💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ቁርአን ጁዝ ➁➇
الشيخ علي الحذيفي
❝ቁርአን በረመዷን አብረንእናኽትም!❞


☞ጁዝ  ሃያ ስምንት

▪الليلة(28)  رمضان

🎙الشيخ علي الحذيفي حفظه الله


ከሱረቱል ሙጃደላህ አንቀፀ
1 እስከ ሱረቱል ተሕሪም አንቀፀ 12

   ⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘
t.me/https_Asselefya1/12025
☞እንዲህም አይነት ደስታ አለ
~
ደግ ልብ በሌሎች ደስታ ይደሰታል። በሌሎች ማዘን ያዝናል። ምቀኛና ክፉ ልብ ደግሞ በሌሎች ደስታ ይከፋል። በሌሎች መጎዳት ይፈነጥዛል። "ምቀኛ ከራሱ ማግኘት ይልቅ የጓደኛው ማጣት ነው የሚያስደስተው" ይባል የለ?
በወገኖቹ ደስታ የሚረካ፣ በሃዘናቸው የሚያዝን ሰው ምንኛ የታደለ ነው?! ከወገኖቹ ልብ ውስጥ ደስታን ለማስገባት የሚተጋ አማኝ ምንኛ የላቀ ነው?! ታላቁ ታቢዒይ ሙሐመድ ብኑል ሙንከዲር - ረሒመሁላህ - "ከዱንያ ሁሉ የሚያስደስትህ ምንድነው?" ተብለው ሲጠየቁ "ሙእሚንን ማስደሰት'' ብለው ነበር የመለሱት። [ቀዷኡል ሐዋኢጅ፣ ኢብኑ አቢ ዱንያ፡ 33]

ከደጋጎቹ_ቀዬ

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
☞የሞራል ከፍታ
~
የሆነ ሰው ሰልማን (አልፋሪሲይ) - ረዲየላሁ ዐንሁ - ዘንድ ገባ። እሳቸው ሊጥ እያቦኩ ነበር።

* "ምንድነው ይሄ?" አላቸው። እንዴት ይህንን ትሰራለህ ማለቱ ነው።
ሰልማን በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉት፡-
"አገልጋያችንን ለሆነ ስራ ልከነዋል። ሁለት ስራ ልንደርብበት ደግሞ አልፈለግንም።" [ሒልየቱል አውሊያእ፡ 1/2ዐ1]

ከደጋጎቹ_ቀዬ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
✍ ጉደኛው ግመል .... የወሎ ትውስታ ክፍል 2 !!

☞ ይገርማል እንደ ሀገሩም የሰው ሁኔታ ልማድ እና ወግ ይለያያል ወገን እኔማ ብዙ የማላውቃቸውን ነገራቶች የተማርኩበት ግዜ ነበር ።

☞ የሚገርም ነገር ላጫውታችሁ ለፈገግታ ያክል እህት ወንድሞች ፈገግታ ሱና ነው ።

☞ በሰሜን ወሎ #ውርጌሳ ከተማ ላይ ከከተማይቱ ከወደ ላይ በኩል ትልቅ ተራራ አለና ወደዛ መሄድ ከጀልኩና ከአንድ ሰው ጋር ሄድን ሓቂቃ በጣም ይገርማል መንገዱ !!

☞ተራራውን ከታች ሁናችሁ ስታዩት በቀላል መድረስ የሚቻል ይመስላል ግን ጠጋ ብለን ስናየው በጣም ከባድ ነበር

☞ እንደምንም ብለን ግማሹ አከባቢ ደርሰን ትንሽ አረፍ ብለን ወደ ታች ተመለስን ግን ጉዳዩ ስንመለስ ነበር ።

☞ ስንመለስ እየመሸ ነበርና ጫካም ስለነበር ቶለ ቶለ እያልን ቁልቁለቱን እየወረድን ነው ድንገት ግን መንገዳችንን የሆነ ነገር ዘጋብን ምን አትሉኝም ..??

☞ ትልቅ ወንድ ግመል መንገዳችንን ዝግት በየት እንለፍ ?? መንገድ እንዳንቀይርም ከጎን እና ጎን ቤት አለ እኛም #ሼም ያዘን እና ዝም አልን አሳፍሮን ድንጋይ ብንወረውርም አይሰማም ግመሉ ..!!

☞ያለን አማራጭ ቢኖር በድፍረት ማለፍ ብቻ ነበር ከዛም እንደምንም ብለን እየፈራንም ቢሆን አለፍን ግመል ሳይ ያቺ ክስተት ትዝ ትለኛለች ።

☞ የአከባቢውን ባህል እና ወግ ያለመደ ሰው አስቸጋሪ ነው ወገን !!

✍ አቡ ዑሰይሚን

t.me/abuUseyminabdurehman
🎈ሰባት የኢድ አልፈጥር በአል ሱናዎች
〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰

①) ተክቢራ፦ የመጨረሻው የረመዷን ቀን ፀሀይ ከጠለቀችበት ጊዜ ጀምሮ ኢማም ለሶላት እስኪነሳበት ጊዜ ድረስ ማለት ይችላል።

②) ዘካተል ፊጥር ማውጣት፦ ይህም ኢድ ሁለት ቀን አለው ሲባል ጀምሮ ሶላት ተሰግዶ ከመጠናቀቁ በፊት መሆን አለበት።

③) ተምር መብላት፦ ይህም ለኢድ ሶላት ከመውጣታችን በፊት ሲሆን በነጠላ ቁጥር መብላት የተወደደ ነው።

④) ያማረ ልብስ መልበስና ሽቶ፦ ይህ ለወንዶች ሲሆን ሴቶች ግን ሽቶና የሚስብ ልብስ ልትጠነቀቅ ይገባል።

⑤) ገላን መታጠብ፦ ኢብኑ ኡመር ይታጠብ ነበር። ኢማሙ ነወውይ የተወደደ ተግባር በመሆኑ ስምምነት አለ ብሏል።

⑥) መንገድ መቀየር፦ ወደ ኢድ የሄደበት መንገድ ትተን በሌላ መንገድ ወደ ቤት መመለስ። መልእክተኛው ይቀይሩ እንደነበር ተዘግቧልና።

⑦) እንኳን አደረሳችሁ መባባል፦ ሶሀባዎች እርስ በርስ ሲገናኙ የእንኳን አደረሰህ መልእክት ይለዋወጡ ነበር። የተወደደ የሚሆነው ሶላት ከተሰገደ በኋላ ጀምሮ ባለው ጊዜ ነው።

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/10557
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/10557
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቢያንስ ለመስጂዶች ክብር ይኑረን እንጂ
~
መስጂዶች የተከበሩ የአላህ ቤቶች ናቸው። ለዒባዳ የተገነቡ ክቡር ስፍራዎችን የመቃሚያ ቦታ ማድረግ የሚሰቀጥጥ ተግባር ነው። ከጥፋት መታቀብ ቢያቅተን ቢያንስ ለጥፋት ቦታ ልንመርጥ ይገባል።
ወገናችንን ከዚህ መርዝ ቅጠል ይገላግለው። ለዚህ ሁሉ ህዝብ በዚህ ቅጠል ሱስ መለከፍ ቀዳሚ ተጠያቂዎች ዱዓቶችና መሻይኾች ናቸው። ለወገኑ ከልቡ የሚቆረቆር እውነተኛ አስተማሪ ማለት መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ ተሸንፎ ህዝብን የሚያስደስት ፈትዋ የሚሰጥ ሳይሆን የአላህ ፍራቻን አስቀድሞ ያለውን መራር እውነታ የሚጋፈጥ ነው። የወገኑ ጉዳት የሚያመው ሁሉ! በሚችለው መድረክ ሁሉ ከዚህ መርዛማ ቅጠል ሰዎችን ሊያስጠነቅቅ ይገባል። በዚህ ቅጠል የተለከፉ ወገኖችን ከሱስ ማውጣት ቢያቅተን እንኳ ቢያንስ ልጆቻቸውን በሚጠብቁበት መልኩ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ብናደርግ ቀላል ስኬት አይደለም።
~
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
تلاوة جميلة رائعة و رهيــــــــــــبة !!! (سعد الغامدي )
esmailtube
اللهم اجعل القرآن ربيع قلبي
ونور صدري وجلاء حزني
وذهاب همي وغمي ..
يارب
እንባህን ለመደበቅ ስትል
ልትስቅ ትችላለህ እንዲሁም ደህና መሆንህን
ለማሳየት ፈገግ ልትልም ትችላለህ‥
⇘
ነገር ግን ውስጥ አዋቂ የሆነ ምትደብቀውንና
ግልፅ የምታወጣውን የሚያውቅ ጌታ አለህና
ጭንቀትህንና ሀዘንህን ለጌታህ ንገረው

( إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ )
" እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም
ሁሉ ያውቃልና ፡፡"
[አል-አዕላ 7]

𝐓𝐞~ t.me/selahudin_Islamic_knowlages
ቁርአን ጁዝ ➁➈
الشيخ علي الحذيفي
❝ቁርአን በረመዷን አብረንእናኽትም!❞


☞ጁዝ  ሃያ ዘጠኝ

▪الليلة(28)  رمضان

🎙الشيخ علي الحذيفي حفظه الله


ከሱረቱል ተህሪም አንቀፀ
13 እስከ ሱረቱል ሙርሰላት አንቀፀ 50

   ⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘
t.me/https_Asselefya1/12046