💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
📌📌አላህን ከመዘከር አትዘናጋ📌📌

🔵 ﻗـﺎﻝ الإمام_ﺍﺑــﻦ_ﺍﻟﻘﻴﻢ - رحمـه الله تعالـى- :

ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንከት እንዲህ ብሏል።

📌【ﺍﻟﺬﻛﺮ ﻳﻨﻮﺭ ﺍﻟﻘﻠﺐ ﻭﺍﻟﻮﺟﻪ ﻭﺍﻷﻋﻀﺎﺀ ، وﻫﻮ ﻧﻮﺭ ﺍﻟﻌﺒﺪ ﻓﻲ ﺩﻧﻴﺎﻩ ﻭﻓﻲ ﺍﻟﺒﺮﺯﺥ ﻭﻓﻲ ﺍﻟﻘﻴﺎﻣﺔ】

♻️👇ዚክር ማለት
🔺ቀልብ
🔺ፊት እንዲሁም
🔺የሰውነት አካል በሙሉ አብሪ ነው።
♻️👇ዚክር ማለት ለአንድ ባሪያ
🔻በዱንያ
🔻በቀብር ህይወቱና
🔻የቂያማ ቀን አብሪ ብርሀኑ ነው።

📚 اﻟﻮﺍﺑــﻞ_ﺍﻟﺼﻴــﺐ ( ١٣٥)

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
1345178359157815
<unknown>
تِـــلاوة 🎧

القارئ الشيخ: علي جابر -رحمه الله-
سورة: فاطر
@MOHAMMEDSIRAJALKEMISSIE
♻️🔺 ሰለፍይ መሆን ፀጋ ነው 🔺♻️

ሸህ ረቢእ ቢን ሀዲ አልመድኸልይ አላህ ይጠብቃቸው እንዲህ አሉ።

♻️ ለአንድ ሰው አላህ ሱብሀነሁወተአላ
🔺የሰለፎችን (ሶሀባዎችና ሶሀባዎችን በመልካም የተከተሉ) ሰዎች መንሀጅ (አካሄድ) እንዲረዳና
🔺በዚሁ መንሀጅ ላፅ እንዲፀና ላደረገው ሰው
♻️አላህን ከልቡ ሊያመሰግን ይገባዋል። ምክንያቱም ይህ
♻️አላህ ለሰው ልጆች ከሚሰጣቸው ፀጋዎች ሁሉ ትልቁና ዋናው ነውና።
📚 اللباب 571
አሏህ ሆይ
♻️ ከኢኸዋን የስልጣን ጥማት ነጥለህ
♻️ ከሱፍይ ከአህባሽ ሽርክና ቢድአ አድነህ
♻️ ከ isis ዳኢሽና ከተክፊሮች ብዥታ አላቀህ
♻️ ከተብሊግ ያለእውቀት መጓዝን አውጥተህ
♻️ ከሀዳድይ ሙሪድነት ነጃ አውጥተህ
♻️ ከሽርክ ከቢድአው ጠብቀህ
♻️ በእስልምናና በሙስሊሙ ስም በዲን ከሚነግዱ አፈ ጮሌዎች ታድገህ
♻️ ከአሻኢራ ከማቱሪድያና ከሙእተዚላ ቅጥፈት ተከላክለህ
♻️ ከሌሎችም የጥፋትና የጥመት ቡድኖች በአጠቃላይ አርቀህ
በጥንት በጠዋቱ በሶሀቦች ጎዳና በትክክለኛው መንሀጅ በሰለፍያ ጎዳና ላደረከኝ እንዲሁም
🔺በሱና ተውበው
🔺በተውሂድ አጊጠው
🔺ሽርክን አሽቀንጥረው
🔺ቢድአን ገርስሰው
🔺እውነት አስተምረው
🔺በሀቅ ላይ ፀንተው
ከሚጓዙት ሰለፍዮች እንድሆን ላደረከኝ ጌታ የላቀ ምስጋና ይገባህ። የስም ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ሰለፍይ ሆኜ በዚሁ መንሀጅ ላይ ወደ አንተ መምጣት እፈልጋለሁና ፅናቱን ለግሰኝ

ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w

♕︎ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! በዚህ ዘመን የኢስላም ጠላቶች ሂጃብሽን አስወልቀው ከተራ

ዱርየዎች ተርታ ሊያሰልፉሽ ተዘጋጅተዋል፡፡

𒊹︎︎︎ለዚህ ተንኮላቸው ደግሞ
ከፍተኛ ሚና
የሚጫወቱት ቴሌቪዥኖች፣ ሞባይሎች ፣ ጋዜጦች እና የተለያዩ ሚዲያዎች ናቸው፡፡

𒊹︎︎︎በመሆኑም አንዲት ሙስሊም ሴት አላህ ባዘዛት መሰረት ቀጥ ካለችና ሒጃቧን ባግባቡ
ከለበሰች በኢማኗ ጥንካሬ የሚከሰቱ ውዝንብሮችን እና የሰይጣን ተንኮሎችን በአላህ
ፈቃድ ትከላከላለች፡፡

𒊹︎︎︎ከዚሀ ቦታ የኡሙ ሰለማን ረዲየሏሁ ዐንሃ ጠንካራ ባህሪ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ረሡል ﷺ
ልብሱን በኩራት እየጎተተ ስለሚሄድ ወንድ ስለሚያጋጥመው ቅጣት በተናገሩ ጊዜ

𒊹︎︎︎ኡሙ ሰለማ ረዲየሏሁ ዐንሃ ሴቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ስትጠይቅ “አንድ ስንዝር
ታስረዝም” አሏት “እንደዛ ከሆነማ እግሮቻችን ይገለጣሉ” አለቻቸው፡፡ “በቃ አንድ
ክንድ ታስረዝም ከዚህ በላይ እንዳትጨምር” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ አህመድ፡ ቲርሚዚይ፡
1731 ነሳኢይ 5336

➪ኢማኗ የደከመባት ሴት በተቃራኒው አንድ ስንዝር ወይም አንድ ክንድ ወይም ከዚያ
በላይ እንደ ኢማኗ ድክመት አካሏን ትገልጣለች፡፡

☞︎︎︎ለቅኑ ጎዳና እንዲመራሽ ፤ ግልጽም ከሆነ ስውር ፈተና እንዲጠብቅሽ ፤ እርሱን
በመታዘዝ ላይ እንዲያግዝሽ ፤ በሐቁ ላይ እንዲያጸናሽ አላህን እማጸናለሁ፡፡ እነሆ አላህ
ዱዓን ሰሚና ተቀባይ ነውና ፡፡
ከሼይኽ አብድረዛቅ በድር ሀፊዘሁሏህ ኪታብ የተወሰደች..!!
︎[ዳዕዋቱል አንቢያ]
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲ኒቃብሽ ብልጠትሽንና እጅግ
ውብ ዘመናዊነትሽን ያሳያል።

➘እንደመሸፋፈኛሽ አንደበትሽም ንቁና የተረጋጋ አሰተዋይ ሀቀኛ ይሁን!
አደብ ሀያእ አኽላቅ በብ አይገዛም አይሸጥምም!

➲አደብ ሀያእ መልካም ስነ ምግባር ስነ-ስርዓት…… ከአላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ለሚወደው ባሪያው የሚሰጠው ትልቅ ኒዕማ (ችሮታው/ስጦታ)ነው!

➘በአላህ ፈቃድ ከትክክለኛ አስተዳደግ ይመነጫል!!

➘እንዲሁም ካደጉ በኃላ ከተገነዘቡት በእውቀትና በኢማን በተቅዋ አላህን በተገቢው መንገድ ለማወቅ ጥረት ባደረግን ቁጥር ይመለሳል!!

➘ካልተገነዘቡት ችላ ብለን የመፈጠራችንን አላማ ከዘነጋን ግን ባዶ ያስቀራል!!!

➲ድህነት የሚጎዳው ገንዘብ ሳይኖረን ብቻ አይደለም!

➘ይልቁንስ! የሀያእ ማጣት የአደብ የአኽላቅ ድህነት የከበበን እንደሆነ ነው

➲አላህ ሆይ!በሀያእ በመልካም ስነ ምግባር አስውበን!!


كَونۨيۧ سۜلۛفُيۧة ۗ علۛى الۛجۚادُة ۗ

ام فلان
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
الواجب على المسلمين أن يحذروا وأن يعرفوا أن هؤلاء هم أعداء الإسلام حقيقة-


الشيخ: محمد بن هادي المدخلي
حفظه الله

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#ተማሪነኝ የጀማልሙሀመድ
#አይሸውደኝም የቢድአ መንገድ
#ተማሪነኝ የኡስታዝ ሳዳት
#አይሸውደኝም የሽርክ ኮተት
#ተማሪነኝ የኡስታዝ ሻኪር
#ብሎ አይሸውደኝም ነኝ እኔ ሰይድና ኸድር
#ተማሪነኝ የኡስታዝ ኸድር
#አይሸውደኝም ሀዳዲ ሰፈር
#ተማሪነኝ የኢብኑ ሙነወር
#አያታለኝም የፓለቲካ መንደር
#ተማሪ ነኝ የአቡ ሙስሪም
#አይሸውደኝምየኢኽዋን ቅመም
#ውድ ኡስታዞቸ አላህ ይጠብቃቸው

#መንቁል
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Photo
#የጀናባና_ሐይድ_ትጥበት_ላይ_ፀጉር_መፍታት ~ #አጫጭር_ፈትዋዎች

🪀ከዛዱል መዓድ ፈታዋ ቁ.31 ላይ የ6ኛው ጥያቄ መልስ

➠ጥያቄ ፦

6.የጀናባ እና የሐይድ አስተጣጠብ ልዩነቱ ምንድን ነው? የምንነይተው ነገር አለን?

➠መልስ ፡ 

🔻ለጀናባም ይሁን ለሐይድ ሲታጠቡ እንደዚሁም ዉዱእ ሲያደርጉ ፣ ለጁሙዓ ሲታጠቡ ኒያ ያስፈልጋል። ነገር ግን ሁሉም ላይ በምላስ የሚባል ኒያ የለም። ወንድም ይሁን ሴት ለጀናባ ከሆነ የሚታጠበው ወደመታጠቢያ ቦታ ሲገቡ ለጀናባ እንደሚታጠቡ ወስነው ከገቡ በቂ ነው። ዉዱእ ሲያደርጉም የተወሰኑ የሰውነት አካሎችን የማጥበው ለዉዱእ ብዬ ነው ብሎ ውስጥ ላይ ከወሰኑ ካቀዱ በቂ ነው።
°
🔻የሐይድ እና የጀናባን ትጥበት ልዩነት በተመለከተ የሁለቱም ትጥበቶች አፈፃፀማቸው አንድ ነው። ምናልባት ልዩነት ሊሆን የሚችለው ከሐይድ ጠርታ የምትታጠብ ሴት ፀጉሯ ተሰርቶ ከሆነ ብትፈታው ይመረጣል። አንዳንድ ዑለማዎች ግዴታ ነው ያሉበት ሁኔታም አለ ግን ከማስረጃ አንፃር የተሻለው አቋም ፀጉሯን ሳይፈታ ሰውነቷ ላይ ውኃ ዘልቆ እንደሚነካ እርግጠኛ ከሆነች መፍታቱ ግዴታ አይሆንባትም። ነገር ግን መፍታቱ በላጭ ነው። ይህ አንዱ የጀናባ እና የሐይድ ትጥበት የሚለይበት ሁኔታ ነው። ለጀናባ ከሆነ በየጊዜው መፍታቱ ስለሚከብድ ፍቺ አትባልም ፤ ሐይድ ከሆነ አልፎ አልፎ የሚከሰት ነገር ስለሆነ ብትፈታው ይመረጣል።
°
🔻ሌላው ሁለተኛው ልዩነት ከሐይዷ ጠርታ የምትታጠብ ሴት በምትታጠብበት ጊዜ ማህፀን አከባቢ ላይ ከደሙ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችልን ሽታ ለማስወገድ ለዚህ ነገር የተዘጋጀ እና ልዩ የሆነ ሽቶ መጠቀም እንደምትችል ሐዲስ ላይ ተነግሯል። እነዚህ ሁለቱ የሐይድ እና የጀናባን ትጥበት የሚለዩ ናቸው ፤ በተረፈ ሁለቱም ላይ ግዴታ የሚሆነው መላ ሰውነትን ማስነካት ነው።
°
🔻ከጀናባ ሲታጠቡ ባለማወቅ ፀጉራቸውን ውኃ የማያስነኩ በርካታ ሴቶች አሉ ፤ እንደዚሁ ደግሞ በሁሉም ሁኔታ ላይ ፀጉራቸውን መፍታት ፣ ማበጠር ግዴታ የሚመስላቸው በብዛት ጥያቄ የሚያነሱ ጥቂት የማይባሉ ሴቶችም አሉ። ፀጉርን ውኃ አለማስነካቱ ትልቅ የሆነ ስህተት ነው ፤ ወንጀልም ነው። እንደዚሁ ደግሞ ለሐይድም ይሁን ለጀናባ ሲታጠቡ ሁሌ ፀጉርን መፍታት እና ማበጠር ግዴታ ነው ብሎ ማመንም ራስን ማስቸገር ነው። ሳይፈቱትም ሆነ ሳያበጥሩት ውኃ እንደሚደርስ እርግጠኛ ከሆኑ ምንም ችግር የለውም።

📕ምንጭ ፡ ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.31 የ6 ኛው ጥያቄ ምላሽ ላይ የተወሰደ

✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ 
📆ረቢዐልአወል 11/1442ሂ.
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ወላጆች ሆይ ጥንቃቄ አድርጉ
ሣትፈልግ ሴትን ልጂ ለማትፈልገው ሰው እድራለሁ ብለህ አታስለቅሷት አላህን ፍሩ!!

ያልፈለገችውን እንድታገባ ማስገደድ

ፈትዋ ቁጥር : 279

#ጥያቄ

=>አንዲትን ሴት #የማትወደውንና ከሷ ጋር የማይገጥምን ሰው እንድታገባ #ማስገደድ እንዴት ይታያል ፣ ኒካሁ ተክክል ነው ወይስ አይደለም⁉️

=>መልስ↶

እንደሚታወቀው ምንም ያክል #አባቷ ወይም የሷ ወልይ ካለው #ልምድ እና ለሷ ካለው #እዝነትና ደስታዋን ለማየት ካለው #ጉጉት አንፃር ከሷ በበለጠ መልኩ ለሷ #የተሻለውን ባል የመምረጥ አቅሙና እውቀቱ ቢኖረውም እሷን ግን የማትፈልገውንና ያልወደደችውን ባል #ያለ ፍላጎቷ አስገድዶ መዳር አይፈቀድለትም።

ለዚህም ነብዪ - ﷺ - ሶሒሕ ቡኻሪ ( 4843) ላይ በተዘገው ሀዲሰ ላይ እንዲህ ብለዋል:" (አግብታ የፈታች ሴት)
#ትእዛዟን በመጠየቅ እንጅ አትዳርም ፣ አግብታ የማታውቅ (ቢክራ) ደግሞ #ፍቃዷን በመጠየቅ እንጅ አትዳርም።" (ከዛም ሶሀቦች) እንዲህ አሉ "እሷኮ ታፍራለች?" እሳቸውም እንዲህ አሉ: " ዝምታዋ #ፍቃዷ ነው።"ስለዚህ አባቷም ይሁን ሌላ ወልይ ሆኖ የሚድራት አካል የማትፈልገውን አካል አስገድዶ እንድታገባ ማድረግ #አይፈቀድለትም



ምንጭ↶

=>መጅሙዑል ፈታዊ ፣ ለኢብኒ ተይሚያህ ፣ 32/25 ፣
=> መጅሙዑል ፈታዊ ፣ ለኢብኑ ባዝ ፣ 20/411 ፣ =>አል – ሊቃኡ አሽበህሪይ ፣ 1/343

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ለሞባይል መንዙማ ፓምፍሌት.pdf
917 KB
መውሊድ ላይ የሚባሉት የሺርክ ስንኞች።
በፓምፍሌት መልክ።
🔺👇ጥያቄ👇🔺
♻️ ለመውሊድ ከቁርአን ከሀዲስ መረጃ አለውን

🔺👇መልስ👇🔺
♻️ ኢማሙ ሸውካንይ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ አሉ።
መውሊድ በሸሪአችን የፀደቀ ጉዳይ ነውን በሚል እስከመጨረሻው መረጃን⤵️⤵️
🔺ከቁርአን
🔺ከሀዲስ
🔺ከኢጅማእ
🔺ከቂያስ
🔺ከሌላም አመላካች ነገሮች ፈልጌ አንድ መረጃ አላገኘሁም።
ይልቁንስ ያገኘሁት
♻️ በነዛ በመልካም ዘመን የነበሩ ሶሀቦች
♻️ ከዛም ቀጥሎ በነበሩት ታብእዮች
♻️ ከዛም በኋላ በነበሩት አትባእ ታብእዮች ዘመን የነበሩ ሙስሊሞች በሙሉ መውሊድ ሚባል ነገር ባለመኖሩ ላይ መስማማታቸውን ነው።

📚 الفتح الرباني (2/1087)
የዛሬ ቀን ረቢአል አወል 12 ነብዩ ﷺ የሞቱበት ነው። ይህን ቀን አመታዊ የደስታ ቀን አድርጎ መያዝ ሰይጣናዊ መንገድ ነው። በኢስላም የሙት አመት የሚባልም ነገርም የለም። በኢስላም የታዘዝነውን ብቻ እንስራ። ከክስረት እንጠበቃለንና። ነብዩ ﷺ "ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው" ብለዋል።
copy

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሰይጣን መውሊድ ፋና
Sadat
ሰይጣን መውሊድ ፋና ቲቪ።
በድምፅ ማስረጃ የተደገፈ።
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
የዛሬ ቀን ረቢአል አወል 12 ነብዩ ﷺ የሞቱበት ነው። ይህን ቀን አመታዊ የደስታ ቀን አድርጎ መያዝ ሰይጣናዊ መንገድ ነው። በኢስላም የሙት አመት የሚባልም ነገርም የለም። በኢስላም የታዘዝነውን ብቻ እንስራ። ከክስረት እንጠበቃለንና። ነብዩ ﷺ "ቢድአ ሁሉ ጥመት ነው" ብለዋል።