💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ቢስሚላሂ ረህማኒሮሂም
••••••••••••••••••••••••

✳️ በተወሱል ርዕስ የሚነሱ ብዢታዎችና
እርምቶቻቸው፦
🔺ሱና ተከታዮችን የሚፃረሩ አንጃዎች
በተወሱል ዙሪያ የተሳሳተ አመለካከታቸውን
ለማጠነካከርና የያዙትን ሀሰት
እምነት ሙስሊሙ ማህበረሰብ
ዘንድ ጥሩ እይታ እንዲኖረው
ሲሉ የሚያነሷቸው ብዢታዎች
አሉ።
ይሁንና የሚያመጧቸው ማጭበርበሪያዎች
ከሁለት ነገሮች አይዘልም።
°°°°°°°°•••••••°°°°°°°°
አንደኛ፦ የዘገባ መንገዳቸው የደከመና
የተቀጠፉ ሃዲሶችን ለአቋማቸው
ማስረጃነት መጠቀም ሲሆን ይህ ግን
ትክክል ያልሆኑ ሀዲሶች መሆናቸውን
በማወቅ ብቻ ያበቃለታል።
--------------------

ከሚጠቅሷቸው ትክክል ያልሆኑ ሀዲሶች፦
🔺1.<< በማዕረጌ አመካኝታችሁ አላህን ለምኑ
አላህ ዘንድ ማዕረጌ የላቀ ነውና።>>አላህን
ስትለምኑበክብሬ ለምኑት ክብሬ አላህ ዘንድ
ትልቅ ነው።>> 👈ይህ አንድም አሊም ያልዘገበውና በየትኛውም የሃዲስ መፅሀፍ
ተፅፎ የማይገኝ የተቀጠፈ ወሬ ነው።✅
••••••••°°°°°°°°°°°°°°°•••••••••••••••••
🔺2.<< ነገሮች ሲከብዷችሁ በቀብር ሰዎች
ታገዙ >> የቀብር ሰዎች ከጭንቅ እንዲያወጧችሁ ተማፀኑ>> 👈ይህም በነቢዩ ዓለይሂ አሶላቱ ወሰላም የተቀጠፈ ሀዲስ እንደሆነ
ኡለማዎች በሙሉ ተስማምተውበታል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
3.<< ለዲንጋይ እንኳን ጥሩን ግምት ብታሳድሩ
ይጠቅማችኋል>>👈 ይህ ሀዲስ ውሼት ከመሆኑም በላይ እስልምናን የሚፃረር
ሙሽሪኮች የቀጠፉት ነው።
••••••••••••••••••••••••••••••°°°°°
🔺4.<< አደም ሃጢአትንከተዳፈረ በኋላ
እንዲ አለ "ጌታዬ ሆይ! በሙሀመድ
መብት ይሁንብህ እንዲትምረኝ እለምንሃለሁ"
አላህም "አደም ሆይ!
ሙሀመድን ገና ሳልፈጥረው እንዴት አወቅከው?ሲለው ፈጥረኸኝ ነፍስ ስትዘራብኝ ራሴን ከፍ ሳደርግ የአርሽ እግር ላይ "ላኢላሃ ኢለሏህ
ሙሀመዱ ረሱሉሏህ" የሚል ፁሁፍ
አነበብኩና ከፍጡራን በጣም የምትወደውን
እንጂ ወደ አንተ ስም እንደማታስጠጋው
ተረዳሁ" ሲል አላህም "በል ምሬሀለሁ ለሙሀመዲም ስል እንጂ አልፈጥርህም
ነበር አለው"።👈 ይህም መሰረት የሌለው
የሀሰት ወሬ ነው።
"ለአንተ ስል እንጂ ከዋክብትን አልፈጥርም ነበር " የሚለውም ሀዲስ ተመሳሳይ ነው።

🔺👆እነዚህን መሰል የውሼት ሀዲሶችና
የተቀጠፉ ዘገባዎችን አንድ ሙስሊም ማስረጃ
አድርጎ ሊመረኮዝባቸው ይቅርና ዞር ብሎም
ሊያያቸው አይገባም።✅
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
🔺ሁለተኛ፦ በትክክለኛ ዘገባ ከነቢዩ ሱላላሁ
ዓለይሂ ወሰለም የተላለፉ ሀዲሶች
ቢሆኑም ነገር ግን እንደዚ አይነት
ሰዎች በትክክል ካለመገንዘባቸው
አልፈው የሚጠቁመውን ትርጉም የሚያዛቧቸው
ሀዲሶች ናቸው።
ከነዚህም ውስጥ፦
🔺1. ኡመር ኢብነል ኸጧብ ዝናብ ሲጠፋ
በአባስ አማካኝነት እንዲ በማለት አላህ
እንዲያዘንብላቸው ይለምኑ ነበር "ጌታዬ ሆይ
በነቢዩ አማካኝነት ዝናብን እንለምንህና
ታዘንብልን ነበር አሁን ደሞ በአጎታቸው
ዓባስ አማካኝነት እንለምንሃለን አጠጣን>>
ይዘንብላቸዋል። [ቡኻሪ ዘግቦታል]
👆ይህን ሀዲስ የሚረዱት ኡመር ያደረገው
ተወሱል አላህ ዘንድ ባለው የአባስ ክብር
እንደሆነ ነው። "በአባስ አማካኝነት••••••••••••••በነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም አማካኝነት ••••••••••••••••ማለት በነሱ አረዳድ አላህ ዘንድ ባላቸው ክብር" ማለት ሲሆን
ይህ ግን መቶ በመቶ የተሳሳተ ግንዛቤና
የራቀ ትርጓሜ ነው። ምክንያቱም
ሰሃቦች ዘንድ በነቢዩ አካልም ይሁን
ክብር አማካኝነት አላህን መለመን አይታወቅም።
ሲፈፅሙት የነበረው ተወሱል
ነቢዩ በሂዎት እያሉ ዱዓ እንዲያደርጉላቸው
መጠየቅ ነበር።
ኡመርም ቢሆን እኛ በነብያችን አጎት
አማካኝነት እንለምንሃለን ማለቱ በእርሱና በክብሩ
ማለት ሳይሆን በእርሱ ዱዓአማካኝነት ማለት ነው።

🔺በሰው ወይም በሰው ክብር አላህን መለመን
እነሱ ዘንድ ተፈፃሚ ቢሆን ኖሮ ዑመር ነቢዩን
ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም ትቶ ወደ አባስ ባልመጣ ነበር። ሶሃቦችም ቢሆኑ እንደት ታላቁን ፍጡር ነቢዩን ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም ትተው ዓባስን
ትመርጣለህ? ሲሉ ይቃወሙ ነበር።

🔺ይህን አለማለታቸውና ነቢዩ በሂወት እያሉ
የሚያደርጉት በእርሳቸው ዱዓ ምክንያት
ተወሱል የሚያደርጉ መሆኑ መታወቁ የተፈቀደው
ተወሱል በዱዓ እንጂ በሰውዬው ክብር እንዳልሆነ ግልፅ ይሆናል።✅
በዚህ መሰረት ሀዲሱ በሰዎች ወይም
በክብራቸው አላህን መለመን እንደሚቻል
የሚጠቁምበት ምንም አቅጣጫ እንደሌለው
ግልፅ ይሆናል።
📌قال شيخ الإسلام ابن تيميّة رحمه الله:
♻️ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
【إذا وجد العبد تقصيرا في حق القرابة والأهل والأولاد والجيران والإخوان، فعليه بالدعاء لهم والاستغفار】
✅ የቅርብ ዘመድህ፣ የቤተሰብህ፣ የልጆችህ፣ የጎረቤቶችህና ባጠቃላይ የወንድሞችህ ሀቅ በተገቢው አልተወጣሁም፤ ሚጠበቅብኝን አላደረኩላቸውም ብለህ ካሰብክ ዱአ አድርግላቸው። ከአላህ ዘንድ መሀርታውንም ለምንላቸው።
📚الفتاوى ( ٦٩٧/١١)
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔺የሶላት አርካኖች (ማእዘናቶች) በሰፊው የተብራራበት

《ክፍል 1⃣1⃣》

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
ቢስሚላሂ ረህማኒሮሂም

🍀1ኛ የአመጋገብና የአጠጣጥ ስርዓቶች በጥቂቱ ፡
••••••••••••••••••••••••••••••
🍂🍂አንደኛ ከመብላት በፊት ቢስሚላህ ማለት
ዑመር ኢብን ኸጧብ እንዳስተላለፉት
የአላህ መልዕክተኛ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ብለዋል አንተ ልጅ ቢስሚላህ በል፤
በቀኝ እጅህ ብላ፤ከፊት ለፊትህ በኩል ብላ።
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

•••••••••••••••••••••••••••••
🌿🍂 ዓኢሻ ባስተላለፈችውም ሀዲስ ነቢዩ
እንዲ ብለዋል
🔺"ስትበሉ ቢስሚላህ በሉ
መጀመሪያ ላይ ከረሳችሁ ስታስታውሱ
"ቢስሚላሂ ፊ አወሊሂ ወአኸሪሂ
{መጀመሪያውም መጨረሻውም
በአላህ ስም ይሁን } በሉ"።
{አቡዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል}

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
☘2ኛ. በቀኝ እጅ መብላት፡🍀
ነቢዩ ሰላላሁ አለይ ወሰለም እንዲ ብለዋል
🔺"ስትበሉ በቀኝ እጃችሁ ብሉ፤
ስትጠጡም በቀኝ እጃችሁ ጠጡ
ሸይጧን የሚበላውም የሚጠጣውም
በግራ እጁ ነው።"{ ሙስሊም ዘግቦታል}
________________________

አንዳንድ ሰዎች ግራም እንዴ ቀኝ እጅ ነው
ወይም ቀኝ እጄ ሌላ ስራ ይዟል በሚልና
በመሳሰሉ ደካማ ምክንያቶች በግራ እጃቸው
ሲመገቡ ይስተዋላል። ይህ ችልትኝነት በዚህ
ርዕስ ላይ አደገኛ ነው።

ምክንያቱም 🔺አንደኛ ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
በግራ መመገብ የሼይጧን ተግባር
መሆኑን በመግለፅ በቀኝ እንድንበላ
በትዕዛዝ መልክ ተናግረዋል።
የእርሳቸውን ትዕዛዝ መፈፀም
ደሞ ግደታ ነው።
_________________________
🔺ሁለተኛ ነቢዩን ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
አንድን ሰውበግራ ሲበላ አይተውት
በቀኝ እንድበላ ቢያዙትም እሱ ግን
በመኩራት "አልችልም" አላቸው
በዚህ ጊዜ ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
"አትቻል" ብለው ረገሙት {ሙስሊም ዘግቦታል}
ወዲያውኑ እጁ ሽባ ሆኖ
ምግብ ወደ አፉ ማቅረብ አቃተው።
ይህ ሃዲስ የሚያስረዳው በዚህም ሆነ
በሌላ ርዕስ ነቢዩን መቃረን አደገኛ መሆኑን ነው።
____________________________
✅ ተደግፎ አለመመገብ። "ነቢዩ እኔ ተደግፌ አልበላም" ብለዋል {ቡኻሪ}
____________________
✅ ከሳህን ዳር ዳር መመገብ፡
ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ብለዋል
🔺"ከሳፋ ዳር ዳር ብሉ ከመሀል አትብሉ በረከት የሚወርደው መሀሉ ላይ ነው።"
[አህመድ ዘግቦታል]


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
አብደሏህ ኢብን መስኡድ ረዲየላሁ አንሁ እንዲህ ይላል
"አላህን በማስታወስ ላይ (እንድታስታውስ) የሚያግዝህን እንጅ ጓደኛ አድርገህ እንዳትይዝ።"

ምንጭ አዝሁድ ሊአቢዳውድ126/1

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
سورة الكهف لمصطفى الفرجاني
🔁 سورة الكهف 🔁
🔺ማራኪ የሱረቱል ከህፍ ቂርአት
🎙القارئ مصطفى الفرجاني
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
💢በቲክ ቶክ ለተሸወዱት አጭር ምክር
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
〰〰〰〰〰
🔹You tube
🔹Tik tok
🔹subscribe
🔹ሰበር ዜና
🔘በማለት ጊዜያችሁን አትግደሉ

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💢ብቻ በሀቅ ላይ ሁን የሰዎች ዋይታ አይረብሽህ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

💎قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله:
🔹ሸኽ ሷሊህ አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

【ما دام أنّك على الحق؛ّ فلا يهمّك كلام النّاس والمخذّلين، أمّا إن كنت على الخطأ؛ فتراجع ولو مدحوك، لا تصبر على الخطأ، وتثبت على الخطأ، ولو مدحوك وشجّعوك، لا يغرّك هذا.】
✅በሀቅ ላይ እስካለህ ድረስ፦
🔹ሰዎች ባነተ ላይ ለሚያወሩት ወሬ አያሳስብህ
🔹አንተን ለማዋረድ በሚያረጉት ጥረትም አይግረምህ
🔘በስህተት ላይ ከሆንክ ግን ሰዎች ቢያወዱሱህም እንኳ ቶሎ ተመለስ።
🔺በስህተት ላይ አትፅና
🔺በስህተት ላይ አትዘውትር
🔘ሰዎች ቢያወድሱህና ቢያበረታቱህም እንኳ ከስህተትህ ከመመለስ እንዳይሸነግልህ።
📚شرح فتح المجيد (٢٤/ ربيع الأوّل/ ١٤٣٩)


💢ልብ በል💢
👌መቸም ቢሆን ከሰዎች ምላስ ልትተርፍ አትችልም። እንኳን ተራው አንተ ውዱ ነብያችንም እንኳን አልተረፋም። ሲያወድሱህ ምትነሽጥ ሲወቅሱህ ምትኮስስ ከሆነ ችግሩ ከኑሱ ሳይሆን ካንተው ነው። ሰው የፈለገው ይበል አንተ ግን በስራህ ወደፊት ቀጥል። አላማህ የአላህን ውዴታ እንጂ የሰዎችን ክብርና ምስጋና አይሁን።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔺ዋጂባቱ ሶላትን በሰፊው የተዳሰሰበት
🔺ስጁዱ ሰህው የሚደረገው መቼ ነው
🔺የአላህን የበላይነት የተወሳበት

《ክፍል 1⃣2⃣》

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💢በምላስህ ጉዳይ አላህን ፍራ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

✅ ሱፍያን አስሰውርይ አላህ ይዘንለትና ለጓደኞቹ እንዲህ በማለት ገሰፃቸው።

🔹ሱፍያን አሰውርይ
🔺🔺🔺🔺🔺🔺⤵️⤵️
🔹አንድ ንጉስ ቢኖርና የምትናገሩት ነገር ሁሉ ወደንጉሱ የሚያደርስ ሰው ከናንተ ጋር ቢኖር ንጉሱን የሚያስቀጣና የማይወደው ንግግር ትናገራላችሁን❓አላቸው።

🔹ጓደኞቹም
🔺🔺🔺🔺⤵️⤵️
🔹ኧረ በጭራሽ አንናገርም ብለው መለሱ።

🔹ሱፍያን አስሰውርይ
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺⤵️⤵️
🔹ታዳ ከናንተ ጋር እኮ በግራና በቀኝ ተቀምጠው የምትናገሩትን ሁሉ ፅፈው ወደ አላህ የሚያደርሱ መላኢካዎች እኮ አሉ። ስለዚህ እሱን ከሚያስቆጣና ከማይወደው ንግግር ለምን አትቆጠቡም❓ በማለት መከራቸው።
📚 التبصرة لابن الجوزي( 2/237 )

↪️አላህም በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
【إِذْ يَتَلَقَّى ٱلْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ ٱلْيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ قَعِيدٌ】
🔘ሁለቱ ቃል ተቀባዮች (መላእክት) ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡

【مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ】
🔘አንድ ሰው ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላኢካዎች) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡
📚 سورة "ق" (18-17) ابو عبدالله https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔺ስለ ተሸሁድ በሰፊው የተብራራበት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔺በውስጡ ብዙ የተውሂድና የፊቅህ እርእሶችን ስተለወሱበት በጥሞና አዳምጡት

《ክፍል 1⃣3⃣》

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

〰〰〰〰〰〰〰〰

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሂስድ ( ቅናት ) (ምቀኝነት)

ሂስድ ➬ በሰው ልጅና በጂኒዎች ላይ ብቻ የሚገኝ በሽታ ነው ።
===

ሂስድ ➬ የአላህን ወሳኔ በመቃወም የሌሎችን እድገትና ስኬት ማየት ካለመፈለግ ከልብ ውስጥ የሚመነጭ ጥላቻ ወለድ በሽታ ነው ።
===

ሂሰድ ➬ በባህሪው በፍጥነት እየተሰፋፋ የሚሄድ አደገኛና አቃጣይ በሽታ ነው ።
===

ሂስድ ➬ ያለበት ሰው የሚፈለገውን ነገር ሁሉ አላህ ቢሰጠውም አይደሰትም ። የእሱ ደስታው የሌሎችን ማጣትና ውድቀት ሲመለከት ብቻ ነው።
===

ሂስድ ➬ ውጤቱ የበሽተኛውን መልካም ስራዎችን ማቃጠል ( ማበላሸት ) ነው ።
#መፍትሄው ሁሌም በኑሮ ፣ በጤና ....ከእኛ በታች ያሉትን በማየትና አላህ በሰጠን በመደሰት ብሎም አላህን በማመስገን ብቻ ነው!!

➹ ቅን እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና➹

አሏህ ውስጣችንን ((ከሂስድና ከንፍቅና)) ያፅዳልን!!
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎የሒጃብ ቀን የሚባል የለም።

☞ የኢስላማዊ አለባበስን አስፈላጊነት ለማስተማር የትኛውንም የአመቱን ቀን መጠቀም ሲቻል አላስፈላጊ ፈጠራ በኢስላም ውስጥ መሰንቀር ተገቢ አይደለም። ለኢስላም መቆርቆር በሸሪዐ ሚዛን እንጂ በመሰለኝ እና በደሳለኝ ሊሆን አይገባም።

☞ደግሞ'ኮ የአንዳንዶቹ የሒጃብ ግንዛቤ ፀጉርን ከመሸፈን የማይዘል ነው። ይቺኑ ቁሪንጣጣ አለባበስ "የሒጃብ ቀን" ብለው ሊያሳዩ ደፋ ቀና ሲሉባት፣ ብዙ ሲያፈሱባት፣ ለገበያ ሲያቀርቧት ያሳዝናሉ።

መንቁል…
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💢አየተል ኩርስይ ከፈርድ ሶላት በኋላ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

【عن أبي أُمامةَ الباهليِّ رضيَ اللهُ عنه قال رسول الله صلى الله عليه وسلم من قرأ آية الكرسي في دبر كل صلاة مكتوبة لم يمنعه من دخول الجنة إلا أن يموت】
(رواه النسائي وصححه الألباني)

✅ አቢ ኡማመተ አልባሂልይ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።
【ግድ ከተደረገበት ፈርድ ሶላት በኋላ አየተል ኩርስይ የሚቀራ ሰው፧ጀነት ለመግባት የሚከለክለው ነገር የለም ሞት ቢሆን እንጂ】
📚ነሳእይ ዘግቦታል ኢማሙ አልባንይ ሶሂህ ብለውታል።

🔺የሀዲሱ መልእክት ባጭሩ🔺
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
👉ከፈርድ ሶላት በኋላ አየተልኩርስይ በሚቀራ ሰውና በጀነት መካከል ያለው ግርዶሽ ሞት ብቻ ነው ማለት ነው። ነገር ግን ይህ ትልቅ ምንዳ የሚረጋገጠው ተውሂድ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። በአላህ ላይ የሚያጋራ ሰው የፈለገ መልካም ስራ ቢሰራ ተቀባይነት አያገኝምና።

🔘አየተል ኩርስይ ከአጭር ትርጉም ጋር
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔸ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْحَىُّ ٱلْقَيُّومُ
🔹አላህ ከእርሱ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡
🔸 لَا تَأْخُذُهُۥ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ
🔹ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡
🔸 لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ
🔹በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ የአላህ ብቻ ነው፡፡
🔸 مَن ذَا ٱلَّذِى يَشْفَعُ عِندَهُۥٓ إِلَّا بِإِذْنِهِۦ
🔹ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?
🔸 يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ
🔹አላህ (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡
🔸 وَلَا يُحِيطُونَ بِشَىْءٍ مِّنْ عِلْمِهِۦٓ إِلَّا بِمَا شَآءَ
🔹በሻውም ነገር ቢሆን እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡
🔸 وَسِعَ كُرْسِيُّهُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ
🔹ኩርስዩን ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡
🔸 وَلَا يَـُٔودُهُۥ حِفْظُهُمَا
🔹ጥበቃቸውንም አያቅተውም፡፡
🔸 وَهُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْعَظِيمُ
🔹እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡

t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Weseteya
Ibnu Munwer
ከኢብኑ ሙነወር ወሳኝ #ሙሐደራዎች

ክፍል ⓫

ርዕስ  â†ˇâ‡Łâ†ś
ወሰጢያ (ሚዛናዊነት)

🎙 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁሏህ
➪➪➪➪➪➪➪➪➪➪
ወሰጥያ ማለት ይህ ነው::
↷⇣↶↷⇣↶↷⇣↶↷⇣↶
ሀቅን ከባጢል ለያይቶ ማህበረሰቡ መረዳት በሚችለው ቋንቋ ብትንትን አድርጎ ማስረዳት እና ለስለስ ማለት ባለብህ ቦታ ላይ መለስለስ
➞➞➞➞➞➞➞➞➞
እያበሸርክ ለደጋግ ባሮቹ አላህ ያዘጋጀውን ፀጋ እየጠቀስክ መቆጣት ባለብህ ቦታ ቆጣ እያልክ የአላህ አሳማሚ ቅጣት እያስታወስክ ልክ ውዱ ነብይ ያደርጉት እንደነበረው ማለት ነው
።
➳➳➳➳➳➳➳➳➳
ወሰጥያ እያሉ አደባብሶ ማለፍ ሰዎች ሀቅና ባጢል ለይተው እንዳያውቁ ወላዋይ እንዲሆኑ ማድረግ ማለት አይደለም!!!
➔➔➔➔➔➔
ወደ አላህ መንገድ እጣራለሁ የሚል ሀቅን ብትንትን አድርጎ በቦታው በማስረጃ ሊያስቀምጥ ባጢልንም እንደ ባጢልነቱ በተንተን አድርጎ በማስረጃ ሰዎች ይጠነቀቁት ዘንዳ ሊያብራራላቸው ተገቢ ነው።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w