💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
متن أصول الثلاثة ۷
Abu Useymin
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖

📚ኪታብ ኡሱሉ ሰላሳ

            ➧ክፍል 
❼

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1

@abuUseyminabdurehman
📲 ተንቀሳቃሽ ስልክ እና አደቦቹ
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
📱خُطْبَةُ الْجُمُعَةِ
📱የጁሙዓ ኹጥባ

📲 الهاتف النقال وآدابه
📲 ተንቀሳቃሽ ስልክ እና አደቦቹ

🕌 ደሴ አል-አዝሐር መስጂድ

📅محرم/28/ 1444

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
      ↓↓↓
t.me/abu_reyyis_arreyyis/6281
t.me/abu_reyyis_arreyyis/6281
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ

• { سورة آل عمران } •
💦ኢማሙ ሻፍእይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

✅ ሰዎችን ሁሉ ላስደስት ብትል በፍፁም አትችልም። ባይሆን ባንተና በአላህ መካከል ያለውን ግኑኝነት አስተካክል። ከዚያ በኋላ ሰዎች ምንም ቢሉህ ቦታ አትስጥ።
📚(توالي التأنيس ،صـ:168)
متن أصول الثلاثة ۸
Abu Useymin
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖

📚ኪታብ ኡሱሉ ሰላሳ

            ➧ክፍል 
❽

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1

@abuUseyminabdurehman
➲ህይወት የፈለገ ያህል ከባድ
ጭንቀተማና አድካሚ ብትሆንም
ሁለት ደስ የሚሉ ጣእምን የሚሰጧት
ነገሮች አሉ
‥ እነሱም

⇘ አላህን ማውሳት እና ለአላህ ብሎ
ከሚወድህ ልብ የሚመጣልህ ዱዓእ ነው።


✍️ብቸኛዋ የእውቀት ፈላጊ
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ 🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ?! ➬➬➬➬➬➬➬ ➲ክፍል ስድስት ➤በአላህ ፍቃድ ባለፉት ክፍሎቻችን ላይ የመልካም ጓደኛን የተወሰኑ ባህሪዎችን ለማየት ሞክረን ነበር ዛሬም የምንቀጥል ይሆናል ኢንሻ አላህ ። ❶❶➛ሚስጥርህን የሚጠብቅ !! ➤ጓደኛ ተብሎ ሚስጥርህን ካልጠበቀ ይሄ ጓደኛ አይባልም ጓደኛ ማለት ከርሱ ጋር ሆንክም ብቻክን ሆንክ ሚስጥርህን የሚጠብቅ ማለት ነው እንጅ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ

🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ?!
➬➬➬➬➬➬➬➬

➲ክፍል ሰባት

➤የመልካም ጓደኛን ባህሪ እያየን ነበር እናም በዝህ ክፍላችን የመልካም ጓደኛ ባህሪዎች በትንሹ እንቋጫለን በቀጣዩ ክፍላችን ደግሞ የመጥፎ ጓደኛ ባህሪዎች ምንድናችሁ የሚለውን እናያለን ኢንሻ አላህ ።

❶❹➛ለአላህ ታማኝነት ያለው!!

➲ይህ ማለት ምን ማለት መሰለህ ወንድሜ አንድ ሰው ለአላህ ታማኝ ካልሆነ ላንተም ታማኝ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም እናም ለአላህ ታማኝ የሆነውን ምረጥ ወንድሜ ።

➲ለአላህ ታማኝ ሲሆን ላንተም ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዳለ ታማኝ ነው የሚሆነውና አላህ ለሁላችንም ይወፍቀን ለኛ ታማኝ ሲሆን በሁሉም ነገር ይህ የጓደኝነትን ማዕረግ አግኝቷል ማለት ነው ።

➤ነገር ግን ምንም ታማኝነት ከለለው ግን ለአላህ ካልታመነ ላንተ ሊታመን ቢሞክርም እንዳታምነው እንዳትሰማው ከቻልክ ብቻ ምክረው ለአላህ ታማኝ እንዲሆን ዘንድ ማለት ነው ።

❶❺➛ሁሌም እውነተኛ የሆነ !!

➲እውነትኝነት ከሙእሚን ባህሪ ሲሆን በተቃራኒው መዋሸት ደግሞ የሙናፊቆች ባህሪ ነው ስለዝህ የሚዋሽ ሰው የሙናፊቅነትን ቁራጭ ይዟልና ይህም ላንተ አይሆንህም ከውሸቱ ወደ አላህ #እስካልቶበተ ድረስ ።

➤እውነተኛ መሆን አለበት በንግግሩም በሁሉም ነገሩ በዝህም ጉዳይ ላይ መጀመሪያ ላይ ከአላህ ጋር እውነተኛ መሆን አለበት ያኔ ላንተም እውነተኛ ይሆንልካል ማለት ነው ።

➲ከአላህ ጋር እውነተኛ ሳይሆን ላንተ እውነተኛ ይሆናል ማለት
#ዘበት ነውና መጀመሪያ ለአላህ እውነተኛ ሊሆን ይገባዋል ወንድሜ ሆይ ዋሾ ሰው ይህ ተግባሩ ወደ ጀሀነም ነው የሚመራው እውነት ደግሞ ወደ ጀነት ያደርሳል ።

❶❻➛ከጫትና ከመሰል ሱሶች የፀዳ!!

➤ብዙ ሰዎችን አየን እኮ በፊት ደህና መልካም ስነምግባር የነበራቸው , ለቤተሰቦቻቸው መልካም የነበሩ , አልባሌ ቦታ ላይ የማገኙ የነበሩ ብዙ ሰዎችን አየን ብዙ ሰዎችን ተመለከትን ።

➲ግን ምን ያደርጋል የሚያሳዝነው ከሱሰኛ ጓደኛ ጋር በመዋላቸው ምክኒያት እንዳለ ተበላሽተው በሱስ ተጨማልቀው አየናቸው መጨረሻ ላይ አላህ ይጠብቀን እንጅ ይህ ትልቅ ፈተና ነው ወላሂ
።

➤ከመጥፎ ጓደኛ ጋር ከሱሰኛ ጓደኛ ጋር በመዋላቸው ምክኒያት እነሱም ከነሱ ሁነው ታያለህ በጫቱ, በሲጋራው, በሺሻው , እረ በስንቱ የሱስ አይነት ተለክፈው እናያለን ብቻ አላህ ይጠብቀን ።


➲ ይህ ሁሉ ችግር በምን መጣ ከመጥፎ ከሱሰኛ ሰው ጋር በመዋላቸው ምክኒያት ነው ስለዝህ አላህ ይጠብቀን ከንዲህ አይነት መጥፎ ጓደኛ ።


➤ስለዝህ የምትጎዳኘው ጓደኛ ከንዲህ አይነት ሱሳሱስ የራቀ የፀዳ መሆን አለበት አንተንም እዛው እንደለመደው ሱስ አለም ውስጥ እንዳይከትህ ተጠንቀቅ አኺ ።


➧ክፍል ስምንት ይቀጥላል ኢንሻ አላህ.......✍️

✍️አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/https_Asselefya1
እህቴ  ሆይ! ዛሬ   ለሙቀት  ብለሽ  እራቁትሽን የምትጓዢው  ነገ  ከሙቀት  በላይ በጣም  ተንቀልቀየዋን  ኢሳት  ፈርተሽ   በትክክል  ሂጃብሽን(ኒቃብሽን) ልበሺ!!!
Audio
▪️سورة. التكوير

🥀تلاوة جميلة.............

▪️የልብ ሰላም ትልቅ ስጦታችን !


https://t.me/https_Asselefya1
{ የእስልምናችን ታላቅነት } !!
Abu Useymin
➡️አድስ ~ሙሓደራ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️

🔊የእስልምናችን ታላቅነት !!

🕌 በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን በዳሞት ጋሌ ወረዳ በሻሻ ጋሌ ቀበሌ በቢላል መስጊድ የተደረገ!!

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➧https://t.me/abuUseyminabdurehman/8912
➧ለአል ኢህሳን ጀግና እህቶቻችን ማስታወሻ ትሁንልኝ

➲ጀግና ነሽ ብርቅየ


❖ሰለፍይ ጀግና በሱና ያጌጥሽው
በሱሀቦች ፋና ኒቃብ የለበስሽው
ተውሂድን በመማር ጊዜ የፈጀሽው
የመንሀጅ እህቴ ኢስላምን ያወቅሽው


በአል ኢህሳን መርከዝ የተገናኘነው
ከእንቁ ኡሰስታዞች በደርስ የተጣድነው
በመንሀጀ ሰለፍን የተረዳዳነው
ድንገት ስንለያይ ቀዘፈኝ እንባየ
እጅጉን ተሰማኝ መጣ ትዝታየ
እንባ ስታፈሽ እህትሽ ስትሄድ
ባጃጅ ስትሳፈር ስትገባ መንገድ
ስተትዘያየሩ በኒቃብ አምራችሁ
በጣም ገራሚ ነው ያስቀናል ፍቅራችሁ

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷

ታሪክ አይረሳውም የሰራሽው ስራ
በተውሂድ ጠንክሪ ምርትሽ ፍሬ ያፍራ
በቀጣይ ትውልዱ ደጋግሞ ይወራ
አንች ውዷ እህቴ መንሀጅ ያገናኘን
እንደ እድል ሆነና ሀገር ያለያየን
አላህ በእዝነቱ በዱኒያ ሰብስቦን
በእንቁ ኡስታዞች ለመማር ወፍቆን
በአል ኢህሳን መርከዝ ወስኖ አሰባስቦን
ደግሞ በውሳኔው ድንገት ያለያን
እንባ እየተራጨን እየተሸኛኘን
መለያየታችን እጅጉን ቢያመኝም
ውሳኔው የአላህ ነው ምንም አናረግም


እኔ ግን እህቴ ብዙ ተምሬ አለሁ
የሴቶች አለቃ መሆንሽ  ተረዳሁ
ቆራጥና አስተዋይ አርቆ አሳቢ ነሽ
ለድንሽ አሳቢ  እንቁ ጀግና የሆንሽ
የተውሂድ ዘበኛ የሱና ነበልባል
ሽርክን አራጋፊ የቢድአ እስክንፋል
መሆንሽ ግልፅ ነው ስራሽ ይናገራል
ለአህባሽ ለሱፍይ የእግር እሳታቸው
ለኢኽዋን ቡቃያ በእውቀት ገራፊያቸው
ሀዳድይ ሀጁሪን አንገት አስደፊያቸው
ለሙብተዲእ ሁሉ የእራስ ምታታቸው
አንች ነሽ እህቴ እኔ አይቸሻለሁ
ከምነግርሽ በላይ ብዙ ሰምቻለሁ
በአላህ ውሳኔ ዛሬ ብንለያይ
ኢንሻኡ ረቡና ብዙ አመት ሳንቆይ
እንገናኛለን በተውሃድ ዳእዋ ላይ
አንች ብቻ በርቺ በጅልባብ በኒቃብ
በአቂዳሽ ኑረሽ በሱናሽ በመዋብ
የነቢን ትእዛዝ ተግብረሽ በአግባብ
በሶብር ላይ ቆይ  እስኪሻ ጌታየ
እስከምንገናኝ አይናችን እያየ
የሁለት ሀገር ውብ ብርቅየ



✍ገጣሚ ወንድማችን አቡ ሹራ አህመድ
አልብኪይ

➷ለአል ኢህሳን መርከዝ ሴት ተማሪወች ማስተዋሻ የተነበበች
እህቶቸ በርቱልኝ አልሀምዱሊላህ የአላህ ውሳኔ ሆኖ ብንለያይም
እንደነገርኳችሁ ትእግስት አድርጉ
፡

➷የእኔ ውዶች በሰላም ግቡልኝ➷
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ 🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ?! ➬➬➬➬➬➬➬➬ ➲ክፍል ሰባት ➤የመልካም ጓደኛን ባህሪ እያየን ነበር እናም በዝህ ክፍላችን የመልካም ጓደኛ ባህሪዎች በትንሹ እንቋጫለን በቀጣዩ ክፍላችን ደግሞ የመጥፎ ጓደኛ ባህሪዎች ምንድናችሁ የሚለውን እናያለን ኢንሻ አላህ ። ❶❹➛ለአላህ ታማኝነት ያለው!! ➲ይህ ማለት ምን ማለት መሰለህ ወንድሜ አንድ ሰው ለአላህ ታማኝ ካልሆነ ላንተም…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ

🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ?!
➬➬➬➬➬➬➬➬

➲ክፍል ስምንት


➤እስከዛሬው ክፍላችን በአላህ ፍቃድ የተወሰኑ የመልካም ጓደኛን ባህሪዎች አይተን ነበር ከዝህኛው ክፍላችን ጀምረን ደግሞ የመጥፎ ጓደኛ ባህሪዎችን የምንመለከት ይሆናል ።

➲ይህንን ስናይ ግን ልታውቁልኝ የምፈልገው ነገር ይህንን የመጥፎ ጓደኛ ባህሪዎች ካላወቅን ልንርቀውና ልንጠነቀቀው ስለማንችል ነው ኸይር የምጠቅሰው ምክኒያቱም አንድን ነገን ለመራቅና ለመጠንቀቅ ግዴታን የሱን ምንነት ልናውቀው ይገባናል ።


⓵➮ዓቂዳው የተበላሸ ተውሂድ የለለው!!

➲ወንድሜ ሆይ ከሁሉም በፊት አንተ ለምን እንደተፈጠርክ እውቅ የተፈጠርክበትን አላማ ስታውቅ ግዜና ያኔ ለተውሂድ ያለህ ቦታ ከፍተኛ ይሆናል ማለት ነው ለተውሂድ ሰዎች ቦታ ትሰጣለህ ያኔ ።

➲ከጓደኛ ሁሉም መጥፎ ጓደኛ ማለት ዓቂዳው የተበላሸ ምንም የተውሂድ ብርሀን የለለው ነው በሽርክና በኹራፋት የተጨማለቀ ከሆነ ይህ በፍፁም ላንተ ጓደኛ ሊሆንክ አይችልም #በፍፁም !!

▪ዓቂዳው የተበላሸ ሰው ለአላህ ራሱ ስላልታዘዘ ምንም ላንተም ጓደኛ ሊሆንክ አይችልም እናም እንዲህ አይነትን ሰው በፍፁም እንዳትቀርብ ከአላህ ውጭ !!

➺ከአላህ ውጭ ላለ ከሰገደ
➺ከአላህ ውጭ ባለ ከተመካ
➺ከአላህ ውጭ ያለን እርዱኝ ካለ
➺ከአላህ ውጭ ያለን ከተጣራ
➺ከአላህ ውጭ ካለ ከከጀለ
➺ከአላህ ውጭ ለቀብር ካረደ

እና ሌሎችም የመሳሰሉትን ታላላቅ ወንጀሎችን ከተዳፈረ ይህ ሰው ላንተ ጠላትህ እንጅ ወዳጅህ አይደለም እናም ተጠንቀቅ ።

⓶➮ በቢድዓህ ባህር ውስጥ የሚዋኝ!!

➤ እንደሚታወቀው ዲናችን ሙሉ ነው #አልሀምዱሊላህ ስለዝህ አንዲስ ነገር ዲናችን አይቀበልም መጤ ነገር ሁሉም ጥመት ነው ይህ ጥመት ደግሞ የጀሀነም ነውና ።


➲ሱናው አልበቃ ብሎት ከሱናው አንድትን እንኳ ሳይሰራና ሳያውቅ በድዓው ባህር ከዋኘ ይህም ትልቅ ቂልነት ይሉካል ይህ ነውና አንተንም ቂል እንዳያደርግህ ተጠንቀቅ ።

▪ሱናውን ትቶ በተለያዩ የቢድዓህ አይነቶች ከገባ ይህ ሰው ለምሳሌ ፦
👇👇👇👇👇👇👇👇
➧የሽርክ መናኸሪያ የሆነውን መውሊድ ካከበረ
➧በነሺዳህ ስም ከጨፈረ ከደነሰ
➧በፊልም ስም ሓራምን ካየ
➧ ጫት የዱዓ መሳሪያ ነው ካለ
➧ በአደባባይ እናፍጥር እያለ ከበጠበጠ

እናም መሰል የቢድዓህ አይነቶች ላይ የሚዋኝ ከሆነ ይህን ሰው እንዳትጎዳኝ!!

➤ አደራህን የሱናው ወንድሜ ሆይ ይህ ሰው ብጥብጥና ሁከትን እና ቢድዓን እንጅ ሌላ አያወስክም ስለዝህ ቆም ብለክም አስብ ።

➲ አንድ ቢድዓን ማምጣት ትልቅ ወንጀል ነው
#ዲንም አልሞላም ብሎ ማሰብ ነውና ይህም ትልቅ ጥፋት ነው ዲናችንን ሙሉ ነው ቢድዓን አይቀበልም ኸይር አላህ ለሁላችንም በሱና ያስውበን ።

➧ክፍል ዘጠኝ ይቀጥላል ኢንሻ አላህ.........🖋

✍️አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/https_Asselefya1
▪️የሴት ልጅ መስተካከልና መበላሸት በባሏ ላይ ተፅእኖ ያሳድራሉ!!

➡️ሀሰኑል በስሪይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:–

“መካ ውስጥ ልብስ ሻጭ የሆነ ሰው ዘንድ ከርሱ ልብስ ለመግዛት ቆምኩኝ፣ እየማለ ልብሱን ማወደስ ጀመረ፣ ከርሱ መግዛቱን ተውኩት፣ ከእንደዚህ አይነት ሰው መግዛቱም ተገቢ አይደለም አልኩና ከሌላ ሰው ገዛሁኝ። ከዚያም  ከሁለት አመት በኋላ (ወደዚያው) ጉብኝት  አደረግኩ፣ እርሱ ዘንደም ቆምኩኝ እየማለም እያወደሰም ሆኖ አላገኘሁትም፣ ለርሱም እንዲህ አልኩት:– ያ  ከአመታት በፊት ያገኘውህ ሰው አይደለህምን? አዎ ነኝ አለ፣ ከዚህ በፊት ከነበርክበት ሁኔታ ወደ ምመለከትህ ሁኔታ ምን አወጣህ? እየማልከና እያወደሰክም ሆነህ አላይህም፣ አልኩት።
እንዲህ አለ:–


⓵➞ለኔ አንዲት ሚስት ነበረችኝ፣ ትንሽ ነገር ይዤ ስገባ የምታመናጭቅና አሳንሳ የምታይ፣ ብዙ ይዤ ስገባ አሳንሳ ተየዋለች፣ ከዚያም አላህ ወደ አኼራ ወሰዳት (ሞተች)።

⓶➞ከርሷ በኋላ ሌላ ሴት አገባሁ፣ ወደ ሱቅ መውጣት ስፈልግ ልብሴን ይዛ ከዚያም እገሌ ሆይ! አላህን ፍራ ጥሩ ነገር እንጂ አትመግበን፣ ትንሽ ብታመጣልን ብዙ አድርገን እንቆጥረዋለን/እናብዛዘዋለን፣ ምንም ይዘህ ባትመጣ እንኳን እናግዝሃለን፣ ትለኛለች።”

ምንጭ:– አል ሙጃለሰቱ ወጀዋሂር አል ዒልም 5/251📚

👉ጥያቄ ለእህቶቼ:– ለመሆኑ እናንተ ከየትኛዋ ሴት ናችሁ ከመጀመሪያዋ ወይስ ከሁለተኛዋ???
መልሱን……… ለአላህ ብላችሁ ከልባችሁ ለራሳችሁ መልሱትና ራሳችሁን ገምግሙበት!!
ከመጀመሪያዋ የሆናችሁ አላህን (ተባረከ ወተዓላ) ፈርታችሁ ተፀፅታችሁ ወደ ሁለተኛዋ ተመለሱ!!
ከሁለተኛዋ የሆናችሁ ሸይጧን ድንበር እንዳያሳልፋችሁ ነፍሳችሁን ዝቅ እንድትልና
ከጌታዋ ከጃይ እንድትሆን አድርጓት! አላህ ፅናት እንዲሰጣችሁም የዘውትር ዱዓችሁ ይሁን!! ምክንያቱም ይህ እጅግ በጣም ከባድ ነዉና!!

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/abuUseyminabdurehman