💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
📌من أعظم نعم الله أن تصبح وتمسي وأنت معافى فهي نعمة لا يدركها إلا من يفتقدها.

"ከተላላቅ የአላህ በረከቶች መካከል በጥዋት እና በማታ ጤነኛ መሆንህ ነው ይህን ፀጋ የሚገነዘቡት ያጡት ብቻ ናቸው።"

አላህ ሆይ የሰጠህን ፀጋ ሳይጎልብን እና የሰው እጅ ውስጥ ሳታስገባን ውሰደን

አሚን

=
telegram.me/abutoiba
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
اسأل الله تعالى من فضله ولا تحسد أخاك ! / الشيخ محمد بن صالح #العثيمين رحمه الله
የፍቅርን ሽታ አፍቃረዉ ብቻ ነዉ የሚያዉቀዉ!!

=
ስለ አለባበስ
~
ራሳችንን ለመጣው ፋሽን ሁሉ ማራገፊያ ልናደርግ አይገባም። አለባበሳችን ከምንኖርበት ማህበረሰብ ያፈነገጠ መሆን የለበትም። የተፈቀደ ማለትም ሐላል የሆነ አለባበስ እንኳ ቢሆን በአካባቢያችን የሚታወቅ ካልሆነ ልንርቀው ይገባል። ለምሳሌ በሆነ አገር የተለመደ ልብስ ወይም የጌጥ አይነት ሌላ ሃገር ላይ የማይታወቅ ከሆነ እንግዳ ሆነን እንድንታይ ከሚያደርገን ሁኔታ መቆጠብ አለብን። ልብ በሉ! በሸሪዐ ትእዛዝ ስለመጣበት አለባበስ አይደለም እያወራሁ ያለሁት። ስለዚህ በተለየ መልኩ ከፍም ይሁን ዝቅ ብሎ ጣት መጠቋቆሚያ የሚያደርግ እንግዳ የሆነ አለባበስ የሹህራ ልብስ ነው። የሹህራ ልብስ ደግሞ በሐዲሥ የተከለከለ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
መታረም ያለበት እሳቤ
~

"የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የወንጀላችን መብዛት ነው። ወደ አላህ እንመለስ" በሚባል ጊዜ "ኧረ ከወንጀል ጋር የሚያያዝ አይደለም ፤ የታወቀ ሳይንሳዊ ምክንያት ያለው ነው" የሚሉ ሰዎች አሉ። እንጂ የፈጣሪ ስራ አይደለም ነው ድምዳሜያቸው። ለሆነ ክስተት ሳይንሳዊ ትንታኔ ወይም የታወቀ ምክንያት ኖረው ማለት ያ ክስተት የፈጣሪ ስራ አይደለም ማለት አይደለም። በፈጣሪ የሚያምን ሰው ያለሱ መሻት በምድርም ይሁን በሰማይ የሚሆን ነገር እንደሌለ ያምናል። ስለዚህ ዝናቡም፣ ንፋሱም፣ ማእበሉም፣ ድርቁም፣ መብረቁም፣ የመሬት መንቀጥቀጡም፣ የፀሐይ ግርዶሹም፣ ወረርሽኙም፣ ...ሁሉም በአላህ ውሳኔና መሻት የሚፈፀም ነው። ደረስንበትም አልደረስንበትም ከአላህ ውሳኔዎች ጀርባ የሱ ጥበብ አለ።

በአላህ የሚያምን አካል ትልልቅ መቅሰፍቶች ቀርቶ ትንንሽ ፈተናዎች ሲገጥሙት እንኳ የራሱን ድክመት ይመለከታል። ሰበቡ ወንጀሌ ሊሆን ይችላል ብሎ ወደ ጌታው ይመለሳል። እውነታውም እንደዚያ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَمَاۤ أَصَـٰبَكُم مِّن مُّصِیبَةࣲ فَبِمَا كَسَبَتۡ أَیۡدِیكُمۡ وَیَعۡفُوا۟ عَن كَثِیرࣲ }
"ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሰሩት (ሃጢኣት) ምክንያት ነው። ከብዙውም ይቅር ይላል።" [አሹራ፡ 30]

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
020-فتح المجيد لشرح كتاب التوحيد
ሸይኽ ሙሐመድዘይን ሸይኽ ኣደም
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት

📚 فتح المجيد لشرح كتاب التوحيد للشيخ عبد الرحمن بن حسن بن محمد بن عبدالوهاب رحمه الله تعالى -٠١٩

🎙لفضيلة الشيخ محمدزين بن آدم حفظه الله ورعاه


✸| ክፍል- 20

═════ ≪ °📓🖇📓° ≫ ════
የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ Pdf መልክ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ ↓↓↓

t.me/SheikhMuhammedZainAdam/7947
ማንኛዉም መረጃ በፌስቡክ ፔጃቸዉ ተከታተሉ ማንም ያላችሁን አትስሙ !!

https://www.facebook.com/share/ZKigQvJUxdh8AEwh/
ትዕግስትን ስንቄ ዝምታን ወደድኩት
ሆኖልኝ እስከማይ በልቤ ያሰብኩት
ትዕግስትን ወድጀ ምርጫ ያደረኩት
ቢመሺም ቢነጋ አይቀርም ያለምኩት።
ሒጃብ ላንች ምንሽ ነው??? ሲሉሺ
እንደህ በያቸው።‼️

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷

ሒጃብ ለኔ ህይወት የለገሰኝ የፈጣሪ ትእዛዝ ነው በያቸው።እኛ ሴቶችን ኢሰላም በሂጃብ ሲያዘን አንዳዶች እንደሚያስቡት ፍላጎታችንን ለማፈን፣ ሴትነታችንን በመናቅ ወይም መብታችንን ለመጋፈት ሳይሆን ካለመኖር ያስገኘንን የአለማቱን ጌታ ትእዛዝ ለመጠበቅ ነው በያቸው

ይህው የአላህ ቃል
➱➱➱➱➱➱➱➱
وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَى جُيُوبِهِنَّ

ለምእምናትም ንገራቸው  አይኖቻቸውን ይከልከሉ።ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ። ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ።ጉፍቶቻቸውንም በአንገቶቻቸው ላይ ያጣፉሱረቱ አል ኑር 31
ሰዎች የሚመቀኙህ፡ስለበለጥካቸውና የደረስክበት ቦታ ላይ መድረስ ስላልቻሉ ነው።ይሄ ደግሞ አንተ ጥሩ ላይ መሆንህን ከሚጠቁም አንድ ማሳያ ነው።እውነትም ያለህበት ጥሩ ከሆነ ጠንክር !

=
t.me/AbuOubeida/5460
ያኢላሂ!!
➱➱➱➱

በኢማን ሙላን፣
በኢስቲቃማ አሳምረን፣
የሚጠቅመንን አሳውቀን

መንገድህን አመላክተን
ፍለጋህን አስተምረን።
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
በነገራችን ላይ ወንድማችን አቡ ዑሰይሚን በአሁን ወቅት እስር ቤት ነዉ አላህ ነጃ እንድያወጣዉ ሁላችሁም በመልካም ዱዓ አስታዉሱት ! የማን ዱዓ ሙስተጃብ እንደሚሆን አይታወቅምና ...! =
👆እየዘነጋሁ እና ትንሽ ያለሁበት ቦታ ስለማይመች ነዉ ! ብዙ የጠየቃችሁኝ ወንድም እህቶች አላችሁ በቦት በግል መስመር እና ወንድማችን አቡ ዑሰይሚን ሰላም ነዉ እሺ በመልካም ዱዓችሁ አትርሱት እሺ ! ለሁላችሁም መልስ ነዉ !


=
~እስልምና ሥራን ያወድሳል፤ጥረትን ያበረታታል። ምድር ላይ ዝምብሎ አላህ! አላህ! እያሉ መቀመጥ የለም። ለሥራና ለዒባዳ እንጂ ለዚክር እና ዱዓ ብቻ የተላከ የሰው ልጅም የለም።ካልሠራን  ሰማይ ወርቅ አትዘንብም፤  ምድር ብር አታበቅልም።በኑሮህ ዉስጥ ሁሉ አላህን ታወራዋለህ፣ ታማክረዋለህ፣ ትለምነዋለህ።ሳትሞክር፣ ሳትሰራ፣ ተኝተህ ... አላህ በደለኝ፣ ከለከለኝ አትበል።

~ባይሆን ባይሆን ትሞክርና አልቻልኩም ትለዋለህ፤ ትጥርና ደግፈኝ ትለዋለህ፣ ትሸሽና አድነኝ ትለዋለህ፣ ታጠራቅምና ሙላልኝ ጎድሎኛል ... ብለህ ትለምናለህ፣ ትበረታና ምራኝ አቅናኝ ትለዋለህ ...እሱ ያለምንም መነሻ ነገሮችን ማድረግ ቢችልም ግና የሚጥሩትን ታታሪዎች ይወዳል።
~t.me/AbuSufiyan_Albenan
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM