💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ኒቃብ (አይነ ርግብ) መልበስ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነው
~
ብዙ ክርስቲያኖች የሙስሊም ሴቶችን አለባበስ (በተለይም ኒቃብን) የዐረብ ባህል እያሉ ሲተቹ ይሰማሉ። በመሰረቱ የፈረንጅ ባህል ተከትለው ሴቶች ከሚራቆቱበት ባህል የዐረብ ባህል ቢሆን እንኳ ግብረ ገብነትን የሚጠቁመው አለባበስ የተሻለ ስርአት ያለው እንደሆነ ግልፅ ነው። ዛሬ የማርያም ምስል ነው ብለው ክርስቲያኖች በሚገልፁት ምስል ላይ ያለው አለባበስ ሙስሊሞች ዘንድ እንጂ ክርስቲያኖች ዘንድ የለም። ለምን የሚለውን ክርስቲያኖች ራሳቸውን ቢጠይቁ መልካም ነው።
ከአለባበስ ጋር ተያይዞ ሙስሊሞች የሚያራምዷቸው መርሆዎች - ፊት መሸፈንን ጨምሮ - በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ ክርስቲያኖች ሊያውቁ ይገባል። ብዙ ክርስቲያኖች ለመፅሀፋቸው ባይተዋር ስለሆኑ ጥቂት ምሳሌዎችን እጠቅሳለሁ፦

1- በኢስላም በሴት የሚመሳሰል ወንድ እና በወንድ የምትመሳሰል ሴት የተረገሙ ናቸው። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል?
"ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ። ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።" [ኦሪት ዘዳግም 22፥5]

2- ሴት ፀጉሯን እንድትሸፍን ኢስላም በጥብቅ ያዛል። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል? ይሄውና :- "ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።" [1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 6]

3- ሴት ፊቷን መሸፈኗ በኢስላም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሐቅ ነው። በመፅሀፍ ቅዱስስ የለም? በሚገባ አለ። ይሄውና፦

* "ርብቃም ዓይኖችዋን አቀናች፥ ይስሐቅንም አየች፥ ከግመልም ወረደች። ሎሌውንም፦ ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው? አለችው። ሎሌውም፦ እርሱ ጌታዬ ነው አላት እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ
#ተከናነበች።" [ዘፍጥረት 24፣ 64- 65]

* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭሽን እንደተከፈለ ሮማን ናቸው።" [መሀልየ ዘሰለሞን 6፡7]
ልብ በሉ! አይነ ርግብ ማለት ኒቃብ ወይም የፊት መሸፈኛ ነው።

* "ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ መቱኝ፥ አቆሰሉኝም ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።" መሀልየ ዘሠለሞን 5፡6]

* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ አይኖችሽ እንደርግብ ናቸው።" [መሀልየ ዘሠለሞን 4፡1]

ስለዚህ ሙስሊም ሴቶች እየተገበሩት ያሉት በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝን እውነት ነው ማለት ነው። ለምንድነው ታዲያ ይሄ ጉዳይ ክርስቲያኖችን የሚያበሳጨው? ከሙስሊም ሴቶች ጎን መቆም ሲገባ ጭራሽ ማንገላታትና ከትምህርት ገበታ ማራቅ ፈፅሞ የማይገባ ነውረኛ ተግባር ነው።
ደግሞም እወቁ! ብዙ ጭቆናዎች በሂደት እንደተቀየሩት ይሄም ያለ ጥርጥር ዛሬ ወይም ነገ ይቀየራል። ለትውልድ የሚቀረው የናንተ የጭቆና ታሪክ ነው። በታሪክ ጥቁር መዝገብ ላይ ስማችሁ እንዲቀር ነው የምትፈልጉት? ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት።

* ባያያዝኩት ምስል ላይ ፊታቸውን ሸፍነው የሚታዩት ሙስሊሞች አይደሉም። ይልቁንም አይሁዶች ናቸው። የሙስሊም ሲሆን ሁሉ ነገር ለሚያስጨንቃቸው አካላት ማስታገሻ ይሆናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
⭕️አጥልም ኒቃቧን‼️
〰➖〰➖〰➖〰

   አጥልም ኒቃባን፣
የሷነቷን ክበር የመገለጫዋን፣
የሀቁን ጓዳና ኢስላም ማሳያዋን፣


መማር አያግዳት አንተን ምን ጨነቀህ፣
በግልፅ ያስታውቃል የኢስላም ጥላቻህ፣

የኒቃባ ጀግና ፈፁም ተስፋ አትቆርጥም፣
አውልቂ ስላልካት ትምህርትን አትጠላም፣

ገና ትሰቅላለች ከድግሪ እስከማስተር፣
የኒቃቧ ጀግና አላት ድንቅ ታምር፣
ግና ስለገባህ ብዙ እደምሰራ፣
ልትሰራ ተነሳህ የጥላቻ ስራ፣

ገና ትበራለች ገና ታፈራለች፣
ለሀገር ልትውልድ ፊሬ ትሆናለች፣
ተምራ የምጠቅም የኒቃብ ጀግና ነች፣


ምን አደረገችህ አልሰነፈችብህ፣
አንደኛ በመወጣት ከኦል ያዘችብህ፣
ጀግንነቷን አይተህ ጥላቻ አደረብህ፣

ይቆጭሀል እንጂ ግና ትደምቃለች፣
በኒቃብ ተውባ ዛሬም ትማራለች፣
ፍትህ ይገባቸው ለእኖር
መስሊሞች፣
እንማር ለሚሉ ጀግና ተማሪወች፣


  âœď¸á‰ áŠ á‰Ą ዑበይዳህ ሶላሁድን


➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
♻️ሰላም ለሙተነቂቦች!

⇛ሰላም ለ ጉንችሬ ሙስሊም ተማሪዎች፣ ሰላም አላህ ይህን አለባበስ ግዴታ አድርጎብናል ብላችሁ ለምትለብሱ ሁሉ፣ ሰላም ወደ አምላካችሁ ለመቃረብ ኒቃብን ለምትለብሱ ሁሉ፣ሰላም የአላህን ዉዴታ ለማግኘት ደፋ ቀና ለምትሉ ሁሉ፣ ሰላም ፊትናዎችን ተቋቁማችሁ በፅናት ለዘለቃችሁ ሁሉ…

⇛ሰላም ለመልካም የአላህ ባሮች ሁሉ፣
አላህ ያጽናችሁ። ሰላማችሁ ይብዛ
⊙_ t.me/AbuSufiyan_Albenan
ይድረስ ለት/ት ሚኒስቴር
Daru tewhid
ት/ት ሚንስቴር ላይ ሚያስቸግሩ ወንበዴዎች ! ታፋ እያየህ አትበድ። ሚኒስከርት አድርጋ ስትገባ ምንም ካላልክ ? የኛ እህቶች ተሸፍነን አገራችንን እናገልግል ሲሉ በቃ አትገግም ! እሄ የሸይጣንን አጀንዳ ለማራመድህ ሀገርህን እንደማትወድ፣ ሀገር አፍራሽ ለመሆንህ በቂ ማስረጃ ነው ! ......

🎙በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ

https://t.me/Darutewhide
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለመጅሊስ!
~
ሰሞንኛውን የጉንችሬ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን የመብት ረገጣ ተከትሎ አንዳንዶች መጅሊሱ በኒቃብ ጉዳይ ላይ ሙስተሐብ ነው፣ ዋጂብ ነው፣ ... በሚለው ላይ ፈትዋ እንዲያወጣ እየጠየቁ ነው። እንደማጠናከሪያም ኒቃብ ከልክለዋል ያሏቸውን የሙስሊም ሃገራት እያጣቀሱ ነው። ይሄ እጅግ ቆ^ሻ ^ሻ የሆነ አካሄድ ነው። ሲጀመር እከሌ አገር ተከልክሏል ብሎ ማጣቀስ ለኢስላም ጠሎች ድንጋይ ማቀበል እንጂ ቁም ነገር ሆኖ የሚጠቀስ አይደለም። እጅግ በርካታ ሙስሊም ያልሆኑ ሃገራት እንደማይከለክሉ እየታወቀ ይህንን እያጣቀሱ ከእህቶቻችን ጎን መቆም ሲገባ እንደ ቱኒዚያ ባሉ ሃገራት ፀረ ኢስላም የፖለቲካ ሃይሎች የሚፈጥሩትን ጫና እየጠቀሱ ለበዳዮች ድንጋይ ማቀበል ወይ እንቅ^ልፋምነት ነው፤ ካልሆነ ግን ብል ^ግና ነው።
ለማንኛውም መጅሊሱም ሆነ ሌላ አካል በዚህ ጉዳይ ላይ የሚጠበቅበት ከግፉኣን ጎን መቆም ብቻ ነው። ጉዳዩ የፈትዋ ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ የመብት ጉዳይ ነው። ያያያዝኳቸውን ፎቶዎች ተመልከቱ። የትምህርት ቤት ቅፅር ግቢ ውስጥ ነው ይህ እየሆነ ያለው። ይህንን እያየ ፊት መሸፈን ዋጂብ ነው ሱና የሚል አካል ካለ ሲበዛ ሙغፈል ነው።
ደግሞ ይታወቅ። ማንም ቢሆን ግለሰብም ይሁን ተቋም አስገዳጅ ፈትዋ ሊያወጣ አይችልም። ቡድናዊ ፍላጎትን የተከተለ፣ ጠላትን የሚያስደስት ፈትዋ በማውጣት በእህቶቻችን ህይወት ላይ ከመቀለድ ባለፈ ራሱን ነው የሚያቀለው። ፈፅሞ የመብት ጥያቄ እና የፈትዋ ርእሶችን ማደበላለቅ አይገባም። ችግሩን መፍታት ባትችሉ እንኳ አጉል ፈትዋ ከምታወጡ ጉዳዩን በዝምታ እለፉት። ኢንሻአላህ ዛሬ ወይም ነጋ መብቱን የሚያስከብር ትውልድ ይመጣል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
ወላሒ ጥግ የደረሰ ጥላቻ እና ምቀኝነት አላቸው።
=============

👉የጉንችሬ ሙሰሊም ተማሪዎች ኒቃብ የሚለብሱ ከሆነ እኛም ነጠላ ለበሰን እንማራለን አሉ......ድንዙዛን ናችሁ እንጅኮ እኛ መች አትልበሱ ብለን እናውቃለን ብትሸፋፈኑማ መልካም ነበር.... ሁሌም ልበሱ እኛ የማይመቸን ራቁታችሁን ስትሄዱ ነው ።

መሸፈን ለሸይጧን አይመቸውም ቢሸፈንም ለምቀኝነት ነው እንጅ ስትሰክሩ ታወልቁታላችሁ።

ሰካራሞች አይደላችሁ እንደ በእምነታችሁ መች ትፀናላችሁና ነው።

👉መጥፎ ነገሮች ሁሉ የናንተ መገለጫወች ናቸውኮ..አታውቁም እንዴ!!

✅ እኛ ሙስሊሞች ነን እንደናንተ የቀልድ እምነት የላግጣ እምነት የምቀኝነት እምነት የለንም።


http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
✍️ውዴ ጠንካራ አይበገሬ ሁኚ!!
〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖


የነፈሰው ሁላ አይወዝውዝሽ
ባጉሎ ነፋስ የምትበር ናፋ አትሁኚ
ኮስታራ የክብራ የድኗ የቤቷ ፍትሃዊ ወታደር ሁኚ!!

ውዷ ሳትታገይ አትሸነፊ!!

ለሽንፈት ቦታ እና ጆሮ አትስጪ
ከቦታው ሸርተት ከአላማሽ ዝቅ ልያደርግሽ የሚመክርን ነብር ሁኚበት ላ ላ ድመት አላልኩም ነብር !!

አንዳንዴ ነብር መሳይ ድመቶች ስላሉ ነው!!

በቀደር እመኝ ምንም ነገር አይከሰትም አላህ ቀድሞ የፃፈው እና ያወቀው ቢሆን እንጂ ምንም ነገር አይደርስብሽም.ከደረሰብሽም " አልሀምዱሊላህ " ብለሽ ከልብሽ ፈገግ ብለሽ ያን ልፍስፍስ ሸይጧን አንጀቱን አሳርሪው ሶብርሽን ትግስትሽን ሊሰልብሽ የሚሰለጥን የተረገመ ሸይጧን በእጥፍ አሳርሪውና አሸናፊ ሁኚ ጀባሩ ዘንድ ውድ ትሆኚ ዘንድ!!

ጀግና ልጅ ታሳድጊ እና ጅግና ፍሬወችን ትተኪ ዘንድ ጀግና ሁኚ !!

ለሁሉ አታጎንብሽ!ዱንያ የጦር ሜዳ ናት ተማም?!!

منقول
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
#የ_ሱ_ና_ዋ__!!
------------------------
አንችኑ ብዬ እንጅ፤
ሌሎች ሲገደሩ ከኋላ ያስቀረኝ፡
አንችን መርጨ እንጅ፤
ይህን ያክል አመት ብቻየን ያኖረኝ፡
አንችን ፈልጌ እንጅ፤
ስጠበስ የኖርኩት እሳቱ ሲወረኝ፡
ተርፎኝ ያስቀመጥኩት ነፍስ መች ነበረኝ፡
                              
ነፍሴ አንችን ፈልጎ፤
አይንሽን ለማየት አይኔ እንዲህ ቢሰጋ፡
ለብዙ ዘመናት፤
ሳላገኝሽ ቀረሁ ባካል ባይነስጋ፡
የሆንኩትን እንጃ፤
አንችን እያሰበ ልቤ መች ረጋ፡
-------------------------------------------
የናፍቆቴ ሲበዛ፤
መምጫሽ ሲርቅብኝ ሐሳቤ በርክቶ ቢበተንብኝም፡
ዛሬ ላይ ሆኜ እንኳን፤
ነይ ከማለት ዉጭ የምልሽ የለኝም፡
--------------------------------------------
#ለማንኛውም__!!

በፍቅር አብበሸ፤
በኒቃብ አጊጠሽ እኔኑ መስክሪ፡
እኔ የምመኘው፤
አንችን ማገኘት ነዉ አደራ እንዳቀሪ፡
-------------------------------------------------
በሩቅ የሚያስታውቅ የመንሀጅ ፋናዋ፡
ተግባሯ እሚገልፀው የተውሒድ ቃናዋ፡
አንችን ብሏል ልቤ አንችን የሱናዋ፡
------------------------------------------------
በኑረዲን አል አረቢ (ከገጠር)2014
                                    
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🎈ተዉሒድ ሲገባህ እንድህ ነዉ የባጢል ሰዎች አጥበህ የምታሰጣ......!!

🏷ተዉሒድ ይቅደም ሺርክ ይዉደም!!

https://t.me/https_Asselefya1
‏قال تعالى : ﴿فَلَمّا نَسوا ما ذُكِّروا بِهِ أَنجَينَا الَّذينَ يَنهَونَ عَنِ السّوءِ ď´ž

وهكذا سنة الله في عباده أن العقوبة إذا نزلت نجا منها الآمرون بالمعروف والناهون عن المنكر.

تفسير السعدي