💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ጀምዕያን ማቋቋም ቢድዓ ነውን⁉️
በውስጥ መስመር ከተላኩ ጥያቄዎች ክፍል 94

ጥያቄ
ብዞ ሰዎች በጀምዕያ ጉዳይ ሲጣሉ ይታያል፣ አንዳንዶች #ቢድዓ ናት ይላሉ እና ማህበራትን መመስረት እንዴት ይታያል ፣ ጀምዕያ የሚባልስ #ቡድን አለን⁉️

መልስ
በሸሪዓችን በመልካም ነገር ላይ #መተባበር የተደነገገና የሚበረታታ ተግባር ነው። ታዲያ ይህንን ምልካም ስራ ለመስራት #እንደመዳረሻ ከሚያገለግሉ ነገራቶች መካከል አንዱ #ጀምዕያ (ማህበር) ነው። ለዚህም ኡሞች ይህ ተግባር ከቁርአኑ አንቀፅ ትርጓሜ ጋር ይገባል ብለዋል።

ይህ ማህበር #ቁርአንና ሀዲስን በሰለፎች አረዳድ የሚከተል ፣ #ቡድንተኝነት የሌለበት ፣ በመልካም እንጂ #በመጥፎ መተባበር የሌለበትና ሌሎች ነገራቶች እስከሌሉበት ድረስ የሚፈቀድ ተግባር ነው። #ያለ_ጀመዓ ነገራቶችን መፈፀም ይቻላል ተብሎ የሚገመት ከሆነ ግን #አለማድረጉ በላጭ ነው። ከዛ ውጭ በዚህ ርእስ ላይ ኡለሞች #የኢጅቲሀድ ጉዳይ ስለሆነ አንዱ ሌላኛውን #ሙብተዲዕ የሚባልበት ርእስ እንዳልሆነና ጀምዕያ የሚባል የጥመት አንጃ #እንደሌለ ጠቅሰው ሰዎች በዚህና በሌሎች ጥቃቅን ነገራቶች #ከመጨቃጨቅ እንዲቆጠቡም መልእክት አስተላልፈዋል።

♻️ ማጣቀሻ ምንጮች :—
📚ሸይኹል አልባኒ ፣ ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር / 371 ፣📚ሸይኽ ረቢዕ አልመድኸሊ ፣ ኪታብ ጀመዐቱን ዋሂዳ ላ ጀመዓት 📚 ኢብኑ ባዝ ፣ መጅሙኡል ፈታዊ ፣ 2/374,376 ፣ 📚ኢብኑ ኡሰይሚን ፣ መጅሙኡል ፈታዊ፣ 16/39 ፣ 📚የሳኡዲ የኢልምና የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ፣ ፈትዋ ቁጥር 6364
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Forwarded from Abu Fewzan (Channel)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
018 Al-Kahf
Maher Al-Muaiqly
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w

የቁርዓን ግብዣ 👆👆👆
♻️ ኢማሙ ሻፍእይ ለመልእክተኛው ሱና እጅ የሰጡ ነበሩ

🔵‏روي عن الشافعيّ -رحمه الله- أنّه قال:

🔵 ከኢማሙ ሻፍእይ እንዲህ የሚል ተወርቷል

📌«إذا وجدتُم سُنَّةً لِرسولِ اللهِ ﷺ فاتَّبِعُوهَا وَلا تلتَفِتُوا إلى أحدٍ»

🔺🔺 የመልእክተኛው አለይሂሶላቱ ወሰላም ሱና (ፈለግ) ባገኛችሁ ጊዜ ተከተሏት ወደ ሌላ ወደ ማንም አትዙሩ።
📚 ذم الكلام للهروي

የመልእክተኛውን ሱና ከማንም በላይ ሊከተሉት የሚገባና ከሁሉ በላይ እንደሆነ ለተከታዮቻቸው የመከሩበት ብዙ የኢማሙ ሻፍእይ ንግግሮች አሉ። ከመሆኑም ጋር ግን አሁን ላይ የሻፍእይ መዝሀብ ተከታይ ነን የሚሉና ራሳቸው ወደ ኢማሙ ሻፍእይ የሚስጠጉ ብዙ ሰዎች ግን የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፣ ሱናው ይህ ነው፣ ይህን ሽርክ ነው፣ ይህ ደሞ ቢድአ ነው ብለህ መረጃ ስታቀርብላቸው ሀቁን ከመቀበል ይልቅ አይ ኢማሙ ሻፍእይ እንዲህ ብሏል ወደ ማለት ይሄዳሉ።

አንዳንዱ አላዋቂማ ጭራሽ የፈለገው ይሁን እሳቸው የገቡበት እገባለሁ በማለት ጭፍን ተከታይነቱን ያሳያል።

🔺እንደዚህ አይነት ሰዎች ሊያውቁት ሚገባው ኢማሙ ሻፍእይ ለሀቅና ለመልእክተኛው ሱና እጅ የሰጡና ለተከታዮቻቸው በዚህ ላይ አበክረው አደራ ስላሉና ንግግሬ የመልእክተኛውን ንግግር ከተቃረነ የኔውን አሽቀንጥራችሁ ጣሉት በማለት ስላስጠነቀቁ አንተ⤵️⤵️
👉 ኢማሙ ሻፍእይ አትወክልም
👉 እሳቸውም አንተን አይወክሉም
👉 ባንተና በኢማሙ ሻፍእይ መካከል የሰማይና የምድር አክል ልዩነት አለ እንላቸዋለን።

ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
የሃጃዊራዎች ውርደት ክ 01
2.2 MB
Audio
ሀጃዊራዎች የተዋረዱበት እና ባዶ መሆናቸው የተጋለጠበት
🎙ኡስታዝ አብዱረህማን( አቡ ሂዛም)【 𝙝𝙖𝙛𝙞𝙯𝙚𝙝𝙪𝙡𝙡𝙖𝙝】 ከሀጃዊራህ ጋር የተደረገ ውይይት
ክፍል2

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሶስቱ ጥያቄዎችና ድንቅ መልሶቻቸው

بسم الله الرحمن الرحيم

ኢማሙ አልቡኻሪይ እና ሌሎችም በዘገቡት ሀዲስ:👇

  《 عن أَنَسٌ بن  مالك ، أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ سَلَامٍ بَلَغَهُ مَقْدَمُ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ الْمَدِينَةَ، فَأَتَاهُ يَسْأَلُهُ عَنْ أَشْيَاءَ، فَقَالَ : إِنِّي سَائِلُكَ عَنْ ثَلَاثٍ لَا يَعْلَمُهُنَّ إِلَّا نَبِيٌّ ؛ مَا أَوَّلُ أَشْرَاطِ السَّاعَةِ ؟ وَمَا أَوَّلُ طَعَامٍ يَأْكُلُهُ أَهْلُ الْجَنَّةِ ؟ وَمَا بَالُ الْوَلَدِ يَنْزِعُ إِلَى أَبِيهِ، أَوْ إِلَى أُمِّهِ ؟ قَالَ : " أَخْبَرَنِي بِهِ جِبْرِيلُ آنِفًا ". قَالَ ابْنُ سَلَامٍ : ذَاكَ عَدُوُّ الْيَهُودِ مِنَ الْمَلَائِكَةِ. قَالَ : " أَمَّا أَوَّلُ أَشْرَاطِ السَّاعَةِ فَنَارٌ تَحْشُرُهُمْ مِنَ الْمَشْرِقِ إِلَى الْمَغْرِبِ، وَأَمَّا أَوَّلُ طَعَامٍ يَأْكُلُهُ أَهْلُ الْجَنَّةِ فَزِيَادَةُ كَبِدِ الْحُوتِ، وَأَمَّا الْوَلَدُ، فَإِذَا سَبَقَ مَاءُ الرَّجُلِ مَاءَ الْمَرْأَةِ نَزَعَ الْوَلَدَ، وَإِذَا سَبَقَ مَاءُ الْمَرْأَةِ مَاءَ الرَّجُلِ نَزَعَتِ الْوَلَدَ ". قَالَ : أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَأَنَّكَ رَسُولُ اللَّهِ. قَالَ : يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّ الْيَهُودَ قَوْمٌ بُهُتٌ فَاسْأَلْهُمْ عَنِّي قَبْلَ أَنْ يَعْلَمُوا بِإِسْلَامِي. فَجَاءَتِ الْيَهُودُ، فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " أَيُّ رَجُلٍ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ سَلَامٍ فِيكُمْ ؟ " قَالُوا : خَيْرُنَا وَابْنُ خَيْرِنَا، وَأَفْضَلُنَا وَابْنُ أَفْضَلِنَا. فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " أَرَأَيْتُمْ إِنْ أَسْلَمَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ سَلَامٍ ؟ " قَالُوا : أَعَاذَهُ اللَّهُ مِنْ ذَلِكَ. فَأَعَادَ عَلَيْهِمْ، فَقَالُوا مِثْلَ ذَلِكَ، فَخَرَجَ إِلَيْهِمْ عَبْدُ اللَّهِ، فَقَالَ : أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ. قَالُوا : شَرُّنَا وَابْنُ شَرِّنَا. وَتَنَقَّصُوهُ، قَالَ : هَذَا كُنْتُ أَخَافُ يَا رَسُولَ اللَّهِ.》
صحيح البخاري :3839

《 ከአነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተዘገበው:
አብደሏህ ኢብኑ ሰላም እኮ የነብዩን ﷺ መዲና መምጣት ሰማና ስለተለያዩ ጉዳዮች ሊጠይቃቸው መጣ። አላቸውም " እኔ ስለ ሶስት ነገሮች እጠይቅሃለሁ ነብይ ካልሆነ በስተቀር ማንም አያውቃቸውም።
የመጀመሪያው የሰኣቲቷ (የቂያማህ) ምልክት ምንድ ነው ?
የጀነት ባልተቤቶች መጀመሪያ የሚበሉት ምግብ ምንድን ነው ?
ህፃን ወደ አባቱ ወይም ወደ እናቱ የሚመስለው ለምንድን ነው ?

እንዲህ አሉት
" ጂብሪል ስለዚህ በቅርብ ጊዜ ነገሮኛል "
አብደሏህ ኢብ ሰላም  አለ
" እርሱማ ከመላዕክት ለአይሁዶች ጠላት ነው " ።

የመጀመሪያዋ የሰኣቲቷ ምልክትማ (ሰዎችን) ከምስራቅ ወደ ምዕራብ የምትሰበስባቸው እሳት ነች።
የጀነት ባልተቤቶች መጀመሪያ የሚበሉት ምግብማ  ከዓሳ ነበሪዉ ጉበት ተቆራጭ ነው።
ህፃንማ  እኮ የወንዱ ፈሳሽ  የሴቷን ፈሳሽ ከቀደመ ህፃን ወደ እርሱ ይመስላል። የሴቷ ፈሳሽ የወንዱን ፈሳሽ ከቀደመ ህፃን ወደ እርሷ ይመስላል።

እነዲህም አለ " ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም አንተም የአሏህ መልዕክተኛ ነህ ብዬ በእርግጥ እመሰክራለሁ ። የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ አይሁዶች እኮ ቀጣፊ ህዝቦች ናቸው። እስኪ መስለሜን ሳያውቁ በፊት ስለ እኔ ጠይቃቸው።"

አይሁዶችም ሲመጡ ነብዩ ﷺ እንዲህ አሉ " እናንተ ውስጥ አብደሏህ ኢብኑ ሰላም እንዴት ያለ ሰው ነው ? "
እነርሱም አሉ " ምርጣችን የምርጣችን ልጅ ፤ በላጫችን የበላጫችን ልጅ ነው "

ነብዩም ﷺ እንዲህ አሉ " አብደሏህ ኢብ ሰላም ቢሰልምስ ምን ትላላችሁ ? "
እንዲህም አሉ
" አሏህ ከዚህ ይጠብቀው"
መልሰው ሲጠይቋቸው ያንው ተመሳሳይ መልስ ሰጡ።

አብደሏህም ወደ እነርሱ ወጣና
" ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ሙሀመድም የአሏህ መልዕክተኛ ነው ብዬ በእርግጥ አመሰክራለሁ " አለ።

ይህን ጊዜ " መጥፏችን የመጥፏችን ልጅ " ብለው አንቋሸሹት።
" ይህን ነው ስፈራ የነበረው የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ " አለ።  》
ሰሂህ አልቡኻሪይ: 3839

ከሀዲሱ ከሚቀሰሙ ቁምነገሮች ውስጥ =
✏️ሶስቱ ጥያቄዎችና ድንቅ መልሶቻቸው

✏️ነብይ ካልሆነ በስተቀር ጥያቄዎች ማንም አይመልስም።

✏️ ልብን ለእውነት ክፍት ማድረግ

✏️የአይሁዶች ቀጣፊነት ፣ ጥመት ፣ ክፋትና ግልፅ ጠላትነት።
የዛሬዎቹ የባሱ ናቸው !

✏️ወደ ሀቅ የተመራ አካል አድናቂዎቹ የነበሩ ደጋፊዎች ሊያንቋሽሹት ይችላሉና ይፅና።

✏️ እውነትን አበጥሮ የሚገልፅ ሁሉ የጠማማዎች ጠላት ነው።

✏️ ያልሰለመ አይድንም ‼️

አቡ ሀመዊያ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን [ሀፊዘሁላህ]
እንዲህ ይላሉ፦
ኢኽዋነል ሙስሊሚን አስሉ መሰረቱ ኸዋሪጅ ነው ነገር ግን ሸራቸው ጨመረ ኢኽዋነል ሙስሊሚን ከኸዋሪጆች።
ኸዋሪጅ ቀጥታ ሂዶ ነው የሚጋደለው ኢኽዋነል ሙስሊሚን ከቤት ተቀምጠው ህፃናትና ሴቶችን ነው የሚያስጨርሱት
ሸራቸው ከኸዋሪጆች የበለጠ ነው። መሰረታቸው ከኸዋሪጅ ነው ግን ጨመረ ሸራቸው...
https://t.me/Ibnumohammedseid/1471
🌱ሶስት ትላልቅ ወንዞች🌱

◌◦ኢብኑል ቀይም ((ረሂመሁላህ)) እንዲህ ይላል◦◌

➥ለወንጀለኞች በዱንያ ላይ ከወንጀላቸው የሚፀዱባቸው ሶስት ትላልቅ ወንዞች አሏቸው!!

➥እነዚህ ወንዞች ካላፀዱዋቸው የቂያማ ቀን በጀሀነም ወንዝ ነው የሚፀዱት!!

➊የተውበተ አንነሱሁ ወንዝ!!

➋ሀጢያትን የምታብሰው የመልካም ስራ ወንዝ!!

➌ወንጀልን የሚያጥብ የሙሲባ ወንዝ!!

➥አላህ ለባሪያው መልካም ከሻለት ከእነዚህ ወንዞች በአንደኛው ያስገባዋል ንፁህ የተጥራራ ሆኖ ወደ ቂያማ ከወረደ አራተኛ ማፅጃ አያስፈልገውም!!

📚#ምንጭ مدارج السالكين ❪٦٤/١❫

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
📌♻️ ጊዜህን በቁም ነገር ላይ አውለው ♻️📌

ሸህ ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ።

🔺 ጊዜውን 👉አላህን በማውሳት (በዚክር)
👉ቁርአን በመቅራት
👉ከመልካም ሰዎች ጋር በመሆን
👉ከዝንጉና ከመጥፎ ጓደኞችን
በመራቅ ያሳለፈ ሰው
🔺 ቀልቡ ያማረና የለሰለሰ ይሆንለታል።

📚 مجموع فتاوى ابن باز (5/244)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➪ሐሰን አልበስሪይ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
"ጥርት ያለ ተውበት ማለት፤
ወንጀልን የወደድከው ያህል መጥላት እና ባስታወስከው ቁጥር በመፀፀት ኢስቲግፋር ማድረግ ማለት ነው።"
📘 ተፍሲሩ ኢብኑ ከሢር (8/169)
ወንጀል ሰርተው እንደ ጀብድ የሚያወሩ፤
ወይ ጥፋታቸው!
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሀቅ ሀቅ ሀቅ ነው ነው

ከወገንተኝነት የወጣ ወንድም አዳምጡት

🌸 በጀምእያ ዙርያ  ከማጥበቅ ወደ ፍትሀዊነት…
ወንድማችን አብዱ ሽኩር ኢብኑ ሙሀመድ
ከሀጁሪዮች ወደ ሰለፊዮች የመጣ ወንድም አዳምጡት !
ሀቅን ሲያገኙ ወደ ሀቅ መመለስ የሰለፎች ባህሪ ነዉ ።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
📌ኡስታዚ ኢብን ሙነወር አላህ ደረጃህን አብዝቶ ከፍ ያድርግልህ

ወላሂ ሚዛናዊነትን, ፍታሃዊነትን የሚያሰተመር ድንቅ ኡስታዜ ኢብኑ ሙነወር

📌በጣም የገረመኝ የሱ ተማሪ ናቸው እያሉ ለማንቋሸሽ የሚሞክሩ አካላቶች ናቸው⁉️
ወላሂ ነው የምለው አይደለም ላፈርበት አይደለም ልሸማቀቅ

ምንኛ ደሰተኛ ነኝ የሱ ተማሪ በመሆኔ ወላሂ በጣም ነው የሚያስደስተው

📣ይህ ስል ተኣሱብነት አይደለም ከተሳሳተ እሳሳታለሁ ማለት አይደለም

አላህ እሱንም እኛንም በሃቅ ላይ አፅንቶ በሱም ላይ ይገደለን

አሚን

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
🌸ውድ የሆነች ምክር🌸

💎እናታችን አዒሻ ረዲየ አላሁ ዓንሀ እንዲት ትላለች፦

➻እናንተ ምዕመናን እንስቶች ሆይ ከእናንተ እንዳችሁ የሆነን ኃጢያት የሰራ እንደሆን አደራ ያንን ለሰው አይነገር፡ነገር ግን አላህን ምህረት ይጠይቅ ወደሱም ንስሓ በማድረግ ይመለስ።

📚مكارم الأخلاق للخرائطي ص (503)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
▸◉የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ይላሉ◉◂

➩◉ከትንሳኤ ➷መቃረብ ምልክቶች ➷መካከል‼️

➩◉የእውቀት መነሳት ➷የአላዋቂነት መብዛት ➷የዝሙት መብዛት ➷የአስካሪ መጠጦች መብዛት ➷ለአንድ ወንድ ሀምሳ ሴት ➷እስክትደርስ ድረስ የሴቶች ➷ቁጥር መብዛት ነው‼️

#ምንጭ 《صحيح البخاري》
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
♻️ ትክክለኛነቱ እርግጠኛ ያልሆንበት ነገር ከመፃፍና ሰዎችም የፃፋት ሳናረጋግጥ ዝም ብሎ ከማሰራጨት ልንቆጠብ ይገባል።

🔵‏قال الشيخ سليمان الرحيلي حفظه الله:



«واليوم الواحدُ منَّا يكتب سطرًا وهو في بيته ربَّما قرأَه الملايين، فإن لم يكن متيقِّنًا أنَّه خيرٌ فلا يُدخل نفسه في هذا الباب، فلربَّما جاء يوم القيامة وهو يجرُْ سيئات كثيرة بسبب هذا السطر»

♻️ሸህ ሱለይማን አሩሀይሊይ (አላህ ይጠብቀውና) እንዲህ ይላል

🔺 ዛሬ ከኛ መካከል አንዳችን እቤቱ ሆኖ አንድ መስመር ፅሁፍ ይፅፋል። ይህንን ፅሁፍ ሚሊዮኖች ነው ሚያነቡት። በትክክለኛነቱ (በመልካምነቱ) እርግጠኛ ካልሆንን እንዲህ አይነት ነገር ውስጥ ልንገባ አይገባም። ምክንያቱም ይህ ሰው በዚህ ፅሁፍ የተሳሳቱና ወንጀል ውስጥ የወደቁ ሰዎችን ወንጀል ይዞ የውመልቂያማ ይመጣልና።

[ شرح رسالة ابن القيِّم (ص٧) ]

👉 መፃፍ ስለቻልን ብቻ አንፃፍ
👉 ምንፅፈው ነገር ቀድመን ከቁርአን ከሀዲስ መልእክት ጋር ያለ መጋጨቱን እናረጋግጥ
👉 ምንፅፈው ነገር ለሰዎች እውቀት የሚያሲዝ ነገር ይሁን
👉 ያልተረጋገጡ ቂሳዎች፣ ቁም ነገር የሌላቸው ፅሁፎች፣ ቀልድና ዛዛታዎች በመፃፍ የኛንም የሰዎችንም ጊዜ ልንገድል አይገባም
👉 አንዳንዶቻችንማ የሆነ ግሩፕ ላይ ስላገኘነው ብቻ ሳናነበው ምን እንደሆነ ነገሩ ሳናይ እናስተላልፋለን ይህም ይስተካከል

ኢብኑ ኸይሩ
ከምን ይሆን የምንማረው?
~~~~~~~~~
በወቅታዊ የሃገራችን ፖለቲካ ትኩሳት የተነሳ ብዙ ነገር እያየን፣ ብዙ ነገር እየሰማን ነው። አላህ ከጠበቀው በስተቀር አብዛኛው ሰው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የችግሩ አካል ሆኗል። ዛሬ ገዳይ ለምን እንደሚገድል፣ ሟች በምን ሰበብ እንደሚገደል በማያውቁበት ሁኔታ እንደዋዛ የሰው ነፍስ እየጠፋ ነው። ነቢዩ - ﷺ - እንዲህ ብለው ነበር፡-
" والذي نفسي بيده ليأتين على الناس زمان لا يدري القاتل في أي شيء قتل، ولا يدري المقتول على أي شيء قتل"
“ነፍሴ በእጁ በሆነው ይሁንብኝ! በሰዎች ላይ ገዳይ በምን ጉዳይ እንደገደለ፣ ሟች በምን ጉዳይ እንደተገደለ የማያውቅበት ዘመን ይመጣል።” ሙስሊም የዘገቡት ነው።
እያየን ያለነው በአመዛኙ ይህንን ነው። በተልካሻ ነገር ህይወት ይቀጠፋል። በተልካሻ ሰበብ ደም ይፈሳል፣ አካል ይቆስላል፣ ደካማ ያለቅሳል፤ ህይወት ይመሰቃቀላል። እንደዋዛ የደካሞች ንብረት ወደ አመድነት እየተቀየረ ነው። ሁሉም የራሱን አጥፊ ከመኮነን፣ ጠማማውን ለማቃናት ከመጣር ይልቅ ጣት የሚቀስርበት ነው የሚፈልገው። ጭፍን ወገንተኝነት አናታችን ላይ ወጥቷል። ስንኮንንም፣ ስናወድስም እየመረጥን ነው፣ የኛና የነሱ ብለን። ከግል እስከ መንግስት ያሉ ሚዲያዎችን ታዘቡ። እየመረጡ ያራግባሉ፤ እየመረጡ ያልፋሉ። አብዛኛው ህዝብም በዚሁ ፋሺን የተሰፋ ሆኗል። ማዶ ለማዶ ቆሞ እሳት የሚጭረውን አጋጋይ (አክቲቪስት) ታዘቡማ። የሌሎችን ጭራቅነት ለማሳየት እስከ ጥግ ይሟሟታል። በራሱ ወገኖች ደካሞች ላይ የሚፈፀመውን ግን እንዳላየ ነው የሚያልፈው። ከተቸም በስሱ ነው የሚነካው። ይሄ ምናልባት የሁሉም ካልሆነ የብዙሃኑ መታወቂያ ሆኗል። እንዲያውም ከሸረሪት ድር የደከሙ ሰበቦችን እየደረደረ የወገኖቹን ጥፋት “ጀስቲፋይ” ሲያደርግ ነው የሚታየው። እንዲያውም ይሄ ከአጋጋዩ አልፎ የአብዛኛው ህዝብ ባህሪ ከሆነ ሰነባበተ። ይህ ባይሆን ኖሮ እነዚህ እሳት አራጋቢዎች ገበያቸው ባልደራ ነበር። ይሄ ግን ለእሳት ጫሪውም፣ ለአጋጋዩም፣ ዳር ቆሞ ለሚታዘበውም አይጠቅምም። ሁላችንም የራሳችንን ክፉ አመል ልንገታ፣ ዋልጌዎቻችንን እጃቸውን ልንይዝ ይገባል። ካልሆነ ግን ውጤቱ አስከፊ ነው።
በእንደዚህ አይነት ከባድ ጊዜ የእርስ በርስ ምክክራችን ከወትሮው ሊጠናከርና ልንተዋወስ ይገባል። አኺል ከሪም ኡኽቲል ከሪማህ! እኛ ሙስሊሞች ነን። የወቃሾች ወቀሳ ሳያስፈራን እያንዳንዱን ነገር በሃይማኖት መነፅር ልንመለከት ይገባል። ኢስላም ማለት መስጂድ ውስጥ ብቻ የሚፈፀም ሳይሆን መላ ህይወታችንን የሚዳስስ እምነት ነው። ከፊታችን ሞት አለ። ከፊታችን ከአላህ ፊት ቆሞ መመርመር አለ። ከፊታችን እሳትና ጀነት አለ። የዛሬ ስግብግብ ምኞት ነጋችንን እንዳያጨልምብን እንጠንቀቅ። ከዛሬ ይልቅ ለነጋችን ቅድሚያ እንስጥ። ጌታችን እንዲህ ብሏል፡-
وَمَا هَٰذِهِ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا لَهْوٌ وَلَعِبٌ ۚ وَإِنَّ الدَّارَ الْآخِرَةَ لَهِيَ الْحَيَوَانُ ۚ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ
“ይህቺም የቅርቢቱ ህይወት መታለያና ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለችም። የመጨረሻይቱም አገር እርሷ በእርግጥ የዘላለም ህይወት አገር ናት። የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ፤ (ጠፊን ህይወት አይመርጡም ነበር)።” [አሩም፡ 64]
ስለሆነም እያንዳንዷ እርምጃችን ይህንን ከግምት ባስገባ መልኩ መሆን አለባት። ወንድም እህቶቼ! ማንም የእኛ ቀብር አይገባልንም። ማንም የእኛን ምርመራ አይመረመርልንም። ስለዚህ ቆም ብለን እንመልከት። ነገ ከአላህ ፊት የሚያሳፍረን ተግባር ውስጥ እንዳንገባ እንጠንቀቅ። በራሳችን ላይ እንዲፈፀም የማንፈልገውን በደል ሌሎች ላይ አንፈፅም። በደል ነገ ንብርብር ጨለማ ነው። ማንንም በህይወቱ፣ በንብረቱ፣ በክብሩ እንዳንበድል እንቆጠብ። በደል ነገ ቀርቶ ዛሬንም ያጨልማል። ነቢያችን - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፡-
اتَّقُوا دَعْوَةَ الْمَظْلُومِ وَإِنْ كَانَ كَافِرًا فَإِنَّهُ لَيْسَ دُونَهَا حِجَابٌ
“የተበዳይን ዱዓ ተጠንቀቁ፤ ከሃዲ እንኳን ቢሆን። ምክንያቱም (አላህ ዘንድ ከመድረስ የሚያግዳት) መጋረጃ የለምና።”
ወንድም እህቶች! ሶሪያ ያማረች አገር ነበረች። የህዝቦቿም ኑሮ ከኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮ በእጅጉ የተሻለ ነበር። ዛሬስ? ዛሬማ ሶሪያ ፈርሳለች። ወደነበረችበት ለመመለስ ዘመናት ያስፈልጓታል። እጅግ በርካታ ህዝቦቿ በአሰቃቂ ሁኔታ አልቀዋል። ሚሊዮኖች በመላው አለም ተበትነዋል። ከፊሎቹ በስደት ላይ ውሃ በልቷቸዋል። ከፊሎቹ ኢትዮጵያም አገር ሆና ወደኛ መጥተዋል። ያለ ጥርጥር ትላንት ላይ ሆነው የዛሬ ሁኔታቸውን ቢመለከቱ ኖሮ ጥፍራቸውን በሰበሰቡ ነበር። ግና እድላቸው አምልጧቸዋል። የሚያሳዝነው እኛ ከነሱ ልንማር አለመፈለጋችን ነው። “እድለኛ ማለት ከሌሎች የሚማር ነው” የሚል አባባል ነበራቸው ዐረቦች። ብዙዎቹ አልተማሩበትም እንጂ። አዎ “ብልጥ ሌሎች ላይ ከሚደርሰው ይማራል። ሞኝ ግን ራሱ ላይ ከሚደርሰው ነው የሚማረው።” እኛስ ከየትኛው ምድብ ነን? ሌሎች ላይ የደረሰውን አይተናል። ግን አልተማርንበትም። እዚሁ ባቅራቢያችን የተለያዩ ክስተቶች እየደረሱም እያየን ነው። ይህም እያስተማረን አይመስልም። ይህ ሁሉ ካላስተማረን ምን ይሆን የሚያስተምረን?
ሳጠቃልል ከበደል እንቆጠብ። በደል ውጤቱ መሪር ነውና። ሰዎች ነንና እንሳሳታለን። ባይሆን አንዳችን ሌላችንን ለማረም አንቦዝን። ተግባራችንም፣ ንግግራችንም በፍትህ ይሁን። የምንናገረውም፣ የምንፅፈውም፣ የምናሰራጨውም ፍትሕ የሰፈነበት ይሁን። ጌታችን እንዲህ ሲል በፍትህ አዞናል፡-
﴿ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَى وَيَنْهَى عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنْكَرِ وَالْبَغْيِ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ﴾
“አላህ በፍትሕ፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል። ከብልግና፣ ከመጥፎ ነገር እና ከመደበልም ይከለክላል። ትገነዘቡ ዘንድ ይገስፃችኋል።” [አነሕል፡ 90]
በተለያዩ ምክንያቶች የምንጠላቸው ሰዎች ካሉም ጥላቻችን ድንበር አያሳልፈን። የላቀው ጌታ እንዲህ ይላል፡-
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ። ህዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይግፋችሁ። አስተካክሉ። እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነውና። አላህንም ፍሩ። አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።” [አልማኢዳህ፡ 8]
በሐዲሠል ቁድሲይም እንዲህ ብሏል፡-
يا عبادي، إني حرمت الظلم على نفسي وجعلته بينكم محرماً فلا تظالموا
“ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በራሴ ላይ ክልክል አድርጌያለሁ። በእናንተ መካከልም ክልክል አድርጌዋለሁ። ስለሆነም አትበዳደሉ።” ሙስሊም ዘግበውታል።
በአላፊ ብልጭልጭ ጥቅሞች፣ በጊዜያዊ ሆይሆይታዎች፣ በወገ