💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድእህት ወንድሞቼ እንዴትናችሁ ትንሽምክርቢጤ ከአረብ ሀገርተመላሽ የሆኑ እህቶች በተመለከተ ነገ እኔም ተመላሽነኝእና


በመጀመሪያ የተከበርሽዋ እህቴ አላሁሱበሀነሁ ታአላ በሠላም በጤና ከቤተሠቦችሽ እንዴተለየሽው እንኳንም በሰላም ቀላቀለሽ አልሃምዱሊላህ በይ ስንቶች በህመም በተለያየ ስቃይ ከአንዱ ሙስታሽፍ አንዱ ሙስታሽፍ እየተንገላቱ ይገኛሉ አንቺግን ጤናሽንይዘሽ ቆመሽእየሄድሽ ከቤተሠብሽ ጋርነሽ አንድብለሽ!!

🍁ሌላው ሀገርከገባሽ በሗላ በወርሽ  ኡፍፍፍ የሀገር ቤት ኑሮ ሲያሥጠላ የምትይውስ ነገር


✍️ልብበይ ሸጊት መቼም ከአረብ ሀገር ተመልሰሽ የተወሰነች ትንሽ ብር አብረሽ ይዘሽ የሄድሻትም ብትሆን አታጭም አይደለ በዛች ለምንአትብቃቂም መጀመሪያ ወዴ ሀገርሽ ስትገቢ ሀገርገብቼ ምን አደርጋለሁ ብለሽ ነበርአስበሽ የገባሽው መቼም ብድግ ብለሽ አልሄድሽም አስበሽበትእንጂ ታድያ የኔ ቆንጆ እዛሄደሽ ባለችሽ አብቃቅተሽ መኖር ለምንአቃተሽ ባለትዳር ከሆንሽም ባልሽ ይስራ አንቺምበቻልሽው ተንቀሣቀሽ አይዞሽ ከትንሽ ካልተነሡ ትልቅ አይደረሰሥም የኔውድ እናማ  ምን ልልሽፈልጌ እንደሆነ ገባሽ አይደለ??


✍️የስደትንም ኑሮ አይተሽው አስመርሮሽ ነው በእርግጥ የምትሄጅው እኔም ስለማውቀው ከገቡበትም ውጡ ውጡ የማይልነው ስልሽም ደግሞ ሞቾት ሣይሆን የማያሣወጣን አላማችን ስለማይሳካ ነው ታድያ ተመልሰሽ ወደዚሁ ከምትመጨ የኔቆንጆ በያሻት ገንዘብሽ ተብቃቅተሽ ትንሽ ስራ ብትከፍቺውጤታማትሆኛለሽ ብቻ ባለሽተብቃቂ እኛየአደም ልጆች እኮ አንድሸለቆ ወርቅ ቢኖረን ሁለተኛ የምንመኝነን ገባሽአይደለ ዱኒያ ከነኮተቷ አታላይ ናት እያታለለች ታሞኘናለች

በስደት ስንትነገር አጣን እድሜ ጤና የሠራነው ገንዘብ ወዴየት እንደሚበተን አናውቀው ሱበሀነአላህ ምን እነግርሻለሁ አንቺ ምታውቂዋለሽ ብቻ አልሀምዱሊላህ ስዴት ዋለልኝ የምለው ነገር ቢኖረኝ ዲናችንን እንድናውቅ አድርጎናል ከምርጥ ሱመያ የተውሂድ እህቶችም ጋር አስተዋውቆናል አልሀምዱሊላህثم አልሀምዱሊላህ ከዛ ውጭ ግን ይሄ የምለው ነገር የለም!!

✍️እና ምን ልልሽ ፈልጌ መሠለሽ  ሀገር የገባሽው ለመግባት ያሠብሽውም እህቴ  አላህፈቅዶልሽ ሀገርሽ ከገባሽ አርፈሽ በሀገርሽ ላይ ተብቃቂ ኢማንሽን ሰብሰብ አድርጊ ባልም ካላገባሽ ሰብር አድርጊና አየት አድርገሽ ጊዜሽንሳታቃጥይ ጥሩ አላህንፈሪ ከሆነ አኸላቁ ያማረ ከሆነ  ምን አለው ይሄ ደግሞ እያልሽ አትሞኚ ሠርቶየሚበላ ከሆነ አብሽሪ አላህ አለበት አንቺብቻ ሰበቡን አድርሺ !!

➬ ስንቶች መሠሉሽ ሀብታም ባለመኪና እያገቡ በስምንት ቀን ትዳራቸውየሚፈርሰው  ትዳርበሀብት አይወሰንም ኡኽታየ ብቻ። ስንቶችስ መሠለሽ የምናውቃቸው ድሀ ሆነው ምኑን አገባችው ምን ሊያበላት እየተባለች አግብታ ዛሬ ላይ የልጆች እናት አባት ባለሀብት ሆነው ቁጭያሉት ። አጣር ምጥን ያለች ምክር ወደ ሀገር ለመግባት ላሰባችሁ እህቶቼ

እንግዲህ  ስዳተኛዋ ውዷ እህቴ ወላሂ ከልቤ ነው የምወድሽ በጣም ነው የማዝንልሽ  ስደት ውስጥ ለላሽዋ እህቴ  ፣አሏህ ይዛንልሽ አሏህ ይጠብቅሽ አንቺ የስዳቷ እንቁዋ እህቴ!! ዛሬ  ትንሽዬ  ነገር ልልሽ ነው የፈለኩት ጆሮሽን ስጪኝ ፦

እሱም እንግዲህ  ምን መሰለሽ ብዙ ግዜ ስደተኛ የሆኑ እህቶች ላይ በብዛት የሚከሰት ነገር ነው።  እናም ጉደዩ የዲን ጉደይ ነው ወደ ሀገር ስትገቢ ነገሮቹ አንቺ እንደሰብሽው ሆኖ አይጠብቅሽም ይልቅ በተቃራኒው ሆኖ ነው የምተገኚው።

ስለዚህ መፍትሄ ነው ብዬ የሰብኩትን ነገር ሹክ ልልሽ ወደድኩኝ።

አንቺ ውዷ የስደትዋ ጓዴ የዲን ተማሪ የሆንሽዋ እህቴ በመጀመሪያ ልታውቂያቸው የምገቡ ነገሮች አሉ ፦

አንደኛ ዲንሽና መንሃጅሽ ለይ  ጥሩ አቋም ልትይዢ ይገበሻል ምክንያቱም አቋምሽ ለይ ደከማ ከሆንሽ ፈተነዎችን መቋቋም አትችይምና።

ሌላው ወደ ሀገር ለማግባት ከማሰብሽ በፊት ማወቅ ያለብሽ ነገር  ስለ ሀገሩ ሁኔታ እንዲሁም  ስለ ዲን ስለ መንሀጅሽ ስለ ዒልም የምትማሪበት ቦታዎችን ማጥናት ( መወቅ) አለብሽ።

ሌላው ልረሳ የማይገባ ነገር ምንድነው 
ትልቅ ሷብር ያስፈልግሻል  ምክንያቱም ሶብር በማጣት የተነሳ ብዙ እህቶች ከስደት መልስ የማይሆነቻው ህወት ውስጥ ገብተው ይሰቀያሉ አሏህ ይጠብቀን እናማ ውዷ እህቴ አዳራ በትዕግሰት ላይ ፅኚ ለሁሉም ነገር ትዕግስት ያስፈልጋል ለዛም ነው ባዚህች ዱኒያ ለይ  ትዕግስትን እኩል የምሆነው ነገር የሌላው ፣አሏህም የታጋሾችን  ደረጃ ከፍ ያደረገው።

قُلْ يَا عِبَادِ الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۗ وَأَرْضُ اللَّهِ وَاسِعَةٌ ۗ إِنَّمَا يُوَفَّى الصَّابِرُونَ أَجْرَهُم بِغَيْرِ حِسَابٍ


(ጌታችሁ) «እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ለነዚያ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው፡የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምትነው» (ይላል) በላቸው፡፡

ጣንካራ እና ጀግና ሁኚ  አየሩ ሲቀያየርብሽ ከሱ ጋ አንቺም አብረሽው አትቀያየሪ በአቋምሽ ላይ ፅኑ ሁኚ በረከሏሁ ፊኪ።

ዋናው ሀሰብሽና ጭንቀትሽ ሊሆን የሚገባው የዲንሽ ና የመንሓጅሽ ጉደይ ሊሆን ይገባል ሌላው ግን ሁሉም ግዜው እና ቀኑን ጠብቆ ይመጣልሻል ኢንሻ አሏህ!!

✍️ቢንትሙሀመድ
ህይወት ከባድ ብትሆንም ያሰብሺዉ ባይሳካም እወቂ  ነገ ዉብ ይሆናል በፍፁም ተስፍ እንዳትቆርጭ !!

🍁
ወላሒ ከእናንተ በመፈጠሬ አዝናለሁ።

➪አሏህ ሒዲያ ይስጣችሁ ሌላ ምን ይባላልሀ!!


t.me/nuredinal_arebi
☞ ትዳር ዉስጥ መቻቻል መተሳሰብ ከሌለ ዘላቂነት የለም። መቻቻል መተሳሰብ ካለ የማይዘልቅበት ምክንያት የለም። so መቻቻል እና መተሳሰብ ሁለየ ሊሰመርባቸዉ የሚገቡ ነጥብ ናቸዉ። 🍁
ለፈገግታ ነዉ...

እኔ ትኩረት ስጥቼ የምጠባበቃቸዉ ነገሮች ቢኖር የምግብ ስዓቴ እና የእንቅልፍ ስዓቴ ነዉ። ከራስ በላይ ንፍስ አሉ ህእ¡¡
«ገንዘብ አላት ብሎ ፥ መልከ-ጥፉ ማግባት፣
ገንዘቡም ያልቅና ፥ ሁለተኛ ጥፋት።»

🍁ይላል የወሎ ሰው ተረት! እ¡

✍️ከማ ከተበት t.me/https_Asselfya
መሆን ያለበት ነገር ሁሉ ይሆናል። ኖ መጨናነቅ ፈታ ብቻ!!
🍁ሴት መቀላቀል፣ መጨበጥ፣ ያለዉ አደጋ !!

🎙ሸይኽ አወል حفظه الله
🍁 በሶሻል ሚድያ ላይ ያለተፈቀደ ሰዉ ላይ ማፍጠጥ ያለዉ አደጋ......!!

🎙ሸይኽ አወል حفظه الله
በፎቶ ተያይቶ መጋባት  «ትልቂቱን ሴት ቆንጆ ያደርጋታል»ወንዱንም ከዛሊክ እናም ኺያና አይጠፋውም።
✍️ منقول
🍁 የስልክ እይታ ጉድ........

አላህ ይጠብቀዎት ያ ሸይኽ አወል
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝ኢስላማዊ ስርዓቶችና መልካም ስነ ምግባሮች❞ « ክፍል  ⓵ » ↷የቤት  አገባብና አወጣጥ ስርዓቶች↶ ⓵⇝የቤቱን ሰዉ ማስፈቀድ፦ አንድ ሰዉ የራሱ ያልሆነ ቤት ከመግባቱ በፊት  ማስፈቀድ ግደታ ሲሆን  የራሱ ቤት ሲገባም  ቢያስፈቅድ መልካም ነዉ። { یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ لَا تَدۡخُلُوا۟ بُیُوتًا غَیۡرَ بُیُوتِكُمۡ…
ኢስላማዊ ስርዓቶችና ስነ ምግባሮች❞
 


« ክፍል  ⓶»

🍁የአመጋገብ ስርዓቶች

➀« ከመብላት በፊት ቢስሚላህ ማለትዑመር ኢብን አቢ ሰለማህ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛۡ ﷺእንዲህ ብለዋል  ቢስሚላህ በል፣በቀኝ እጂህ ብላ፣ከፊት ለፊት በኩል ብላ ።

ዓኢሻ ባስተለፉት  ሀዲስ ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል"ስትበሉ ቢስሚላህ በሉ በመጀመሪያ ላይ ከረሳችሁ  ስታስታዉሱ "ቢስሚላሂ ፊ አወሊሂ ወአኺሪሂ(መጀመሪያዉም መጨረሻዉም በአላህ ስም ይሁን)በሉ።

➁« በቀኝ እጂ መብላት፦ ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል "ስትበሉ በቀኝ እጃችሁ ብሉ፣ስትጠጡም በቀኝ እጃችሁ ጠጡ ሸይጧን የሚበላዉም የሚጠጣዉም በግራ እጁ ነዉ።

አንዳድ ሰዎች ግራም እንደ ቀኝ እጂ ነወለ ወይም ቀኝ እጂ ሌላ ስራ ይዟል በሚልና በመሳሰሊ ደካማ ምክንያቶች በግራ እጃቸዉ ሲመገቡ ይስተዋላል። ይህ ችልተኝነት  በዚህ ርዕስ ላይ አደገኛ ነዉ። ምክንያቱም አንደኛ ነብዩ ﷺ በግራ መመገብ የሸይጧን ተግባር መሆኑን በመግለፀ በቀኝ እንድንበላ በትዕዛዝ መልክ ተናግረዋል።የእርሳቸዉ ትዕዛዝ መፈፀም ደግሞ ግደታ ነዉ። ሁለተኛ ነብዩ ﷺ አንድን ሰዉ በግራ ሲበላ አይተዉት  በቀኝ እንድበላ ቢያዙትም  እሱ ግን በመኩራራት "አልችልም"አላቸዉ በዚህ ግዜ ነብዩ ﷺ" አትቻል" ብለዉ ረገሙት! ወድያዉኑ እጁ ሺባ ሆኖ ምግብ ወደ አፎ ማቅረብ አቃተዉ።ይህ ሀድስ የሚያስረዳዉ በዚህም ሆነ በሌላ ርዕሶች ላይ ነብዩን መቃረን አደገኛ መሆኑን ነዉ።

➂« ከፊት ካለዉ እያነሱ መብላት፦ከላይ ባሳለፍነዉ ሀዲስ ነብዩﷺከፊት ለፊትህ ብላ ብለዋል።

➃« ከመብላት በፊትና ከተበላ በኋላ እጅን መታጠብ፦ከነብዩﷺ እንደተዘገበዉ "የምግብ በረከት  ከመብላት በፊት ከተበላ በኋላ መታጠብ ነዉ። አቡ ሑረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩﷺ እንዲህ ብለዋል"እጁ ላይ ቅባት እያለ ሳይታጠብ በመተኛቱ አንዳች ነገር ቢነካዉ እራሱንጂ እንዳይወቅስ።

➄ «ተደግፎ አለመብላት፦ ነብዩﷺእኔ ተደግፌ አልበላም ብለዋል።

➅«በሆድ ተኝቶ አለመመገብ፦ከኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፉት ነብዩﷺ አስካሪ  መጠጥ የሚጠጣበት ማዕድ ላይ ተጥዶ መብላትና በሆድ ተኝቶ መመገብ ከልክለዋል።

➆« ከሳህን ዳር ዳር መመገብነብዩﷺእንዲህ ብለዋል "ከሳፍ ዳር ዳር ብሉ ከመሀል አትብሉ በረከት የሚወርደዉ መሐሉ ላይ ነዉ።

በወርቅ ወይም በብር ሳህን አለመብላት፦ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል ከወርቅ እና ከብር ኩባያ እንዳትጠጡ በሳህኑም አትብሉ።

➈« በህብረት መብላት ነብዩﷺእንዲህ ብለዋል ምግባችሁ ላይ ተሰባሰቡ የአላህንም ስም ጥሩበት ይባርክላችኋል። ሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል"አንድ ሰዉ ምግብ ለሁለት ይበቃል።የሁለት ሰዉ ምግብ ለአራት ይበቃል የአራት ሰዉ ምግብ ለስምንት ይበቃል።

➉« በሶስት ጣት መብላት፦ካዕብ ኢብኑ ማሊክ እንዳስተላለፉት ነብዩ ﷺበሶስት ጣታቸዉ ይበሉ ነበር።

✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል◍◍◍◍◍◍◍

📝أم عثيمين الجامية

⇘⇩⇘⇩⇘⇩⇘⇩⇘⇩⇘⇩⇘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1