💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ የ«بسم الله» ትርጉም
☑️ የ«الله» ትርጉም በሰፊው
☑️ የ«الرحمن الرحيم» ማብራሪያ

ክፍል ②


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
መንዙማ
➫➫➫➫➫

◾️ተከታታይ ፅሁፍ


➧ክፍል አንድ


ከንግግር ሁሉ በላጭ የአላህ ንግግር ነው። ምርጥ የሚባለው መመሪያ የሙሐመድ صلى الله عليه وسلم መመርያ ነው። ከነገሮች ሁሉ የከፋው በዲን ላይ ፈጠራ ነው። ፈጠራ የተባለ ሁሉ ቢድዐ ነው። ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።

ይህች አጠር ያለች መፅሐፍ በአላህ ፍቃድ አብዛኛው ሰው ዘንድ የሚደመጠው “መንዙማ” ውስጥ የተገኙትን የክህደት፣ በአላህ ላይ ማጋራት ሺርክ ፣ ከአላህ ጌትነት፣ አምላክነት፣ ስምና መገለጫዎች ጋር የሚጋጩ፣ በአላህ ላይ እና በሸሪዓተል ኢስላም ላይ የተዋሹ ቅጥፈቶችን የያዙ ስንኞችን እና ሌሎችንም በማስረጃ መልስ የምሰጥባቸው እና ማህበረሰቡ ከዚህ አስከፊ አደጋ እራሱን እና ቤተሰቡን ይጠብቅ ዘንድ አቅጣጫ የምጠቁምባት ናት።

በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ይህችን አጠር ያለች መልእክት ሳዘጋጅ የተጠቀምኩት ቋንቋ እና መልእክት በተቻለ መጠን ለህዝበ ሙስሊሙ የሚገባ እና ቀላል ለማድረግ ጥሬያለሁ።

ከምንም በፊት እምነትን ማስተካከል ይቀደማል። እምነት ደግሞ በአላህ አንድነትና ብቸኝነት በማመን እና ከእርሱ ውጭ በሚመለኩት በጠቅላላ በመካድ ቢሆን እንጂ ሊስተካከል አይችልም። አላህ እንዲህ ይላል

فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

➧በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ አል በቀራህ 256

ማስረጃዎቼን ከስህተት ከፀዳው የአላህ ቃል ቁርኣን፣ የአላህ ጥበቃ ከማይለያቸው መልክተኛው صلى الله عليه وسلم ሱና፣ ከመልካም ቀደምቶች እና የነሱን መልካም አርዓያ የተከተሉትን አስተምህሮት ለማድረግ መርጫለሁ። ምክንያቱም ከጥመት የመዳኛው ብቸኛው መንገድ ይህ ስለሆነ

📚 (መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ)




📖አንብብ !! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል።

ኢንሻአላህ
ይቀጥላል……
=
https://t.me/https_Asselefya1
Kitabu Tewhid #51
Ibnu Munewor
↪️ ተከታታይ የኪታቡ ተውሒድ ደርስ


↪️ርዕስبَابُ قَوْلِ اللَّهِ تَعَالَى: ﴿وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَندَادٗا يُحِبُّونَهُمۡ كَحُبِّ ٱللَّهِۖ ﴾ [البقرة: 165]



↪️ ክፍል 5⃣1⃣↩️


🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔻حفظه الله تعالى
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሀሰኑል በስሪይ አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦

የአንድን ሙስሊም ሃጃ(ጉዳይ) መፈፀሜ አንድ ሺህ ረከዓን ከመስገድ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው፡፡
[ቀዷኡል ሃዋኢጅ 48].

https://t.me/abumahi13
Audio
◾️አዝካር ወል አዳብ

🔻الأذكار والآداب


➡️ የሀያእ አስፈላጊነት
➡️ ኒቃብ ግዴታ መሆኑ
➡️ አይንን ከሀራም መስበር
➡️ አጅነብይ ማየት በተመለከተ
➡️ ከሴት ጋር ለብቻ ማግለል

↪️ ክፍል 4⃣4⃣ ↩️


🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አራት ➠ሩህ” የተባለው ጅብሪል ነው፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጆች ልቦና ህያው የሚሆንበትን ቁርኣን በማውረዱ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ምድራዊ ዓለምም ይሁን በወዲያኛው ዓለም ትክክለኛ ህይዎትን ለመጎናጸፍ በእውቀትም ይሁን በተግባር በዚህ የተባረከ መጽሐፍ ባለን ድርሻ አማካኝነት የሚወሰን መሆኑን ማወቅ በእያንዳንዳችን ላይ ግዴታ ይሆናል፡፡ …
የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

➭ክፍል አምስት

ከመሳሳት ነጻ ሆነ ማለት ቅን የሆነውን ጎዳና ተመራ ማለት ነው፡፡ ከውስብስብ ችግሮች ነጻ ሆነ ማለት ደግሞ መልካም ህይዎትን ተጎናጸፈ ማለት ነው፡፡ ቅኑን ጎዳናእንዲሁም መልካምን ህይዎት ለመጎናጸፍ የፈለገ ቁርኣንን አጥብቆ ይያዝ፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

●طه ◍مَا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لِتَشْقَىٰ

“(ጧሃ) ቁርኣንን ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም፡፡” ጧሃ፡1_2

የዚህ ቁርኣን ትርጉም ፣ ይህን ቁርኣን በአንተ ላይ ያወረድነው በመልካም ነገሮችእንድትጎናጸፍ ነው፡፡ በአንዳንድ የቁርኣን ተርጓሚዎች ዘንድ ደግሞ የሚከተለው ትርጉም ተሰጦታል፡

ቁርኣን በረሡል صلى الله عليه وسلم ላይ እንደወረደ ረሡል صلى الله عليه وسلم እና ባልደረቦቻቸው ተግባራዊ ለማድረግ በጽናት ቆሙ፡፡ “ይህን ቁርኣን በሙሐመድ ላይ አልወረደም ሊቸገር እንጅ”በማለት ቁረይሾችና የመካ አጋሪዎች ተናገሩ፡፡ ይህን አባባላቸውን ለማስተባበል የሚከተለውን ቁርኣን አላህ አወረደ፡

طه ◍مَا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لِتَشْقَىٰ
“(ጧሃ) ቁርኣንን ባንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም
፡፡” ጧሃ፡1_2

ይህ ማለት ፡ ቁርኣንን በአንተ ላይ ያወረድነው ልናስቸግርህ ሳይሆን መልካምን ነገር ልናጎናጽፍህ ነው። መልካምን መጎናጸፍ ፣ ደስተኛ ህይዎትን መኖር ፣ የዲንና የእምነትን ጣፋጭነት መቅመስ የሚቻለው የጌታችንን መጽሐፍ ቁርኣንን አጥብቀን ስንይዝ ብቻ ነው፡፡

ተፍሲር ኢብኑ ከሲር፡ ባሮች ትክክለኛ የሆነውን ጣፋጭነት ለመቅመስ ቁርኣንን በማስተንተን ማንበብ እንዳለባቸው አላህ በተለያዩ የቁርኣን አንቀጾች ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ አስተንትኖ ያነበበ ፣ በውስጥ ያቀፈውን መልክት የተገነዘበ ፣ ትርጉሙን ያወቀ ካልሆነ በቀር የቀርኣንን ጣፋጭነት መቅመስ የሚችልና በእርሱ ተጠቃሚ የሚሆን ሰው አንድም ሊኖር አይችልም፡፡ የቁርኣን ተንታኞች ቁንጮ የሆኑት ኢማም ጦበሪ የሚከተለውን
ተናግረዋል፡-


"إني أعجب ممن قرأ القرآن ولم يعلم تأويله كيف يلتذ بقراءته؟"

➧“ትርጉሙን ሳያውቅ ቁርኣንን የሚያነብ ሰው ያስገርመኛል ፤የቁርኣኑን ጣፋጭነት እንዴት ሊያጣጥም ይችላል?”በሙዕጀም አል አድባን ያቁት አልሃመዊይ አውርተውታል፡6/2435

➧የተከበረውን ቁርኣን አስተንትነን እንድናነበው የሚያዙ በርካታ የቁርኣን አንቀጾች ወርደዋል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጹ የሚከተለውን ተናግሯል:
أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡አኒሳዕ 82

أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ أَمْ عَلَىٰ قُلُوبٍ أَقْفَالُهَا

ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አልሉባትን
?ሙሀመድ 24
كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ
(ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡ሷድ 29

➢ኢንሻአላህ ይቀጥላል..........

📚አንብብ!ተጠቃሚ ትሆናለህ

https://t.me/https_Asselefya1
መንዙማ
➫➫➫➫➫

ክፍል ሁለት


በአላህ ፈቃድ ይህችን አጭር ማስታወሻ በውስጣቸው አርእስቶች የያዙ ሁለትዋና ክፍሎች አድርጌ አዘጋጅቻታለሁበክፍል አንድ መግቢያ እና መንደርደሪያ፣የተፈጠርንለትን አላማ (ተውሒድን)፣ እዚህ ምድር ላይ የሰው ልጆች እንዴት በአላህ ላይ ማጋራት እንደጀመሩ፣ በፍጡራን እና በፈጣሪ አላህ መሃል ያለው ታላቅ ልዩነት፣አምልኮ ለማን እንደሚገባው እና ከማንስ ላይ መግፈፍ መንፈግ እንዳለብን፣ ነብያት በምን መልእክት እንደተላኩ፣ ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ለምን አይነት ሰዎች እንደተላኩ፣የሺርክን አስከፊነት በአጭሩ የተቃኘበት ክፍል ነው።

ክፍል አንድ ላይ የተዘረዘሩት አንኳር ነጥቦች ክፍል ሁለት ላይ ያሉት የሺርክ፣
የክህደት ስንኞች ምን ያህል አደገኛ እንደሆኑ ለሙስሊሙ ኡማ ማስገንዘቢያ የሚሰጡ መንደርደሪያ ናቸው።
አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ሀቅን በሃቅነቱ እንዲያሳየን የምንቀበለውም እንዲያደርገን፣ ባጢልን በባጢልነቱ እንዲያሳየን የምንርቀውም እንዲያደርገን ጌታችንን አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እለምነዋለሁ።

የሰው ልጆች እንዴት በአላህ ላይ ማጋራት ጀመሩ?
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

ወንጀልን ወንጀል ይበልጠዋል። ለምሳሌ ዝሙት ከታላላቅ ወንጀሎች ውስጥ ነው። አንድ ሰው ከሌላ ሴት ጋር ዝሙት መስራቱ እና ከእናቱ ጋር ዝሙት መስራቱ በጣም ልዩነት አለው። እናቱን መገናኘቱ ይከፋል። ልክ እንደዚሁ የሰው ልጅም ይሁን አጋንንት የተፈጠሩበት ዋና አላማ አላህን በብቸኝነት ለመገዛት ነው

ይህንን የተፈጠሩለትን ታላቅ አላማ ተቃርነው በእርሱ በአላህ ላይ ቢያጋሩ ታላቁን በደል ሰርተዋል። የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم ከወንጀሎች ሁሉ ታላቁ እና የከፋው የትኛውእንደሆነ ሲጠየቁ “እሱ አላህ ፈጥሮህ ሲያበቃ በእርሱ አላህ ላይ ብጤን ሸሪካን ልታደርግለት ነው” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 4477፣ ሙስሊም፡ 86]

አላህ ዘንድ ታላቁ ወንጀል ምን እንደሆነ በሰፊው ሊዳሰስ ይገባል። አላህ በእያንዳንዱ ህዝብ መሃል መልክትኞቹን መጽሀፍ አስይዞ የሚልክበት ዋና መልእክት በምን እንደሚደፈርስ ሊታወቅ ይገባዋል።

በምን ምክንያት የሰው ልጆች የተፈጠሩለትን አላማ ተቃርነው፣ የአባታችንን አደም ንጹህ የተውሒድ መንገድ ተቃርነው፣ በብቸኛው
ፈጣሪያችን እና አምላካችን አላህ ላይ ፍጡራንን አማልክት አድርገው ያዙ?


📚መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ



ኢንሻአላህ ሀሳቡ ይቀጥላል

ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋልና አንብብ!!
=
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም


➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ የምስጋና ምንነትን በተመለከተ

ክፍል ③


🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
◾️አቡልጀውራእ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አለ።

➡️ ሙናፊቅ የሆነ ሰው ቁርአን ከሚቀራ ቋጥኝ መንቀል ይቀለዋል።
📚حلية الأولياء (ج ١ ص ٤٥٩)

➲ቁርአን መቅራት ኢባዳ እንደሆነ ሁሉ በጥሩ ንያ ማዳመጥም አጅር የሚገኝበት ኢባዳ ነው።


➲ጆሮህ ሁሌ የሚሰማውና የለመደውን ነገር ስለሚጠይቅህ፦ ሙዚቃ፣ ነሺዳና መንዙማ አስለምደህ ሱሰኛ ከምታደርገው ቁርአንና ሀዲስ ማዳመጥን አስለምደው።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️አዝካር ወል አዳብ

🔻الأذكار والآداب

➡️ ሰከራተል ሞት
➡️ አላህን መገናኘት
➡️ የሙእሚን የሩህ አወጣጥ
➡️ የካፊርና አመፀኛ ሩህ አወጣጥ

↪️ ክፍል 4⃣5⃣ ↩️


የሰውን ነብስ እንዲያወጣ የሚታዘዘው መላኢካ መለከል መውት ነው በዚህ ኦድዮ ላይ ጅብሪል ብዬ የተጠቀምኩት የምላስ ወለምታ ነውና አስተካክሉት።

🩸የመጨረሻ ክፍል

🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲አንተ"ትዳር ፈላጊ ወንድሜ ሆይ!!አመራረጥህን አሳምር።
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

قَال الشيخ ابن عثيمين - رحمه الله - :

>إذَا وُفق الإنسان لِامرَأة صالِحة فِي دينِها وعقلِها فهَذا خيرُ متَاعِ الدُّنيا.

ሰውየው በዲኗ እና በአስተሳሰቧ መልካም ሴትን(ሚስትን)ከተገጠመ፡ይህ የዱኒያ መልካም መጣቀሚያ ነው።

شرح رياض الصالحين : (549)

https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
📚ሸይኽ ሱለይማን አር-ሩሃይሊ ሐፊዘሁላህ እንዲ ይላሉ፦

[💎 الـمـرأة الـصـالـحـة إذا سَكَنتِ
البيتَ سَكَنَ البَيتُ 💎]


💎አንድ ቤት መልካም ሷሊህ ሴት ስታርፍበት ቤቱ የረጋ ይሆናል!!

📚المصدر: محاضرة بعنوان أسباب نجاح الأسرة
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w