💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
◾️አዝካር ወል አዳብ

🔻الأذكار والآداب


➡️ የሀሜት አስከፊነት
➡️ ሰዎችን ለማሳቅ መዋሸት
➡️ ሰዎችን በፊታቸው ማወደስ
➡️ ጥሩ ስነምግባርና ምንዳዎቹ

↪️ ክፍል 4⃣1⃣ ↩️


🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌹قصيدةُ أنا السّلفي يا أبتِ لحسّانة إبنة الشيخ ابن باز رحمه ﷲ🌹
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Kitabu Tewhid #50
Ibnu Munewor
↪️ ተከታታይ የኪታቡ ተውሒድ ደርስ


↪️ርዕስمسائل:
بَابُ مَا جَاءَ فِي الاسْتِسْقَاءِ بِالْأَنْوَاءِ


↪️ ክፍል 5⃣0⃣↩️


🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔻حفظه الله تعالى
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧“የተዘረጋው የአላህ ገመድ” የሚለው ስያሜ ክቡር ለሆነው የአላህ ቁርኣን የተሰጠ ስያሜ ሲሆን ስያሜው በነብዩ صلى الله عليه وسلم ትክክለኛ ሐዲስም ተረጋግጦ ይገኛል፡፡

فقد روى الإمام مسلم في "صحيحه" من حديث زيد بن أرقم رضي الله عنه أن النبي صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم قال: "ألا وإني تارك فيكم ثقلين : أحدهما كتاب الله عز وجل ، هو حبل الله، من اتبعه كان على الهدى ، ومن تركه كان على ضلالة"

በሙስሊም ዘገባ ዘይድ ብን አርቀም رضي الله عنه የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡-

➠“ንቁ! እኔ በእናንተ ውስጥ ሁለት ታላላቅ ነገሮችን ትቸላችኋለሁ፡፡ አንደኛው የአላህ ኪታብ ነው፡፡ እርሱም የአላህ ገመድ ነው፡፡ እርሱን የተከተለው በቅን ጎዳና ላይ ይሆናል፡፡ እርሱን የተወው ደግሞ በጥመት ላይ ይሆናል፡፡” ሙስሊም፡ (2408)

"وروى الإمام أحمد في "مسنده" من حديث أبي سعيد الخدري رضي الله عنه أن النبي صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم قال: "كتاب اللّٰه حبل ممدود من السماء إلى الأرض"

ኢማም አህመድ በዘገቡት ደግሞ አቡሰዒድ አል'ኹድርይ ረድየሏሁ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

➠“የአላህ መጽሐፍ ከሰማይ ወደምድር የተለቀቀ የአላህ ገመድ ነው፡፡” አህመድ፡11104 ቲርሚዚይ፡3788

وروى ابن أبي شيبة في "مصنفه" من حديث أبي شريح الخزاعي رضي الله عنه أن النبي صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم قال: "أبشروا أبشروا ، أليس تشهدون أن لا إله إلا الله وأني رسول الله ؟" قالوا : نعم ، قال : "فإن هذا القرآن سبب طرفه بيد الله، وطرفه بأيديكم فتمسكوا به ، فإنكم لن تضلوا ، ولن تهلكوا بعده أبدا"

ኢብን አቢ ሸይባ በዘገቡት አቡ'ሹረይህ አል'ኹዛዒይ ረድየሏሁ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

➲“አብሽሩ! አብሽሩ! ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ፣ እኔም የአላህ መልክተኛ እንደሆንኩ ትመሰክራላችሁ አይደል?” በማለት ረሡል صلى الله عليه وسلمሶሃቦችን ጠየቁ
፡፡ ሶሃቦችም “አዎ!” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ የአላህ መልክተኛም “ይህ ቁርኣን ገመድ ነው፡፡ አንዱ ጫፍ በአላህ እጅ ነው ፤ ሌላኛው ጫፍ ደግሞ በእናንተ እጅ ነው፡፡

እርሱን አጥብቃችሁ ያዙ ፣ ከእርሱ በኋላ ፍጹም አትጠፉም” በማለት ተናገሩ፡፡ ሙሰነፍ ሊብኒ አቢ ሸይባ፡ አልባኒ ሐዲሱን በሙስሊም መስፈርት ሶሂህ ነው ብለውታል አስ ሶሂህ፡

وروى الدارمي عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه أنه قال : "إن هذا الصراط محتضر تحضره الشياطين ينادون يا عبد الله هذا الطريق ، فاعتصموا بحبل الله ، فإن حبل الله القرآن"
አድ ዳሪሚይ በዘገቡት ዓብደሏህ ብን መስዑድ ረድየሏሁ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

➳“ይህ (ቀጥተኛ የኢስላም) መንገድ ሰይጣናት ይገኙበታል ፤ (ሰይጣናት) “አንተ የአላህ ባሪያ ሆይ! ቀጥተኛ ያልሆነውን መንገድ ይህ ትክክለኛው መንገድ ነው” እያሉ ጥሪ ያደርጋሉየአላህን ገመድ አጥብቃችሁ ያዙ ፤የአላህ ገመድ በእርግጥ ቁርኣን ነው” አድ ዳሪሚይ፡ 3360

➢ኢንሻአላህ
ይቀጥላል

https://t.me/https_Asselefya1
Audio
📚 አዲስ የተጀመረ ኪታብ
~~~~~~~~~~~~~~~~

#ኡሱሉ_አስሱናህ

📓 متن أصول السنۃ

إمام أحمد بن حنبل رحمه الله

ክፍል => 1⃣

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ልጄን ልዳረው ወይ Fejr Ena Zeweje
Sheh Fewzan
ልጄን ልዳረው ወይ

የሸኽ ፈውዛን አስደማሚ መልስ

የሴት ልጅ አባት አስተዋይነት ስንቶች ይሁን ኢሄን ጥያቄ ሚጠይቁት በልጃቸው ትዳር ላይ

ትርጉም፦
በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ
Audio
◾️አዝካር ወል አዳብ

🔻الأذكار والآداب


➡️ ወደ ኸይር ማመላከት
➡️ ለሰዎች መልካም መዋል
➡️ መተናነስና ዝቅ ማለት

↪️ ክፍል 4⃣2⃣ ↩️


🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ወንድማችን ኸዲር አሕመድ ከሚሴን አሁን ስልክ ደውሎ አጊንቼዋለሁ። አካባቢው ሰላም ነው ብሎኛል። አብዛኛው የሚወራው ነገር ውሸት ነውና አትሸበሩ። ዱ0 ላይ እንበርታ።
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧“የተዘረጋው የአላህ ገመድ” የሚለው ስያሜ ክቡር ለሆነው የአላህ ቁርኣን የተሰጠ ስያሜ ሲሆን ስያሜው በነብዩ صلى الله عليه وسلم ትክክለኛ ሐዲስም ተረጋግጦ ይገኛል፡፡ فقد روى الإمام مسلم في "صحيحه" من حديث زيد بن أرقم رضي الله عنه أن النبي صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم قال: "ألا…
የተዘረጋ የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ክፍል ሁለት

ይህ ፣ የተዘረጋ ገመድ (ቁርኣን) የሰውን ልጅ ለመምራት ፣ ለማስተካከል አማኞችን ለመገሰጽ ፣ በደረቶች ውስጥ ያለውን በሽታ ለመፈወስ ፣ ለቁርኣን ባለቤቶች በረከትን ፣ ብርሃንን እና ነጸብራቅን ለማጎናጸፍ አላህ ያወረደው መንገድ
ነው
፡፡

➧አሏህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡


كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ይህ ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡


إِنَّ هَٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ وَيُبَشِّرُ الْمُؤْمِنِينَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا كَبِيرًا

ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለእነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል፡፡

قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ ۚ قَدْ جَاءَكُم مِّنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُّبِينٌ◍يَهْدِي بِهِ اللَّهُ مَنِ اتَّبَعَ رِضْوَانَهُ سُبُلَ السَّلَامِ وَيُخْرِجُهُم مِّنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ بِإِذْنِهِ وَيَهْدِيهِمْ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

➻ “ከአላህ ዘንድ ብርሐንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ አላህ
ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገዶች በእርሱ ይመራቸዋል፡፡
በፈቃዱም ከጨለማዎች ወደ ብርሐን ያወጣቸዋል፡፡ ወደ ቀጥተኛም መንገድ
ይመራቸዋል፡፡” አ
ል ማኢዳህ፡
ቁርኣንን ፣ ለሰዎች ሒዎት ለስነ-ምግባራቸው ፣ ለስነ-ስርዓታቸው ፣ ለማህበራዊ ሒዎታቸው ፣ ለአምልኳቸው ፣ በአጠቃላይ ወደአላህ ለመቃረብ የሚጓዙበት ጎዳና አድርጎ አላህ አውርዶታል
፡፡
ለዚህ ነው የአማኞች እናት ዓኢሻ ረድየላህ አንሃ ስለነብዩ صلى الله عليه وسلم ስነ-ምግባር በተጠየቀች ጊዜ የሚከተለውን ምላሽ የሰጠችው፡-
"كان خلقه القرآن"

ስነ-ምግባራቸው ቁርኣን ነበር” አህመድ፡

ማንኛውም በቁርኣን ውስጥ የአምልኮት ፣ የስነ-ምግባር ፣ የስነ-ስርዓት ፣የማህበራዊ ህይዎት እና የሌሎችም ሰዎች የሚገለጹባቸው ባሕሪያት አይኖርም ፣የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚገለጹበት ቢሆን እንጅ፡፡ ረሡል صلى الله عليه وسلم ከሰዎች ሁሉ አላህን በጣም ተገዥ ፣ በብዛት ፈሪው ፣ በከፍተኛ ሁኔታ ተጠንቃቂው ፣ በስነ-ምግባራቸው የተሟሉ ፣ ስርዓታቸው በጣም ያማረ ፣ ከሰዎች ጋር የነበራቸው ማህበራዊ ግንኙነት መልካም የነበሩ ናቸው፡፡

➛ኢንሻአላህ
ይቀጥላል◉◉◉◉◉
https://t.me/https_Asselefya1
أصول السنۃ ٢.mp3
Abu Useymin
📚 አዲስ የተጀመረ ኪታብ
~~~~~~~~~~~~

#ኡሱሉ_አስሱናህ

📓 متن أصول السنۃ

إمام أحمد بن حنبل رحمه الله

ክፍል => 2⃣

🎙 አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
PDF ለማገኘት⤵️⤵️⤵️
https://t.me/Asselefya1/2926
https://t.me/Asselefya1/2926
❝ የስኬትሽ ሚስጥር
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
⇓ ⇓

የአንድ አማኝ ሴት መልካምነት
(ሳሊህነት) መገለጫ


አምልኮን ባማረ መልኩ
በመፈፀም ወደ አላህ መቃረብና
በአምልኮ ላይ በመፅናት
ከጌታዋ ጋር ያላትን ግንኙነት
መልካም ማድረጓ ነው።

ይህ ሳሊህ ሴት ለመሆኗ ለፅናቷ
የስኬት ሚስጥሮች ናቸው።


【 ሸይኽ አብዱረዛቅ በድር 】
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የተዘረጋ የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➳ክፍል ሁለት ➧ይህ ፣ የተዘረጋ ገመድ (ቁርኣን) የሰውን ልጅ ለመምራት ፣ ለማስተካከል አማኞችን ለመገሰጽ ፣ በደረቶች ውስጥ ያለውን በሽታ ለመፈወስ ፣ ለቁርኣን ባለቤቶች በረከትን ፣ ብርሃንን እና ነጸብራቅን ለማጎናጸፍ አላህ ያወረደው መንገድ ነው፡፡ ➧አሏህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ…
የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯➯

➻ክፍል ⓷

➧ኢብን አል'ቀይም ረሂመሁሏህ - “ቲብያን ፊ አቅሳሚል ቁርኣን” በሚለው መጽሐፋቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
➳ይህ ፣ ከቁርኣን ብርሐን የተወሰደ የሆነው የረሡል صلى الله عليه وسلم ስነ-ምግባር ነው፡፡ ንግግራቸው ከቁርኣን ጋር የሚስማማ ፣ ለእርሱም ዝርዝር ማብራሪያ ነው፡

እውቀቶቻቸው የቁርኣን እውቀቶች ናቸው፡፡ ፍላጎታቸውና ተግባራቸው ቁርኣን ግዴታ ወይም የተወደደ ያደረገው ነው፡፡ መራቃቸው ወይም መተዋቸው ከእርሱ ቁርኣን የከለከለውን ወይም እንዲርቁት ያዘዘውን ነው፡፡ፍላጎታቸው የቁርኣን ፍላጎት ነው፡፡ የተውት ፣ ቁርኣን የተወውን ወይም ትኩረት ያልሰጠውን ነው፡፡ ጥላቻቸው እርሱ የጠላውን ነው ፡፡ እርሱ የወደደው ውዴታቸው ነው፡፡ እንቅስቃሴያቸውና ትግላቸው ትዕዛዙን ለመፈጸም ፣መልክቱን ለማድረስ ፣ የእርሱን ህግጋት ቀጥ ለማድረግ ነው፡፡ አሁን ያሳለፍነውን ሁሉ በቁርኣንና በረሡል صلى الله عليه وسلم እውቀት የተካነችው የሙእሚኖች እናት በአማረ አገላለጽ እንደሚከተለው ገልጻዋለች፡-
"كان خلقه القرآن"
“ስነ-ምግባራቸው ቁርኣን ነበር”አት ቲብያን ፊ አቅሳሚል ቁርኣን፡ ገፅ፡ 196

➲ይህ የአማኖች ስንቅ ፣ የቀልባቸው ሩህ የነፍሳቸው መብቃቂያ ነው፡፡ የሰው ልጅ ትክክለኛ የሆነውን ህይዎት በተከበረው ቁርኣን ካልሆነ በቀር በሌላ መንገድ
ሊያገኘው አይችልም
፡፡ ለዚህ ነው አላህ ቁርኣንን በበርካታ ቦታዎች “ሩህ” በማለት የጠራው፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን ቁርኣንን አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን መንፈሱን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡አሹራ 52


أَتَىٰ أَمْرُ اللَّهِ فَلَا تَسْتَعْجِلُوهُ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ●يُنَزِّلُ الْمَلَائِكَةَ بِالرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ أَنْ أَنذِرُوا أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاتَّقُونِ

➧“የአላህ ትዕዛዝ መጣ ይመጣል ፤ ስለዚህ አታስቸኩሉት፤ ከማይገባው ሁሉ
ጠራ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ ፤ ከባሮቹም በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል፡፡”
አን ነሕል፡1_2

➠ጌታችን አላህ ጥበበኛ የሆነውን ወህይ ፤ ታላቅ የሆነውን ተግሳጽ ፣ የተከበረውን
ቁርኣን “ሩህ” በማለት ሰይሞታል፡፡
ትክክለኛ የልቦና ህይዎት በቁርኣን እንጅ በሌላ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ ወህይ የሚያወርድ የሆነውን መላኢካ - ጅብሪልን - “ሩህ” በማለት ጠርቶታል ፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡
نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ

እርሱን ታማኙ መንፈስ (ጂብሪል) አወረደው፤አሽ ሹዕራእ193

●تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ
በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡አል ቀደር 4

ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን
ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ!!


◉◉◉◉ኢንሻአላህ ይቀጥላል

https://t.me/https_Asselefya1
︎قال عبد الله بن مسعود -رضي الله عنه-:

• لا تسألن امرءا عن وده، وانظر ماله في قلبك، فإن لك في قلبه مثل ذلك.

➧አብደሏህ ቢን መስዑድ "رضي الله عنه"እንዲህ አሉ፦አንድን ሰው ለአንተ ስላለው ውዴታ አትጠይቀው
በአንተ ልብ ውስጥ ያለውን ቦታ እዪ
በእሱም ልብ ውስጥ ተመሳሳይ ቦታ አለህ!

📙[اعتلال القلوب (٢٣٧)].

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w