💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ሼይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -
አሏህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ


➴ዒባዳን ከማብዛት ኢባዳን ማሳመር
(አሳምሮ መስራት) በጣም አሳሳቢ ነው።
(ቡሉጉል መራም ፥ 3/534 )
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
▪️قال النبي ﷺ :

" أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشراً ".


قال المحدث الألباني : حسن
📕السلسلة الصحيحة 1407

https://t.me/https_Asselefya1
Audio
📚ቁርአን በረመዷን አብረንእናኽትም!


➡️ ጁዝ ሃያ አንድ
⬅️الليلة(21) رمضان

🎙الشيخ علي الحذيفي حفظه الله

🎧ይቀጥላል ኢንሻ አላህ .........

https://t.me/https_Asselefya1
Forwarded from التوحيد سبل النجة
ከምላስ ያለፈ ላኢላ ሃኢለሏህ
➴➴➴➴➴➬➬➬➬➴➴➴➴➴

➲ላኢላ ሃኢለሏህ ዘርፈ ብዙ ትሩፍቶች ያቀፈች ቃለ_ተዉሒድ ናትላአላ ሃኢለሏህ ምንም እንኳን ተቆጥረዉ ለማያልቁ በርካታ ቱርፍት ወሳኝ ቁልፍ ብትሆንም ሊስተዋል የሚገባዉ ነገር ግን ከልብ እምነትና ከተግባራዊ ማረጋገጫ የተራቆተ ላኢላ ሃኢለሏህ ፍይዳ_ቢስ መሆኑ ነዉ።

መሰረታዊ መልዕክቶቿን ገሸሽ በማድረግ ከአሏህ ሌላ አካላትን እየተጣሩ ፣እየለመኑ፣ለፍጡር እያረዱ፣በፍጡር እየተመኩ፣ወደ ፍጡር እየሸሹ፣ በምላስ ላኢላ ሃኢለሏህ ቢያስተጋቡት ፋይዳ_ቢስ ነዉ።ይስተዋል ኢስላም ለደረቀ''እመን ትድናለህ''ቦታ የለዉም።

ተዉሒድ በምላስ ጫፍ ተቀባብሎ የሚተኮስ ባዶ ''ሰለምኩ'' አይደለም።

ተዉሒድ ማለት ከሽርክ ሳይርቁ ከጣኦት ሳይፍቱ እንዲሁ ላኢላ ሃኢለሏህ ማነብነብ አይደለም። ነገሩ በምላስ ቢያልቅማ እነ አቡ ጀህል ለሰይፍ አንገታቸዉ ባልሰጡ ነበር

➲ባዶ በምላስ መፈከር ቢሆንማ ቁረይሾች ነብዩን ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም በላያቸዉ ላይ ለማንገስ ወይንም ሴቶች ልጆቻቸዉን ለመስጠት ፣ አለያም ሀብት ንብረታቸዉን ሰብስበዉ ለማስረከብ ጥያቄ ባላቀረቡ ነበር።

ባዶ ላኢላ ሃኢለሏህ ቢጠቅምማ ምናፍቃን በርግጥ ከእሳት በታችኛዉ አዘቅት ዉስጥ ናቸዉ ባልተባለ ነበር። በጭራሺ!!

እርግጥ ነዉ ነብዩ ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም እዳሉት ላኢላ_ሃኢለሏህ ያለ ሰዉ ህይወቱ ንብረቱ የተጠበቀ ነዉ።

የመጨረሻ ንግግሩ ላኢላ ሃኢለሏህ የሆነ ሰዉ የጀነት ነዉ።
➻ላኢላ ሃኢለሏህ ከሰማይ ከምድር የከበደች ቃል ነች።
➻ላኢላ ሃኢለሏህ ነብያት ከተናገሯቸዉ ንግግር ሁሉበላጭ ነች።
➻ላኢላ ሃኢለሏህ ወደ ኢስላም መግቢያ በር፣የጀነት መክፈቻ ቁልፍ ነች። ነገር ግን ላኢላ ሀኢለሏህ በምላስ ከመናገር በተግባር መልዕክቷን ማስገኘት የግድ ይላል።

ወሀብ ኢብኑ ሙነቢህ ረሒመሁሏህ'''ላኢላ ሀኢለሏህ የጀነት ቁልፍ አይደለችም?''ተብለዉ ሲጠየቁ''እሱማ ነች። ነገር ግን ጥርስ የሌለዉ ቁልፍ የለም። ስለዚህ ጥርሶች ያለዉ ቁልፍ ካመጣህ ይከፍትልሀል። አለበለዚያ አይከፍትልህም ብለዉ ነዉ የመለሱት።(ፈትሑል_ባሪ:3/149)እዉነት ብለዋል!

የላኢላ ሃኢለሏህ መስፈርቶች አሏህ ያዘዛቸዉ ህግጋቶች የቁልፉ ጥርሶች ናቸዉ።

➠በአሏህ ላይ ማጋራት፣ ከባባድ ወንጀሎች መፈፀምወይ ቁልፉን ከመሠረቱ የሚያጠፍ ወይ ደግሞ ጥርሶቹን የሚጎዱ ናቸዉ። ለዚህምነበር ሐሰኑል በስሪይ''የሆኑ ሰዎች'' ላኢላ ሃኢለሏህ ያለ ጀነት ገባ'ይላሉ ሲባሉ
``ላኢላ ሃኢለሏህ ብሎ የሷን ሐቆችና ድንጋጌዎች ያደረሰ ጀነት ገባ ያሉት።(ከሊመቱል ኢኽላስ ሊብኒ ረጀብ:13_14)

➧እናም ላኢላ ሃኢለሏህ መመስከር፡ ከአሏህ በስተቀር የሐቅ አምላክ እንዴሌለ ከነ መስፈርቶቿ በተጨባጭ ማስገኛት የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ከእያንዳንዱ ሙስሊም የግድ ሊረጋገጥ የማገባ ሙስሊም የመሆንና ያለ መሆን ወሳኝ ነጥብ ነዉ።

ስለዚህ ~ይቺ የተዉሒድ ቃል ጀነት ለመግባት፣ ከእሳት ለመራቅ ወሳኝ ሰበብ ነች። ነገር ግን ይህ ይሆን ዘንድ መስፈርቶቿ መሟላት አለባቸዉ ማለት ነዉ።{ጃሚዑል ወልሒከም:1/522}

ተዉሒድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ!ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁሏህ መፀሀፍ ከገፀ 106 እስከ107የተወሰዴ!!

«𝐔𝐦𝐮~𝐔𝐬𝐞𝐲𝐦𝐢𝐧»

➤ወደ ቻናላችንJoin ይበሉ ይ ጠ ቀ ማ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ዘካችሁን ለንግድ ባንክ እንዳትሰጡ!
~~~~~ ~~~~~~ ~~~~~~
ባያያዝኩት ማስታወቂያ ላይ እንደምታዩት ንግድ ባንክ ዘካ እሰበስባለሁ እያለ ነው። ንግድ ባንክ ፈፅሞ ለዚህ ኃላፊነት የሚሆን አይደለም። ማንንም የሸሪዐ ቦርድ አድርጎ ስላቀፈ እንዳትሸወዱ። ዘካ ቀልድ አይደለም። ቀላል ሃላፊነትም አይደለም። ወይ በራሳችሁ ወይም ደግሞ ታማኝነቱን በምታውቁት አካል በኩል ብቻ አውጡ።
~
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Audio
◾️ተከታታይ ስለ ረመዷን ዳሰሳ


➡️ የመጃሊሱ ሸህሪ ረመዳን ቂርአት

ክፍል 8⃣8⃣


♦️የመጨረሻ ክፍል

🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
ኢእቲካፍ በምናደርግበት ጊዜ የተወደዱ ተግባሮች
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛

ኢእቲካፍ ከሌሎች ጉዳዮች ራሱን አግልሎ መስጂድ ውስጥ የሚቆይበት ተግባር በመሆኑ በኢእቲካፍ ጊዜ ሰላት፣ ዚክር፣ ዱዓ (ፀሎት)፣ ቁርአን ማንበብ፣ ምህረትን መማፀንና ሌሎችንም አምልኳዊ ተግባራት በብዛት መፈፀም ይወደዳል::

ኢእቲካፍ ለሚፈፅም ሰው የተፈቀዱ ነገሮች
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➧ኢእቲካፍ ላይ ያለ ሰው ምግብ የማይቀርብለት ከሆነ ለመመገብ ለመፀዳዳት ለጀናባ ትጥበትና ውዱእ ለማድረግ ከመስጂድ መውጣት ይፈቀድለታል፡፡

እንዲሁም በጠቃሚ ጉደዮች ከሰው ጋር ማውራት የተፈቀደ ሲሆን ነገር ግን በማይጠቅሙ አሉባልታ ወሬዎች ጊዜውን ማጥፋት ከኢእቲካፍ ዓላማ ጋር ተፃራሪ ነው::ኢእቲካፍ በመፈፀም ላይ ያለን ሰው መጥቶ መጎብኘትና በአንዳንድ ጉዳዮች ማውራት እንግዳውንም ለመሸኘት መውጣት ይፈቀዳል፡፡ ሶፊያ ረድየሏህ ዐንሃ እንዲህ ብላለች

➧“ነቢዩ(ﷺ) ኢእቲካፍ ላይ ባሉበት በምሽት መጥቼ ሰላም ብዬ ትንሽ ካጫወትኳቸው በኋላ ስመለስ ለመሸኘት ተከትለውኝ ወጡ”::አልቡኻሪ (2ዐ35) ሙስሊም (2175)

ኢእቲካፍ ላይ ያለ ሰው የመስጂዱን ንፅህና ጠብቆ መስጂድ ውስጥ መመገብ መጠጣትና መተኛት ይችላል፡፡

ኢእቲካፍን የሚያፈርሱ ነገራቶች
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➲ያለ ምክንያት ከመስጂድ መውጣት የኢእቲካፍ ዋናው መሰረት መስጂድ ውስጥ መቆየት በመሆኑ ያለምክንያት ትንሽ ለመቆየት ቢሆንም እንኳን ሆን ብሎ ከመስጂድ ውጭ መውጣት ኢእቲካፉን ያበላሻል:: አዒሻ ረድየሏህ ዐንሃ እንድህ ብላለች

➲“ነቢዩ(ﷺ) ኢእቲካፍ ላይ ሆነው ለጉዳይ እንጂ ቤት አይገቡም ነበር፡፡”አል ቡኻሪ (2ዐ29)

የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የግብረ ስጋ ግንኙነት በሌሊትና ቤት ውስጥም ቢሆን ኢእቲካፍን ያፈርሳል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፦

▪️وَلَا تُبَـٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَـٰكِفُونَ فِى ٱلْمَسَـٰجِدِ البقرة: ١٨٧

እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው”፡፡አል-በቀራህ 187

ከግብረ ስጋ ግንኙነት ውጭ የዘር ፈሳሽ እንዲፈሰው ማድረግም ኢእቲካፍን ያፈርሳል::

የአእምሮ ጤና ማጣት በእብደት ወይም በስካር አእምሮን ማጣት ኢእቲካፍን ያበላሻል::

የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም መምጣት ኢእቲካፍን ይበላሻል፡፡

ከእስልምና መውጣት፡- ከእስልምና መውጣት ስራን ሙሉ በሙሉ ያበላሻል። አላህ እንዲህ ብሏል፦

▪️لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُك الزمر: ٦٥

“ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል” አል-ዙመር 65

ምንጭ፦አል ፊቅሕ ሙየሰር

🖊ام فاروق

ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
📚ቁርአን በረመዷን አብረንእናኽትም!


➡️ ጁዝ ሃያ ሁለት
⬅️الليلة(22) رمضان

🎙الشيخ علي الحذيفي حفظه الله

🎧ይቀጥላል ኢንሻ አላህ .........

https://t.me/https_Asselefya1
اللهمّ إنّكَ عفوٌ تُحب العَفو فَاعفُ عنّا.
▪️قال الإمام أحمد رحمه الله:

سامح أخاك
وما ينفعك أن يعذب الله أخاك المسلم بسببك.

📓سير أعلام النبلاء (٢٦٢/١١)