💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
القارئ سعد الغامدي | إن الدين عند الله الإسلام
💭🌸خدمة تلاوات🎧
🌸 تلاوة صباحية

﴿إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَـٰمُ ۗ وَمَا ٱخْتَلَفَ ٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلْكِتَـٰبَ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلْعِلْمُ بَغْيًۢا بَيْنَهُمْ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِـَٔايَـٰتِ ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ ٩١۝﴾

🎙القارئ : سعد الغامدي
=
t.me/https_Asselefya1
መልካም ( ጥሩ ) ሴት

የአሏህ መልክተኛ ( ﷺ ) እንዲህ ይላሉ ፦

አላህ መልካም ሚስት የቸረው ሰው በግማሹ ዲኑን ረድቶታል በቀሪው ግማሹ አላህን ይፍራ።

( السلسلة الصحيحة للألباني 2/124)


=
t.me/https_Asselefya1
" ከንግግርሽ  የበለጠ  መልካም ተግባርሽ ሰዎችን ወደ ሂዳያ ይመራል።

#መልካም ስነ ምግባር

=
t.me/https_Asselefya1
ሂወት ብዙ መንገዶች አላት! በዚህ ላይ ቫላንስሽን ጠብቀሽ የማትሄጂ ከሆነ ትሰበሪያለሽ።
ለሰው ልጅ ከባድ ቅጣቱ ሰውን በሚበድል ጊዜ የነብስያ ወቀሳ ነው

ነብስያው የግድ እያስታወሰች ትወቅሰዋለች ትጮህበታለች

የዛኔ የበደለውን ሰው ቀጥ ብሎ ማየት ይከብደዋል መገናኘት ይከብደዋል ስሙን ሲሰማ ጅስሙን ይወረዋል ይቅርታ ጠይቆ ለራሱ ነብስያው እሺ አትለው

እሚገርመው ደግሞ የአላህን ሀቅ ስናጒድል ይህን ያክል ነብስያችን አትወቅሰንም ምን ይሆን ያረብ

ያወዱድ ምን አይነት ቅጣት ነው ያረብ ድንቅ እኮ ነህ በነገራቶች ሁሉ ብናስተነትንህ

https://t.me/Sahabaa1344
https://t.me/Sahabaa1344
∙ የኔ የምትይውን ወንድ /ባል ማግኝት የምትፈልጊ ከሆነ  ከዝህም ከዛም መተዋወቅና ሰልክ መለዋወጥ አይጠበቅብሽም የምታገኛቸው ወንዶች ሁሉ ለአንች ባል አይሆኑም  አንችም ለሚያገኙሽ ወንዶች ሁሉ ሚስት መሆን አችይም ትዳር ለገበያ አይቀርብም አሰር ያባረረ አንድ እኳን አይዝም በቃ ላንች ያለው ቢዘገይ እንጂ ፈፀሞ አይቀርም ሁሉም ነገር ስትር ብለሽ  #አላህን_በዱዓ  ጠይቂው!

منقول
=
t.me/https_Asselefya1
~ የአንዳንድ ሰዎች ባህሪይ « መታኝ እና አለቀሰ ነዉ። ሰዉ ለመጉዳት ርቀዉ ሄደዉ አልሳካ ሲላቸዉ መልሰዉ ጎዱኝ በደሉኝ ብለዉ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላሉ። ተዉ እንጅ አታሳስቱን!

=
~ እርሱ ነዉ የዉስጤ ሰላም እርሱ ነዉ ደስታዬ  አፀናኝ ጌታዬ   አላህዬ አንተን ለመዉደድ እልፍ ምክንያት አለኝ  አልሃምዱሊላህ ....!

=
t.me/https_Asselefya1
" ትተዉሽ አይደለም!  አላህ ከህይወትሽ አስወግዶልሽ ነዉ   የተሻለ ስለሚገባሽ!

=
t.me/https_Asselefya1
ያንች ችግር ከሸሪዓዊ እውቀት ውጭ
ለሁሉም ነገር ጊዜ መስጠትሽ ነው።
أغيثوا قلوبكم بذكر الله، ولا تَحبسوا عنها ماء الحياة: (سبحان الله، والحمد لله، ولا إله إلَّا الله، والله أكبر).

#تغريد_العصيمي
👉ቁጥብ ጥንቁቅ እህቶቼን አይመለከትም!!

#ከልክ_አትለፉ__!!
---------------------------
የወንድን ልጅ ጉድለት የሞላች በሀሴት፡
አይናፋር የሆነች እርሷ ናት ቁጥብ ሴት።
በኒቃቧ አጊጣ በመንሀጅ የፀናች፡
ምክሯ ሰበብ ሆኖ ብዙ ሰው ያቀናች፡
ሁሉ የሚያከብራት በፀባይ በእምነቷ፡
ከሩቁ የሚታይ አይናፋርነቷ፡
ይህች አይነቷ እህቴ ወደት ተሰወረች!?
በኒቃብ ተውባ እዚህ አልነበረች!?
ማን ምን አላትና እንድህ ሆና ቀረች!?
#ኸረ_እህቶቻችን_!!
--------------------------------------------
ስቶዱም ስትጠሉም ከልክ አትለፉ፡
በሌለበት ነገር ሰውን አትዝለፉ፡
ወረት አትልመዱ ሁሉን አትልከፉ፡
የዋሆችን ሁሉ አታድርጉ ክፉ፡
-----------------------------------
ስቶዱ አደብ የለ ይዛችሁ ልቀቁኝ፡
ስጠሉ አቅል ማጣት በገመድ እነቁኝ፡
እጅግ ስትረብሹ ይዘው ሲለቋችሁ፡
ለሰው ሰላም አይሰጥ ይሔ ምላሳችሁ፡
ስትጠሉ
ለአስተሳሰባችሁ መርህ አብጁለት፡
ቅርፅ አትቀያይሩ ሁልጊዜ እለት ከእለት፡
ሞትኩልህ ሔድኩልህ ብለሽ ሳትጨርሽ፡
እስኪ ተረጋጊ ኪዳን አታፍርሽ፡
ሚስቱ መሆንሽን ፈፅመሽ ሳትርሽ፡
ተጣላን ተያለሽ በተራ አሉባልታ፡
ከዚያም ረስተሽው ያን ሁሉ ውለታ፡
ስሙን ታጠፋለች በሚዲያ መጥታ፡
ነገር ትሰካለች ለላይክ ፍጆታ፡
ስቶዱ ቸኳላ ያዙኝ ልቀቁኝ ባይ፡
ስትጠሉ መዋሸት ያውም ባደባባይ፡
እንድህ አትሁኑ እጂጉን ያስጠላል፡
ግርማ ሞገሳችሁ ይወርዳል ይቀላል፡
---------------------------------------
ስትወዱ ምክንያት ሰበብ ይኑራችሁ፡
ስትጠሉ በወጉ ሁኑ አስተንትናችሁ፡
ለምን ከዚያ ከዚህ ትጣደፋላችሁ!?
#ለምንስ_ሌሎቹን_ታሰድባላችሁ!?
አቦ ተረጋጉ ስርዐት ይኑራችሁ!?
👉#ስትወዱ__!!
እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ዘመን ሲያልፉ፡
ድንግል ነበር ልቤ ያልተገኘ ቁልፉ፡
ለመውደድ ለፍቅር በሩን ያልከፈተ፡
ከማንም ወንድ ጋር ያልተከላፈተ፡
በሀሳብ በናፍቆት እሩቅ ያልዘመተ፡
ወዶ ያልተጎዳ ያልተቆራመተ፡
እንደዚህ ብላችሁ ስትፅፉ ከርማችሁ፡
በስምንተኛው ቀን ከተለያያችሁ!?
ልክ እንደ አባት ገዳይ ትፋለማላችሁ!?
#እንዴ_ምንድን_ነው?
ትዳር ፍቅር ማለት ምላስኮ አይደለም፡
ትልቅ ቃል ኪዳን ነው ለመኖር ዘላለም፡
በናንተ ምክንያት ትዳር ጠላንኮ፡
በስንቱ እንፈተን ስንቱ ሆኖን ታኮ፡
ያኔኮ ስቶጂው የግሉ ሲያደርግሽ፡
እንዲያ ስትፈልጊው እሱም ሲፈልግሽ፡
ነፃ ነበር ውስጤ አየር ብቻ ያለው፡
ፍቅር አረገዘ ዘንድሮ ላይችለው!?
ልቤ ነበረኮ ሀሳብ የለሽ ጀግና፡
ዛሬ ተሸነፍኩኝ በዛ ልጅ ቁንጅና፡
ብለሽ ብዙ አውርተሽ ለወዳጅ ለጠላት፡
በሰባተኛው ቀን በነገር መባላት፡
ይህ የበሽታ እንጂ የሰላም አይደለም፡
ነገ ልንፋታ ብሎ ትዳር የለም፡
👉#ኸረ_ይደብራል...!!
የታየውን ሁሉ በመንጋ ስቶዱ፡
ደግሞ ወረቱ ሲያልቅ በበደል ስትፈርዱ፡
ሰቅላችሁ ከጣራ ብላችሁ ሞትኩለት፡
ስትፅፉ ዘወትር ስትሉን ሔድኩለት፡
ሀላሌ ብላችሁ ፕሮፋይል መስቀል፡
አርማ ማዘጋጀት መትከልና መንቀል፡
------------------------------------------
ልባችን በፍቅር ፈፅሞ አልተቃኘም፡
ለሱ ነበር እንጂ ለሌላ አልተሞኘም፡
ከርሱ በቀርኮ ወንድን አልተመኘም!!
ልቤ ነበርኮ በፍቅር ያልተቦካ፡
ውስጡ ያልተቃኘ ምንም ያልተነካ፡
ሰው ወዶ የማያውቅ ጭራሽ ያልተለካ፡
በህይወት ዘመኑ ወንድን ያልወደደ፡
በናፍቆት ተጉዞ ርቆ ያልሔደ፡
ለርሱ ግን ተገዝቶ በፍቅር አበደ፡
ይህንን ባላችሁ በሶስተኛው ማግስት፡
ፍቅራችሁ አብቅቶ መቀየር እንደስስት!!
---------------------------------------------
ወደድኩት የኔ ነው እንደናት አባቴ፡
እርሱ ነው ከንግድህ ወንድምም እህቴ፡
እንደዚህ ብላችሁ በአለም አደባባይ፡
ስትለዩ ደግሞ አንተም ባይ እኔም ባይ፡
ከሰአት በኋላ ሁላችሁም ዋይዋይ!!
አልገባንምኮ ምንድን ነው ነገሩ፡
ትዳር ረከሰ ጠፋብን ሚስጥሩ!!?
#ስቶዱ__!!
ልቤ ግንድ ነበር ልብሱ ያልተላጠ፡
ለናፍቆት ሰጠብኝ ሲያየው ደነገጠ፡
ማንነቱን ሁሉ መክፈቻውን ሰጠ፡
ልቤ ቢክራ ነበር ውስጡ ያልተቃኘ፡
አልሀምዱ ሊላሒ ዛሬ አንተን አገኘ፡
አልፈልግም ፍጥረት ወንድ ካንተ ሌላ፡
በቃኝ በቃ እንግድህ ቃልና መሐላ፡
እንደዚህ ብላችሁ ወሬውን ሳንጠግብ፡
በሚዲያው አለም ሆነሽለት እርግብ፡
ገንዘብ አልፈልግም መንሀጅ ነው መስፈርቴ፡
አይዞህ ሀላሌ እምነትህ ነው ሀብቴ፡
ብለሽ ብዙ አውርተሽ ካፍሽ ሳታበቂ፡
ድጋሜ አቋም ቀየርሽ እንደ ጠጣ አረቂ፡
-----------------------------------------------
ስቶዱ ለፍቅር ድንበር ገድቡለት፡
በመጠኑ ይሁን እስከሚለይለት፡
ስትጣሉ ደግሞ የሌለ አትፍጠሩ፡
ፊትና ለማራገብ ዘበኛ አትቅጠሩ፡
እስኪ በልክ ይሁን ፍቅር ጥላቻችሁ፡
ለፈራጅ ቸገረን ግሩም ሁኔታችሁ፡
ውደታ ጥላቻን በውስጣችሁ ያዙት፡
ከሀያዕ አትራቁ መርከሱን አታብዙት፡
-----------------------------------------
በየሚዲያው ላይ ብሶትን መናገር፡
የግል ወሬወችን ተራ ርካሽ ነገር፡
ያለ የሌለውን መቀበጣጠሩ፡
ወዶ ጠላኝ ብሎ ቂምን መቋጠሩ፡
ለቀጣህ ህይወትሽ አደጋ ስላለው፡
እስኪ ዝም በሉ እሱ ነው ሚሻለው፡
ኮሽ ባለ ቁጥር ሰውን አትዝለፉ፡
ስቶዱም ስትጠሉም ከልክ አትለፉ፡
--------------------------------------------
✍️በኑረዲን አል አረቢ
-------------------------------------------
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi