💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ትዕግስት ➖➖➖➖ ➽ክፍል አራት 〰〰〰〰〰 ➥ይህ ፣ ሰዎች በሚያደርሱት መከራ ላይ ለመታገስ ከሚያግዙ ነገሮች ሁለተኛው ከዚህ በፊት ባሳለፍነው ነጥብ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የባሮች ስራ ፍጡር መሆኑን ካስተዋለ ፣ በእርሱ ላይ መከራ እንዲመጣ ያደረገውን አካል ከተመለከተ ሰዎችን ከመውቀስ ፣ ከማማረር ይልቅ በእኔ ላይ የደረሰብኝ መከራ ነፍሴ በፈጸመችው…
➲ትዕግስት "الصبر"
〰〰〰〰〰〰

➳ክፍል አምስት
➖➖➖➖➖

➳ሰዎች በሚያደርሱት መከራ ለሚታገሱና ይቅር ለሚሉ ሰዎች አላህ ቃል የገባው ምንዳ እንዳለ ማረጋገጥ ነው፡፡

➽የትዕግስት ደረጃዎች ሁለት
ሲሆኑ አንዱ ከሌላው ከፍ ያለ ደረጃ አለው፡፡ የመጀመሪያው ፡ ሰዎች በሚያደርሱት መከራ ላይ መታገስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በደል እየተፈጸመበት ይቅርታ ማድረጉ ነው፡፡ ይቅር ማለት ከትዕግስት ደረጃዎች ላቅ ያለው ደረጃ ነው
፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

●وَالْعَافِينَ عَنِ النَّاسِ ۗ وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ


“ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሰሪዎችን
ይወዳል” አል ዒምራን፡ 140

➠ይህ ደረጃ ማንም ሊደርስበት የማይችለው የኢህሳን (የበጎ ሰሪነት) ደረጃ ነው፡፡ ከዚህ ደረጃ የሚደርሱት በጎ ሰሪና የአላህ ቅርብ ባለሟሎች ናቸው
፡፡

➲ለዚህ አጋዥ የሚሆነው ታጋሾች አጅር ወይም ምንዳ እንዳላቸው ማረጋገጡ ነው፡፡ ከአላህ ዘንድ ያለውን ምንዳ ተስፋ አድርጎና ቋምጦ ሰዎች በሚያደርሱበት ስቃይ ሁሉ ታጋሽ በመሆን ከአላህ ዘንድ የሚያገኘውን ምንዳ ተስፋ አድርጎ ሰዎችን ይቅር ማለት ነው፡፡ አላህ ይቅር
የሚሉ ሰዎችን ይወዳል
፡፡

ሸይኹ ራሂመሁሏህ የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ ለማስረጃነት አቅርበዋል፡-

● وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ

“የመጥፎም ነገር ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም፡፡” (አሽ’ሹራ፡ 40
)

➠በዚህ አንቀጽ መሰረት ሰዎች ከሚደርስባቸው መከራ አኳያ በሶስት ደረጃዎች ይከፈላሉ፡-

የመጀመሪያው ደረጃ፡- መጥፎ ድርጊት ሲፈጸምባቸው በተመሳሳይ የሚበቀሉ ናቸው፡፡
ድንበር ሳያልፉ ወሰን አላፊዎችን በተመሳሳይ የሚቀጡ ናቸው፡፡ ይህ በሸሪዓ የተፈቀደ ነው፡፡ ይህ የተወሳው በሚከተለው የቁርኣን አንቀጽ ነው፡-

●وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ

➳የመጥፎም ነገር ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡” አሽ ሹራ፡ 40

●وَإِنْ عَاقَبْتُمْ فَعَاقِبُوا بِمِثْلِ مَا عُوقِبْتُم بِهِ ۖ وَلَئِن صَبَرْتُمْ لَهُوَ خَيْرٌ لِّلصَّابِرِينَ

“ብትበቀሉም በርሱ በተቀጣችሁበት ብጤ ተበቀሉ፡፡ ብትታገሱም እርሱ
ለታጋሾች በእርግጥ በላጭ ነው፡፡” አን ነህል፡ 126


ሁለተኛው ደረጃ፡- ይቅር የሚሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ ከፍተኛው ደረጃ ነው፡፡ ይህን
አስመልክቶ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

●ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ

“ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡” አሽ ሹራ
፡ 40

➻ስጦታ በሰጭው መጠን ነው፡፡ አላህ ሱበሀኑሁ ወተአላ “ምንዳው በአላህ ላይ ነው” በማለት የተነባበረ ክፍያ ለመክፈል ሀላፊነቱን ወስዷል፡፡ ታጋሾች እና ይቅር ባዮች ከእርሱ ዘንድ የሚሰጣቸው ምንዳና ዋጋ የተነባበረና ላቅ ያለ ነው፡፡

➠ኢንሻአላህ ይቀጥላል

https://t.me/https_Asselefya1
03 ተብሲሩል ኸለፍ
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
ትናንት ሰኞ በቀጥታ ስርጭት የነበረው ደርስ
ክፍል =03

📚📚 ኪታብ "ተብሲሩል ኸለፍ"
✍✍ አዘጋጅ ሸይኽ አሕመድ ነጃር

🎙🎙 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ኢማሙል አውዛዒ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:–

እምነት አይፀናም በመናገር ቢሆን እንጂ
መናገርም አይፀናም በተግባር ቢሆን እንጂ
እምነትም መናገርም ተግባርም አይፀናም በትክክለኛ ኒያና ሱንናን በመግጠም ቢሆን እንጂ።

ከቀደምቶቻችን ያለፉ ትውልዶች እምነትን ከተግባር አይለያዩም ነበር፣ ተግባር ከእምነት ነው፣ እምነትም ከተግባር ነው።

[አል ኢባነቱል ኩብራ ሊብኒ በጠህ 1183]
እምነታችን ክፍል 1
Sadat
➲አድስ ኪታብ ቂርዓት

➳እምነታች

➠ክፍል አንድ

🎙በሳዳት ከማል አቡ መሬም

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➳አላህ ሆይ አንተ ሰላም ነህ!ሰላምም ካንተ ነው። ሃገራችንን ሰላም አድርግል!
Audio
...........

اللهم اغفر لنا وارحمنا يا رب

🎤 أبو ماهر الأثري.
➽ትክክለኛና የተረጋገጠ ዓቂዳ (እምነት)
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

➠ትክክለኛ አቂዳ ማለት ረሡል صلى الله عليه وسلم የተላኩበትና ወደርሱ ጥሪ ያደረጉበት ነው፡፡

➻የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በሚከተለው መልኩ ግልጽ አድርገውታል፡-

●"أن الأمة ستفترق من بعده على ثلاث وسبعين فرقة كلها في النار إلا واحدة"
قالوا: من هي يا رسول الله؟ قال: "من كان على مثل ما أنا عليه اليوم وأصحابي"

➳ከእርሳቸው በኋላ ኡመታቸው (ህዝባቸው) ከሰባ ሶስት ክፍል እንደሚከፈል ፤ አንዷ ብቻ ስትቀር ሁሉም የእሳት እንደሚሆን ተናገሩ፡፡ ሶሃቦች “የአላህ መልክተኛ ሆይ! (ይህች ቡድን) ማን ነች?” በማለት ጠየቁ፡፡ “ዛሬ እኔ እና ሶሃቦች በነበርንበት አይነት የሆኑት ናቸው፡፡”
በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ አህመድ፡ አቡዳውድ፡ አድ ዳሪሚይ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሐሰን ብለውታል ሶሂህ አት ተርጊብ፡

➠አንድ ሰው እርሱ የያዘው ዓቂዳ ከረሡል صلى الله عليه وسلم እና ከሶሃቦች ዓቂዳ ጋር ከተስማማ ከአላህ ቅጣት ነጻ ሆኖ ጀነት ይገባል፡፡ ለዚህ ነው ይህን ትክክለኛ የሆነ ዓቂዳ አጥብቃ
የያዘች ቡድን
“ፊርቀቱ አንናጅያ” በመባል የተጠራችው፡፡

➠የዚህ ስያሜ መልዕክት የሚያጠነጥነው ከአላህ ቅጣት ነጻ መሆኗን ነው፡፡ ይህች ፣ ከሰባ ሶስቱ መካከል የምትገኝ አንዷ ቡድን ነች፡፡ ቀሪ ቡድኖች - አላህ ይጠብቀንና - የእሳት ናቸው፡፡

➛ስለዚህ ፣ “ፊርቀቱ አንናጅያ” በማንኛውም ዘመን አህለሱና ወልጀማዓ ናቸው፡፡

መነሻቸው ከረሡል صلى الله عليه وسلم ሶሃቦች ተነስቶ የሙሀመድ ኡመት ፍጻሜ እስከሚሆንበት የትንሳኤ ቀን ድረስ ይዘልቃል፡፡

የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ሐዲስ ተናግረዋል፡-

"لا تزال طائفة من أمتي على الحق ظاهرين، لا يضرهم من خذلهم، ولا من خالفهم، حتى يأتي أمر الله وهم على ذلك"

➠"ከኡመቶቸ - በሀቅ ላይ ይፋ ከመሆን የማትወገድ ፤ ከእነርሱ ላይ እርዳታን ያቋረጠ ፣ እነርሱን የተቃረነ (ምንም ዓይነት) ጉዳት የማያደርስባቸው ፣ የአላህ ትእዛዝ እስኪመጣ ድረስ በዚያው በሐቅ ላይ ጸንታ የምትቆይ - አንዲት ቡድን አትወገድም፡፡” ሙስሊም፡1920

➴ኢንሻአላህ
ክፍል ሁለት ይቀጥላል


🖊ام فاروق
=
https://t.me/https_Asselefya1
سورة النجم - الآية [27 - 62] - هزاع البلوشي
www.tvQuran.com
🌸የማለዳ ምርጥ ቲላዋ🌸

‍ أَفَمِنْ هَٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ
ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?


وَتَضْحَكُونَ وَلَا تَبْكُونَ
ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን?


وَأَنتُمْ سَامِدُونَ
እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡ 📖አል ነጅም


ቃሪእ፦ ሀዛእ አልብሉሽይ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የኪታብ ቂርአት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የአልዋጂባት ሸርህ ደርስ

➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹ከሸሪአ ፍርድ ውጪ ባለ መፍረድና መፋረድ በተመለከተ

🔻【ክፍል 5⃣3⃣】
〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህች ነች ሰለፊያ!
-----
🎙ሸይኽ በድር አል-ዑተይቢ ሐፊዞሁላህ

https://t.me/Daru_Sunnah/1882

➲ይህች ነች ሰለፊያ!

(ከሸይኹ ምክር ጭማሪ)

➠ አንዳንድ ሰዎች ሰለፊያ ረድ ማድረግ፣ ሰለፊያ የሰው ስም አንስቶ ማዋረድ ብቻ ይመስላቸዋል። ሰለፊያ ሌሎች ኸይር ስራዎች የሚሰሩባት አይመስላቸውም። እንዲያውም ትክክለኛ ሰለፊያ ሁሉም ኸይር ስራዎች የሚሰሩባት ናት። አሁን ላይ ያለው ተጨባጭ በትክክል ሰለፊያን የተረዳ ያለ አይመስልም።

➳ሰለፎች የነበራቸውን ሁኔታ ማጥናት ያስፈልጋል። ሰለፊያ በቢድዓ ሰዎች ላይ ረድ ማድረግ ብቻ አይደለም። ይህ ሲባል ግን ምላሽ መስጠት ከሰለፊያ አይደለም ለማለት አይደለም። እንዲያውም
፦
"#الرد أصل من أصول الدين!"

➳ነገር ግን ረድ የማያደርግ ከሆነ ከሱና አጥር ይወጣል ማለትም አይደለም። ሰለፊያ ረድ ማድረግ ብቻ ነው ብሎ የሚያስብ ሰው እንደውም የራሱ ሰለፊይነት ያጠራጥራል። አቅሉን የሳተ ሰው ራሱ እንዲህ አያስብም እንኳን አቅል ኖሮን!።

➠ሰለፊይነት የሚረጋገጠው ትክክለኛውን ነብያዊ ፋና ስንከተል ነው እንጂ ረድ ስላደረግን ወይም የሰው ስም ስላነሳን አይደለም።

➳ሰለፊያ ወሬ ብቻ አይደለም ፣ሰለፊያ ተግባር ነው!
➳ሰለፊያ ስነምግባር (አዳብ) ያስተምራል፣ አሁን ላይ ግን ተጨባጩን ተመልከቱ!
➳ ሰለፊያ ውሸትን፣ ስርቆትን፣ ዝሙትን እና ሌሎችንም ትላልቅም ሆነ ትናንሽ ወንጀሎችን ከመስራት ይከለክላል። አሁን ላይ ማነው ትዝ ብሎት ስለነዚህ የሚያወራ?
➳ሰላት፣ ፆም ፣ ሰደቃ፣ ሰውን መርዳት እና ሌሎችም ኸይር ስራዎችን መስራትን የሚያስታውስ ጠፋ?! ለምን ረድ ብቻ
!!!

አላህ ይመልሰን!
فضيلة الشيخ بدر بن علي العتيبي حفظه الله وأثابه

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➽ትክክለኛና የተረጋገጠ ዓቂዳ (እምነት) ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ➠ትክክለኛ አቂዳ ማለት ረሡል صلى الله عليه وسلم የተላኩበትና ወደርሱ ጥሪ ያደረጉበት ነው፡፡ ➻የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በሚከተለው መልኩ ግልጽ አድርገውታል፡- ●"أن الأمة ستفترق من بعده على ثلاث وسبعين فرقة كلها في النار إلا واحدة" قالوا: من هي…
➽"ጥቅል የቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ዓቂዳ"
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

➻ክፍል ሁለት

➲ሐቅ የማይከፋፈል አንድና አንድ ብቻ ነው!
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➠አዎ ፣ ፊረቆች ወይም አንጃዎች በርካታ ናቸው ፤ እምነቶችና መዝሀቦች እልፍ አእላፍ ናቸው ፤ ንግግሮች ብዙ ናቸው ይሁን እንጅ ፣ ይህ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم
ዲን ነው
፡፡

➻አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

● وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

➠“ይህም ቀጥተኛ ሲሆን መንገዴ ነው፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ። ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡ እንሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ
፡፡” አል አንዓም፡ 153

➻የአላህ መንገድ ፡ ረሡልን صلى الله عليه وسلم የላከበት ፤ የተከበሩ ሶሃቦች ፣ ምርጥ ክፍለ ዘመን ላይ የነበሩት - ታብዒይና ታብዒዩ ታብዕይ - እንዲሁም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ የእነርሱን
ዱካ የተከተሉ የዚህ ኡመት ማህበረሰቦች የተጓዙበት መንገድ ነው፡፡ ይህ የአላህ
መንገድ ነው ፤ ይህን የአላህ መንገድ የተቃረኑ ሁሉ የጥመት መንገዶች ናቸው
፡፡

➳ነብዩ صلى الله عليه وسلم ቀጥ ያለ መስመር አሰመሩ ፤ ጠማማ የሆኑ መስመሮችን ደግሞ በጎን እና በጎን አሰመሩ ፡፡ ከዚያም ቀጥ ስላለው መስመር የሚከተለውን ተናገሩ፡ “ይህ
የአላህ መንገድ ነው” ፤ በጎን እና በጎን ስላሉት የተለያዩ መንገዶች ደግሞ “እነዚህ መንገዶች ናቸው፡፡ በእያንዳንዱ መንገድ ላይ ወደርሱ ጥሪ የሚያደርጉ ሰይጣናት አሉ” በማለት ተናገሩ
፡፡

አህመድ፡ ቲርሚዚይ፡ አድ ዳሪሚይ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ተኽሪጁ መሸካቲ አል መሷቢህ፡

➳ይህ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ንግግር ለሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ የተሰጠ ግልጽ ማብራሪያ ነው፡፡

● وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا

“ይህም ቀጥተኛ ሲሆን መንገዴ ነው” አል አንዓም፡153

➠ስለዚህ የሰላማዊ ዓቂዳ ባለቤቶች ፤ ከጥመት ፣ ከእሳትና ከልብ ወለድ ነጻ የሆኑ ጀማዓዎች ናቸው፡፡ እነርሱ ናቸው አህለሱና ወልጀማዓዎች፡፡ እኛንም እናንተንም ከእነርሱ ጋር አብሮ ያድርገን ፣ይሰብስበን! እርሱን እስከምንገናኝ ድረስ በእነርሱ ጎዳና የምንጓዝ ያድርገን!!

➠ኢንሻአላህ
ይቀጥላል


🖊ام فاروق
=
https://t.me/https_Asselefya1