💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Kitabu Tewhid #51
Ibnu Munewor
↪️ ተከታታይ የኪታቡ ተውሒድ ደርስ


↪️ርዕስبَابُ قَوْلِ اللَّهِ تَعَالَى: ﴿وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَندَادٗا يُحِبُّونَهُمۡ كَحُبِّ ٱللَّهِۖ ﴾ [البقرة: 165]



↪️ ክፍል 5⃣1⃣↩️


🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔻حفظه الله تعالى
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሀሰኑል በስሪይ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦

የአንድን ሙስሊም ሃጃ(ጉዳይ) መፈፀሜ አንድ ሺህ ረከዓን ከመስገድ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው፡፡
[ቀዷኡል ሃዋኢጅ 48].

https://t.me/abumahi13
Audio
◾️አዝካር ወል አዳብ

🔻الأذكار والآداب


➡️ የሀያእ አስፈላጊነት
➡️ ኒቃብ ግዴታ መሆኑ
➡️ አይንን ከሀራም መስበር
➡️ አጅነብይ ማየት በተመለከተ
➡️ ከሴት ጋር ለብቻ ማግለል

↪️ ክፍል 4⃣4⃣ ↩️


🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አራት ➠ሩህ” የተባለው ጅብሪል ነው፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጆች ልቦና ህያው የሚሆንበትን ቁርኣን በማውረዱ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ምድራዊ ዓለምም ይሁን በወዲያኛው ዓለም ትክክለኛ ህይዎትን ለመጎናጸፍ በእውቀትም ይሁን በተግባር በዚህ የተባረከ መጽሐፍ ባለን ድርሻ አማካኝነት የሚወሰን መሆኑን ማወቅ በእያንዳንዳችን ላይ ግዴታ ይሆናል፡፡ …
የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

➭ክፍል አምስት

ከመሳሳት ነጻ ሆነ ማለት ቅን የሆነውን ጎዳና ተመራ ማለት ነው፡፡ ከውስብስብ ችግሮች ነጻ ሆነ ማለት ደግሞ መልካም ህይዎትን ተጎናጸፈ ማለት ነው፡፡ ቅኑን ጎዳናእንዲሁም መልካምን ህይዎት ለመጎናጸፍ የፈለገ ቁርኣንን አጥብቆ ይያዝ፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

●طه ◍مَا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لِتَشْقَىٰ

“(ጧሃ) ቁርኣንን ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም፡፡” ጧሃ፡1_2

የዚህ ቁርኣን ትርጉም ፣ ይህን ቁርኣን በአንተ ላይ ያወረድነው በመልካም ነገሮችእንድትጎናጸፍ ነው፡፡ በአንዳንድ የቁርኣን ተርጓሚዎች ዘንድ ደግሞ የሚከተለው ትርጉም ተሰጦታል፡

ቁርኣን በረሡል صلى الله عليه وسلم ላይ እንደወረደ ረሡል صلى الله عليه وسلم እና ባልደረቦቻቸው ተግባራዊ ለማድረግ በጽናት ቆሙ፡፡ “ይህን ቁርኣን በሙሐመድ ላይ አልወረደም ሊቸገር እንጅ”በማለት ቁረይሾችና የመካ አጋሪዎች ተናገሩ፡፡ ይህን አባባላቸውን ለማስተባበል የሚከተለውን ቁርኣን አላህ አወረደ፡

طه ◍مَا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لِتَشْقَىٰ
“(ጧሃ) ቁርኣንን ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም
፡፡” ጧሃ፡1_2

ይህ ማለት ፡ ቁርኣንን በአንተ ላይ ያወረድነው ልናስቸግርህ ሳይሆን መልካምን ነገር ልናጎናጽፍህ ነው። መልካምን መጎናጸፍ ፣ ደስተኛ ህይዎትን መኖር ፣ የዲንና የእምነትን ጣፋጭነት መቅመስ የሚቻለው የጌታችንን መጽሐፍ ቁርኣንን አጥብቀን ስንይዝ ብቻ ነው፡፡

ተፍሲር ኢብኑ ከሲር፡ ባሮች ትክክለኛ የሆነውን ጣፋጭነት ለመቅመስ ቁርኣንን በማስተንተን ማንበብ እንዳለባቸው አላህ በተለያዩ የቁርኣን አንቀጾች ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ አስተንትኖ ያነበበ ፣ በውስጥ ያቀፈውን መልክት የተገነዘበ ፣ ትርጉሙን ያወቀ ካልሆነ በቀር የቀርኣንን ጣፋጭነት መቅመስ የሚችልና በእርሱ ተጠቃሚ የሚሆን ሰው አንድም ሊኖር አይችልም፡፡ የቁርኣን ተንታኞች ቁንጮ የሆኑት ኢማም ጦበሪ የሚከተለውን
ተናግረዋል፡-


"إني أعجب ممن قرأ القرآن ولم يعلم تأويله كيف يلتذ بقراءته؟"

➧“ትርጉሙን ሳያውቅ ቁርኣንን የሚያነብ ሰው ያስገርመኛል ፤የቁርኣኑን ጣፋጭነት እንዴት ሊያጣጥም ይችላል?”በሙዕጀም አል አድባን ያቁት አልሃመዊይ አውርተውታል፡6/2435

➧የተከበረውን ቁርኣን አስተንትነን እንድናነበው የሚያዙ በርካታ የቁርኣን አንቀጾች ወርደዋል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጹ የሚከተለውን ተናግሯል:
أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡አኒሳዕ 82

أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ أَمْ عَلَىٰ قُلُوبٍ أَقْفَالُهَا

ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አልሉባትን
?ሙሀመድ 24
كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ
(ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡ሷድ 29

➢ኢንሻአላህ ይቀጥላል..........

📚አንብብ!ተጠቃሚ ትሆናለህ

https://t.me/https_Asselefya1
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ሁለት


በአላህ ፈቃድ ይህችን አጭር ማስታወሻ በውስጣቸው አርእስቶች የያዙ ሁለትዋና ክፍሎች አድርጌ አዘጋጅቻታለሁበክፍል አንድ መግቢያ እና መንደርደሪያ፣የተፈጠርንለትን አላማ (ተውሒድን)፣ እዚህ ምድር ላይ የሰው ልጆች እንዴት በአላህ ላይ ማጋራት እንደጀመሩ፣ በፍጡራን እና በፈጣሪ አላህ መሃል ያለው ታላቅ ልዩነት፣አምልኮ ለማን እንደሚገባው እና ከማንስ ላይ መግፈፍ መንፈግ እንዳለብን፣ ነብያት በምን መልእክት እንደተላኩ፣ ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ለምን አይነት ሰዎች እንደተላኩ፣የሺርክን አስከፊነት በአጭሩ የተቃኘበት ክፍል ነው።

ክፍል አንድ ላይ የተዘረዘሩት አንኳር ነጥቦች ክፍል ሁለት ላይ ያሉት የሺርክ፣
የክህደት ስንኞች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ለሙስሊሙ ኡማ ማስገንዘቢያ የሚሰጡ መንደርደሪያ ናቸው።
አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ሀቅን በሃቅነቱ እንዲያሳየን የምንቀበለውም እንዲያደርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ እንዲያሳየን የምንርቀውም እንዲያደርገን ጌታችንን አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እለምነዋለሁ።

የሰው ልጆች እንዴት በአላህ ላይ ማጋራት ጀመሩ?
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

ወንጀልን ወንጀል ይበልጠዋል። ለምሳሌ ዝሙት ከታላላቅ ወንጀሎች ውስጥ ነው። አንድ ሰው ከሌላ ሴት ጋር ዝሙት መስራቱ እና ከእናቱ ጋር ዝሙት መስራቱ በጣም ልዩነት አለው። እናቱን መገናኘቱ ይከፋል። ልክ እንደዚሁ የሰው ልጅም ይሁን አጋንንት የተፈጠሩበት ዋና አላማ አላህን በብቸኝነት ለመገዛት ነው

ይህንን የተፈጠሩለትን ታላቅ አላማ ተቃርነው በእርሱ በአላህ ላይ ቢያጋሩ ታላቁን በደል ሰርተዋል። የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم ከወንጀሎች ሁሉ ታላቁ እና የከፋው የትኛውእንደሆነ ሲጠየቁ “እሱ አላህ ፈጥሮህ ሲያበቃ በእርሱ አላህ ላይ ብጤን ሸሪካን ልታደርግለት ነው” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 4477፣ ሙስሊም፡ 86]

አላህ ዘንድ ታላቁ ወንጀል ምን እንደሆነ በሰፊው ሊዳሰስ ይገባል። አላህ በእያንዳንዱ ህዝብ መሃል መልክትኞቹን መጽሀፍ አስይዞ የሚልክበት ዋና መልእክት በምን እንደሚደፈርስ ሊታወቅ ይገባዋል።

በምን ምክንያት የሰው ልጆች የተፈጠሩለትን አላማ ተቃርነው፣ የአባታችንን አደም ንጹህ የተውሒድ መንገድ ተቃርነው፣ በብቸኛው
ፈጣሪያችን እና አምላካችን አላህ ላይ ፍጡራንን አማልክት አድርገው ያዙ?


📚መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ



ኢንሻአላህ ሀሳቡ ይቀጥላል

ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋልና አንብብ!!
=
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ የምስጋና ምንነትን በተመለከተ

ክፍል ③


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
◾️አቡልጀውራእ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ።

➡️ ሙናፊቅ የሆነ ሰው ቁርአን ከሚቀራ ቋጥኝ መንቀል ይቀለዋል።
📚حلية الأولياء (ج ١ ص ٤٥٩)

➲ቁርአን መቅራት ኢባዳ እንደሆነ ሁሉ በጥሩ ንያ ማዳመጥም አጅር የሚገኝበት ኢባዳ ነው።


➲ጆሮህ ሁሌ የሚሰማውና የለመደውን ነገር ስለሚጠይቅህ፦ ሙዚቃ፣ ነሺዳና መንዙማ አስለምደህ ሱሰኛ ከምታደርገው ቁርአንና ሀዲስ ማዳመጥን አስለምደው።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️አዝካር ወል አዳብ

🔻الأذكار والآداب

➡️ ሰከራተል ሞት
➡️ አላህን መገናኘት
➡️ የሙእሚን የሩህ አወጣጥ
➡️ የካፊርና አመፀኛ ሩህ አወጣጥ

↪️ ክፍል 4⃣5⃣ ↩️


የሰውን ነብስ እንዲያወጣ የሚታዘዘው መላኢካ መለከል መውት ነው በዚህ ኦድዮ ላይ ጅብሪል ብዬ የተጠቀምኩት የምላስ ወለምታ ነውና አስተካክሉት።

🩸የመጨረሻ ክፍል

🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲አንተ"ትዳር ፈላጊ ወንድሜ ሆይ!!አመራረጥህን አሳምር።
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

قَال الشيخ ابن عثيمين - رحمه الله - :

>إذَا وُفق الإنسان لِامرَأة صالِحة فِي دينِها وعقلِها فهَذا خيرُ متَاعِ الدُّنيا.

ሰውየው በዲኗ እና በአስተሳሰቧ መልካም ሴትን(ሚስትን)ከተገጠመ፡ይህ የዱኒያ መልካም መጣቀሚያ ነው።

شرح رياض الصالحين : (549)

https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
📚ሸይኽ ሱለይማን አር-ሩሃይሊ ሐፊዘሁላህ እንዲ ይላሉ፦

[💎 الـمـرأة الـصـالـحـة إذا سَكَنتِ
البيتَ سَكَنَ البَيتُ 💎]


💎አንድ ቤት መልካም ሷሊህ ሴት ስታርፍበት ቤቱ የረጋ ይሆናል!!

📚المصدر: محاضرة بعنوان أسباب نجاح الأسرة
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሁለት ➭በአላህ ፈቃድ ይህችን አጭር ማስታወሻ በውስጣቸው አርእስቶች የያዙ ሁለትዋና ክፍሎች አድርጌ አዘጋጅቻታለሁ። በክፍል አንድ መግቢያ እና መንደርደሪያ፣የተፈጠርንለትን አላማ (ተውሒድን)፣ እዚህ ምድር ላይ የሰው ልጆች እንዴት በአላህ ላይ ማጋራት እንደጀመሩ፣ በፍጡራን እና በፈጣሪ አላህ መሃል ያለው ታላቅ ልዩነት፣አምልኮ ለማን እንደሚገባው…
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ሶስት


ከሰው ልጆች ሁሉ አባት ነብዩላህ አደም (አለይሂ ሰላም)እስከ መጀመሪያው መልእክተኛ ኑሕ(አለይሂ ሰላም)ድረስ አስር ክፍለ ዘመን ነበር።በዚህ ወቅት የሰው ልጆች ሁሉ በአንድ ሃይማኖት በእስልምና ውስጥ ነበሩችግሩ የተፈጠረው አንድነቱ የፈረሰው ኑሕ(አለይሂ ሰላም) የተላኩባቸው ሰዎች በደጋጎች ላይ ድንበር አልፈው የባእድ አምልኮት ላይ ሲወድቁ ግዜ ነው

🔁በዚህም የተነሳ አዛኙ አላህ እነዚያ ህዝቦች የተፈጠሩለትን አላማ ያውቁ ዘንድ የመጀመሪያውን መልእክተኛ ኑሕ (አለይሂ ሰላም)ወደ ተውሂድ እንዲጠሯቸው ላካቸውኑሕም(አለይሂ ሰላም) ዘጠኝ መቶ ሀምሳ አመት የተውሂድ ጥሪ እንዲቀበሉ ይህን የተቀበለም ብስራት እንዳለው ፣ከአላህ ውጭ ሌላ አካል እሚፈጽሙትን አምልኮ እንዲርቁ ይህን ካላደረጉ ከባድ አደጋ እንደሚያጋጥማቸው በማስጠንቀቅ ተጣሩ።

ልብ እንበል የሰይጣ ወጥመዱ ከባድ ነው። በአንድ ሀይማኖት ላይ የነበሩትን ህዝቦች በታተናቸው። አብዛሀኛዎቹ የመጀመሪያውን መልእክተኛ ኑሕ ጥሪ አንቀበልም ብለው ለጥፋት ተዳረጉ።

አላሁ(ሱብሀነሁተዓላ )የነዚህን አጋሪያን (መጥፎ ፉጡሮች) መጨረሻ ከባድ የሆነ ቅጣት ቀጥቷቸው ከባድ አደጋንም ተከናነቡ። ጥፋታቸው ከባድ ስለነበረ በአላህ ትእዛዝ ሰማይ የያዘችውን ውሃ ለቀቀች ።ምድር የያዘችውን ውሃ ተፋች፣ተራራ የሚያካክሉ ፣ማእበሎች ተነስተው እነዚህ ሁሉ አመጸኞች ውርደትን ቀመሱ። በሁለት አገርም ተዋረዱ።

📘ዝግጅት መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ።

°
°
°
ኢንሻአሏህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

✏️መጻፍ ካልቻልክ አንብብብ‼️ማንበብ የተሻለ ሰው ያድርጋል።

⤵️ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ቀጣይ ክፍሎችን ይከታተሉ።

ጆይን በማለት ተጠቃሚይ ሁኑ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
ከምላስ ያለፈ ላኢላ ሃኢለሏህ
➴➴➴➴➴➬➬➬➬➴➴➴➴➴

➲ላኢላ ሃኢለሏህ ዘርፈ ብዙ ትሩፍቶች ያቀፈች ቃለ_ተዉሒድ ናትላአላ ሃኢለሏህ ምንም እንኳን ተቆጥረዉ ለማያልቁ በርካታ ቱርፍት ወሳኝ ቁልፍ ብትሆንም ሊስተዋል የሚገባዉ ነገር ግን ከልብ እምነትና ከተግባራዊ ማረጋገጫ የተራቆተ ላኢላ ሃኢለሏህ ፍይዳ_ቢስ መሆኑ ነዉ።

መሰረታዊ መልዕክቶቿን ገሸሽ በማድረግ ከአሏህ ሌላ አካላትን እየተጣሩ ፣እየለመኑ፣ለፍጡር እያረዱ፣በፍጡር እየተመኩ፣ወደ ፍጡር እየሸሹ፣ በምላስ ላኢላ ሃኢለሏህ ቢያስተጋቡት ፋይዳ_ቢስ ነዉ።ይስተዋል ኢስላም ለደረቀ''እመን ትድናለህ''ቦታ የለዉም።

ተዉሒድ በምላስ ጫፍ ተቀባብሎ የሚተኮስ ባዶ ''ሰለምኩ'' አይደለም።

ተዉሒድ ማለት ከሽርክ ሳይርቁ ከጣኦት ሳይፍቱ እንዲሁ ላኢላ ሃኢለሏህ ማነብነብ አይደለም። ነገሩ በምላስ ቢያልቅማ እነ አቡ ጀህል ለሰይፍ አንገታቸዉ ባልሰጡ ነበር

ባዶ በምላስ መፈከር ቢሆንማ ቁረይሾች ነብዩን ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም በላያቸዉ ላይ ለማንገስ ወይንም ሴቶች ልጆቻቸዉን ለመስጠት ፣ አለያም ሀብት ንብረታቸዉን ሰብስበዉ ለማስረከብ ጥያቄ ባላቀረቡ ነበር።

ባዶ ላኢላ ሃኢለሏህ ቢጠቅምማ ምናፍቃን በርግጥ ከእሳት በታችኛዉ አዘቅት ዉስጥ ናቸዉ ባልተባለ ነበር። በጭራሺ!!

እርግጥ ነዉ ነብዩ ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም እዳሉት ላኢላ_ሃኢለሏህ ያለ ሰዉ ህይወቱ ንብረቱ የተጠበቀ ነዉ።

የመጨረሻ ንግግሩ ላኢላ ሃኢለሏህ የሆነ ሰዉ የጀነት ነዉ።
➻ላኢላ ሃኢለሏህ ከሰማይ ከምድር የከበደች ቃል ነች።
➻ላኢላ ሃኢለሏህ ነብያት ከተናገሯቸዉ ንግግር ሁሉበላጭ ነች።
➻ላኢላ ሃኢለሏህ ወደ ኢስላም መግቢያ በር፣የጀነት መክፈቻ ቁልፍ ነች። ነገር ግን ላኢላ ሀኢለሏህ በምላስ ከመናገር በተግባር መልዕክቷን ማስገኘት የግድ ይላል።

ወሀብ ኢብኑ ሙነቢህ ረሒመሁሏህ'''ላኢላ ሀኢለሏህ የጀነት ቁልፍ አይደለችም?''ተብለዉ ሲጠየቁ''እሱማ ነች። ነገር ግን ጥርስ የሌለዉ ቁልፍ የለም። ስለዚህ ጥርሶች ያለዉ ቁልፍ ካመጣህ ይከፍትልሀል። አለበለዚያ አይከፍትልህም ብለዉ ነዉ የመለሱት።(ፈትሑል_ባሪ:3/149)እዉነት ብለዋል!

የላኢላ ሃኢለሏህ መስፈርቶች አሏህ ያዘዛቸዉ ህግጋቶች የቁልፉ ጥርሶች ናቸዉ።

➠በአሏህ ላይ ማጋራት፣ ከባባድ ወንጀሎች መፈፀምወይ ቁልፉን ከመሠረቱ የሚያጠፍ ወይ ደግሞ ጥርሶቹን የሚጎዱ ናቸዉ። ለዚህምነበር ሐሰኑል በስሪይ''የሆኑ ሰዎች'' ላኢላ ሃኢለሏህ ያለ ጀነት ገባ'ይላሉ ሲባሉ
``ላኢላ ሃኢለሏህ ብሎ የሷን ሐቆችና ድንጋጌዎች ያደረሰ ጀነት ገባ ያሉት።(ከሊመቱል ኢኽላስ ሊብኒ ረጀብ:13_14)

➧እናም ላኢላ ሃኢለሏህ መመስከር፡ ከአሏህ በስተቀር የሐቅ አምላክ እንዴሌለ ከነ መስፈርቶቿ በተጨባጭ ማስገኛት የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ከእያንዳንዱ ሙስሊም የግድ ሊረጋገጥ የማገባ ሙስሊም የመሆንና ያለ መሆን ወሳኝ ነጥብ ነዉ።

ስለዚህ ~ይቺ የተዉሒድ ቃል ጀነት ለመግባት፣ ከእሳት ለመራቅ ወሳኝ ሰበብ ነች። ነገር ግን ይህ ይሆን ዘንድ መስፈርቶቿ መሟላት አለባቸዉ ማለት ነዉ።{ጃሚዑል ወልሒከም:1/522}

ተዉሒድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ!ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁሏህ መፀሀፍ ከገፀ 106 እስከ107የተወሰዴ!!

«𝐔𝐦𝐮~𝐔𝐬𝐞𝐲𝐦𝐢𝐧»

Join ይበሉ ይ ጠ ቀ ማ ሉ ሺርር

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1