💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
♻️🔺❗️ላስተዋለው ትልቅ ሙሲባ❗️🔺♻️

✅ قال الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله:
〰 〰 〰 〰
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📌♻️ሸህ አብዱረዛቅ ቢን አልበድር አላህ ይጠብቃቸው እንዲህ ብለዋል።

📌♻️ كثير من الناس عنده استعداد يجلس ساعات طويلة ليتعلم أمرا دنيويا، ويمكن يُفني أو سنتين ثلاث ما عنده مشكلة، وينفق أموال طائلة في سبيل تعلمه
📌♻️ብዙ ሰዎች ዱንያዊ ጥቅም ብቻ የሚገኝበትን ትምህርትና እውቀት ለማግኘት በሚገባ ይዘጋጃሉ። ለዚህም ሲሉ ሳይሰለቹ ለብዙ ሰአታት ቁጭ ብለው ይማራሉ። በዚህም ላይ ሁለትና ሶስት ከዚህም በላይ የሆነን ሰአት ይሰጣሉ። ከዚህም አልፎ ይህንን አላማው ይሳካ ዘንድ ብዙ የሆነን ወጪ ያወጣሉ። ብዙ ገንዘብንም ይመድባሉ።

📌♻️ لكن التوحيد الذي هو الغاية التي خلق لأجلها وأوجِد لتحقيقها، ربما يستكثر على نفسه «ربع ساعة» يجلسها لتعلُّم التوحيد، هذه مصيبة

📌♻️ ነገር ግን በዋናነት ሊያረጋግጠው የተፈጠረለት አላማና እዚህ ምድር የመምጣቱ ዋና ምክንያት የሆነውን #ተውሂድ ግን እንደዛ አይማርም። አንዳንዴ ይህ ዋናው ጉዳይ ተውሂድን ለመማር የሰጣትን #እሩብ_ሰአት ብዙ እንደሆነ ያስባል። ሀቂቃ ይህ #ትልቅ_ሙሲባ ነው።

📘دروس وفوائد من آية الكرسي الدرس: -٥- (46:55)
🔸ረሱል-ﷺ-እንዲህ አሉ:-አንድ አካል ለሌላ አካል ሱጁድ እንዲወርድ ባዝ ኖሮ፡ሚስት ለባሏ ሱጁድ እንድትወርድ ባዘዝኳት ነበር፡በአላህ ስም እምላለሁ ሚስት የባሏን ሀቅ እስካልተወጣች ድረስ የጌታዋን ሀቅ አትወጣም።
ምንጭ፦ ኢብኑ ማጀህ (1853)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
በ Ibnu Munewor
~~~~ለሴቶች!
በርካታ እህቶቻችን በዲን አስተማሪዎች እንደሚበደሉ ይወራል። "ዲኔን ያስተምረኛል"፣ "አላህን ይፈራል" ያሉት ሰው ለህይታቸው መዘባረቅ ሰበብ ሲሆን ያጋጥማል። እኔ ለዚህ ችግር ቀዳሚ ሰበብ የራሳቸው የእህቶቻችን አለማስተዋል ይመስለኛል። በርግጥ ዲንን መስፈርት አድርገው ልባቸው ሰፍ ቢል አይፈረድባቸውም። ኧረ እንዲያውም የሚደነቁበት ነው።
ነገር ግን ከዲን ጎን ለጎን የሰውየው ስነ ምግባር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። አንድን ሰው ደዕዋ ላይ መሳተፉ፣ ዒባዳ ማብዛቱ፣ ወዘተ ጥሩ ነገር ሆኖ ሳለ አብሮ ለመኖር የሚያስችል ወሳኝ ቅመም ግን ሊጎድለው ይችላል። ስነ ምግባር። ለዚህም ነው ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ዲኑንና ስነ ምግባሩን የምትወዱለት ሰው ከመጣችሁ (ልጃችሁን) ዳሩት" ያሉት። 
ስነ ምግባር ከዲን ጋር በተጓዳኝ እንደተገለፀ ያስተውሉ።
እናም እህቶች ሆይ!
ዲንን እንደ መስፈርት ስታስቡ አኽላቅንም አትርሱ። በምትችሉት መንገድ ሁሉ አጣሩ። መስፈርታችሁን በጣም ጥብቅ አታድርጉት። ጭራሽም አታላሉት። በልክ።

ግልባጭ:– ለወንዶች! እባካችሁን ፀባያችሁን አሳምሩ። ካልሆነ ግን ህ
ሀ/ ጥሩ ሚስት ያመልጥሀል
ለ/ ጥሩ ህይወት ያመልጥሀል
ሐ/ ጥሩ እድል ያመልጥሀል።



https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
🎤 ቀልድ በእስልምና ይፈቀዳል?

ዛሬ ዛሬ ቀልዶች በዝተዋል ሚቀለድበትም ነገር በዝቷል እስኪ እስልምና ስለ ቀልድ ምን ይላል
1) ቀልድ በመሰረቱ ይፈቀዳል።ግን ለራስነቱ ቀልድ ስለሆነ ተብሎ ሚፈለግ ተግባር አደለም ።
- ራስን ነቃ ለማድረግ ፣ ነሻጣ ለማምጣት፣ ሌሎች ሙስሊም ወንድሞቻችንን ለማስደሰት ( ሙስሊም ወንድምን ማስደሰት ኢባዳ ነው) ሸሪያዊ መርሆን ሳይፃረር ሊቀለድ ይችላል።
👉ነገር ግን አንድ ሰው በቀልድ መታወቅ የለበትም ።ይህ ዳኢ ቀላጅ ነው ተብሎ ሰዎች ዘንድ በሙሉ እስኪታወቅ ድረስ መቀለድ ተገቢ አደለም።ምክንያቱም ይህ እስላማዊ አደብ አደለም ከጨዋ ሰውም ሚጠበቅ አደለም ሰለፎችም እንዲህ አልነበሩም
2)የአላህ መልእክተኛ ከሰሀቦች፣ከቤተሰባቸው እና ከህፃናት ጋር በተለያየ አጋጣሚ እንደቀለዱ ተረጋግጧል።
3)ቀልድ በፍፁም ውሸት ያለበት መሆን የለበትም
የአላህ መልእክተኛ እርሶ ይቀልዳሉ እንዴ ተብለው ሲጠየቁ
: " لا أقول إلا حقا "
እውነት እንጂ አልናገርም ብለዋል
👉ስለዚህ ለቀልድም ቢሆን መዋሸት አይቻልም
💎በሌላ ሀዲስ ላይ እንዲህ ብለዋል
‏وقد وعد عنه صلى الله عليه وسلم أنه قال: " ويل للذي يكذب ليضحك الناس ويل له ويل له "
"ወየሁለት ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ የሚዋሽ ወየሁለት ወየሁለት።
4)የክህደት ቃላትን እየተጠቀሙ መቀለድ ከእስልምናም ያስወጣል።
ጌታችን እንዲህ ይላል
قال تعالى {ولئن سألتهم ليقولن إنما كنا نخوض ونلعب ..} الآيات.
"ብትጠይቃቸው እኛማ ስንቀልድ እና ስንጫወት ነበር ይሉሀል።በአላህ በመልእክተኛው እና በአንቀፆቹ ነው ምታላግጡት በላቸው።ምንም ኡዝር አታቅርቡ ከእምነታችሁ በሇላ ክዳችሇል በላቸው።
5) የሙስሊም ወንድሙን ክብር በሚነካ መልኩ መቀለድ፣ወይም በቀልድ አድርጎ የሙስሊም ወንድሙን ቀልብ መስበርም አይፈቀድለትም።
6)በእስልምና ድንጋጌ መቀለድም አይፈቀድም።ለምሳሌ; በሂጃብ፣በፂም ፣በሰላት፣ በሀጅ ፣በፆመ ....በመሳሰሉት
7)በኡለሞች መቀለድም ከባድ ወንጀል ነው
8)እየተሳደቡ ወይም እየተማቱ መቀለድም አይፈቀድም
9)ሰዎች ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እየፈጠሩ ሚደረግም ቀልድ አይፈቀድም።መኪናውን ሰርቆ በማስደንገጥ ሚደረግ ቀልድን ይመስል
10)ሙስሊም ወንድሙ ላይ የጦር መሳሪያ በመደቀን የሚደረግ ቀልድ የተከለከለ በመሆኑ ላይ ሀዲስ መጥቷል
11) የሚፈቀደውን ቀልድም ቢሆን ማብዛት ተገቢ አደለም ። ቀልድ ሲበዛ ቀልብ ያደርቃል

‏قال عمر بن ؚبد العزيز : " اتقوا المزاح، فإنه حمقة توع؍ الضغينة "

👉👉👉👉👉👉
ቀልድ ልክ እንደ ጨው ነው።መግባት ባለበት ቦታ እና ሰአት ይገባል።ሲበዛ ማጣፈጡን ትቶ ያበላሻል


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
يقول الإمام الجليل الفضيل ابن عياض - رحمه الله تعالى -
" اتبع طرق الهدى ولا يضرك قلة السالكين ، وإياك وطرق الضلالة ، ولا تغتر بكثرة الهالكين "
الإعتصام :(135/ 1)
🔷 ታላቁ ሊቅ ፉደይል ኢብኑ ዒያድ - ረሒመሁ ላሁ - እንዲህ ይላል
" ቀጥተኛውን መንገድ ተከተል የተከታዮቹ ማነስ አይጎዳህም
የጥመትን መንገድ ተጠንቀቅ በሚጠፉ ሰዎች ብዛት አትሸንገል "
አል ኢዕቲሳም: ( 1/135 )
➪ኢማሙ አህመድ ተጠየቁ፡

ጥያቄ፦ መልካም ስነምግባር ማለት ምን ማለት ነው ?
መልስ፦ መልካም ስነምግባር ማለት ከሰወች የሚደርስብህን አዛ መቻል ማለት ነው።
☞︎︎︎ ሹዕቡል ኢማን (7726)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የ ተውሒድ አንገብጋቢነት
ወንድማችን ዐብድል መሊክ
ከኡስታዝ ኸድር አሕመድ የፈለቁ ምርጥ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ
ወንድማችን ዐብድል መሊክ
በመርከዝ ኢብኑ አባስ የተደረገ ህዳር 6 እለተ እሑድ

ርዕስ የተውሒድ አንገብጋቢነት

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
🌹የተረሳ ሱና ...!

🔴ውዱዕ አድርጎ መተኛት

🔸የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለበራእ ቢን አዚብ እንዲህ ብለውታል :

ማረፊያ ቦታህ በመጣህ ግዜ ለሰላት ምታደርገውን ውዱ አድርግ ከዛም በቀኝ ጎንህ ተኛና ይህንን በል

" اللهم أسلمت وجهي إليك وفوضت أمري إليك وألجأت ظهري إليك رهبة ورغبة إليك لا ملجأ ولا منجى منك إلا إليك آمنت بكتابك الذي أنزلت ونبيك الذي أرسلت"

«አላሁመ አስለምቱ ወጅሂየ ኢለይክ ወፈወቱ አምሪ ኢለይክ ወአልጃእቱ ዟህሪ ኢለየክ ራህበተን ወረግበተን ኢለይክ ላ መልጀአ ወላ መንጃ ሚንከ ኢላ ኢለይክ አመንቱ ቢኪታቢከለዚ አንዘልተ ወነብይከለዚ አርሰልተ

ከዛም እንዲህ አሉት
ከሞትክ የሞትከው በፊጥራ ላይ ሆነክ ነው ።ስትተኛ መጨረሻ ምትናገረው ይህን አድርግ

📕متفق عليه ||6311-6882||

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁለት ሊጋቡ የተስማሙ ሴት እና ወንድ ከኒካህ በፊት እንደፈለጉ እየተደዋወሉ ማዉራት ይችላሉን??
♦️♦️♦️ታላቁ የእውቀት ባህር ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–

"ዲናዊ ዝምድና ከጭቃዊ ዝምድና የላቀ ነው። በልቦችና በሩሖች መካከል ያለው መቀራረብ በአካላት መካከል ካለው መቀራረብ የበለጠ ነው።"


📚ሚንሃጁ አስሱንናህ: 7/78

ያአላህ ምንኛ ያማረና ልብ ቀስቃሽ ንግግር ነው ‼

የሱና ወንድምና እህቶች በያላችሁበት የአላህ ሰላምታ በናንተ ላይ ይሁን አድርሱልኝ የሱናህ

✍ወንድማችሁ አቡ አዩብ
#አታውልቂው_ያምርብሻል
ሚያስደስተኝ እኔ ሳይሽ
ተሸፋፍነሽ በኒቃብሽ
በሽተኛን አደናብረሽ
የሱናን ሰው ልቡን ማርከሽ
ረመድ ረመድ ስትይ አንገት ደፍተሽ
እያት እስኪ ተነቅባ
ሃያእ ከላይ ደራርባ
ብለው ሰዎች ሲያወሩ
በውበትሽ ሲፎክሩ
አይቅርብኝ እኔም ብዬ
በተቻለኝ ሞራል የአቅሜን ችዬ
የውበት ጥግ አላብሶሻል
አታውልቂው ያምርብሻል!!
𝑨𝒃𝒖 𝒔𝒐𝒇𝒊𝒚𝒂...✍️

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የሱና ዑለማዎችን ለሚያከብሩ ብቻ!
~~~~~~~~~~
ኢኽዋንዮችን ተዋቸው። የሱና ዑለማዎችን ማንቋሸሽ የመንሃጃቸው አካል ነው። በሰለፊያ ስም የሚንቀሳቀሱ፣ የኢኽዋንን ጅራት ተከትለው የሚነፍሱ፣ እያንቀላፉ እንደነቁ የሚያስቡ፣ ከጊዜ ጊዜ ቁልቁል እየተጓዙ ያሉ ሳይሞቅ ፈላዎችን እያየን ነው። "ሰለፍዮች ነን" ይላሉ። ለሰለፊያ መንሃጅ ግን ክብር የላቸውም። መመሪያውን አይጠብቁም። ከወሰኑ አይቆሙም። ልካቸውን አያውቁም። ድመት ሳያክሉ እንደ ነብር ይሰራቸዋል። ዑለማዎች ከቆሙበት አይቆሙም። አሁንማ ይባስ ብለው ጭራሽ ዑለማዎቹንም መዳፈር ጀምረዋል። ለኢኽዋን አጋፋሪዎች፣ ለአሕባሽ ዐቂዳ አራማጆች ሙገሳ የሚሰፍረው ብእራቸው ለሱና ሰዎች ግን እሾህ እየሆነ ነው። ሒክማቸው፣ ሪፍቃቸው፣ ዐድላቸው ለቢድዐ አንጃዎች ነው። ለኢኽዋኖች ከሚሰፍሩት ሪፍቅና ዐድል እሩቡን ለሰለፍዮች አይሰጡም።
ይሄ የሱና ዑለማዎችን ክብር መዳፈር፣ በነገር መውጋት፣ ባደባባይ በክፉ እየነካኩ ክብራቸውን ማቃለል፣ በዚህ አይነት መሰሪ አካሄድ ከቢድዐ አንጃዎች ጋር መጋፋት ጀግንነት ሳይሆን አጉል ጀብደኝነት ነው። ሰውዬ! የምትጎዳው እነሱን ሳይሆን እራስህን ነው። ታላቁ ዓሊም አቡ ሓቲም አራ፞ዚይ ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ይላሉ:–
علامةُ أهل البدع الوقيعةُ في أهل الأثر
"የቢድዐ ሰዎች መታወቂያ የቀደምቶችን ፈለግ የሚከተሉ ሰዎችን ማንቋሸሽ ነው።" [ዐቂደቱ ሰ፞ለፍ: 105]

ሰለፊይነት በተግባር እንጂ በምላስ አይደለም። ኢኽዋንን በመተቸታቸውና ኸዋሪጅን በማውገዛቸው ምክንያት ዑለማዎች ላይ የሚሳለቅ ሰው ፈፅሞ የሱና፞ ሰው ሊሆን አይችልም። የሱና፞ ሰው ማለት ታላቁ ሰለፍ አቡበክር ብኑ ዐያ፞ሽ ረሒመሁላ፞ህ እንዳሉት "ስሜቶች (ቢድዐዎች) በሚወሱ በሚወገዙ ጊዜ ለየትኛውም ወግኖ የማይቆጣ ነው። [አሸሪዐ ሊልአጁሪ፞]
ዛሬ የኢኽዋን ቫይረስ ተንሰራፍቷልና ኢኽዋን ተነካ ብሎ የሚነጫነጭ፣ ኸዋሪጅ ተወገዘ ብሎ ፀጉሩን የሚነጭ ሰው ማየት የሚደንቅ አይደለም። የሚደንቀው አንድ ሰው ሰለፊ ነኝ ካለ በኋላ እነዚህ የጥፋት አንጃዎች ስለተነኩ ተበሳጭቶ የሰለፊያ ዑለማዎችን ባደባባይ ማጠልሸቱ፣ በነገር መውጋቱ ነው።
ለማንኛውም ለዑለማእ ክብር ያላቸው ሰዎች ይገሰፁበት ዘንድ ተከታዩን የሸይኽ ሱለይማን አሩሐይሊን ሐፊዞሁላ፞ህ ንግግር አያይዣለሁ።

✍ኢብኑ ሙነወር
🖊نصيــحـة الشيـــخ صــالح الفــوزان -حفظه اللّه- للمـرأة السلفيّـة

🌷احرصي على تنظيم وقتك حتى يكون عملك متعة

🌷واجعلي البيت دائمًا كالروضة نظافة وترتيبًا
فالبيت دليل على صاحبته

🌷النظافة والترتيب يكون البيت بأجمل صورة

🌷ولو كان الأثاث متواضعًا والعكس بالعكس .



📜[دور المرأة في تربية الأسرة].


https://t.me/g4448
ኢኽላስ እና ሙታበዓ ስራ ተቀባይነት እንዲኖረው መስፈርቶች ናቸው
አንገብጋቢነት
በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን
አዲስ ሙሐደራ

ሙሐደራ ቁ·120
#ኢኽላስ እና ሙታበዓ ስራ ተቀባይነት እንዲኖረዉ መስፈርት ናቸዉ

🔶 በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ በቡታጅራ ከተማ በቆዳና ሌጦ መስጅድ የተደረገ ሙሐደራ።

🎙 በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
"የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም!"
~~~~~~~~~~
በነብያችን ﷺ ላይ የሚሳለቅ እራሱን እንጂ እሳቸውን ምንም ሊያደርጋቸው አይችልም። የላካቸው አምላክ "መወሳትህን/ዝናህን ከፍ አደረግንልህ" ብሏቸዋል። ይሄው የዝናቸው ከፍ ማለትም ነው ዛሬ በርካታ ውሾችን እያስጮኻቸው ያለው። ትላንትም የዛሬዎቹ ውሾች አያቶች የመልእክተኛውን ክብር ሊያንቋሽሹ ሞክረው ነበር። አላህ ግን እራሱ ለመልእክተኛው ﷺ ተከላካይ ጠበቃ ይሆንና መልእክተኛው ግን ነገሩን ንቀው እንዲተውት እንዲህ ይጠቁማቸዋል፡-

(فَٱصۡدَعۡ بِمَا تُؤۡمَرُ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِینَ ۝ إِنَّا كَفَیۡنَـٰكَ ٱلۡمُسۡتَهۡزِءِینَ ۝ ٱلَّذِینَ یَجۡعَلُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَـٰهًا ءَاخَرَۚ فَسَوۡفَ یَعۡلَمُونَ ۝ وَلَقَدۡ نَعۡلَمُ أَنَّكَ یَضِیقُ صَدۡرُكَ بِمَا یَقُولُونَ ۝ فَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ ٱلسَّـٰجِدِینَ ۝ وَٱعۡبُدۡ رَبَّكَ حَتَّىٰ یَأۡتِیَكَ ٱلۡیَقِینُ)

"የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለፅ፤ አጋሪዎችንም ተዋቸው። እኛ ተሳላቂዎችን ሁሉ በቅተነሃል። (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፤ በርግጥም (የስራቸውን ዋጋ) ወደፊት ያውቃሉ። አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን በርግጥም እናውቃለን። ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው፤ ከሰጋጆቹም ሁን። እውነቱም (ሞት) እስከሚመጣህ ድረስ ጌታህን አምልክ።" [አልሒጅር 94-99]

ስለዚህ ተሳላቂዎቹ ውሾች ቢሳለቁም የነብያችን ﷺ ዝና የበለጠ ይገናል። የውሾቹ ስም ይከስማል። ውሻ ደግሞ ምን ታሪክ አለውና?!! እስኪ የነብያችንና የትላንት ጠላቶቻቸውን ዝና አወዳድሩ። ሲጀመር መወዳደር ይችላሉ? በጭራሽ!! “የሰማይና የመሬት ያክል ነው” ብንል እንኳ በትክክል አይገልፀውም።
ግን የነብያችንን ﷺ ክብር ለማጉደፍ ተፍ ተፍ የሚሉ ሰዎች አላማቸው ምን ይሆን? መልሱ ግልፅ ነው።
1. አንዳንዶቹ በነብዩ ﷺ እውቅና ሂሳብ እውቅና መሸመት የሚፈልጉ ናቸው። “አንዳንዶች ታዋቂዎችን በመተቸት ታዋቂ መሆን ይፈልጋሉ” ሲባል አልሰማችሁም?
2. ሌሎቹ ደግሞ የኢስላም ውበቱና ሁለንተናዊነቱ የሚያስቀናቸው፤ ከፍተኛ ግስጋሴው የሚያስበረግጋቸው ናቸው። ስለሆነም ሙሐመድን ﷺ ሲያንቋሽሹ የኢስላም ውበቱ የሚደበዝዝ፣ ግስጋሴው የሚገታ ይመስላቸዋል። እውነታው ግን ተቃራኒው ነው። ኢስላም ዛሬ ጠላቶቹን እንቅልፍ በሚነሳ መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ ነው። ስለዚህ ውሾቹ አመል ሆኖባቸው ይጮሃሉ እንጂ የኢስላምን ግስጋሴ ሊገቱት አይችሉም!! ውሾቹ ይጮሃሉ፣ ዋው! ዋው!....። ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል። ውሻ ግመልን ማስቆም ከቻለች ትሞክር።
ባይሆን ከኛ አንድ ነገር ይጠበቃል። ከሃዲዎችን የነብያችንን ﷺ ስም ለመዘለፍ ያበቃቸው ለነብዩ አስተምሮ ያላቸው ጥላቻ መሆኑ ይታወቃል። አዎ የነቢዩ ﷺ ሱና እጅጉን ያስቆጫቸዋል!! እውነቱ ይህ ከሆነ ከሃዲዎችን የበለጠ ለማስቆጨት የሚጓጓ፤ ለሙሐመድ ﷺ እውነተኛ ወዳጅነቱን ማንፀባረቅ የሚፈልግ፣ ብሎም የአላህን ውዴታ ማትረፍ የሚሻ የበለጠ ወደ መልእክተኛው ሱና ይቅረብ፤ ትእዛዛቸውንም ይፈፅም፤ ከከለከሉትም ይራቅ። ይህን የሚያደርግ ጠላቱን የበለጠ ያስቆጫል። የአላህንና የመልክተኛውንም ﷺ ውዴታ ያፍሳል። ያ ሱብሓላህ!!! የአላህና የመልክተኛውን ውዴታ ያገኘ ምን የቀረበት ነገር አለ?!!!! ያ ወሃ፞ቡ አንተ ወፍቀን!!! ኣሚን

(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 08/2005)

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor