💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔺የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

【مَنْ صلَّى عليَّ صلاَةً، صلَّى اللَّه علَيّهِ بِهَا عشْرًا】
🔻በኔ ላይ አንድ ሶላት ያወረደ አላህ በሱ ላይ በአስር እጥፍ አድርጎ ያወርድበታል።
📚 رواهُ مسلم

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት

◾️የፃም ዋጅብነት በመረጃ
◾️ረመዷንን ያስተባበለ ሰው ሁክሙ
◾️ረመዷን የተደነገገበት ደረጃና ሁኔታ
〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰
《ክፍል 0⃣6⃣》
〰〰〰〰〰〰

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#እህቴ ሆይ! ለዱኒያ ውበት ብለሽ አሂራሽን አታበላሺ በዱኒያ ብልጭልጭ አትታለይ! እመኚኝ #ሀያዕ ካለሽ ከማንም በላይ #ውብ ነሽ!
➬ኢማሙ አሽሻጢቢይ - ረሂመሁላሁ - እንዲህ ይላል ;-
" አንድ ባሪ ደስተኛ የመሆኑ ምልክት
ለሱ አላህን መታዘዝ መግራቱ
ስራው ሱናን የገጠመ መሆኑ
ሳሊሆችን መጎዳኘቱ
ከወንድሞቹ ጋር ፀባዩ ማማሩ
ለሰዎች መልካም መስራቱ
ለሙስሊሞች ጉዳይ ትኩረት መስጠቱ
ጊዜውን መጠበቁ " ናቸው
▪️እናማ ይችን የቀረችውን የረመዷን ቀናቶች እንጠቀምባቸው ጊዜያችንን ባረባ ነገር ከማሳለፍ እንቆጠብ!!

አል ኢዕቲሳም ( 2/152 )
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ﻳَﺴْﺄَﻟُﻪُ ﻣَﻦ ﻓِﻲ اﻟﺴَّﻤَﺎﻭَاﺕِ ﻭَاﻷَْﺭْﺽِ ۚ ﻛُﻞَّ ﻳَﻮْﻡٍ ﻫُﻮَ ﻓِﻲ ﺷَﺄْﻥٍ

በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉት ሁሉ ይለምኑታል፡፡ በየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው ጭንቀትን ያስወግዳል
ወንጀልን ይምራል
ሪዝቅ ይሰጣል
ህሙማንን ያድናል
የተቸገረን ያደላድላል
የከበደን ያቀላል
የተሰበረን ይጠግናል...
ሱብሀነላህ ብቻ ሁሌ ስራ ላይ ነው

»[{እንደታዘዝከው ቀጥ በል}]

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
◾️የረመዷን መግባቱ በምን ይረጋገጣል
◾️ጨረቃ ለብቻው ምን ማድረግ አለበት
◾️ጨረቃ አየሁ የሚል ሰው እንቀበለው ዘንድ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
〰〰〰〰〰〰
〰〰〰〰〰〰
《ክፍል 0⃣7⃣》
〰〰〰〰〰〰
🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
ለሶላት የውጭ ድምፅ ማጉያ መጠቀም ይፈቀዳልን?
~~~~~~~~~~~~~~~
በረምዳን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት የውጭ ድምፅ ማጉያዎችን ለሶላት መጠቀም አላስፈላጊ ተግባር ነው። በዚህ ተግባር የሚከተሉት ጥፋቶች አሉበት:-
1/ በቁርኣን አንዱ በሌላው ላይ እንዳይጮህ የሚከለክልውን ሐዲሥ መጣስ አለበት።
2/ ባጎራባች ያሉ ሰዎችን መረበሽ አለበት።
3/ ባጎራባች መስጂዶች ያሉ ሰጋጆችን በሩኩዕ በሱጁድ… ያሳስታል።

ሌሎችም ጥፋቶች አሉት። እንዲያውም በተሀጁድ ብቻ ሳይሆን #በሌሎችም ሶላቶች የውጭ ድምፅ ማጉያዎችን መጠቀም ክልክል ነው ይላሉ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ። ይሄውና:

ጥያቄ:- “ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የመስጂድ ኢማሞች የውጭ ድምፅ ማጉያዎችን መጠቀም አብዝተዋል። ድምፅ ማጉያዎቹ በአብዛኛው ሚናራ ላይ የሚሆኑ ሲሆን በጣም ከፍ ያለ ድምፅ ይጠቀማሉ። በዚህ ድርጊት የተነሳ ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው ሶላቶች ጊዜ ከፊል መስጂዶች በቁርኣን ንባብ ጊዜ ድምፅ ማጉያዎችን ስለሚጠቀሙ ሌሎቹን ይወሰውሳሉ። እና ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው ሶላቶች ጊዜ የድምፅ ማጉያዎችን መጠቀም ብይኑ ምንድነው?

መልስ:-
የሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር:-
ድምፅ ከፍ በሚደረግባቸው ሶላቶች ጊዜ ድምፅ ማጉያዎችን ከሚናራ ላይ
መጠቀም ክልክል ነው። ምክንያቱም በአቅራቢያ ባሉ #ነዋሪዎችና_መስጂዶች ላይ መረበሽ አለበትና። ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ በዘርቃኒ ትንታኔ ላይ እንደሚገኘው ሙወጦእ (178) ላይ በ (باب العمل في القراءة) የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እየሰገዱ ከነበሩ ሰዎች ዘንድ ወጡ። በቁርኣን ድምፃቸው ከፍ ብሏል። በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ:-
"إن المصلي يناجي ربه فلينظر بما يناجيه به ولا يجهر بعضكم على بعض بالقرآن"
“ሰጋጅ ከጌታው ጋር ነው የሚንሾካሾከው። ስለዚህ የሚንሾካበትን ይመልከት። አንዳችሁ በሌላው ላይ በሶላት አይጩህ። አቡ ዳውድ (1332) (رفع الصوت بالقراءة في صلاة الليل ) በሚል ርእስ ስር ከአቡ ሰዒድ አልኺድሪ ረዲየላሁ ዐንሁ በዘገቡት የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመስጂዳቸው ኢዕቲካፍ አድርገው ነበር። በቁርኣን ሲጮሁ በሰሟቸው ጊዜ መጋረጃውን ገልጠው እንዲህ አሉ:-
"ألا إن كلكم مناج ربه فلا يؤذين بعضكم بعضاً ، ولا يرفع بعضكم على بعض في القراءة ، أو قال في الصلاة"
“ንቁ! እያንዳንዳችሁ ከጌታው ጋር ነው እየተንሾካሾከ ያለው። ስለሆነም አንዳችሁ ሌላችሁን አያስቸግር። በቁርኣን ንባብ / በሶላት አንዳችሁ ሌላችሁ ላይ አይጩህ።” [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብኒ ዑሠይሚን: 13/74-96]

በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል:-

“ሶላቶችን ከሚናራዎች ላይ በድምፅ ማጉያዎች ማስተላለፍ ጠያቂው እንዳለው በየቤታቸው ያሉ ሰዎችን መወስወስ ነው። የግል ዚክሮቻቸውንና ተስቢሖቻቸውን ማናጋት ነው። ምናልባትም ከዚህ ጊዜ ውጭ ማረፊያ ያጡ የተኙ ሰዎችንና ህመምተኞችን መረበሽ ሊኖርበትም ይችላል።
በተጨማሪም ከዚህ ድምፅ ባጎራባች ላሉ መስጂዶች መረበሽና መወስወስ አለበት።” ፈትዋው ረጅም ነው። [ኑሩን ዐለ ደርብ:176]

የሁለቱንም ፈትዋዎች ይዘት ሙሉውን ስላላቀረብኩ የፈለገ ሰው ምንጩን ተከትሎ ያንብብ።
https://t.me/IbnuMunewor

(ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዳን 19/1442፤ ሚያዚያ 23/2013)
Audio
◾️ሶላት ላይ ኢማምን መቅደም
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔻ከኢማም መሽቀዳደም ሁክሙ
🔻ከኢማም ጋር እኩል እኩል መሆን
🔻ከኢማም ወደ ኋላ መዘግየት

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
♻️📌ኢእቲካፍ📌♻️
➖➖➖➖➖➖➖

🔺✅የኢቲካፍ ትርጉሙና ሸሪዓዊ ድንጋጌው
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

#ኢእቲካፍ_ማለት አምልኮን አስቦ መስጂድ ውስጥ መቆየት ሲሆን ሸሪዓዊ ብይኑ ሱና ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፦

وَعَهِدْنَآ إِلَىٰٓ إِبْرَ‌ٰهِۦمَ وَإِسْمَـٰعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْعَـٰكِفِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ

 Ř§Ů„بقع؊: ٥٢ټ

“ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን”

 áŠ áˆ-በቀራህ 125

وَلَا تُبَـٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَـٰكِفُونَ فِى ٱلْمَسَـٰجِدِ

 Ř§Ů„بقع؊: ٥٨٧

“እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው”፡፡

 áŠ áˆ-በቀራህ 187

አዒሻ ረዲየሏህ ዐንሀ እንዳለችው

“ነብዩ(ﷺ) የረመዳንን የመጨረሻዎች አስር ቀናት እስኪሞቱ ድረስ ኢእቲካፍ ያደርጉ ነበር፡፡”

🔶 #የኢእቲካፍ_መስፈርቶች

↪️ኢእቲካፍ ፈፃሚው ሙስሊም መሆን፣ የመለየት እድሜ የደረሰና አእምሮው ጤናማ መሆን አለበት፡፡ በአንፃሩ ከሃዲ የአእምሮ ህመምተኛ ወይም የመለየት እድሜ ያልደረሰ ህፃን ኢእቲካፋቸው ትርጉም አይኖረውም፡፡ ለኢእቲካፍ አቅመ አዳም (ሄዋን) መድረስና ወንድ መሆን መስፈርቶቹ አይደሉም፡፡ የመለያ እድሜ (ሰባት አመት) የደረሰ እንዲሁም ሴት ልጅ ኢእቲካፍ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

↪️ኒያ፦ ነቢዩ (ﷺ) “ስራዎች የሚለኩት በኒያ ነው” ብለዋል::

↪️መስጂድ ውስጥ መሆን አለበት፦

“እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ”

 áŠ áˆ-በቀራህ 187

⏫ነቢዩም (ﷺ) ኢእቲካፍ የሚያደርጉት መስጂድ ውስጥ ብቻ እንጂ ቤት ውስጥ ወይም ሌላ ቦታ ኢእቲካፍ አድርገው አያውቁም፡፡

↪️🔶 የኢእቲካፍ ወቅት ተወዳጅ ተግባሮቹና ኢእቲካፍ ላይ ላለ ሰው የሚፈቀዱ ነገሮች

📌የኢእቲካፍ ወቅት፦ኢእቲካፍ ሊባል የሚችለው አንድ ግለሰብ መስጂድ ውስጥ ለተወሰነ ወቅት ሲቆይ እንጂ ምንም ካልቆየ ኢእቲካፍ አይሰኝም፡፡ ትንሹ የኢእቲካፍ መጠንን በተመለከተ በዑለማዎች መካከል የተለያዩ ሃሳቦች ቢኖሩም ነገር ግን የተሻለው አቋም ገደብ የለውም የሚለው ነው፡፡

ይሁንና ከአንድ ቀን ባያንስ የተሻለ ነው ምክንያቱም ነቢዩም (ﷺ) ሆኑ ከሰሃቦች አንድም ግለሰብ ከአንድ ቀን ያነሰ ወቅት ኢእቲካፍ እንዳደረጉ አልተዘገበም፡፡

ኢእቲካፍ ከሚደረግባቸው ጊዜያት በላጩ የመጨረሻዎቹ የረመዳን አስር ቀናት ናቸው፡፡ ይህን በተመለከተ አዒሻ ረድየሏህ አንሀ እንዳለችው

“ነብዩ(ﷺ) እስኪሞቱ ድረስ የረመዳን የመጨረሻ አስር ቀኖችን ኢእቲካፍ አድርገዋል፡፡”

 áŠ áˆ ቡኻሪ (2ዐ2ዐ) ሙስሊም (1172)
የረመዳን አስር ቀኖችን ኢእቲካፍ ማድረግ የፈለገ የሃያ አንደኛውን ቀን ንጋት ሱብሂ ሰላት ኢእቲካፍ ያሰበበት መስጂድ ውስጥ በመስገድ ይጀምርና የመጨረሻው የረመዳን ቀን መግሪብ ከሰገደ በኋላ ያጠናቅቃል፡፡
⤵️⤵️⤵️
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ኢብኑ ባዝ እንዲህ አሉ፦ የረመዳን መጨረሻወቹን አስር ሌሊቶች በሶላትና በተለያዩ ዒባዳዎች ያሳለፈ ሰው ያለምንም ጥርጥር ለይለተል ቀድርን አገኛት ።

📚 አል ኢኽቲያራቱል ፊቅሒያ (15/430)
↘Join
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◾️ለይለተል ቀድርና አስርቱ ውድ ቀናቶች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

💦قال العلامة ابن عثيمين رحمه الله
🍂ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ብለዋል።

{}من قام العشر الأواخر من رمضان كلها إيمانا واحتسابا فإننا نجزم بأنه أصاب ليلة القدر{}
✅ በአላህ አምኖ እና ከሱ ምንዳንም አስቦ የረመዷን አስርት የመጨረሻ ቀናቶችን የቆመ (በኢባዳ ያሳለፈ) በርግጠኝነት ለይለተል ቀድር አገኘ ብለን ቁርጥ አርገን መናገር እንችላለን።

📕 فتاوى أركان الإسلام 429
💢ልብ ያለው ልብ ይበል
◾️አስር ቀን በኢባዳ አሳልፈህ ከሰማንያ ሶስት አመታት በላይ የሆነ የኢባዳ አጅር ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ እነዚህን አስርተረ ሌሊቶች በኢባዳ ህያው አድርግ። ይህንን ታላቅ ትርፋማ እድል በከንቱ አያምልጥህ። ምናልባትም ይህ የእድሜህ የመጨረሻው አሽረል አዋሒር ሊሆን ይችላልና በአግባቡ ተጠቀምበት።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
◾️ለይለቱል ቀድር በተመለከተ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🌙 لــــــــــيــــــــلـــــة الـــــــــقـــــــــدر 🌙

💢ወሳኝ የኡለማዎች ምክር
①) የለይለተል ቀድር ትሩፋቶች
②) ለይለተል ቀድር መቼ ነው?
③) የለይለተል ቀድር ሱናዎች
④) ለይለተል ቀድር ተስፋ ሚደረግበት ቀን መቼ ነው

◾️የኡለማዎች ስብስብ
🔻ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን
🔻ሸይኽ ኢብኑ ባዝ
🔻ሸይኽ ፈውዛን
🔻አብዱልአዚዝ ኣሉ ሸይኽ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◾️የመጀመርያው የአሽረል አዋሂር ሌሊት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

✅ ለይለተል ቀድር ከሚከጀሉባቸው ቀናቶች ውስጥ አንዱ ሀያ አንደኛው የመጀመርያው የአሽረል አዋሂር ሌሊት ነው። በዚህ በ21 ኛው ሌሊት ውስጥ በመልእክተኛው ዘመን ለይለተል ቀድር እንደተከሰተም ተወርቷል። የተወሰኑ ኡለማዎችም የመጀመርያው የአሽረል አዋሂር ሌሊት ለይለተል ቀድር ሊሆን እንደሚችል ገምተዋል። ይህም የሚጀምረው የዛሬ የመግሪብ አዛን ከተሰማበት ሰአት ጀምሮ ነው። በተለያዩ ኢባዳዎች ላይ በመሆን ሌሊቱን ህያው ልናደርገው ይገባል።
✅📌በነዚህ ተወዳጅ በሆኑት አስርት ቀናቶች ይህቺን ዱአ እናብዛ!

《اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني》
{አሏህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ!!}
ሸይኽ መሀመድ ኢብኑ ኡሰይሚን (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላሉ ፦

💎🌸ሴት ልጅ ማወቅ ያለባት ሷሊህነት (ጥሩነትን))እምታገኘው በዒልም ብቻ ነው ይህም ስል ሸሪዓዊ ዒልም ማለቴ ነው።
➛ምንጭ
【دور المرأة : ص 7】
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
"ሁለት ነገሮች ላይ ላለመውደቅ እራሱን የተጠባበቀ ፆሙ ተጠበቆለታል፤
ሐሜት እና ውሸት።"
✍ሙጃሒድ ኢብኑ ጀብር ረሂመሁላህ
📚【አልሙሰነፍ ሊኢብኒ አቢ ሸይባ (8887)】
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w