💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ረመዳን ቀን 1
Sadat
ረመዳን ቀን 1
1) ላኢላሃ ኢለላህ ትርጉም፣
2) 3 ዱአዎች
ረመዳን ቀን 2
Sadat
ረመዳን ቀን 2
1) ተውሒድ እና ሺርክ
2) 3 ዱአዎች
ረመዳን ቀን 3
Sadat
ረመዳን ቀን 3
1) ስራዎች ተቀባይነት የሚያገኙበት መስፈርቶች
2) 3 ዱአዎች
ረመዳን ቀን 4
Sadat
ረመዳን ቀን 4
1) እምነት ምንን ይይዛል?
2) 3 ዱአዎች
ረመዳን ቀን 5
Sadat
ረመዳን ቀን 5
የእስልምና ማእዘናት
3 ዱአዎች
ረመዳን ቀን 6
Sadat
ረመዳን ቀን 6
የእምነት ማእዘናት
3 ዱአዎች
ረመዳን ቀን 7
Sadat
ረመዳን ቀን 7
የመጀመሪያው እና የመጨረሻው መልክተኞች ኑሕ እና ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂም ወሰለም)
ሁለት ዱአዎች
ለዲናችን ምን ያክል ከ ጊዛችን ሰተናል
Abu Imran
MuhammedSirage M.NUR
السلفية
ለዲን እውቀት ፍለጋ ምን ያህል ግዜ እንሰጣለን?!
አንዳንድ ከሃዲያን ኢስላምን ለማጥቃትና ፈሳድ ን በምድር ላይ ለማሠራጨት ኢስላምን ለረጅም ዓመታት ይጠናሉ ፣ እኛስ ይህንን እንከን የማይገኝለት የተዋበ እምነት ለመገንዘብ ምን ያህል ግዜ እየሰጠን ነው??
የ 7 ደቂቃ ያህል ምክር
t.me/Muhammedsirage
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ረመዷን_የለውጥ_ወር_ነው!

ለተጠቀመበት አትራፊ
ለዝንጉወች ደግሞ ክስረት ነው!

ረመዷን ላይ ጠቅላላ የመልካም ስራ ምንዳችን በእጥፍ ሲሆን መጥፎ ስራችን/ወንጀላችንም ደግሞ ይበልጥ የከፋ ይሆናል so መጥፎውን ትተን መልካሙን እያደገግን ከአትራፊወች እንሁን እላቹሀለው!

ረመዷን የቁረአን ወር እንደመሆኑም
በቁርአን ላይ አደራ ልንታገል ይገባል!

በዚህ ውድ ወር ሁለት ሶስት ጊዜ ቢቀር
#አንዴ እንኳ ያላኸተመ እመኑኝ በቁሙ ሞቷል!

እናም በርቱ እንበርታ ዓለይኩም ብል ቁርአን
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
✅💢ሁለት የቁርአን አያቶች የሚጀምሩት ወዬለትበሚል ቃል ነው
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹وَيْلٌۭ لِّلْمُطَفِّفِينَ
🔹وَيْلٌۭ لِّكُلِّ هُمَزَةٍۢ لُّمَزَةٍ
▪️የመጀመሪያው፦ ስፍር ለሚያጐድሉ'፣በሚዛን ለሚያጭበረብሩና ተመሣሣይ ባህሪ ያላቸውን
ሰዎች የሚያስጠነቅቅ ሲሆን

▪️ሁለተኛው ደግሞ፦ ነገር አሳባቂን፣ ሐሜተኛንና ተመሣሣይ ባህሪ ያላቸውን ሰዎች የሚያስጠነቅቅ
ነው።
🔸ወዳጄ! አደራህን መዳን ከፈለግክ ከእንደዚህ
ዓይነት ባህሪያቶች ራቅ።
Audio
◾️ረመዷን የቁርአን ወር
➖➖➖➖➖➖➖➖

👉ቁርአን መቅራት ያለው ትሩፋት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
Audio
ተከታታይ የፆም ትምህርት

ማጠናቀቂያ ክፍል ④

ፆምን የሚያበላሹ ነገሮች

ባለማወቅ ፈጅር ወቶ ሱሁር ቢበላ ወይም ፀሓይ የገባ መስሎት ቢያፈጥር ብይኑ ምንድን ነዉ?

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
እስኪ ይህን ትልቅ ልዩነት ተመልከት‼


✅በዚህ ታላቅ ወር ባል ከውጭ ወደ ቤት ሲገባ ባለቤቱ ቁርኣን በመቅራት የሚያገኝ አለ

✖️ሌላው ወደ ቤት ሲገባ ሚስቱ ፊልም ላይ ተፅዳ የሚያገኝ አለ

ይህ ፊልም የስንት ሰዉን ጓዳ ነው ያፈረሰው ‼❓

አባት ሆይ አደራ ቤተሰብህን በተለይ ልጆችህን ሚስትህን በማነፅ ላይ

منقول
◼️የሱሁር (የሌሊት ምግብ)፡-

ሱሁር መብላት የዚህችን ኡማ የፆም ሥርዓት ካለፉት ህዝቦች የሚለይ ሲሆን በውስጡ ብዙ ኸይር ነገር ይዟል፤ ይህንንም ነቢያችን ﷺ እንዲህ በማለት ገልፀውልናል፡-

“በኛና በመጽሐፍት ባልተቤቶች ፆም መካከል ያለው ልዩነት ሱሁር መብላት ነው” (ሙስሊም ዘግበውታል)።

በሌላ ቡኻሪና ሙስሊም በተስማሙበት ሐዲስ ነቢያችን ﷺ


تسحروا فإن في السحور بركة

《ሱሁር ብሉ፤ ስሁር መብላት በረካ አለውና》 ሲሉ ተናግረዋል
(📚ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል)።
#ፆመኛ_የሆነ_ሰው_የሚከተሉትን_ቢፈፅም_ይወደዳል፦

#ሱሁር (ከጎህ በፊት መመገብ)፡- ነቢያችን (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

🔸“ሱህር (ከሱብህ በፊት) ተመገቡ በሱሁር ረድኤት አለ፡፡”


 áŠ áˆ ቡኻሪ (1923) ሙስሊም (1ዐ95)
ጥቂት መጉረስ ወይም አንድ ጉንጭ እንኳ መጎንጨት ሱሁር ያስብለዋል፡፡ ወቅቱ ከእኩለ ሌሊት ጎህ እስኪቀድ ድረስ ነው::

#ሱህርን ማዘግየት፡- ዘይድ ኢብን ሳቢት

🔸“ከነቢያችን (ﷺ) ጋር ሱህር ከተመገብን በኋላ ሱብህ ሰገድን” ብለው ሲናገሩ “በመካከላቸው የነበረው ወቅት ምን ያህል ነበር”? ብለው ጠየቋቸው:: እሳቸውም “ሀምሳ የቁርአን አንቀፆች የሚያስነበብ ወቅት ነበር”አሉ::


 áŠ áˆ ቡኻሪ (575) ሙስሊም (1097)

#ቶሎ ማፍጠር (ፆም መፍታት)፦ ፀሐይ መጥለቁ ሲረጋገጥ በፍጥነት ማፍጠር የተወደደ ተግባር ነው:: ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

🔸“ሰዎች ፍጡር ላይ እስከቸኮሉ ድረስ ከመልካም አይወገዱም፡፡”


 áŠ áˆ ቡኻሪ (1957) ሙስሊም (1ዐ97)

#በተምር እሸት ማፍጠር፡- አነስ ባስተላለፉት ሀዲስ

🔸“ነቢዩ(ﷺ) ካገኙ በተምር እሸት ካላገኙ በተምር ተምርም ካላገኙ ውሃ በመጎንጨት ያፈጥሩ ነበር”::


 áŠ á‰Ąá‹łá‹á‹ľ (2356) ቲርሚዚ (696)

#በፍጡር ወቅት ዱዓ (ፀሎት) ማድረግ፡- ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

🔸“የሶስት ሰዎች ዱዓ ተመላሽ አይሆንም ፆምኛ ፆሙን እስኪፈት፣ ፍትሃዊ መሪና ተበዳይ”


 á‰˛áˆ­áˆšá‹šá‹­ (2526) በይሀቂይ (31345)

#አቅም እስከፈቀደው ድረስ በብዛት መመፅወት ቁርአን ማንበብ፣ ፆመኛን ማስፈጠርና ሌሎችንም መልካም ተግባሮችን መፈፀም፡፡ኢብኑ ዓባስ እንዳስተላለፉት

🔸“ነቢዩ(ﷺ) መልካምን በመቸር አቻ አልነበራቸዉም በተለይ በረመዳን ከጅብሪል ጋር ሲገናኙ ቸርነታቸው እጅግ ይጨምራል:: ጅብሪል በየረመዳኑ እየመጣ ቁርአንን ይማማሩ ነበር፡፡ የአላህ መልዕክተኛ ከጅብሪል ጋር ሲገናኙ ከተላከ ንፋስ የፈጠኑ ቸር ይሆናሉ፡፡”


 áŠ áˆ ቡኻሪ (6) ሙስሊም (23ዐ8)

#የሌሊት ሰላት ማብዛት፡- በተለይም የመጨረሻዎቹን የረመዳን አስር ቀናት የሌሊት ሰላት ማብዛት የተወደደ ነው፡፡አኢሻ ረዐ እንዳሉት

🔸“የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ጅማሬ ላይ ሽርጣቸውን ጠበቅ አድርገው ሌሊቱን ያለእንቅልፍ ያሳልፋሉ:: ቤተሰቦቻቸውንም ያነቃሉ”


 áŠ áˆ ቡኻሪ (2ዐ24) ሙስሊም (1174)

በሚከተለውም ሀዲስ በጥቅሉ እንዲህ ብለዋል “የረመዳንን ሌሊት በእምነትና ምንዳን በማሰብ የሰደገ ቀደም ሲል የፈፀማቸው ኃጢአቶች ይታበሳሉ፡፡”
 áˆ™áˆľáˆŠáˆ (759)

#ዑምራን መፈፀም፡- ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

🔺“በረመዳን ዑምራን መፈፀም ከእኔ ጋር ሐጅ እንደማድረግ ነው፡፡”


 áŠ áˆ ቡኻሪ (1863) ሙስሊም (1256)

#ሰው ሲሰድበው ፆመኛ ነኝ ማለት፡- ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

“አንድ ሰው ከሰደበው ወይም ከመታው እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል፡፡”
 
አል ቡኻሪ (19ዐ4) ሙስሊም (1151)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የዝናብ መጥፋት ሰበቡና መፍትሄዉ
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
🎤 የጁሙዐ ኹጥባ

ርዕስ

مَاهِيَ أَسْبَابُ مَنْعِ المَطَرِ مِنَ السَّمَاء؟ وَمَاهُوَ الْعِلَاجُ

🌐 ዝናብ ከሰማይ መዉረዱን የሚከለክሉ ሰበቦች ምንድን ናቸዉ?
መፍቲሄዉስ ምንድን ነዉ⁉️

🕌 ደሴ አል አዝሓር መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

ረመዷን ቀን ①① 1442

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💦‏قال الشّيخ ‎صالح الفوزان حفظه اللّه:
◾️ሸኽ ሷሊህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ

【«فإن من أدعك شهر ‎رمضان ومكّنه اللّه من الإنتفاع به، فقد أنعم اللّه عليه نعمة عظيمة لا يعدلها شيء»】
✅ አንድ ሰው አላህ ረመዷንን በሰላም አድርሶት እንዲጠቀምበት ካደረገው፦ አላህ ለዚህ ሰው የሚስተካከለው የሌለ የሆነን ትልቅ ፀጋ ውሎለታል።
📚 [ مجالس شهر رمضان ١١]
◼️ሴት ልጅ ፈተና እንደማይመጣባት ከታመነ። በነዚህ መስፈርቶች ሳትገላለጥ፤ ሳትዋብ፤ ሽቶ ሳትቀባ በመውጣት ሰላተ “ተራውሒን” ብትሳተፍ ምንም ችግር የለውም”
ኢማሙ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ
[መጅሙዓ አልፈታዋ፡ (14/211)]
Audio
تلاوة خاشعة مؤثرة من سورة الزمر
عشاء الثلاثاء ٢٩ رجب ١٤٤١هـ
لفضيلة الشيخ د. ⁧ ماهر المعيقلي⁩
@Mahir_al_meaqli_sa https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
♻️📌በአላህ ላይ መመካት📌♻️
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

💢ከአምልኮ አይነቶች ሁሉ ትልቁ “ተወኩል” ወይም በአላህ ላይ መመካት ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

▪️وعلى الله فتوكلو إن كنتم مؤمنين.

🔻“ምእመናንም እንደሆናችሁ በአላህ ላይ ተመኩ” በላቸው ሱረቱ አል ማኢዳህ፡

በዚህ ቁርኣናዊ አንቀጽ በአላህ ላይ መመካትን ለኢማን መስፈርት አደረገ፡፡
አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ለነብዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን አላቸው፡-

▪️فإذا عزمت فتوكل على الله

🔻“ቁርጥ ሀሳብ ባደረግህም ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ” ሱረቱ አል ዒምራን ፡

በሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ደግሞ ሰዎች በአላህ ላይ እንዲመኩ ለነብዩ صلى الله عليه وسلم ትዕዛዝ
አስተላለፈ፡፡

▪️يا أيها النبي حسبك الله ومن اتبعك من مؤمنين

🔻“አንተ ነብይ ሆይ! አላህ በቂህ ነው፡፡ ለተከተሉህም ምእምናን (አላህ በቂያቸው
ነው)፡፡ ሱረቱ አል አንፋል፡

▪️ومن يتق الله يجعل له مخرجا. ويرزقه من حيث لا تحتسب ومن يتوكل على الله فهو حسبه إن الله بالغ أمره قد جعل الله لكل شيء قدرا

🔻“አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡ ከማያስበውም
በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፡፡ አላህ
ፈቃዱን አድራሽ ነው፡፡ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል፡፡”
ሱረቱ አጦላቅ፡

በሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ አምልኮትን በአላህ ከመመካት ጋር አቆራኘ፡-

▪️{فاعبده وتوكل عليه }

“ስለዚህ ተገዛው ፡፡ በእርሱም ላይ ተጠጋ፡፡” ሱረቱል ሁድ

🔻ሰዎች በእርሱ ላይ ብቻ እንዲመኩ አላህ አዘዘ ፤ የመመካት ባለቤቶችንም
አወደሰ ፤ በእርሱ የሚመኩ ሰዎችንም እንደሚወድ በበርካታ አንቀጾች ላይ ተናገረ፡፡
ይህ ሁሉ ፣ በአላህ ላይ መመካት ምን ያክል አንገብጋቢ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡
በአላህ መመካት በአካል የሚተገበር ሳይሆን ልቦናዊ ተግባርና አምልኮ ነው፡፡

በአላህ መመካት በልብ ብቻ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው፡፡ ለምሳሌ፡- ፍርሃት ፣ ስጋት ፣ የእርሱን
ውዴታ ፈልገንና ቅጣቱን ፈርተን አላህን መገዛት የልብ ተግባር ናቸው፡፡
አንዳንድ የእውቀት ባለቤቶች “በአላህ መመካት በዲን ውስጥ ያለው ድርሻ ልክ
ቅንጭላት ከአካል ዘንድ ያለውን ድርሻ ይወክላል” በማለት ይናገራሉ፡፡

🔻በአላህ መመካት የሌለበት ዲን ፣ ቅንጭላት የሌለው አካል ማለት ነው፡፡
ቅንጭላት የሌለው አካል ህይዎት እንደሌለው ይታወቃል፡፡ ዲንም በአላህ መመካትን
ካጣ እንደዚሁ ነው፡፡ ጤናማ ዲን አይሆንም፡፡
ለአላህ ተፈጻሚ ከሚሆኑ የአምልኮ ተግባራቶች ሁሉ ትልቁ በአላህ ላይ መመካት
ነው፡፡ ከሌሎች ባሮቹ ሁሉ አማኞች የተለዩበት በእርሱ ነው፡፡ ፍጹም ከመሰረቱ በአላህ
ላይ ያልተመካ ከሀዲ ነው፡፡ በአላህና በሌሎች አካላት የተመካ ሙሽሪክ ወይም በአላህ
ላይ አጋሪ ነው፡፡ በአላህ ብቻ የተመካ ሰው እምነቱ በትክክለኛ መሰረት ላይ የተገነባ
በመሆኑ አላህ የሚወደው ፣ ስራውን እና ንግግሩን የሚቀበለው ትክክለኛ ሙእሚን የተውሂድ ሰው ነው ።

👉በአላህ ላይ የመመካት እውነታ ከሚለው ኪታብ የተወሰደ

🔺ኩታቡን ሙሉውን ለማንበብ👇👇👇
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/2053

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w