💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
➾ጌታቹህን እስከምትገናኙ ድረስ ታገሱ ‼

ረሱል "ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም" እንዲህ አሉ፦

"ታገሱ! አንድ ዘመን አይመጣም ያ ከእርሱ ቡሃላ ያለዉ ዘመን ከርሱ የበለጠ የከፋ ቢሆን እንጂ ጌታቹህን እስከምትገናኙ ድረስ"

[ቡኻሪይ ዘግበዉታል]
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
http://t.me/https_Asselefya1
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ከናንተ አንዳችሁ አመስጋኝ ልብ፣ ጌታዋን የምትዘክር አንደበት፣ በአኼራው ጉዳይ የምታግዘው አማኝ ሚስትን ይያዝ።"

«ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል/አልባኒ ሰሒህ ብለውታል።»

=
t.me/https_Asselefya1
«ጤናማው ከዓፊያ ውጪ የህይወትን ጣፋጭ ነገሮች ሁሉ ይመኛል። ህመምተኛው ግን ከዓፊያ ውጪ ሌላ ምኞት የለውም!»
አላህ ሆይ! ካንተ ውጪ ህመሙን ማንም የማያውቅለትን በሽተኛ ሁሉ ዓፊያ ለግሰው!

=
........አንዳንዴ....


አንድት መስመር አለች ሲከፋኝ የፃፍኳት፡
ሰው ያላነበባት ደብቄ የያዝኳት
.....

......እንድህ ትቀኛለች.....

ቀን በሔደ ቁጥር የሚታየኝ ፊደል፡
ህይወት ያልኩት ቅዥት ሞት የሚባል ገደል፡


.....ኑር......

https://t.me/nuredinal_arebi
አሁንም እላለሁ ወደፊትም እደግመዋለሁ ከትዳር በፊት ማንም ላይ ልባችሁን አትስቀሉ ! ያ የሰቀላችሁበት ሳይሳካ ሲቀር ሌላ ሒወት ለመጀመር ትቸገራላችሁ እና ልባችሁ ጠብቁ ተጠንቀቁ እሺ።

=
👉"ከዱንያም ድርሻህን እንዳትረሳ"!!

ከዱንያ ድርሻህን እንዳትረሳ ሚበቃህም ያህል ያዝ ነገር ግን ዱንያን ልብህ ውስጥ ሳይሆን እጅህ ላይ አድርጋት።

📝ሸርህ ሪያዱ ሷሊህን 3/369
ያለ መድሃኒት የምትተኛ ከሆነ
ያለ ህመም እና ድካም ከተኛህበት የምትነሳ ከሆነ አንተን ካማንም በላይ ሀብታም ነህ
الحمد لله በል !!
  
منقول
=         
በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
የባልሽ እህት ለአንችም እህት ነች ሁለዬ አክብረሽ እና ወደሽ መኖር ያለብሽ ! ግን እሷ ጠልተሽ እና ንቀሽ ከሱ ልኑር ብተይ ለተወሰነ ባልሽ ታግሶሽ ሊኖር ይችላል ግን ከጠና ነገሩ ምርጫዉ እህቱ እንደሆነች አትርሺ ሚስት በሚስት ይተካል እሕት ግን እሕት ነች መተኪያ የላትም።

እና ደረጃሽ እወቂ ማለቴ ነዉ! የሚስትነት ቦታሽ ብቻ ይዘሺ ተቀመጪ ያለ ደረጃሽ አትንጠላጠይ!

=
t.me/https_Asselefya1
ታገስ!

አውሮፕላን ውስጥ ሆነህ አንድ የሚያበሳጭ ነገር ቢገጥምህ "ወራጅ አለ!" አትልም እኮ ብስጭትህን ዋጥ አርገህ መሬት እስክታርፍ ትታገሳለህ። አሁን የሚገጥሙህን ፈታኝ ነገሮች በትዕግስት ማሳለፍ ከቻልክ የጊዜ ሚዛን ላንተ ማዳላቱ አይቀርም፤ ታገስ ወዳጄ!

=
t.me/https_Asselefya1
قال: العلامة صالح الفوزان حفظه الله : حُسنُ الظّن بالله واجبٌ  مِن وا؏بات التّوحيد.

[إعانة المستفيد 587]

=
【ቀኑ ሙሉ በተለያዬ ነገሮች ተጠምደን ዉለን ማታ ማረፊያ እንቅልፍ ባይኖር ኖር ምን ይዉጠን ነበር ?! በሉ በጊዜ አረፍ በሉ የሌሊት እንቅልፍ ጥሩ ነዉ ተኙ አታምሹ ይበቃል ! ስልካችሁ ዝጉ !
ነገ ካቆምንበት እንቀጥላለን ..!

=
‏{ اهدِنا الصراط المستقيم}

قال الإمام ابن القيم - رحِمهُ الله

"العبد لا سبيل له إلى سعادته إلا
بإستقامته على الصراط المستقيم ،
وأنه لا سبيل له إلى الإستقامة إلا بهداية ربه له".

الفوائد صـ٢٦


=