💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
የዙል ሒጃ ስምንቱን ቀናት መፆም
~


ነብያችን ﷺ የዙልሒጃን አስር ቀናት አስመልክቶ እንዲህ ብለዋል፦

مَا مِنْ أَيَّامٍ الْعَمَلُ الصَّالِحُ فِيهِنَّ أَحَبُّ إِلَى اللَّهِ مِنْ هَذِهِ الأَيَّامِ الْعَشْرِ . فَقَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، وَلا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ؟ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : وَلا الْجِهَادُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ، إِلا رَجُلٌ خَرَجَ بِنَفْسِهِ وَمَالِهِ فَلَمْ يَرْجِعْ مِنْ ذَلِكَ بِشَيْءٍ

''በውስጣቸው መልካም ስራ ከሚፈፀምባቸው ቀናት ውስጥ ከነዚህ አስር ቀናት በላይ አላህ ዘንድ የተወደደ የለም።" "በአላህ መንገድ መታገልም ቢሆን?" ብለው ሲጠይቋቸው የአላህ መልእክተኛ ﷺ "በአላህ መንገድ መታገልም ቢሆን! በነፍሱም፣ በገንዘቡም ወጥቶ ከዚህ ውስጥ ምንም ያልተመለሰ ሰው ሲቀር" ብለው መለሱ። [አልቡኻሪይ፡ 969]

በዚህ መሰረት በነዚህ የተከበሩ ቀናት የተለያዩ ዒባዳዎችን መፈፀም በጣም ትልቅ ዋጋ ያለው ነው። ፆም ወደ አላህ መቃረቢያ ከሆኑ ዒባዳዎች ውስጥ አንዱ መሆኑ ግልፅ ነው። ከመሆኑም ጋር በያመቱ "የዙል ሒጃን አስር ቀናት መፆም ይቻላል ወይ?" የሚል ጥያቄ ሲነሳ ያጋጥማል። የግርታው መነሻ እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ "በነዚህ አስር ቀናት ውስጥ የአላህ መልእክተኛን ﷺ ፈፅሞ ፆመው አላየሁም" ማለቷ ነው። [ሙስሊም፡ 1179]

ይሄ ግን ግርታ ሊፈጥር የሚገባው አይደለም። እንደሚታወቀው የነብዩ ﷺ ሱና በሶስት መንገድ ይተላለፋል።
1- በቃላቸው
2- በተግባራቸው እና
3- ሌሎች ሲፈፅሙ አይተው የሚሰጡት ይሁንታ (ኢቅራር)።


የዙል ሒጃን ስምንት ቀናት መፆም ከነዚህ ውስጥ በቃላቸው የተላለፈው ሐዲሥ ውስጥ ይካተታል። ሐዲሡ አስተማማኝ፣ መልእክቱም ፆምን አካታች ነው። ከዚህ በኋላ የዓኢሻ ነብዩን ﷺ ሲፆሙ አለማየት የሳቸውን ጥቅል የቃል መልእክት ለመገደብ መነሻ መሆን የለበትም። ለዓኢሻ አለማየት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ደግሞ የሚገድብ መረጃ እስከሌለ ድረስ በጥቅል ቃላዊ መረጃ የተገኘው በቂ ነው።
ስለዚህ ሌሎች መረጃዎች ደካማዎች (ዶዒፎች) ቢሆኑ እንኳ መግቢያ ላይ የተጠቀሰው ሐዲሥ በቂ ማስረጃ ነው።

ይሄ እንግዲህ ስምንቱን ቀናት በተመለከተ ነው።
* ዘጠነኛው ቀን የሁለት አመት ወንጀል እንደሚያሳብስ አስተማማኝ መረጃ መጥቶበታል። [ሙስሊም፡ 1162] ስለዚህ ብዥታ የሚነሳበት አይደለም።
* አስረኛው ቀን በአል ስለሆነ አይፆምም።


ወሏሁ አዕለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ولك الوو.....

ምን ይታያችኋል 👓 በሉ ሰላም እደሩ
🛑👉ምላስህን ከውሸት ጠብቅ‼️


አቡሀቲም ኢቢኑ ሂባን "አላህ ይዘንለት" እንዲህ ብሏል።

ጥራት የተገባው ጌታ አላህ ምላስን ከሌሎች የሰውነት አካል ክፍሎች በላጭ አድርጓታል። በላጭነቷ ግልፅ የሆነው ከሌላው አካል በተለየ ተውሂድን "لا إله إلا الله" እንድትናገር በመደረጓ ነው። አንድ አቅል ያለው ሰው አላህ ተውሂድን እንዲናገር ብሎ የፈጠረውን የሰውነት አካል ውሸት ሊያስለምደው ይገባል። ይህን ምላስ እውነትን እንዲይዝና በዛም ላይ እንዲቀጥል መጠበቅ ግዴታ ነው። በሁለቱም ሀገር ላይ ሊጠቅማት የሚችል የሆነን ነገር ሊያሲዛት ግድ ይሆናል። ምክንያቱም ምላስ የለመደውን ነገር ይይዛል። የለመደው እውነት ከሆነ እውነት ውሸት ከሆነም ውሸት ይላበሳል።

| مفتاح دار السعادة (٣٠١/١)


=
t.me/https_Asselefya1
የደዕዋው ጉዳይ ለሚያሳስባችሁ ሁሉ!
~
እውቀት ያለው በእውቀቱ፣
ሃብት ያለው በሀብቱ፣
በየትኛውም በምንችለው መንገድ ሁሉ ለደዕዋ አስተዋፅኦ ይኑረን። መስጂዶችን፣ ማህበራዊ መገናኛዎችን፣ ... ለደዕዋ እንደሚገባ እንጠቀማቸው። ካልሆነ የተጋረጡብንን አደጋዎች መቋቋም አንችልም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
🔖 ሰዉን አዋርዳለሁ ሲሉ ለራስ መዋረድ እንዳለ ስንቶች አስተዉለናል ህእ!? ለምሳሌ ፦ ከአንድ ሰዉ ጋር እኛ ካልመለስን ካልፃፍን ሲደወል ካላነሳን በግድ አዉሩኝ ብሎ አያስገድድማ!? So በራስ እጅ ስንፀፍ ስንደዉል ሲደወል ስናነሳ ብዙ ስንጃጃል ስናጃጅል ቆይተን ያ ሰዉየ ብቻ ጥፋተኛ ማድረግ ይሄ ጅልነት ነዉ።

ለመፍረድ ከሁለቱም ጎን ያለ ነጥብ መታየት ያለበት ከአንድ በኩል ይዞ መሮጥ ይሄ አሽቃባጭነት ይባላል።



=
በቁንጅናሽ ልትወደጂ ትችያለሽ
👉የምትከበሪውና ትዳርሽ ፍሬያማ የሚሆነው

በአስተሳሰብሽ እና በዲንሽ ቀጥ ስትይ ብቻ ነው።
➭ያአሏህ!

አልቻልኩም ያ አሏህ አሁንስ ከፍቶኛል፡
መውጫና መግቢያዬ ቀኑ ጨልሞኛል
፡
ከላይም ከታችም ወንጀል አስምጦኛል፡
የአርሹ ባለቤት የአለም ፈጣሪ፡
ከእናት በላይ አዛኝ እጂጉን መሀሪ
፡
ያ አሏህ እባክህ በል ሀጂን ወፍቀኝ፡
ሀዘን በዝቶብኛል ደስታ ያጥለቅልቀኝ፡
እንደ አድስ ልወለድ መንገደም ይሁን ቀኝ
፡

ለበይክ አልኩ አምላኬ__!!

ወዜ ተመጠጠ የልጂነት መልኬ፡
ልብሴም አልሆን አለኝ ገዝቸው በልኬ፡
ስለዚህ ከንግድህ ሀጂ ይሁን ታሪኬ፡
መካና መድናን ከማየው በስልኬ፡
በአካል ውሰደኝ ለበይክ አልኩ አምላኬ፡

✍ከወንድሜ ኑረድን ፅሁፍ የተቆረጠች

http://t.me/https_Asselefya1
🛑👉 ወደኋላ በመዟዟር ጊዜን እያባከኑ ወደፊት ተጉዞ ውጤታማ ለመሆን መሞከር አድካሚ ነው።ስለዚህ ለውጥ ስናስብ፦

{  وَلَا یَلۡتَفِتۡ مِنكُمۡ أَحَدࣱ وَٱمۡضُوا۟ حَیۡثُ تُؤۡمَرُونَ }

"ከእናንተ ውስጥ አንዳችሁም ወደኋላ አይዙር። ወደታዘዛችሁበት ብቻ ቀጥሉ" ብሎ ወደነብዩላህ ሉጥ صلى الله عليه وسلم የደረሰውን ትእዛዝ ማስተንተን ትልቅ አጋዥ ነው።

=
t.me/https_Asselefya1
  
አይ የኛ ሞኝነት! ሰዉ መሳደብ ስንፈልግ በማያቁን አካዉንት በሚያቁን አካዉንት ደግሞ መልካም መልካም ያጫዉተናል ህእ? ግን ማን እያታለልን ይሆን ? መለይካዎች ስራ መዝገባችን ላይ በራሳችን ስም እንደሚፀፉ የት እየረሳነዉ ነዉ ግን !? አይገርማችሁም ??

#ትገርሚኛለሁ
=
ትዳር ማለት፦
~ሁለት ልቦችን ማስተሳሰር
~ሁለት ነፍሶችን ማያያዝ
~ሁለት ሩሖችን መቀላቀል
~በመጨረሻም ሁለት አካሎችን ማቀራረብ ማለት ነው።

በሺር አል ኢብራሂምይ [አል አሣር 3/297]
Audio
"በሙሓዶራው የተወሱ ነጥቦች"

√
የሰለፎች አቋም በሀሜት ላይ!
√ የሀሜት ሰበቦችና ምክንያቶች!
√ የመጥፎ ጓደኛ ተፅእኖ
!

🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/14516
ኹጥባ { የዙልሒጃህ 10 ቀናቶች }
𝐀𝐛𝐝𝐮𝐫𝐞𝐡𝐦𝐚𝐧 𝐀𝐛𝐮 𝐔𝐬𝐞𝐲𝐦𝐢𝐧
« የጁሙዓህ ኹጥባ »
   ă€°âž–〰➖〰➖

ÂŤ  á‹¨á‹™áˆ ሒጃህ 10 ቀናቶች ትሩፋት   Âť

➭ የዙልሒጃህ ወር ትሩፋት
➭ የመጀመሪያ 10 ቀናቶች በላጭነት


🕌በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ { ዙልሒጃ 1 / 1445 Úž }   የተደረገ !!

🎙 በአብዱረሕማን አቡ ዑሰይሚን

    = t.me/MuhaderahChannel