💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
የኢኣነቱል ኢኽዋን ተከታታይ ደርስ


በደርሱ ውስጥ የተካተቱት ነጥቦች
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
ሹፌሮችና ፃም በተመለከተ
የበሽተኛና የሽማግሌ ፃም
ከወር አበባና ወሊድ ደም መጥራት
ስለ ፆም ማዕዘናት (አርካኖች)
🔻ሌሎችም ነጥቦች ተወስቶበታል

ክፍል 0⃣9⃣


🎙በኡስታዝ አቡ ሂዛም አብዱረህማን ሰኢድ (حفظه الله)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
🔸ዐጂብ ሱብሐነሏህ
#የሰለፎች ኢኽላስ

አዩብ አስሰኽቲያኒ ረሒመሁሏህ
ለሊቱን ሙሉ በኢባዳ ቆመው ሲያበቁ ይህንንም ተግባራቸው ከሰዎች ይደብቁ ነበር።
የሱብሂ ጎህ ሲቀድ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ
ገና በዛች ሰአት ከእንቅልፋቸው እንደተነሱ
ያስመስሉ ነበር !!
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ


የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት

◾️የፃም ትሩፋቶች


ክፍል 0⃣4⃣

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◼️በፆም ጊዜ እጣን ማጬስ
«እጣንን ማጬስ ይፈቃዳል ነገር ግን ወደ አፍንጫ መሳብ የለበትም። »
ሼይኽ አብድል አዚዝ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁሏህ መጅሙዓል ፈታዋ [{15/262}]
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◾️ሁለት ወሳኝ የረመዷን ጅሀዶች


💦ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

ለሙእሚን በዚህ በተከበረው ወር ረመዷን ላይ በቀንና በሌሊት የሚተገበሩ ሁለት ጅሀዶች ይሰበሰቡለታል።
👉የቀኑ ጅሀድ፦ ፃሞ መዋል ሲሆን
👉የሌሊቱ ጅሀዱ፦ ለይል መስገድ (ተራዊህ መስነድ) ናቸው።
🔻አንድ ሰው እነዚህን ሁለት ጅሀዶች ሰብስቦ በሚገባ የተወጣ፣ ሀቃቸውን ያሟላና በዚሁ ላይ ፀንቶ የታገሰ ሰው፦ አላህ ለሶብረኞች እንደ ሚመነዳው ሁሉ ይህም ሰው አላህ ያለ ገደብ ብዙ ምንዳዎችን ይሰጠዋል።

📚الطائف المعارف (1/171)
Audio
من تقرب فيه بخصلة من الخير كان كمن أدى فريضة فيما سواه ومن أدى فيه فريضة كان كمن أدّى سبعين فريضة فيما سواه
👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇
🔻ረመዷን ላይ ሱና የሰራ እንደ ፈርድ ይቆጠራል። ፈርድ የሰራ ደሞ ሰባ ፈርዶችን እንደሰራ ይቆጠራል የሚለው ሀዲስ ደካማነት ማብራሪያ
🔻ደኢፍ ሀዲስ እንደመረጃነት መጠቀም ይቻላልና? የሚቻል ከሆነ መስፈርቶቹ ምንድ ናቸው?

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
የኢኣነቱል ኢኽዋን ተከታታይ ደርስ


በደርሱ ውስጥ የተካተቱት ነጥቦች
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
①) በፆም ጊዜ ኒያ እና ሁክሟ
②) ጾም የሚያበላሹ ነገራቶች

🔻ሌሎችም ነጥቦች ተወስቶበታል

ክፍል 1⃣0⃣


🎙በኡስታዝ አቡ ሂዛም አብዱረህማን ሰኢድ (حفظه الله)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎ሴት ልጅ ከወንድ ልጅ በዋነኝነት ፍቅርን ትኩረትን እና እንክብካቤ ትፈልጋለች!!

ወንድ ልጅ ደግሞ ክብርና ታዛዥነትን ይፈልጋል ከሴት ልጅ !!
... በትዳር ውስጥ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ለሁለቱም ስኬትን ያጎናፅፋቸዋል ቢዕዚኒሏህ!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ስናምፀው የሚሰትረን አዛኝ ጌታ!!
◼️ወኪዕ ቢን አልጀራሕ -አላህ ይማረውና-"በአላህ ሽፋን ውስጥ ካልሆነ በቀር አንኖርም... ግርዶሹን ቢገልጥ ኖሮ፣ ታላቅ ነገር ባጋለጠን ነበር

📚 الجرح والتّعدیل : (٢٢٣/١) .

‏✿ قال وكيع بن الجراح : 

ما نعيش إلا في ستره
ولو كشف الغطاء
لكشف عن أمر عظيم٠

📖الجرح والتّعدیل(٢٢٣/١)
•⊰✿📚✿⊱
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
سورة إبراهيم كاملة من تراويح ١٤٤٢
عمر الدريويز
وَإِذَا قُرِئَ ٱلْقُرْءَانُ فَٱسْتَمِعُوا۟ لَهُۥ وَأَنصِتُوا۟ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
👉ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡
↪️ በረመዳን ፆም ዙርያ ጥያቄና መልስ


🔺ጥያቄ፦ #እናቴ አላህ ይማራትና ከመሞቷ በፊት በጭንቅላቷ ወድቃ አዕምሮዋ ስለተነካ ለአንድ አመት ያክል ሰላትም ሆነ ፆም አትችልም ነበር አሁን እኔ ልጇ ምን ላድርግላት ?

🔺መልስ፡- #እናትህ እንደምትለው አዕምሮዋ ከተነካ ፆም ግዴታ አይሆንባትም ነበር ግን አዕምሮዋ ጤነኛ ከሆነና ከተወችው ከውርስ ንብረት ላይ ተወስዶ ከፋራ መከፈል አለበት የተወችው ንብረት ከሌለ ከቤተሰብ አንዱ ቢከፍልላትም ሆነ ቢፆምላት ሊጠቅማት ይችላል ፡፡

🔹 ጥያቄ ፡- #እድሜው አሥራ ስድስት አመት የሞላው ተማሪ በረመዳን ፆም የትምህርት ቤት ፈተና ቢገጥመው ለፈተናው እንዲመቸው ብሎ ማፍጠር ይችላል?

🔺መልስ ፡- #ለአካለ መጠን የደረሰ ተማሪ በፈተና ሰበብ ማፍጠር አይችልም አላህ በቁርአኑ ፡-

‏{‏فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ...}

ትርጉም (( ከናንተ ውስጥ ወሩን ያገኘ ይፁም ..))

በቀራህ -185

ስለዚህ ካለሕመም በስተቀር በሌላ ምክንያት ፆምን መተው አይቻልም ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናት ግን ቢያፈጥሩ ምንም አይደለም ፡፡

🔹ጥያቄ  #አራት መቶ ኪሎ ሜትር የሚገዝ መንገደኛ ማፍጠር ይችላል ᐀ የሚችል ከሆነ ስንት ቀን ድረስ ነው የሚያፈጥረው?

🔺መልስ ፡- #መንገደኛ የሚገዘው ከሰማንያ ኪሎ ሜትር በላይ ከሆነ ማፍጠርም ሆነ ሰላትን አሳጥሮ መስገድ ይችላል መንገደኛው የሚመለስበትን ቀን የማያውቀው ከሆነ ላልተወሰነ ጊዜ ፆሙን ማፍጠርም ሆነ ሰላቱን ማሳጠር ይችላል ፡ የተጓዘበት አካባቢ ሲደርስ እዛው ለመኖር ከነየተ ከአራት ቀንና ሌሊት በላይ ማፍጠርም ሆነ ሰላት ማሳጠር አይችልም

🔹ጥያቄ ፡#እባኮትን እስኪ ስለረመዳ የመጨረሻ አስር ቀኖች (ዓሸረል አዋኺ) ጥቅምና ደረጃውን ቢያብራሩልን?

መልስ ፡- የዓሸረል አዋኺ ደረጃው በጣም ትልቅ ነው ረሱልም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በረመዳን ከመጀመርያዎቹ ቀኖች ይበልጥ በዓሸረል አዋኺ በዒባዳ ይጥራሉ፣ ተሐጁድ ሰላት ይሰግዳሉ፣ ኢዕቲካፍ ለማድረግ መስጊድ ተጠቃለው ይገባሉ ፣ ለይለተል ቀድርንም ለማግኘት በዓሸረል አዋኺ በይበልጥ ተስፋ ያደርጋሉ ፡፡

🔹ጥያቄ #በተባረከው የረመዳን ወር የተወደዱት ሥራዎች የትኞቹ ናቸው?

🔺መልስ  #በረመዳን የተወደዱ ሥራዎች በጣም ብዙ ናቸው ከነሱም ውስጥ አላህ ግዴታ ያደረጋቸውን ሰላትም ሆነ ፆም በትክክል መፈፀም፡ ግዴታ ያልሆኑ ተጨማሪ ሥራዎችን ማብዛት ይኸውም ቁርአን መቅራት ፣ ተራዊሕ እና ተሃጁድ መስገድ፣ ሰደቃ መስጠት፣ ኢዕቲካፍ መግባት ፣ አላህን ማውሳት ማብዛት፣ ለዒባዳ ብሎ መስጊድ መቀመጥ ማብዛት፣ ከተጠሉና ከተከለከሉ ሥራዎችና ቃሎችን መቆጠብ እና ፆም እንዳይበላሽ መጠንቀቅ ናቸው ፡፡

🔹ጥያቄ #ኢዕቲካፈ ምን ማለት ነው? ደንቡስ እንዴት ነው? ቤቴ ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ እችላለሁ?

🔺መልስ #ኢዕቲካፍ በኢስላም ትልቅ ዒባዳ ነው አላህም በቁርአኑ ‏ለነብዩ ኢብራሂምና ኢስማዒል (አለይሂማ ሰለም) እንዲህ ብሏቸዋል፡-

ለኢብራሂም የቤቱን (የከዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ በኔ ምንንም አታጋራ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸው ለሚደፉት ንፁሕ አድርግላቸው /ባልነው ጊዜ አስታውስ/

አል ሐጅ / 26

ረሱልም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በረመዳን ግማሽ ጀምሮ ኢዕቲካፍ ይገቡ ነበር በሕይወታቸው መጨረሻ አካባቢ ለይለቱል ቀድር ይበልጥ ተስፋ የሚደረገው በዓሸረል አዋኺ` ሊሆን እንደሚችል ሲገለፅላቸው በረመዳን በመጨረሻ አስሩ ቀኖች ኢዕቲካፍ ለማድረግ ከነባለቤቶቻቸው መስጊድ ይገቡ ጀመር ፡፡

ኢዕቲካፍ ከመስጊድ በስተቀር ቤትም ሆነ ሌላ ቦታ አይቻልም አላህም በቁርአኑ

እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትሆኑ /ሴቶችን/ አትገናኙዋቸው)) ይላል

🔹 ጥያቄ  #በረመዳን ቀኑን ሙሉ ተኝቶ በማፍጠርያ ሰዓት ከንቅልፉ የሚነሳ ሰው እንዴት ይታያል (ሁክሙ) ምንድነው?

🔺መልስ፡- ከፈጅር በፊት ፆም ነይቶ ቀኑን ሙሉ የተኛ ፃሚ ፆሙ ትክክል ነው ነገር ግን በሰላቶች ወቅት መተኛቱ ሐራም ነው መጀመርያ ሰላቱን በወቅቱ ያለመስገዱ ሁለተኛ ጀማዓ ሰላት መስጊድ ያለመሄዱ ሲደመርበት ትልቅ ወንጀል ሰራ ማለት ነው ፡፡ በዚህ አጋጣሚ በጣም የሚያሳዝነኝ ጉዳይ ብዙ ሰዎች ልምድ አድርገዋ የያዙት በረመዳን ሌሊቱን በማይረባ ነገር አምሽተው ፈጅር ሲደርስ ሱሑር በልተው ቀኑን ሙሉ ይተኛሉ ፆም ደግሞ ያለሰላት ተቀባይነት የለውም ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ሰዎች አደጋ ላይ ነው ያሉት ፡፡


🔹ጥያቄ:- #በረመዳን ወር ቴልቪዥን እና ቪዲዮ መመልከት ፆምን ያጓድላልን?

🔺መልስ: #አንድ ሠው የሚያዳምጠው ወይም የሚመለከተው ነገር ከተፈቀዱ ነገሮች (ሙባሀት) ከሆነ ምንም ችግር የለውም ፆሙ ላይ እንከን አይሆንም፡፡ ሆኖም ግን ፆመኛ ሰው ጊዜውን ወደ አላህ ሊያቃርበው በሚችል ነገር ብቻ ነው ማሳለፍ ያለበት፡፡ ቁርዓንን ያነባል አላህን ያወድሳል ወዘተ... አላህ ሀራም ያደረገውን ነገር ማዳመጥ ወይም መመልከት ግን ፆምን እንደሚያጓድል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የዚህም ምክንያት ፆም የተደነገገበት አላማ የአላህን ፍራቻ(ተቅዋን) መላበስ ነው፡፡

ፆምና ህጎቹ ከሚለው ኪታብ የተወሰደ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
ኢኣነቱል ኢኽዋን ተከታታይ ደርስ


በደርሱ ውስጥ የተካተቱት ነጥቦች
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
❶ ጾምን የሚያበላሹ ነገራቶች
⓶ ምስኪን ለሚመግብ መጠኑ
③ ለፃመኛ የሚፈቀዱ ነገራቶች
🔻ሌሎችም ወሳኝ ነጥቦች ተዳሶበታል።

ክፍል 1⃣1⃣


🎙በኡስታዝ አቡ ሂዛም አብዱረህማን ሰኢድ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
💢ተከታታይ ስለ ረመዳን ዳሰሳ


የመጃሊስ ሸህር ረመዳን የኪታብ ቂርአት

◾️የፃም ትሩፋቶች


ክፍል 0⃣5⃣


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💢እውቀት

▪️ኢማሙ አህመድ እንዲህ አሉ፦ የሰው ልጅን ከእንስሳት የለየው እውቀት ነው እውቀት ባይኖርማ ሰወች ልክ እንደ እንስሳት በሆኑ ነበር።

📚ኢዕላሙል ሙወቂዒን 182-2

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➧ ሸይኽ ዓብዱረዛቅ አል በድር - ሀፊዘሁላሁ - እንዲህ ይላል :-

💢የተከበረውን ቁርኣን በመቅራት በሱ በመስራት በማስተንተን ትኩረት መስጠት አለብን
ጭንቀት የበዛብን በመካከላችን ጭነቀትና ሀዘን የተንሰራፋው ከቁርኣን በመራቃችን ነው
ቁርኣንን የሙጥኝ ብለን ቢሆን ኖሮ
ወደርሱ የቀረብን ሆነን የሚገባው አይነት መቅራትን ብንቀራው ከማንም በላይ ደስተኞች እንሆን ነበር "

ጃሚዑል ሙአለፋት ወረሳኢል ( 14/297 )
💎መቼም ባለትዳር መሆንሽ አይቀርም !
ቤትሽን ጥለሽ ወደ ሆነ ስፍራ መሄድ ስታስቢ ባለቤትሽን አስፈቅደሽው ። ከፈቀደልሽ ወደ ፈለግሽው ቦታ ሂጅ ካልሆነ ግን ቤትሽ ተቀመጭ።በሐይማኖታችን ያለ ባለቤትሽ ፍቃድ ከቤትሽ መውጣት አይፈቀድም !!
~الزوجة~
وليس لها أن تخرج من منزله
إلا بإذنه، سواء أمرها أبوها أو أمها أو غيرهما باتفاق الأئمة .
الفتاوى لابن تيمية ٣٢ /٢٦١-٢٦٣
Ibnu seid
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w