💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
«ዉለታ በከንቱ»


ቋንጃዉ እስኪላላጥ በሬ አርሶ ከገባ፣
ለድካሙ ፍሬ ተሰጠዉ ገለባ፣

ወገቡ እስኪላላጥ አህያ ተጫነ፣
ቁርስ ምሳ እራቱ ዱላ ብቻ ሆነ፣

እንቁላሏን ጥላ ሰዉን በመገበች፣
ዶሮም በየቦታዉ አንገቷን ታረደች

በርግዝና በምጥ እናት እቅልፍ አጣች፣
ልጅ ሚስትን አገባ እናትም ተረሳች፣

አባት ልጀን ብሎ ተርቦ አጉርሶ፣
ያሳደገዉ ልጁ ሰደበዉ መልሶ፣

ባሏን ለማስደሰት ደከመች ሚስቲቱ፣
ባሏ ግን ሸፈተ አስጠላዉ የቤቱ፣

ኑሮን ለማሸነፍ ባል ዋለ ከስራ፣
ሚስትም ጠበቀችዉ ፊቷን አኮሳትራ፣

ርቦታል ብላችሁ ብትሰጡት ዳቦ፣
አልበላሁም ይላል ሰዉ ይክዳል ጠግቦ፣

ተደገፍ ብላችሁ ብትሰጡት ምርኩዝ፣
ከናንተ ይጀምራል ከዘራዉን መምዘዝ፣

ብታወጡት ጓጆ ድሀ ነዉ ብላችሁ
ቢይዝ ይሞክራል ሊገዛ ቤታችሁ

እንኳንስ ዉለታ ትንሿን ስጦታ፣
አምላኩን ይከዳል የሁሉንም ጌታ፣


በሶላሁዲን አቡ ዑበይዳ

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
~በገንዘብ🏠 ቤት ልትገዛ ትችላለህ 👉 መኖሪያህን ግን አትገዛም።

~በገንዘብ⌚️ ሰአት ልትገዛ ትችላለህ 👉ጊዜህን ግን አትገዛም።

~በገንዘብ🛌 አልጋ ልትገዛ ትችላለህ እን👉ቅልፍህን ግን አትገዛም

~በገንዘብ🥙  ምግብ ልትገዛ ትችላለህ 👉የመብላት ፍላጎትህን ግን አትገዛም።

~በገንዘብ👉 ዶክተር ልትቀጥር ትችላለህ 👉ጤናህን ግን ልትገዛ አትችልም።

~በገንዘብ👉 ''ኢንሹራንስ'' ልትገዛ ትችላለህ 👉ደህንነትህን ግን ልትገዛ አትችልም።

«ስንት አለ ገንዘብ የማይገዛው

@AbuHafsaYimam
Audio
አዲስ የአቂዳ ኪታብ ቂርአት❞
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️


የኪታብ ርዕስ፦ሚን ኡሱሊ አቂደቲ አህሊ ሱነቲ ወልጀመዓ!!

ክፍል   10

📜የኪታብ 𝐏𝐝𝐟 ⇩⇩
t.me/https_Asselefya1/11411

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

  ⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇙⇙⇙⇙⇙⇙
    t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
➭ቤተሰብ ያዉ ቤተሰብ ነዉ¡ሲከፍሽ አይወዱም!

=
ከማንም በላይ ቤተሰቦችሽ ዉደጂ ሌላዉ ከነሱ በኋላ ነዉ መሆን ያለበት!!
=
t.me/https_Asselefya1
ዉዷ ......

ከቤተሰቦችሽ የሚያርቅሽ እራቂ ተጠንቀቂ ከቤተሰብ ያራቀሽ ግዜዊ ነዉ ቤተሰቦችሽ ግን ሂወትሽ እስካለ ከጎንሽ ናቸዉ ቤተሰቦችሽ አጥብቀሽ ያዢ !! ለጊዜዊ ስሜት አትሸነፊ!! ቤተሰብሽ አትጣሊ አትራቂ ጠንካራ ሁኚ በቤተሰቦችሽ ለመጣ እጂ እንዳትሰጪ ቅድሚያ ለቤተሰብ።

=
𝐓𝐞« t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝ የሙናፊቆች ባህሪያት ❞ « ክፍል  ⓵ ፦  መግቢያ » ☞ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ይሁን። በአላህ እንታገዛለን ።እርሱንም ምህረት እንለምነዋለን።ከነፍሳችን ተንኮልና ከመጥፎ ስሬችን በአላህ እንጠበቃለን። አላህ ላቀናዉ አጥማሚ የለዉም። አላህ ላጠመመዉ አቅኒ የለዉም።አላህ ብቸኛ አጋር የሌለወለ፣በሀቅ የሚመለክ አምላክ መሆኑን እመሰክራለሁ። መሀመድም ﷺየአላህ ታማኝ መልዕክተኛ ታዛዥ ባሪያ…
የሙናፊቆች ባህሪያት ❞


«ክፍል  ⓶፦ መግቢያ  የቀጠለ!»

ከዚህሞ በመቀጠል፦ይህቺ አጠር ያለች ፁሁፍ ስለተወገዘኹና አስቀያሚዉ ባህሪ፣ልብን በከፋ ስለሚጎዳዉ ልክፍት ፣እየተንሰራፍ ስለመጣዉ ወረርሽኝና መቅሰፍት ፣ማህበረሰባችን ስላደከመዉ  መከራ እና መከራን ሁሉ ስለሚያስከትለዉ ፣በረከትንና መልካምን ስለሚያስወግደዉ፣መልካምን ሁሉ ስለሚመልሰዉ፣ክፉዉን ሁሉ ስለሚጎትተዉ፣ከዚህሞ አልፎ ከእስልሞና ስለሚያስወጣዉ የንፍቅና በሽታ ነዉ።

የንፍቅና ባህሪ የተላበሰ ሰዉ በዚች ዱኒያ ይዋረዳል። በመጨረሻይቱና በመመለሻይቱም ህይወት ከከሳሪዎቾ ይሆናል። ይህ የክስረቶች ሁሉ ክስረት ነዉ።

ንፍቅና የእስልምና እና የእምነት ፀር ፣የሰላምታ የፀጥታ ጠንቅ፣የደህንነት እና የመረጋጋት ጠላት፣የሞራልና የእሴት ዉድቀት ነዉ።ሙናፊቆች በሙስሊምች መካከል ፀብ መንዛት ተቀዳሚዉ አጀንዳቸዉ፣ሙስሊሙን ማህበረሰብ ወደ መከራ እና ዉድቀት  መጎተት ዋና አላማቸዉ፣ሀገር ማፍረስና ባሪያን  ማበላሸት የመጨረሻ ግባቸዉ አድርገዉ የሚይቀሳቀሱ አደገኛ ፍጡሮች ናቸዉ።

በድሎት ግዜ  ተስፍ የማይደረግባቸዉ፣በችግር ግዜ አመኔታ የማይጣልባቸዉ አስቀያሚ መዘዞችን ያስከተሉ፣አስከፊ ችግሮችን የጎተቱ፣አያሌ ቀዉሶችን የፈጠሩ፣በአሀዝ የማይሰሉ አደጋዎች  ያደረሱ እርኩሶች ናቸዉ።

ነገር ግን ይህን ሁሉ ግፍና  መከራ ሲፈፀሙ በላኢላ ሀኢለላህ  ሙሀመድ ረሱለሏህ ባንድራ ተልከዉ፣በእስልምና ምሽግ ተጠልለዉ መሆኑ መሆኑ ችግሩ አክፍቶታል። ጉዳዩን አባብሶታል።

የሙናፊቆችንና የንፍቅናን ባህሪ ማወቅ ለመጠንቀቅ በመረዳቱ ለመራቅ በማገዙ አላህ እኔንም እናንተንም ከሙናፊቆች ባህሪ ያጥራን እና ያርቀን ዘንድ በማሰብ ይህቺን አጠር ያለች ፁሁፍ ሳዘጋጂ አላህ ዉስጣዊ እምነታችንን እና ዉጫዊ ተግባራችንን ከንፍቅና እንድያፀዳልን እርሱን በመፍራት ላይ ያፀናን ዘንድ በመለመን ነዉ።

አላህ ከሙናፊቆች ያርቀን ከንፍቅና ያፀዳን።በመልካም ነገሮች ሁሉ አዛዥ  ከመጥፎ ነገሮች ሁሉ ከልካይ  በሆኑት ነብያችን ሙሐመድﷺ ላይ የአላህ ሶላት እና ሰላም ይዉረድ፣በቤተሰቦቻቸዉ እና  በባልደረቦቻቸዉ ላይ ሁሉ ይስፈን። የመጨረሻ ፀሎታችንም ለአላማቱ ጌታ አላህ የተገባ ይሁን።

📝ይቀጥላል  ኢንሻ አላህ◍◍◍◍◍◍📝

         «ዝግጂት  ኡስታዝ ሰኢድ ሙሳ»

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
«ገበሬው አባቴ»


ሳይማር ያስተማረኚሳይበላ ያበላኝ
እሱ እየበረደው እኔን ያለበሰኝ
ገበሬው አባቴ ክፉኛ ናፈቀኝ


እሾህ እንዳይወጋኚ ለኔ ጫማ ገዝቶ
እሱ በባዶ  እግሩ  ሁልግዜ   ባዘቶ


ምንም ሳይበግረው  ዳገት ቁልቁለቱ
ለወገኑ ደራሺ  ይሄ ክደ ብርቱ
አርሶና ቆፍሮ  ብሎ ደፋ ቀና

ገበሬው አባቴ ናፈቀኚ በጠና
መነሻየ እሱ ነው ለዛሬ እንድ በቃ

ደክሟል ለህይወቴ እንድትታይ ደምቃ
አስር ግዜ የሚያጎርስ እያለ በሞቴ
ምስጋና ይገባው ገበሬው አባቴ!!


[ ትቀመጥ ለትዝታ¡¡]

=
https://t.me/https_Asselefya1
Forwarded from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے (لَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق)
አብዛኛውን ጊዜ ዱዓዎች ስኬታማ የሚሆኑት በሚስጥር ወደ አሏህ ሲደርሱ ነው።

إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ نِدَاءً خَفِيًّا

ጌታውን የምስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡_መርየም 3

ከሰው ልጅ ጆሮ እና አይን የምትደብቃቸው የህመሞችህ ሹክሹክታዎች የምድር እና የሰማያት ጌታ ይሰማልሃል። ጌታህን በዱዓህ አናግረው ፣ ቅሬታህን ንገረው፣ ልመናህን አሰማው። ከእርሱ የሚያስደስትህንም ተጠባበቅ።
t.me/abdu_rheman_aman
Audio
🍁تلاوة من سورة مريم

🎙 القارئ:
#أحمد_الفحام

•••━══❁✿❁══━•••
አንዳንዴም የማንሰራቸው ስራዎች ላይ በተደጋጋሚ ሰዎችን በመምከር ከምንጎተጉት፡እራሳችንን ዘወር ብለን ብንመለከት ጥሩ ነው።አንድም ሚስት የሌለው ስለሁለተኛ ሚስት ሲያወራ ስትሰማ ከርሱ ይልቅ አንተ ታፍራለህ።ሌላኛው እንድ እንኳን ያለገባው፡ይነሳና ሁሌ ትዳር ትዳር እያለ ሰዎችን በምክር ይወዝወዛል፡ያ አኺ በሌለህበት ስራ ላይ ወሬ ስትደፍር አያሳፍርህም? አረ እንደው ሞራሉንስ ከየት አገኘኸው?! ከመድረክ ስትወርድ ትዳርህሳ እንዴት ነው? ብለው ቢጠይቁህ አትሸማቀቅም?!

=>መቼም የዞረበት አዙሮ መተርጎሙ አይቀርም፡እንዳሻህ አድርገው፡የምትያዝበት አንተው!!።

ከጠቀመህ ተመከርበት
t.me/AbuOubeida
Audio
አዲስ የአቂዳ ኪታብ ቂርአት❞
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️


የኪታብ ርዕስ፦ሚን ኡሱሊ አቂደቲ አህሊ ሱነቲ ወልጀመዓ!!

ክፍል   11

📜የኪታብ 𝐏𝐝𝐟 ⇩⇩
t.me/https_Asselefya1/11411

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

  ⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇙⇙⇙⇙⇙⇙
    t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝ኢስላማዊ ስርዓቶችና መልካም ስነ ምግባሮች❞ «ክፍል  ⓺» 【የመፀዳጃ ቤት ስርዓቶች】 1🍁 መፀዳዳት የተከለከሉባቸዉ ቦታዎች ላይ ከመፀዳዳት መቆጠብ። ሀ//መንገድ ላይ ለ//ሰዎች የሚጠቀሙት ጥላ ስር ሐ//ነብዩ ﷺእንድህ ብለዋል ሶስት አስረጋማ ተግባሮች ተጠንቀቁ፦ወደ ወንዝ መዉረጃ መንገድ አዉራ ጎዳና ላይ ጥላ ስር መፀዳዳት። መ//ኩሬ ዉሀ ላይ፦ ነብዩﷺእንዲህ ብለዋል በማይወርድ…
ኢስላማዊ ስርዓቶችና መልካም ምግባሮች


    « ክፍል ⓻ »

የአለባበስና የመዋብ ስርዓቶች

1🍁የተከለከሉ ልብሶችና አለባበሶች መራቅ፦

ሀ//የሀር ልብስ ለወንድ፦ ነብዩﷺእንድህ ብለዋል"ዱኒያ ላይ የሀር ልብስ የሚለብስ በአኼራ እጣ ፈንታ የሌለዉ ነዉ። ለሴት ግን የተፈቀደ ነዉ። ነብዩ ﷺ እንድህ ብለዋል ወርቅና ሀር ለሴቶች የተፈቀደ ሲሆን ለወንዶች ግን ክልክል ነዉ።

ለ//የወንድ ልብስ ለሴት የሴት ልብስ ለወንድ የተከለከለ ነዉ። ነብዩ ﷺ እንድህ ብለዋል "ከሴቶች ወንድን የሚመሳሰልና ከወንዶች ሴትኖ የሚመሳሰልን አላህ ከእዝነቱ አባሯል።

ሐ//የሌላ ሀይማኖት ተከታዮችን አለባበስ መልበስ ክልክል ነዉ። ነብዩ ﷺ እንድህ ብለዋል፦ "ህዝቦችን የተመሳሰለ  ከእነሱ ነዉ።

መ//ለወንድ ልጂ በወርቅ መጋጌጥ ተከልክሏል።


2🍁የወንዶ ልብስ ከቁርጭምጭሚቱ በላይ ከፍ ማድረግነብዩ ﷺ እንድህ ብለዋል "ከቁርጭምጭሚት በታች የወረደ ሽርጥ የእሳት ነዉ። በሌላም ሀዲስ እንድህ ብለዋል,ሽርጥህን ከቁርጭምጭሚት እንዳታወርድ ይህ ከኩራት ነዉ አላህ አይወደዉም።

3🍁የሴት ልብስ ደግሞ ማስረዘም፦ ነብዩ ﷺ ሴት ልጂ አንድ ስንዝር ልብሷን ወደ ታች ወረድ ማድረግ አለባት "በሚሉ ኡሙ ሰለማ እንድህ ከሆነ እግሯ ይገለፃል አለቻቸዉ እሳቸዉም ወድያዉኑ እንድህ አሉ"በቃ አንድ ክንድ ያርዝሙ ከዚያ እንዳይጨምሩ።

4🍁ልብስ ሲለበስ የሚከተለዉን ዚክር ማለት፦

«الحمد الله الذي كساني هذا (الثوب) ورزقنيه من غير حول مني ولا قوة »

ትርጉም፦ ይህን ልብስ ያለበሰኝና ያለ ብልሀትና ሀይሌ ሲሳይን የለገሰኝ አላህ ምስጋና ይገባዋል

5🍁አድስ ልብስ ለለበሰ  ሰዉ የሚደረግ ዱዓ፦

«البس جديد, وعش حميدا ومت شهيدا ويرزقك الله  قرة عين في الدنيا والآخرة»

  ትርጉም፦(አድስ ልብስ፤ምስጉን ሆነህ ኑር፣ሸሂድ ሆነህ ሙት፣ አላህ በዱኒያም በአኺራም የአይን ማረፊያ ይለግስህ።

6🍁 ልብስ ሲለበስ ቀኝን ማስቀደም፦ አቡ ሑረይራ እንዳሉት ነብዩ ﷺ ቀሚስ ሲለብሱ በቀኝ ቀኛቸዉ ይጀምሩ ነበር።

7🍁ሲወለቅ ግራን ማስቀደም።

✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል...........

📝أم عثيمين الجامية

𝐓𝐞 ⇝ t.me/https_Asselefya1