💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ለፈገግታ ነዉ...

እኔ ትኩረት ስጥቼ የምጠባበቃቸዉ ነገሮች ቢኖር የምግብ ስዓቴ እና የእንቅልፍ ስዓቴ ነዉ። ከራስ በላይ ንፍስ አሉ ህእ¡¡
«ገንዘብ አላት ብሎ ፥ መልከ-ጥፉ ማግባት፣
ገንዘቡም ያልቅና ፥ ሁለተኛ ጥፋት።»

🍁ይላል የወሎ ሰው ተረት! እ¡

✍️ከማ ከተበት t.me/https_Asselfya
መሆን ያለበት ነገር ሁሉ ይሆናል። ኖ መጨናነቅ ፈታ ብቻ!!
🍁ሴት መቀላቀል፣ መጨበጥ፣ ያለዉ አደጋ !!

🎙ሸይኽ አወል حفظه الله
🍁 በሶሻል ሚድያ ላይ ያለተፈቀደ ሰዉ ላይ ማፍጠጥ ያለዉ አደጋ......!!

🎙ሸይኽ አወል حفظه الله
በፎቶ ተያይቶ መጋባት  «ትልቂቱን ሴት ቆንጆ ያደርጋታል»ወንዱንም ከዛሊክ እናም ኺያና አይጠፋውም።
✍️ منقول
🍁 የስልክ እይታ ጉድ........

አላህ ይጠብቀዎት ያ ሸይኽ አወል
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝ኢስላማዊ ስርዓቶችና መልካም ስነ ምግባሮች❞ « ክፍል  ⓵ » ↷የቤት  አገባብና አወጣጥ ስርዓቶች↶ ⓵⇝የቤቱን ሰዉ ማስፈቀድ፦ አንድ ሰዉ የራሱ ያልሆነ ቤት ከመግባቱ በፊት  ማስፈቀድ ግደታ ሲሆን  የራሱ ቤት ሲገባም  ቢያስፈቅድ መልካም ነዉ። { یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ لَا تَدۡخُلُوا۟ بُیُوتًا غَیۡرَ بُیُوتِكُمۡ…
ኢስላማዊ ስርዓቶችና ስነ ምግባሮች❞
 


« ክፍል  ⓶»

🍁የአመጋገብ ስርዓቶች

➀« ከመብላት በፊት ቢስሚላህ ማለትዑመር ኢብን አቢ ሰለማህ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛۡ ﷺእንዲህ ብለዋል  ቢስሚላህ በል፣በቀኝ እጂህ ብላ፣ከፊት ለፊት በኩል ብላ ።

ዓኢሻ ባስተለፉት  ሀዲስ ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል"ስትበሉ ቢስሚላህ በሉ በመጀመሪያ ላይ ከረሳችሁ  ስታስታዉሱ "ቢስሚላሂ ፊ አወሊሂ ወአኺሪሂ(መጀመሪያዉም መጨረሻዉም በአላህ ስም ይሁን)በሉ።

➁« በቀኝ እጂ መብላት፦ ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል "ስትበሉ በቀኝ እጃችሁ ብሉ፣ስትጠጡም በቀኝ እጃችሁ ጠጡ ሸይጧን የሚበላዉም የሚጠጣዉም በግራ እጁ ነዉ።

አንዳድ ሰዎች ግራም እንደ ቀኝ እጂ ነወለ ወይም ቀኝ እጂ ሌላ ስራ ይዟል በሚልና በመሳሰሊ ደካማ ምክንያቶች በግራ እጃቸዉ ሲመገቡ ይስተዋላል። ይህ ችልተኝነት  በዚህ ርዕስ ላይ አደገኛ ነዉ። ምክንያቱም አንደኛ ነብዩ ﷺ በግራ መመገብ የሸይጧን ተግባር መሆኑን በመግለፀ በቀኝ እንድንበላ በትዕዛዝ መልክ ተናግረዋል።የእርሳቸዉ ትዕዛዝ መፈፀም ደግሞ ግደታ ነዉ። ሁለተኛ ነብዩ ﷺ አንድን ሰዉ በግራ ሲበላ አይተዉት  በቀኝ እንድበላ ቢያዙትም  እሱ ግን በመኩራራት "አልችልም"አላቸዉ በዚህ ግዜ ነብዩ ﷺ" አትቻል" ብለዉ ረገሙት! ወድያዉኑ እጁ ሺባ ሆኖ ምግብ ወደ አፎ ማቅረብ አቃተዉ።ይህ ሀድስ የሚያስረዳዉ በዚህም ሆነ በሌላ ርዕሶች ላይ ነብዩን መቃረን አደገኛ መሆኑን ነዉ።

➂« ከፊት ካለዉ እያነሱ መብላት፦ከላይ ባሳለፍነዉ ሀዲስ ነብዩﷺከፊት ለፊትህ ብላ ብለዋል።

➃« ከመብላት በፊትና ከተበላ በኋላ እጅን መታጠብ፦ከነብዩﷺ እንደተዘገበዉ "የምግብ በረከት  ከመብላት በፊት ከተበላ በኋላ መታጠብ ነዉ። አቡ ሑረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል"እጁ ላይ ቅባት እያለ ሳይታጠብ በመተኛቱ አንዳች ነገር ቢነካዉ እራሱንጂ እንዳይወቅስ።

➄ «ተደግፎ አለመብላት፦ ነብዩﷺእኔ ተደግፌ አልበላም ብለዋል።

➅«በሆድ ተኝቶ አለመመገብ፦ከኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፉት ነብዩﷺ አስካሪ  መጠጥ የሚጠጣበት ማዕድ ላይ ተጥዶ መብላትና በሆድ ተኝቶ መመገብ ከልክለዋል።

➆« ከሳህን ዳር ዳር መመገብነብዩﷺእንዲህ ብለዋል "ከሳፍ ዳር ዳር ብሉ ከመሀል አትብሉ በረከት የሚወርደዉ መሐሉ ላይ ነዉ።

በወርቅ ወይም በብር ሳህን አለመብላት፦ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል ከወርቅ እና ከብር ኩባያ እንዳትጠጡ በሳህኑም አትብሉ።

➈« በህብረት መብላት ነብዩﷺእንዲህ ብለዋል ምግባችሁ ላይ ተሰባሰቡ የአላህንም ስም ጥሩበት ይባርክላችኋል። ሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል"አንድ ሰዉ ምግብ ለሁለት ይበቃል።የሁለት ሰዉ ምግብ ለአራት ይበቃል የአራት ሰዉ ምግብ ለስምንት ይበቃል።

➉« በሶስት ጣት መብላት፦ካዕብ ኢብኑ ማሊክ እንዳስተላለፉት ነብዩ ﷺበሶስት ጣታቸዉ ይበሉ ነበር።

✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል◍◍◍◍◍◍◍

📝أم عثيمين الجامية

⇘⇩⇘⇩⇘⇩⇘⇩⇘⇩⇘⇩⇘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ኹጥባ አህሉሱና ሰለፍዮች ናቸዉ
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም
«የጁሙዓ ኹጥባ»

☜أهل السنة هم السلفيون

አህሉ ሱና ሰለፊዮች ናቸዉ!!

🕌 ኮ/ቻ አንሷር መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣
t.me/abu_reyyis_arreyyis/7527
አንዳዴ የሚገርመኝኮ አለ በሉ፦ ስደት ሁኔታዉ በደንብ አዉቀዉት ኖረዉ በቃኝ ብለዉ ገብተዉ ከዛ መልሰዉ ተሰደዉ ስደት እያሉ የሚያለቃቅሱት ነገር መችም ታታቁት አልተመለሳችሁምኮ ሶብር አድርጋችሁ ብትቀመጡ የሚሻል ስደት እያሉ በፓስት ከማለቃቀስ እ¡¡ 👆
🎈አዲስ ኪታብ ደርስ ተጀመረ በዋትሳፕ !
ዋትሳፕያልተቀላቀላችሁተቀላቀሉ➴➴➴➴➴➴➴

ኮድ ⓵
https://chat.whatsapp.com/Hy8VXIPn2kwDcpSJZ0Y1a1

ኮድ ⓶
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://chat.whatsapp.com/D1Sh8x6HoJlJArrzMrwOUD

ኮድ ⓷
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://chat.whatsapp.com/D1SwoMDQ5CE7ypmQ2ulTuR

✍️ማስጠንቀቂያ!!መግባት የሚቻል አንድ ላይ ብቻ ነዉ 3ቱም ተመሳሳይ ስለሚለቀቅበት!!!
Forwarded from «𝐓𝐞𝐰𝐮𝐡𝐢𝐝 𝐀𝐧𝐝 𝐒𝐮𝐧𝐧𝐚𝐡 𝐜𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥»
ትሸፍነው

ትሸፍነው እንጂ በመላ አካላቷ
ጅልባቧ ነውና የሴት ልጅ ውበቷ

ጀነት እዲያስገባሽ ነው ና ምኞቴ
የአላህን ትዛዝ ጠብቂው እህቴ''

ክብሯን እዲጠብቅ ዱሪዬ እንደይደፍራት
''ባለጌና አጃቢ በሩቅ እዲፈራት''

ስሞን እንዲጠብቅ ሰውም እዲያከብራት
በውበት ላይ ውበት እንዲጨምርላት''

ለሴት ልጅ መሸፈን አላህ መረጠላት''
ለማስቸገር ሳይሆን መልካም አስቦላት
⇙⇘⇙⇘⇙⇘⇙⇘⇙⇘⇙⇘⇙⇘
T⃨e⃨~⃨ t.me/Tewuhid_We_sunnah
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝ኢስላማዊ ስርዓቶችና ስነ ምግባሮች❞   « ክፍል  ⓶» 🍁የአመጋገብ ስርዓቶች ➀« ከመብላት በፊት ቢስሚላህ ማለት፦ዑመር ኢብን አቢ ሰለማህ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛۡ ﷺእንዲህ ብለዋል  ቢስሚላህ በል፣በቀኝ እጂህ ብላ፣ከፊት ለፊት በኩል ብላ ። ዓኢሻ ባስተለፉት  ሀዲስ ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል"ስትበሉ ቢስሚላህ በሉ በመጀመሪያ ላይ ከረሳችሁ  ስታስታዉሱ "ቢስሚላሂ ፊ…
ኢስላማዊ ስርዓቶችና ስነ ምግባሮች❞


« ክፍል ⓷»

🍂የአመጋገብ ስርዓቶች ከትላንት የቀጠለ!!

➀➀ከልክ በላይ አለመመገብ፦
ነብዩ ﷺእንዲህ ብለዋል "ሙዕሚን የሚበላዉ በአንድ አንጀት ሲሆን ካፊር ግን የሚበላዉ በሰባት አኖጀት ነዉ።በሌላም ሀድስ እንዲህ ብለዋል"የሰዉ ልጂ ከሚሞላቸዉ ሁሉ የከፍዉ ሆዱ ነዉ። የተወሰኑ ጉርሻዎች በቂዉ ነዉ።ከዚያ ባለፈ ግን የሆዱን ሲሶ  ለምግብ ሲሶዉን ለመጠጥና ሲሶዉን ደግሞ ለእስቲንፍት ያድርግ።

➀➁ በጣም ትኩስ ምግብ በረድ እስኪል መጠበቅ፦ አስማዕ ቢንት አቢ በክር  ፍርፍር ከሰሩ በኋላ ከድነዉ እስኪበርድ ያቆዩትና እንዲህ ይሉ ነበር"ነብዩﷺ በረከቱ የሚበዛዉ  እንዲህ ሲሆን ነዉ ሲሉ ሰምቻለሁ።

➀➂የምግብን አቃቂር አለማዉጣት፦አቡ ሑረይራ እንዳሉት ነብዩ ﷺ ምግብን በፍፁም አያነዉሩም ካሰኛቸዉ ይበሉታል  ከጠሉት ይተዉታል።

➀➃አቅራቢያ ያለዉን ሰዉ መጋበዝ፦ከቸርነትና ከታላቅነት ባህሪያት አንዱ ምግብሲበላ አካባቢዉን ያለዉን እንብላ በማለት አብሮ እንዲበላ መጋበዝ ነዉይህን አለማድረግ የስስት የስግብግብነት ባህሪ ነዉ።

➀➄ አገልጋዩን አብሮ እንዲበላ ማድረግ ወይም ካቀረበዉ ምግብ መስጠት፦ ነብዩ  ﷺእንዲህ ብለዋል"አገልጋያችሁ ምግብ ሲያቀርብላችሁ እንፍሎቱንና ድካሙን ስለተወጣላችሁ አብሯችሁ እንዲቀመጥ አድርጉት። ማታስቀምጡት ከሆነ ግን ከምግቡ ስጡት።

➀➅ለሚስት ማጉረስ፦ነብዩﷺለሰዕድ ኢብን አቢ ወቃስ እንዲህ ብለዉታል ለአላህ ብለህ የምትለግሰዉ ማንኛዉም ወጪ ለሚስትህ ምታጎርሰዉ ሳይቀር ምንዳ ታገኚበታለህ።

➀➆መሬት የወደቀን በማንሳት ጠራርጎ መብላት፦ ነብዩ ﷺእንዲህ ብለዋል የምትጎርሱት ከወደቀ አንስታችሁ  ቆሻሻዉን አስወግዳችሁ ብሉት ለሸይጧን እንዳትተዉት።

➀➇ ሲጨርሱ ጣቶቹን መላስ፦አነስ እንዳሉት ነብዩ ﷺምግብ በልተዙ ሲያጠናቅቁ ሶስቱን  ጣቶቻቸዉን ይልሱ ነበር።

➀➈የተበላበት ሳህን መጠራረግ፦ ነብዩﷺእንዲህ ብለዋል ሳህኑን ጠራርጋችሁ ብሉ ከምግቡ የትኛዉ ላይ በረከት እንዳለ አታዉቁም።

➁⓪ ምግብ ሲያጠናቅቅ የሚከተለዉን ዚክር ማለት፦
{الحمد الله الذي أطعمني هذا ورزقني من غير حول مني ولا قوة}
አልሐምዱሊላሂ ለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒ ሚይ ገይሪ ሃዉሊን ሚኒ ወላ ቁወህ! ትርጉም፦{ይህን የመገበኝና ያለ ብልሃቴናሀይሌ ሲሳይን የለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባዉ ነዉ።}

   🍂 የአጠጣጥ  ስርዓቶች🍂

1➴ቢስሚላህ  ማለት
2➴በቀኝ እጂ  መጠጣት
3➴ተቀምጦ መጠጣት!!
አነስ እንዳስተላለፎት ነብዩﷺቆሞ መጠጣትን ከልክለዋል።

👉ነብዩ ﷺቆመዉ እንደጠጡ የሚጠቁሙ ሀዲሶችም መኖራቸዉ ዑለማኦች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቆሞ መጠጣትም እንደሚፈቀድም ይናገራሉ።

✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል ◕◕◕◕◕◕


📝أم عثيمين الجامية

↷⇊↷⇊↷⇊↷⇊↷⇊↷⇊↷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1