💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
قال رسول الله ﷺ : أربع من السعادة

المرأة الصالحة ،
② والمسكن الواسع ،
③ والجار الصالح ،
④ والمركب الهنيء ،


የአላህ መልእክተኛ-ﷺ-እንዲህ ብለዋል

➛አራት ነገሮች የደስታ ምንጭ ናቸው

1-- ሳሊህ ሚስት
2--- ሰፊ መኖሪያ
3--- መልካም ጎረቤት
4--- ምቹ መጓጓዣ


وأربع من الشقاوة

① الجار السوء ،
② والمرأة السوء ،
③ والمسكن الضيق ،
④ والمركب السوء .

➛አራት ነገሮች የጥበት ምንጭ ናቸው

1--- መጥፎ ሚስት
2--- መጥፎ ጎረቤት
3--- መጥፎ መጓጓዣ
4--- መጥፎ መኖሪያ


📚صححه الألباني في الصحيحة 282
Audio
ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ

📌 الدروس المهمة لعامة الأمة
♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
🔺ኢህሳን ማለት ምን ማለት ነው?
🔺የሶላት ሸርጦችን በሰፊው የተዳሰሰበት

《ክፍል 0⃣9⃣

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
የሩቅ ሚስጥር አቃለሁ ባይነትና
ከዚህጋ የተያያዙ ነጥቦች፡
••••••••••••••••••••••••••••
🔺የሩቅ ሚስጥር "ገይብ" ማለት
ከሰዎች አዕምሮና እይታ የተሰወረ
ነገር ሲሆን አሁን ያለ፣ ያለፈ ወይም
የወደፊት ሊሆን ይችላል።
ይህ የአላህ መለያ በመሆኑ
ከሱ ሌላ ማንም ሊያውቀው
አይችልም።

'አላህ እንዲህ ይላል፡
👉 "በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ሚስጥር አያውቅም"።
ግን አላህ ያውቀዋል። (አል ነምል 65)
••••••••••••••••••••••
👉"አላህ የቆዩትን ልክ አዋቂ ነው በላቸው።"
( አል ከህፍ 26)
••••••••••••••••••••

👉"ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ታላቅ የላቀ ነው።" (ረዕድ 9)
••••••••••••••••••••••••••••••
🔺ስለ ሁድ ሲናገርም እንዲህ ይላል፡
👉"ዕውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው። ያን በእርሱ
የተላኩበትንም አደርስላችኋለሁ>> አላቸው።
[ አል አህቃፍ 23]
••••••••••••••••••••••••••••

🔺አላህ ለነቢዩ ሰላላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብሏል፡
👉"ለእናንተ የአላህ ግምጃ
ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም።
ሩቅንም አላውቅም።>> በላቸው።
[አል አንዓም 50]
••••••••••••••••••••••••

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
አርበዒን 19ኛ ሐዲሥ
Ibnu Munewor
ደርስ
~~~~

~ አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር
~ በመርከዘ ተውሒድ ላሉ የቁርኣን ሒፍዝ ተማሪዎች እየቀረበ ያለ
~ ሐዲሥ ቁጥር – 19
~ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ pdf መልክ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/1672
👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#አሰር_ጥቆማ!!
#ከላጤነት__ጨለማ¡¡
#ወደ__ትዳር___ማማ¡¡
<{==========================}>

(1፩)#ትዳር_ማለት:~}>
ርዕሱን አይተህ ጆይን የምትልበትና ሲደብርህ ሊፍት የምትልበት ግሩፕ አይደለም።

(፪2)#ትዳር_ማለት :~}>
ሲበርድህ የምትለብሰው ሲሞቅህ አውልቀህ የምትጥለው ከቦርት አይደለም።

(፫3)#ትዳር_ማለት:~}>
ከሰወች ጋር ተጋፍተህ ገብተህ ተደግፈህ የምትወጣበት መሸታቤት አይደለም።

(፬4)#ትዳር_ማለት :~}>
በፈጣሪ ቃል መሀላ ፈፅመህ የምትገባበት ደማቅ ህይወት እንጂ በገመድ የተወጠረና ስትፈልግ የምትፈታው ሲየሻህ የምትበጥሰው ሲባጎ አይደለም።

(፭5)#ትዳር_ማለት:~}>
ተቻችለህ የምትኖረው የሁለት ሀገር ስኬት እንጂ አንተን ተሸክሞ የሚኖር መቀመጫ ወንበር አይደለምና እኔን ብቻ ስሙኝ አትበል።

(፮6)#ትዳር_ማለት:~}>
የበሳሎች የስኬት እርከን ታላቅ #ውቅያኖስ እንጂ የህፃኖች መንቦጫረቂያ#ኩሬ አይደለም።

(፯7)#ትዳር_ማለት:~}>
የአዋቂወች፣የአስተዋዮች፣የብልጦች ካንፖስ እንጂ የመሀይማኖች #መዋለ_ህፃናት አይደለም።

(፰8)#ትዳር_ማለት:~}>
መስፈርቱን ማሟላት ከቻልክ ሁለት፣ ሶስት፣ አራት የምታገባበት የወንድነት ፀጋ የሴትነት ክብር እንጂ በየሳምንቱ አንዷን አናደህ አባረህ ላላኛዋን አሳደህ የምታመጣበት የግል ማሰልጠኛ ተቋም አይደለም።

(፱9)#ትዳር_ማለት:~}>
ከመጥፎ ነገር ማለትም ከዝሙት ያልተፈቀደ ከማየት ያልተፈቀደ ከመንካት የምትቆጠብበት የአሏህ ድንጋጌ እንጂ ሚስትህን እያስለቀስክ በሚዲያ እየዋሸህ የሌሎችን ልብ የምትሰርቅበት #የስዳደጎች_መድረክ አይደለም።

(፲10)#ትዳር_ማለት:~}>
እሾህ ያለው አበባ ነው አበባው እንዳፈራልህ ከፈለክ#የእሾኩን_ውጋት መታገስ አለብህ።!!

#እሾኩ_አንዳንዴ_አለመግባባት_ሲሆን፡~
#ያኔ_ታጋሽ_ሁን_____

አበባው እውነተኛ ፍቅር ሲሆን፡~
#አውነተኛ_ባል_ሆነህ_አበባውን_ቅዘፍ__

ፍሬው የአብራክህ ክፋይ ልጆች ሲሆኑ፡~
ለልጆችህ እውነተኛና ጀግና አባት ሆነህ በተርቢያ አሳድገህ #የፍሬው ባለቤት ሁን።
#ወሏሁ_አዕለም
<{========================}>
#በኑረዲን_አል_አረቢ
<{=====================}>
فالمسلم ولو كان بعبد الدار فهو أخوك في الدين
♻️ሙስሊም የሆነ አካል በሀገር ማትገናኙና የተራራቃችሁ ቢሆንም የዲን ወንድምህ ነውና ዘመድህ እንኳን ባይሆን ልትቀርበው ይገባው።
والكافر ولو كان أخاك في النسب فهو عدوك في الدين
♻️ ካፊር ደሞ የፈለገ ቢቀርብህና ወንድህ እንኳ ቢሆን የዲን ጠላትህ ነውና ልትርቀው ይገባል።
አርበዒን 20ኛው ሐዲሥ
Ibnu Munewor
ደርስ
~~~~

~ አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር
~ በመርከዘ ተውሒድ ላሉ የቁርኣን ሒፍዝ ተማሪዎች እየቀረበ ያለ
~ ሐዲሥ ቁጥር – 20
~ የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ pdf መልክ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/1672
👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የሰለፎችን መንገድ መያዝና ወደሱ መጣራት።።
_
የሰለፍያ እምነት በኢማሙ አህመድ ወይም በሀንበልያ ብቻ የታጠረች አይደለችም።
ሌሎችን ሳይጨምር በነሱ ብቻ የምትገደብ አይደለችም።

ኢብኑ ተይሚያ እንድህ አሉ፣
የአህለሱና ወልጀምዓህ አካሄድ የታዋቀና ከድሮ ጀምሮ ያለ ነው
አላህ አቡ ሀኒፋን ፣ማሊክን፣ ሻፍዒይን ፣አህመድን ሳይፈጠር በፊት የነበር ነው።
እነሆ(የሰለፍያ እምነት)የሱሀቦች አካሄድ ነው እነዛ ከነብያቸው የተቀበሉት።

ምንጭ:::ሚንሃጁ አስሱና (2/601)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ

📌 الدروس المهمة لعامة الأمة
♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
🔺የአርካንና የሸርጥ ልዩነት
🔺የሱረቱል ፋቲሀ አንገብጋቢነት
🔺የሱረቱል ፋቲሀ ትርጉም የተዳሰሰበት

《ክፍል 1⃣0⃣

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ

📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች

🔺የሶላት አርካኖች (ማእዘናቶች) በሰፊው የተብራራበት

《ክፍል 1⃣1⃣》በአቡ አብደላህ


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ቢስሚላሂ ረህማኒሮሂም
••••••••••••••••••••••••

✳️ በተወሱል ርዕስ የሚነሱ ብዢታዎችና
እርምቶቻቸው፦
🔺ሱና ተከታዮችን የሚፃረሩ አንጃዎች
በተወሱል ዙሪያ የተሳሳተ አመለካከታቸውን
ለማጠነካከርና የያዙትን ሀሰት
እምነት ሙስሊሙ ማህበረሰብ
ዘንድ ጥሩ እይታ እንዲኖረው
ሲሉ የሚያነሷቸው ብዢታዎች
አሉ።
ይሁንና የሚያመጧቸው ማጭበርበሪያዎች
ከሁለት ነገሮች አይዘልም።
°°°°°°°°•••••••°°°°°°°°
አንደኛ፦ የዘገባ መንገዳቸው የደከመና
የተቀጠፉ ሃዲሶችን ለአቋማቸው
ማስረጃነት መጠቀም ሲሆን ይህ ግን
ትክክል ያልሆኑ ሀዲሶች መሆናቸውን
በማወቅ ብቻ ያበቃለታል።
--------------------

ከሚጠቅሷቸው ትክክል ያልሆኑ ሀዲሶች፦
🔺1.<< በማዕረጌ አመካኝታችሁ አላህን ለምኑ
አላህ ዘንድ ማዕረጌ የላቀ ነውና።>>አላህን
ስትለምኑበክብሬ ለምኑት ክብሬ አላህ ዘንድ
ትልቅ ነው።>> 👈ይህ አንድም አሊም ያልዘገበውና በየትኛውም የሃዲስ መፅሀፍ
ተፅፎ የማይገኝ የተቀጠፈ ወሬ ነው።
••••••••°°°°°°°°°°°°°°°•••••••••••••••••
🔺2.<< ነገሮች ሲከብዷችሁ በቀብር ሰዎች
ታገዙ >> የቀብር ሰዎች ከጭንቅ እንዲያወጧችሁ ተማፀኑ>> 👈ይህም በነቢዩ ዓለይሂ አሶላቱ ወሰላም የተቀጠፈ ሀዲስ እንደሆነ
ኡለማዎች በሙሉ ተስማምተውበታል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
3.<< ለዲንጋይ እንኳን ጥሩን ግምት ብታሳድሩ
ይጠቅማችኋል>>👈 ይህ ሀዲስ ውሼት ከመሆኑም በላይ እስልምናን የሚፃረር
ሙሽሪኮች የቀጠፉት ነው።
••••••••••••••••••••••••••••••°°°°°
🔺4.<< አደም ሃጢአትንከተዳፈረ በኋላ
እንዲ አለ "ጌታዬ ሆይ! በሙሀመድ
መብት ይሁንብህ እንዲትምረኝ እለምንሃለሁ"
አላህም "አደም ሆይ!
ሙሀመድን ገና ሳልፈጥረው እንዴት አወቅከው?ሲለው ፈጥረኸኝ ነፍስ ስትዘራብኝ ራሴን ከፍ ሳደርግ የአርሽ እግር ላይ "ላኢላሃ ኢለሏህ
ሙሀመዱ ረሱሉሏህ" የሚል ፁሁፍ
አነበብኩና ከፍጡራን በጣም የምትወደውን
እንጂ ወደ አንተ ስም እንደማታስጠጋው
ተረዳሁ" ሲል አላህም "በል ምሬሀለሁ ለሙሀመዲም ስል እንጂ አልፈጥርህም
ነበር አለው"።👈 ይህም መሰረት የሌለው
የሀሰት ወሬ ነው።
"ለአንተ ስል እንጂ ከዋክብትን አልፈጥርም ነበር " የሚለውም ሀዲስ ተመሳሳይ ነው።

🔺👆እነዚህን መሰል የውሼት ሀዲሶችና
የተቀጠፉ ዘገባዎችን አንድ ሙስሊም ማስረጃ
አድርጎ ሊመረኮዝባቸው ይቅርና ዞር ብሎም
ሊያያቸው አይገባም።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
🔺ሁለተኛ፦ በትክክለኛ ዘገባ ከነቢዩ ሱላላሁ
ዓለይሂ ወሰለም የተላለፉ ሀዲሶች
ቢሆኑም ነገር ግን እንደዚ አይነት
ሰዎች በትክክል ካለመገንዘባቸው
አልፈው የሚጠቁመውን ትርጉም የሚያዛቧቸው
ሀዲሶች ናቸው።
ከነዚህም ውስጥ፦
🔺1. ኡመር ኢብነል ኸጧብ ዝናብ ሲጠፋ
በአባስ አማካኝነት እንዲ በማለት አላህ
እንዲያዘንብላቸው ይለምኑ ነበር "ጌታዬ ሆይ
በነቢዩ አማካኝነት ዝናብን እንለምንህና
ታዘንብልን ነበር አሁን ደሞ በአጎታቸው
ዓባስ አማካኝነት እንለምንሃለን አጠጣን>>
ይዘንብላቸዋል። [ቡኻሪ ዘግቦታል]
👆ይህን ሀዲስ የሚረዱት ኡመር ያደረገው
ተወሱል አላህ ዘንድ ባለው የአባስ ክብር
እንደሆነ ነው። "በአባስ አማካኝነት••••••••••••••በነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም አማካኝነት ••••••••••••••••ማለት በነሱ አረዳድ አላህ ዘንድ ባላቸው ክብር" ማለት ሲሆን
ይህ ግን መቶ በመቶ የተሳሳተ ግንዛቤና
የራቀ ትርጓሜ ነው። ምክንያቱም
ሰሃቦች ዘንድ በነቢዩ አካልም ይሁን
ክብር አማካኝነት አላህን መለመን አይታወቅም።
ሲፈፅሙት የነበረው ተወሱል
ነቢዩ በሂዎት እያሉ ዱዓ እንዲያደርጉላቸው
መጠየቅ ነበር።
ኡመርም ቢሆን እኛ በነብያችን አጎት
አማካኝነት እንለምንሃለን ማለቱ በእርሱና በክብሩ
ማለት ሳይሆን በእርሱ ዱዓአማካኝነት ማለት ነው።

🔺በሰው ወይም በሰው ክብር አላህን መለመን
እነሱ ዘንድ ተፈፃሚ ቢሆን ኖሮ ዑመር ነቢዩን
ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም ትቶ ወደ አባስ ባልመጣ ነበር። ሶሃቦችም ቢሆኑ እንደት ታላቁን ፍጡር ነቢዩን ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም ትተው ዓባስን
ትመርጣለህ? ሲሉ ይቃወሙ ነበር።

🔺ይህን አለማለታቸውና ነቢዩ በሂወት እያሉ
የሚያደርጉት በእርሳቸው ዱዓ ምክንያት
ተወሱል የሚያደርጉ መሆኑ መታወቁ የተፈቀደው
ተወሱል በዱዓ እንጂ በሰውዬው ክብር እንዳልሆነ ግልፅ ይሆናል።
በዚህ መሰረት ሀዲሱ በሰዎች ወይም
በክብራቸው አላህን መለመን እንደሚቻል
የሚጠቁምበት ምንም አቅጣጫ እንደሌለው
ግልፅ ይሆናል።
📌قال شيخ الإسلام ابن تيميّة رحمه الله:
♻️ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል።

【إذا وجد العبد تقصيرا في حق القرابة والأهل والأولاد والجيران والإخوان، فعليه بالدعاء لهم والاستغفار】
የቅርብ ዘመድህ፣ የቤተሰብህ፣ የልጆችህ፣ የጎረቤቶችህና ባጠቃላይ የወንድሞችህ ሀቅ በተገቢው አልተወጣሁም፤ ሚጠበቅብኝን አላደረኩላቸውም ብለህ ካሰብክ ዱአ አድርግላቸው። ከአላህ ዘንድ መሀርታውንም ለምንላቸው።
📚الفتاوى ( ٦٩٧/١١)
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ

📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች

🔺የሶላት አርካኖች (ማእዘናቶች) በሰፊው የተብራራበት

《ክፍል 1⃣1⃣

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
ቢስሚላሂ ረህማኒሮሂም

🍀1ኛ የአመጋገብና የአጠጣጥ ስርዓቶች በጥቂቱ ፡
••••••••••••••••••••••••••••••
🍂🍂አንደኛ ከመብላት በፊት ቢስሚላህ ማለት
ዑመር ኢብን ኸጧብ እንዳስተላለፉት
የአላህ መልዕክተኛ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ብለዋል አንተ ልጅ ቢስሚላህ በል፤
በቀኝ እጅህ ብላ፤ከፊት ለፊትህ በኩል ብላ።
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

•••••••••••••••••••••••••••••
🌿🍂 ዓኢሻ ባስተላለፈችውም ሀዲስ ነቢዩ
እንዲ ብለዋል
🔺"ስትበሉ ቢስሚላህ በሉ
መጀመሪያ ላይ ከረሳችሁ ስታስታውሱ
"ቢስሚላሂ ፊ አወሊሂ ወአኸሪሂ
{መጀመሪያውም መጨረሻውም
በአላህ ስም ይሁን } በሉ"።
{አቡዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል}

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
2ኛ. በቀኝ እጅ መብላት፡🍀
ነቢዩ ሰላላሁ አለይ ወሰለም እንዲ ብለዋል
🔺"ስትበሉ በቀኝ እጃችሁ ብሉ፤
ስትጠጡም በቀኝ እጃችሁ ጠጡ
ሸይጧን የሚበላውም የሚጠጣውም
በግራ እጁ ነው።"{ ሙስሊም ዘግቦታል}
________________________

አንዳንድ ሰዎች ግራም እንዴ ቀኝ እጅ ነው
ወይም ቀኝ እጄ ሌላ ስራ ይዟል በሚልና
በመሳሰሉ ደካማ ምክንያቶች በግራ እጃቸው
ሲመገቡ ይስተዋላል። ይህ ችልትኝነት በዚህ
ርዕስ ላይ አደገኛ ነው።

ምክንያቱም 🔺አንደኛ ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
በግራ መመገብ የሼይጧን ተግባር
መሆኑን በመግለፅ በቀኝ እንድንበላ
በትዕዛዝ መልክ ተናግረዋል።
የእርሳቸውን ትዕዛዝ መፈፀም
ደሞ ግደታ ነው።
_________________________
🔺ሁለተኛ ነቢዩን ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
አንድን ሰውበግራ ሲበላ አይተውት
በቀኝ እንድበላ ቢያዙትም እሱ ግን
በመኩራት "አልችልም" አላቸው
በዚህ ጊዜ ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
"አትቻል" ብለው ረገሙት {ሙስሊም ዘግቦታል}
ወዲያውኑ እጁ ሽባ ሆኖ
ምግብ ወደ አፉ ማቅረብ አቃተው።
ይህ ሃዲስ የሚያስረዳው በዚህም ሆነ
በሌላ ርዕስ ነቢዩን መቃረን አደገኛ መሆኑን ነው።
____________________________
ተደግፎ አለመመገብ። "ነቢዩ እኔ ተደግፌ አልበላም" ብለዋል {ቡኻሪ}
____________________
ከሳህን ዳር ዳር መመገብ፡
ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ብለዋል
🔺"ከሳፋ ዳር ዳር ብሉ ከመሀል አትብሉ በረከት የሚወርደው መሀሉ ላይ ነው።"
[አህመድ ዘግቦታል]


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w