ሲሆኑብህ የአላህ ውሳኔ ነውና ወደህ ተቀበል። ሲሳካለትና ሲያገኝ የሚደሰት ሲያጣና ሲቸገር የሚማረር ጥቅሙን ብቻ የሚያሳድድ ልሾ ወዳድ አትሁን። ነገራቶችን ቀለል አድርገህ ኑር። የሁል ጊዜ ሀሳብና ጭንቅህ ከሞት በኋላ ስላለው ለዘልአለማዊ ህይወትህ ይሁን። ከዱንያው ይልቅ ለአሄራው ቤትህ አብዝተህ ልፋ ተጨነቅ። በትንሽ ትልቁ አትማረር። በዱንያ ላይ ስትኖር የበታችህን እንጂ የበላይህን አትመልከት። የሌሎችን እያየህ እራስህን በቅናት አትግደል። በአላህ ካመንክና በሱ ላይ ትክክለኛ መመካትን ከተመካህ በማጣት ውስጥ ሆነህ ማግኘትን ታያለህ። በችግር ውስጥ ሆነህ ደስታን ታጣጥማለህ።

🛑👉ዱንያ በባህሪዋ አጭርና ጠባብ ናት የባሰ ደግሞ አንተ አታጥባት። ሲጀመር ዱንያ የተፈጠረው ላንተ እንጂ አንተ ለሡ አይደለም። ነግደህ ስላላተረፍክ አትበሳጭ። ከትምህርት ስለወደቅክ የህይወትህ መጨረሻ አድርገህ አትመልከት። ህይወትህ ሊለውጡ የሚችሉ ከዛ ውጪ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሉህ። አንዱ ካልተሳካልህ የግብህ መጨረሻ ያ አታድርግ። በጌታህ ታግዘህ ነገራቶችን ቀያይረህ ሞክር። እንደ ጋሪ ወደ አንድ አቅጣጫ ወደፊት ብቻ አትመልከት። በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ። ተስፋ መቁረጥ የስኬት ግርዶሽ ነው። ማወቅ ያለብህ ያንተ ጥረትና ልፋት ሰበብ እንጂ ሌላ አይደለም። ሰጭውና ከልካዩ የበላይና የበታች አድራጊው አላህ ነው። áˆľáˆˆá‹šáˆ… ሁሌም አመስጋኝ፣ ታጋሽ፣ ታታሪ፣ ጠንካራና ማራል ያለው ጀግና ሁን። ባጣኸው ነገር ውስጥ ሊደርስብህ የነበረ መጥፎ ነገር ስለማታውቅ ለምን አጣሁት ብለህ ችክ አትበል።

🛑👉ሁሌም ደስተኛ ሁን። ለሀዘን ለትካዜ በር አትክፈት። ደስታን ለማግኘት እሩቅ አትሂድ እጅግ በጣም ቀላል ነው። በአላህ ማመን እሱን በብቸኝነት መገዛትና መልካም መስራት ብቻ ነው የሚጠበቅብህ። ይህ ካደረግክ አላህ በዱንያም በአሄራ ደስተኛ ህይወት ሊያኖርህ ቃል ገብቷልና።
مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡


📚 ሱረት አን_ነህል 97

t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
▹ ሰምተሀል እሺ ማዶ ላይ አንተን ነዉ!!

=
የህይወት ህጎች•••
ልታደርገው የምታስበውን ሁሉ አትናገር _
ራእይ የምትኖረው የምታደርገው ነገር እንጅ የምትናገረው አይደለም።
አንዳንዴ••••
ለራስህ ንገረው ይህን ነገር በንግግር አደለም በተግባር ነው እምገልጸው በል! ህልሞች( ራእዬች) በተግባር የምንገልጻቸው ናችዉ። ስራህ ራሱ ጥሩ ይናገራል።አንተ የምታስበውን ለስዎች መናገር አይጠበቅብህም።

መልካም ለሊት••••••
Audio
❝አዲስ የአቂዳ ኪታብ ቂርአት❞
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️


☞የኪታብ ርዕስ፦ሚን ኡሱሊ አቂደቲ አህሊ ሱነቲ ወልጀመዓ!!

📍 ክፍል   1
8 የመጨረሻ

📜የኪታብ 𝐏𝐝𝐟 ⇩⇩
t.me/https_Asselefya1/11411

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

  ⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇙⇙⇙⇙⇙⇙
    t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
❝ሙሉ ትምህርት ❞

📚 أمن_البلاد_أهميته_ووسائل_تحقيقه

ÂŤ
የሃገር ደህንነት አሳሳቢነቱና የማረጋገጫ መንገዶቹ።»

☞ክፍል ❶ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2429

☞ክፍል ❷ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2430

☞ክፍል ❸ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2431

☞ክፍል ❹ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2432

☞ክፍል ❺ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2433

☞ክፍል ❻ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2434

☞ክፍል ❼ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2435

☞ክፍል â˝ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2436

☞ክፍል ❾ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2437

☞ክፍል ❿ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2438

☞ክፍል❶❶ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2439

☞ክፍል ❶❷ ⇣⇣
t.me/AbumuslimKitaboch/2440
            •┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•

🎙በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን  አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)  


«ትምህርቱን ለመከታተል á‹­áˆ…ን ቻናል ይቀላቀሉ»
https://t.me/AbumuslimKitaboch
http://t.me/AbumuslimAlarsi
ሴቶችዬ ማለዳ ስራ ከመጀመራችን በፊት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እናድርግ እሺ!! ግደታ ስፓርት መስሪያ ቤት መሄድ አይጠበቅብንም እድሜ ለኢንተርኔት ዩቱብ ሰርች አድርገን በቀላሉ እያየን በቤታችን መንቀሳቀስ እንችላለን እሺ¡ እየሰራችሁ ማለቴ ነዉ¡

=
ዛሬ እሁድ የደስታ እንባ የሚነባበት ቀን ቀጠሮ የሚደረግበት ቀን ኢላሂ.....ደስታዉ የተለዬ ነዉ!

ደግ ዋሉልኝ 🍁 ጥቅምት 11/2/2016

ትቀመጥ ለትዉስታ.....¡
=
t.me/https_Asselefya1
«የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው»

የዋትሳፕ ቻናላችን ይቀላቀሉ➷➷➷
https://whatsapp.com/channel/0029Va7et0L7YSd6xtUu0q36
✍️ልናስተውለዉ የሚገባ ድንቅ አባባል፦ኢብኑል ቀዪም(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦“አንድ የአላህ ባሪያ አላህ ዘንድ ሁለት መቆሚያ ስፍራ አለው።

የመጀመሪያው፦ ለሰላት እርሱ ዘንድ መቆም ሲሆን
ሁለተኛው ደግሞ፦የቂያማ ዕለት አላህ ዘንድ የሚቆመው መቆም ነው፤የመጀመሪያውን ላይ በአግባቡ በመቆም የተወጣ ከሆነ፣ሁለተኛውና ሌላኛው የመቆሚያ ስፍራ ላይ ነገሩ ሁሉ ገር በገር ይሆንለታል።” [“አልፈዋኢድ”(ገፅ:274)]

قال ابن القيم رحمه الله
للعبد بين يــدي الله موقفان :
موقف بين يديه فى الصلاة وموقف بين يـديـه يوم لقائه
فمن قام بحق الموقف الأول هون عليه الموقف الآخر ، ومن استهان بهذا الموقف ولم يوفه حقه شـدد عليه ذلك الموقف

كتاب الفوائد ص (274)

=


https://whatsapp.com/channel/0029Va7et0L7YSd6xtUu0q36
ለማንም ከመሆንክ በፊት ለራስክ ሁን‼️

=
ወንድ ልጅ ኮስተር ሲል እጅ ሴቶች ጋ ሲርመጠመጥ አያምርበትም‼️

ኮስተር ስትል ሴቶችም አተን ለመዳፈር ይከብዳቸዋል‼️

አለዛ ግን ከሴቶቹጋ አንድ አርገው ያዩሀል  ያአኺ ጀግና ወንድ ሁን በሴቶች ዙርያ ስትርመጠመጥ አትዋል‼️

=
منقول
አላህ የሚወደውን ማንኛውንም መልካም ተግባር እውን ለማድረግ መፍጠን የሚወደድ ተግባር ነው። ትዳርም ከመልካም ተግባራት ተመዳቢ ነውና  መቻኮሉ የሚያስመሰግን እንጂ "ምን ያጣድፍሃል" የሚያስብል አይደለም።

منقول

እየቸኮላችሁ.......¡

t.me/https_Asselefya1
«አላህን የመፍራት ተምሳሌቱ ወጣት
ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.....!!
Âť

⏠⏠
ክፍል  ⓵
⏡⏡
«አንተ በሴት ልጅ ዉበት የተማረከውና
የተታለልከው ሰው ሆይ አህመድ ቢን ሰዒድ አል ዐባዲ ከአባቱ ሰምቶ ያስተልለፈውን ድንቅ ታሪክ ታነብ ዘንድ እነሆ ጋበዝኩህ፡፡
Âť

☞በኩፋ ከተማ በሚገኘው ታላቁ መስጅድ ዉስጥ አዘውትሮ የሚገኝ አንድ አላህን ፈሪ ወጣት ነበር፡፡ ይህ ከመስጅድ የማይርቀው ወጣት መልከ መልካም፣ ጸባየ ሰናይ እንድሁም ዉብ ተክለ ቁመና የተቸረው ነው፡፡ ከእለታት በአንዱ ቀን አንዲት ቆንጆና በጣም አስተዋይ የምትባል ሴት በአጠገቡ ስታልፍ በትኩረት ተመለከተችው፡፡ ☞ዉቧ ልጃገረድ በዉቡ ወጣት በመልኩና ከዉጭ በሚንጸባረቀው መልካም ስነምግባሩ ተማረከች፡፡ በፍቅሩ ተጠቃች፡፡ ይህ ወጣት ምናልባትም ከእኔ ቀድሞ እሱ በኔ ፍቅር ተጠቅቶ ሊሆን ይችላል ብላ በማሰብ ከዛሬ ነገ ይቀርበኛል፤ ከዛሬ ነገ ይጠይቀኛል እያለች ታስብ ጀመር፡፡ ነገር ግን ልጁ ሳይጠይቃት ጊዜው ረዘመ፡፡ በዚህም ከእሷ ምንም አይነትፍላጎት እንደሌለው ተገነዘብች፡፡

☞ታዲያ ይቺ ቆንጆ ወጣት ይሄ ልጅ እሱ ባይፈልገኝም እኔ ላናግረው ይገባል በሚል ከእለታት በአንዱ ቀን ወጣቱ ከመኖሪያ ቤቱ ወደ መስጅድ በሚሄድበት መንገድ ላይ ጠበቀችና አንተ ወጣት ሆይ ላናግርህ ፈልጋለሁ፡፡ ባክህ አንድ ጊዜ ስማኝ፡፡ ለምጠይቅህ ጉዳይ ፈቃደኛ ከሆንክልኝ ያሰብኩት ተሳካልኝ ማለት ነው፡፡


☞ፈቃደኛ ካልሆንክልኝ ደግሞ አንተ የመሰልህን የማድረግ መብትህ የተከበረ ነው ብላ በትህትና ጠየቀችው፡፡ ዐቢዱ ግን አጅነቢይ ከሆነች ሴት ልጅ ጋር የማውራት ድፍረቱም ይሁን ፍላጎቱ አልነበረውምና ምንም ቃል ሳይመልስላት ወደ መስጅዱ አቀና፡፡ ወጣቷ በዚህ ሙከራዋ ተስፋ ሳትቆርጥ በሌላ ቀን ከመስጅድ ወደ ቤቱ ሲመለስ በተመሳሳይ ቦታ ጠበቀችና አናገረችው፡፡ አንተ ወጣት ሆይ አድምጠኝ አለችው፡፡ እሱም ትንሽ አሰበና ማድመጡን አደምጥሽ ነበር፡፡

☞
ነገር ግን እንደዚህ አይነት ቦታ ላይ ከባእድ ሴት ጋር ቆሞ መታየትም ይሁን ማውራቱ አስነዋሪ ተግባር ነውና አላደርገውም፡፡ መጥፎ በሚያስጠረጥርና ክብርን በሚያጎድፍ ቦታ ላይ መገኘት አልሻም ብሎ መለሰላት፡፡

⊰ይቀጥላል⊰ ⬞⬞⬞⬞⬞⬞⬞⬞⬞⬞⬞✍️

↴↲↴↲↴↲↳↲↴↲↴↲↴
https://t.me/https_Asselefya1
«ሙሉ ተቀርቶ የተጠናቀቀ የሚን ኡሱሊ አቂደቲ አህሊ ሱነቲ ወል ጀመአ ኪታብ ቂርአት ደርስ»

⊰⊰ የኪታብ Pdf ⊱⊱
t.me/https_Asselefya1/11411

⊰ክፍል  01➴➴
t.me/https_Asselefya1/11412

⊰ክፍል  02➴➴
t.me/https_Asselefya1/11433

⊰ክፍል 03➴➴
t.me/https_Asselefya1/11505

⊰ክፍል 04➴➴
t.me/https_Asselefya1/11526

⊰ክፍል 05➴➴
t.me/https_Asselefya1/11577

⊰ክፍል 06➴➴
t.me/https_Asselefya1/11654

⊰ክፍል 07➴➴
t.me/https_Asselefya1/11664

⊰ክፍል 08➴➴
t.me/https_Asselefya1/13477

⊰ክፍል 09➴➴
t.me/https_Asselefya1/13533

⊰ክፍል  10➴➴
t.me/https_Asselefya1/13722

⊰ክፍል  11➴➴
t.me/https_Asselefya1/13741

⊰ክፍል 12➴➴
t.me/https_Asselefya1/13757

⊰ክፍል 13➴➴
t.me/https_Asselefya1/14137

⊰ክፍል 14➴➴
t.me/https_Asselefya1/15596

⊰ክፍል  15➴➴
t.me/https_Asselefya1/15627

⊰ክፍል 16➴➴
t.me/https_Asselefya1/15642

⊰ክፍል 17➴➴
t.me/https_Asselefya1/15650

⊰ክፍል  18➴➴
t.me/https_Asselefya1/15683

=

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ ሀፊዘሑሏህ
𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
Video
እየተለማመዳችሁ ልምድ ዉሰዱ ዝም ብላችሁ እንደተመቻችሁ እየሰራችሁ ራሳችሁን እንዳትጎዱ እሺ¡ ሁሉም ስራ ባለሙያ አለዉ ባለሙያ አይቶ መስራት እና ዝም ብሎ በደመ ነፍስ መስራት አንድ አይደለም።💪👈ሁሉም ሙስሊም ወጣት የጡንቻ ባለቤት መሆን አለበት ከሴት ጡንቻ አትመሳሰሉ ወንዶች ስሩ ስፓርት በደንብ !!
=