💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ①⑧➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ማንኛውም በዱንያ ላይ ለሚደርስብን መከራ፣ ስቃይ፣ ችግር፣ ሙሲባና ስብራት መጠገኛውና መካሻው ጀነት ውስጥ ነው። ብቻ በሶብር ላይ እንበርታ!
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➳መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አስራ አምስት قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ ۗ قُلْ إِنِّي أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ «ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው…
➽መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ⓵⓺

➲እናት፡- በአላህ አምና እና እሱን ፈርታ፣ የባሏን ሃቅ ጠብቃ፣ ልጆቿን በስነ ስርዐት ካሳደገች የአላህ ወልይ ናት።

➛ልጅ፡- ልጆች በአላህ አምነውና እሱን ፈርተው፣ ለወላጆቻቸው ታዝዥ ሆነው፣
ወላጆቻቸውን ካገዙ የአላህ ወልዮች ናቸው።

➛ነጋዴው፡- ኢማንና ተቅዋን አስገኝቶ ንግዱን በአግባቡ ነግዶ፣ ከሃላል ከስቦ፣ ዘካውን ካወጣ ይህ የአላህ ወልይ ነው። ወዘተ….

➧ደግሞም ወልዮች የሚበላለጡት በኢማናቸው እና ለአላህ ባላቸው ፍራቻ ነው።

➲ታላላቆቹ የአላህ ወልዮች ነብዮች ናቸው። ከነብዮቹም ውስጥ መልክተኞቹ ናቸው።ከመልክተኞቹም ውስጥ አምስቱ የቁርጠኝነት ባለቤቶች የሚባሉት ቁንጮዎች ናቸው።ከአምስቱ የቁርጠኝነት ባለቤቶች ውስጥ ደግሞ የሁሉ ቁንጮ የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ ናቸው።صلى الله عليه وسلم ለምን ይህን አርእስት እዚህ መጸሀፍ ላይ ማንሳት አስፈለገ? ምክንያቱም አገራችን
ላይ በብዛት ከአላህ ውጭ አምልኮ የሚፈጸምላቸው “ወልዮች” ተብለው የሚገመቱ ሰዎችን ነው።
አንዳንዶች በድፍረት “ወልዮች ነብያትን ይበልጣሉ” ሁሉ ይላሉ። ይሄ የሰዎቹ ቅጥፈትና ድፍረት የት እንደደረሰ የሚያሳይ ነው።

➲ዛሬ በተገላቢጦሹ ማህበረሰባችን ዘንድ ከእምነት ክፍል ብዙ የሚያጓድሉ፣ክህደትን እና ሺርክን (ለምሳሌ የሚጠነቁሉና ትንቢት ተናጋሪ ነን የሚሉ፣ የሚያጓሩ) እያጨማለቁ፣ በኢስላም ንፅህና የኢማን ግማሽ ሆኖ ሳለ በተገላቢጦሽ ንፅህናቸውን
የማይጠብቁ፣ ሶላት ወይ ከነጭራሹ የማይሰግዱ ወይም ደግሞ ጀመአ የማይገኙ ወልይ ተብለው የሚገመቱ ብዙ ወንበዴዎች አሉ።


እንዲህ አይነቱ የሰይጣን ወልይ እንጂ
በፍፁም የአላህ ወልይ አይደለም።

➧ረመዳንን ምንዳውን ምን ያጓድለዋል?
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➤ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት ውስጥ አንዱ ነው። ረመዳን የቁርኣን
ወር ነው። ረመዳን የሰደቃ ወር ነው። ረመዳን ተራዊህ የሚሰገድበት ወር ነው። ረመዳን ብዙ መልካም ስራዎች የሚሰሩበት ወቅት ነው። ረመዳን ቁርኣን የወረደበት ወር ለመሆኑ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል


شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ

➧የረመዳን ወር ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት)
ከሚለዩም ገላጮች ሲሆን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው።
” [አልበቀራህ: 185]

➛በዚህ በተከበረ የቁርኣን ወር የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم (ከጂብሪል ዐለይሂ-ስሰላም ጋር አንድ ጊዜ እየተቃሩ ሙሉ 30 ጁዝ ቁርኣንን ይጨርሱ ነበር። የሞቱ አመትም ሁለት ጊዜ ጨርሰዋል።
◉

◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል..........

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➤ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴
➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1
Muhammad al Muqit سورة الدخان - محمد المقيط | AD-DUKHAN (THE SMOKE)…
Quran Cure for the Hearts
➧ትልቅ ቅጣት ማለት ባንተና በቁርአን መረዳት መካከል እገዳ መኖር ነው!

﴿وَجَعَلْنَا عَلَى قُلُوبِهِمْ أَكِنَّةً أَنْ يَفْقَهُوهُ وَفِي آذَانِهِمْ وَقْراً﴾

" በልቦቻቸውም ላይ እንዳያውቁት ሺፋኖችን በጆሮዎቻቸውም ላይ ድንቁርናን አደረግን ፡፡"
[አንዓም 25]

➧ቁርአንን ልክ ንፁህ ያልሆነ ሰው
እንደማይነካው


➮ንፁህ ልብ የሌለውም የቁርአንን መረዳትና ጥፍጥናውን አያገኝም

➮የምንሰራቸው ወንጀሎች ከቁርአን እያራቁንና ልቦቻችንን አድርቀው
እያቆሸሹብን ይገኛሉ
ኢስቲግፋር ወደ አላህ መመለስ እናብዛ አላህ ወደርሱ ይመልሰን ።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌹ተጋበዙልኝ🌹

➲ቁረአንን ላስተነተነው ሰው የማይጠገብ የአላህ ፀጋ ልብን የሚያረጋጋ ሀሳብን የሚያስረሳ ያአላህ ... የአርሹ ጌታ ልባችንን በዚህ በማይጠገበው ቃሉ ያለምልምልን ይሙላልን ሀቂቃ ለአወቀው ሰው እኮ እንደ ቁረአን የደስታ ሰበብ የለምምምም!
ጠፊዋ ዱኒያ የማይጠገበውን የአላህ ፀጋ ጀነትን እንዳታሳጣን ጌታችንን እንለምነው ወደ ጌታችን እንመለስ!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
✅የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمእንድህ አሉ፣

▪️የመጨረሻ ሶላታችሁን በለሊት ዊትር አድርጉ !
📚ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ①⑨➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
۞ أَتَأْمُرُونَ النَّاسَ بِالْبِرِّ وَتَنسَوْنَ أَنفُسَكُمْ وَأَنتُمْ تَتْلُونَ الْكِتَابَ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ሥራ ታዛላችሁን? ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን? (የሥራችሁን መጥፎነት) አታውቁምን?

📚ሱረቱል በቀራ 44
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➽መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ⓵⓺ ➲እናት፡- በአላህ አምና እና እሱን ፈርታ፣ የባሏን ሃቅ ጠብቃ፣ ልጆቿን በስነ ስርዐት ካሳደገች የአላህ ወልይ ናት። ➛ልጅ፡- ልጆች በአላህ አምነውና እሱን ፈርተው፣ ለወላጆቻቸው ታዝዥ ሆነው፣ ወላጆቻቸውን ካገዙ የአላህ ወልዮች ናቸው። ➛ነጋዴው፡- ኢማንና ተቅዋን አስገኝቶ ንግዱን በአግባቡ ነግዶ፣ ከሃላል ከስቦ፣ ዘካውን ካወጣ ይህ የአላህ ወልይ ነው።…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➭ክፍል ⓵⓻

➢አላህ ሙሉ ምንዳ የሚከፍለው ረመዳንን አምኖ፣ ሂሳቤን አላህ ይከፍለኛል ብሎ፣ መልካምን በመስራት ከአልባሌ ነገሮች በመራቅ ነው። የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم )እንዲህ ብለዋል፡

قَالَ رَسُوْل اللّٰه صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم :- مَن لَم يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ والعَمَلَ بِهِ فَلَيْسَ لِلَّهِ حاجَةٌ فِي أَنْ يَدَع طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ

➧“አንድ ባሪያ የቅጥፈት ወሬን እና በሱ መስራትንም ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን ከመተው አላህ ደንታ የለውም።”
አል- ቡኻሪ

➮ተራ ቅጥፈቶች ለዚህ የሚዳርጉ ከሆነ ሺርክ እና ቢድአ ደግሞ ከነዚህ ሁሉ የባሰ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው። ይህ ሆኖ ሳለ ዛሬ በሃገራችን በተውሒዱ ወር በረመዳን ሰው ቁርኣን እየቀራ እንዳያሳልፍ መንዙማ ባዮች በየቋንቋው ሺርክ፣ ጭፈራ እና ብዙ ጉድ ያለባቸውን መንዙማዎች ይዘው በየመስጂዱ እና ገበያ ቦታ ላይ ከታላቅ ማስታወቂያ ጋር ብቅ ይላሉ። ሀስቡነላህ ወኒእመል ወኪል። ይሄ እንደዋዛ ሊታይ የማይገባው አደገኛ ጥፋት ነው።

➳ብዙዎቻችን ግን ጥፋቱ ከመንሰራፋቱ፣ ዘወትር ከመሰማቱ የተነሳ ጆሯችን ለምዶት ውስጣችን እስከማይደፈርስ ደርሷል።

➧ሌላው አገራችን ላይ አንዳንድ መስጊዶች ለአፍጥር ሰኣት 30 ደቂቃ ሲቀረው በሚያሳዝን ሁኔታ ማይክሮፎን ከፍተው በአላህ ላይ የማጋራትን ንግግር በአንድነት በዜማ ሲያስተጋቡ ይስተዋላሉ። ለምሳሌ እንዲህም ይላሉ፡-

“ኹዝ ቢየዲ ያረሱለላሀ፣ አጊስና ያረሱለላህ”

➛ትርጉሙም


➛“አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! እጄን ያዙኝ። አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርዱን (አጠጡን?)።”ፆሞ ውሎ በሺርክ ማፍጠር ምንኛ ልብ ያደማል?!

➲መንዙማ እና መውሊድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧መውሊድ ማለት የአንድን ግለሰብ የተወለደበት ቀን አመት ጠብቆ ማክበር ማለት ነው። የነብያት ሁሉ ሃይማኖት እስልምና የማንም ግለሰብ የልደት በአል እንዲከበር አልደነገገም።

➠ በእስልምና አንድ ሰው ልጅ ሲወለድለት ለጌታው ምስጋና ለማቅረብ እና ደስታውን ለመግለጽ ልጅ በተወለደለት በሰባተኛው ወይንም በአስራ አራተኛው ወይንም በቻለ ጊዜ ወንድ ከተወለደለት ሁለት በግ ወይንም ፍየል፣ ሴት ከተወለደለት አንድ በግ ወይንም ፍየል ያርዳል። ከወዳጅ ከዘመዶቹም ጋር በጋራ ይመገበዋል።

➳ አላህ የደነገገው እንግዲህ ይህን ነው።ከዚህ ውጭ ያለውና ከሱና ባፈነገጡት ሺአዎች የተጀመረው የሺርክ መነሀሪያ የሆነው መውሊድ ግን ቢድአ ነው። እዚሁ መውሊድ የሚሉት ላይ “ሀድራ”፣“መንዙማ” እየተባለ እዚሁ መፅሀፍ ላይ ወደፊት የምናያቸው በርካታ ጥፋቶች ይፈፀማሉ።
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📖መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➧ ጥሩ ፀሐፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!

📩ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
በሀላል መንገድ ኒካህ ማሰር አጅር የሚያስገኝና ሪዝቅን የሚያሰፋ ሲሆን በተቃራኒው ከኒካህ በፊት የሚደረግ የሀራም ግኑኝነት ግን ወንጀል ሲሆን ሪዝቅንም ያጠባል።

አላህ ሆይ! በነገራቶች ሁሉ ሀላሉን ወፍቀን ከሀራም ጠብቀን
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➖የሱረቱል ኢህላስ ትርጉም
➖የሱረቱል ኢህላስ ትሩፋት
➖ኢስባትና ነፍይ በተመለከተ

➰ክፍል ②∅➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (MuhammedSirage MuhammedNoor)
የሰዎች ኢስላምና ተውሒድ አላጠግብህ ብሎት የዘር ሃረጋቸውን መመዘኛ ያደረገ ሁሉ በጉዳዩ ላይ የታላቁን ነብይ ሳይሆን የታላቁን ከሃዲ የአቡ ጀህልን ና የመሠሎቹን ኮቴ በመከተል ላይ ነው!
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ⓵⓻ ➢አላህ ሙሉ ምንዳ የሚከፍለው ረመዳንን አምኖ፣ ሂሳቤን አላህ ይከፍለኛል ብሎ፣ መልካምን በመስራት ከአልባሌ ነገሮች በመራቅ ነው። የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم )እንዲህ ብለዋል፡ قَالَ رَسُوْل اللّٰه صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم :- مَن لَم يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ والعَمَلَ بِهِ…
➛መንዙማ
➬➬➬➬➬

➲ክፍል አስራ ስምንት

➧ከዚህ ውጭ ያለውና ከሱና ባፈነገጡት ሺአዎች የተጀመረው የሺርክ መነሀሪያ የሆነው መውሊድ ግን ቢድአ ነው። እዚሁ መውሊድ የሚሉት ላይ “ሀድራ”፣ “መንዙማ"እየተባለ እዚሁ መፅሀፍ ላይ ወደ ፊት የምናያቸው በርካታ ጥፋቶች ይፈፅማሉ::

➲ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል፡-
“ከንግግር ሁሉ በላጭ የአላህ ንግግር ነው፣ ምርጥ የሚባለው መመሪያ
የሙሐመድ صلى الله عليه وسلم መመርያ ነው፤ ከነገሮች ሁሉ የከፋው (በዲን ላይ) ፈጠራ ነው፤ ፈጠራ
የተባለ ሁሉ ቢድዐ ነው፤ ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።”
[ሙስሊም፡ ]867

➧ሰርጋችን እስልምና ውብና የተሟላ የህይወት መመሪያ ነው። ትልልቅ የህይወታችን ክፍሎች ቀርቶ ትንንሽ የሚባሉት እራሱ ዝርዝር መመሪያ ተቀምጦላቸዋል። አንዳንዶች ግን ይህን እውነታ በመዘንጋት ወይም ችላ በማለት ከሸሪአው መመሪያ ወጥተው በራሳቸው ሲጓዙ ያጋጥማሉ። ለምሳሌ ሰርግን ብንወስድ ምን መምሰል እንዳለበት፣ ምን መባል እንዳለበት፣ ሙስሊሞች በሰርግ ላይ እንዴት መደሰት እንዳለባቸው ሸሪአ ጠቁሞናል።

➩ሆኖም ግን ዛሬ ከሳቸው ንግግር እና ከኢስላም በተቃራኒ ኢስላማዊ ዲጄ እየተባለ፣ የሺርክ መንዙማዎች እየተዜሙ፣ ወንዶች እየጨፈሩ እና እያጨበጨቡ፣ ሴቶች ባልተፈቀደላቸውየሙዚቃመሳሪያእየጨፈሩ፣ሴትእናወንድ ተቀላቅለው እየጨፈሩ፣ እያፏጩ ወዘተ ታላቁን የደስታ ቀን አላህን በማመጽ የሚያሳልፉት አሉ።

➲የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ይህን ታላቅ የደስታ ቀን ኒካሁ እንደታሰረ ለሙሽራው እና ለሙሽሪቷ “ባረከላሁ ለኩማ ወባረከ አለይኩማ ወጀመኣ በይነኩማ ፊ ኸይር” ተብሎ ዱአ እንደሚደረግላቸው ከውዱ ነብይ (صلى الله عليه وسلم) ፈለግ ተምረናል። ይህንን ዱአ ያደረጉት ለኡመቱ ታማኝ እና አዛኝ መካሪ የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم) ናቸው።

➧ልብ እንበል! አሁንም ይህንኑ ዱአ በሙዚቃ መሳሪያ እና በጭፈራ “ባረከላሁ ለኩማ” ብለን ካልቀወጥነው “ለቅሶ ቤት እኮ አይደለም የመጣነው”፣ “የእነ እገሌ ዘፋኝን ከመስማት አይሻልም ወይ?” የሚሉ አሉ። ይሄ አደብ የቀለለው አነጋገር ነው። ሙስሊም ማለት ለፈጣሪው ህግ እጅ የሚሰጥ ነው። ሙስሊም ማለት የሶሐቦችን አርአያ የሚከተል ነው። ሶሐቦች ሰርጋቸውን የጋጠ ወጦች አይነት ካላደረግን “ለቅሶ ቤት” ይሆንብናል የሚሉ ግብዞች አልነበሩም።

➲የደስታ ቀንን እንዴት ጌታቸውን እያመሰገኑ ማሳለፍ እንዳለባቸው ስለሚያውቁ በነብዩ ሱና መሰረት ነው የተጓዙት። صلى الله عليه وسلم

➣መንዙማ ድሮ እና ዘንድሮ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭አብዛኞች ከሚሸወዱባቸው ነገሮች ውስጥ “የድሮ መንዙማ እና የአሁን መንዙማ ይለያያሉ”፣“የድሮመንዙማዎችሺርክአለባቸው”፣“ድቤአላቸው”፣“የአሁኖቹ ደግሞ እንጎርጉሮ የሆነም አለ”፣ “ድቤ ያለውም ከሽርከ የጸዳ ነው” የሚሉ አሉ።

◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል......

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➳አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

በተለያዩ እውቀቶች ይጠቀሙ ዘንድ ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ!!

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➖የአየተል ኩርስይ ትርጉም
➖የአየቱል ኩርስይ ትሩፋት

➰ክፍል ②①➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w