💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💘ብታቂዉ ክብርሽን💘

ቁንጅና ክብር አይሆን
መልክ መተማመን፣

ታጥቦ እማይጠጣ እረጋፊ ዉበት፣
እኔ ቆንጆ ብለሽ  ብትመኪበት፣

ከክበር አይበልጥም ሲለካ በስሌት፣

በታዉቂዉ ክበርሽን፣
ላኳኳልሽ ሁሉ ባልከፈትሽ በርሽን፣
ላንኳኳልሽ መክፈት፣ለመጣ መረታት፣
ፈፁም ለማያቅሽ፣ወደሽ መረታትሽ፣
ይህ አይደለም ክበርሽ የሴትነት ወግሽ፣
ተይ አታሶቅሽ አትጣይ ክብርሽን፣
ማንም አያኳኳ ቁጥቡ በርሽን፣


ለመጣልሽ ሁሉ አመነሽ ከተረታሽ፣
ደግሞ እሷን እያለ ንቆ እያሳለፈሽ፣
ዉድ የሆንሽዉን ልጅ ባፉ እያረከሰሽ፣


መቆንጀት መዋቡ ዘመነኛ መስሎሽ
ካየ ይወደኛል እያለሽ ተገልጠሽ፣

የሴትነት ወጉን መሽኮርመሙን ትተሽ
የወደደን ገፍተሽ. ያልወደደን ወደሽ
ታዋቂ ማግባትሽ ዝና እየመሰለሽ፣
የህትሽን ትዳር ገብተሽ ባልበጠበጥሽ


   ✍️አቡ ዑበይዳህ ሶላሁዲን
=
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የኛ ሀገር ገፀታ አሁን ጃማ ደጎሎ 015 ቀበሌ !

=
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
«ቁርኣን የህይወት ብርሃን» «ቁርኣን ወደ ቀጥተኛዉ መንገድ የሚመራና በጎ ሰሪዎችንም የሚያበስር መሆኑን አላህ ተናግሯል።» «إِنَّ هَـٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ یَهۡدِی لِلَّتِی هِیَ أَقۡوَمُ وَیُبَشِّرُ ٱلۡمُؤۡمِنِینَ ٱلَّذِینَ یَعۡمَلُونَ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ أَنَّ لَهُمۡ أَجۡرࣰا كَبِیرࣰا » «ይህ ቁርአን ቀጥተኛ ወደ ሆነችዉ…
«ደጋግ ቀደምቶች ስለ ቁርአን ምን አሉ ?»


የሶሓቦች አዉራ አቡበክር ُرَضِيَ اللهُ عَنْه ፦ ቁርአን ቀርቶ (አዉቆ)ከዛም ከሱ የተሻለ ስጦታን የተሰጠ ሰዉ አለ ብሎ ያመነ ሰዉ  ትንሽና ቀላሉን ነገር  አልቋል፣ ታላቅና ዉዱን ነገር አርክሷል (ንቋል)።

ዑመር ኢብኑል አል ኸጧብرَضِيَ اللهُ عَنْهُ፦ ቁርአንን ተማሩት አላህ ዘንድ ትታወቁበታላችሁ፣ ስሩበትም፣አላህ ዘንድ ልዩ ክብር ካላቸዉ የቁርአን ሰዎች ትሆናላችሁ፣ አላህ ፊት ሳትመዘኑ(ሳትገመገሙ)በፊት እራሳችሁን መዝኑ(ገምግሙ)።

ዑሥማን ኢብኑ ዐፋንرَضِيَ اللهُ عَنْهُ ፦ ልቦቻችን ንፁህ ቢሆኑ ኖሮ የጌታችንን መፀሀፍ ከማንበብ መቼም ባልጠገብን ነበር።

​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
https://t.me/https_Asselefya1
فَفُز بِعِلمٍ تَعِش حَيًّـا بهِ أبـدًا
النَّاسُ مَوتَیٰ وأهلُ العِلم أحيَاءُ

=
«ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ »

“ዲን ያላት ሴት ማለት፦የአላህን ትዕዛዛትን በአግባቡ የምትወጣ፣የባሏን መኝታ፣ልጆቹንና ንብረቱን ባጠቃላይ ሐቁን የምትጠብቅ ናት፣በተጨማሪም የአላህ ትዕዛዛትን እንዲወጣ በማስታወስ የምትረዳው፣ ከዒባዳ ሲሰላች እንዲነቃ የምታደርገው ሲሆን ሲበሳጭ ወይም ሲናደድ ቁጣውን የምታበርድ ሴት ናት።"
[አዝ–ዘዋጅ ገፅ 20]

──────⊹⊱✫⊰⊹──────
https://t.me/https_Asselefya1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📔ከእንቅልፍ ነቅተዉ ስልክ ላይ የሚቸከሉ ልጆች በበዙት ዘመን ቁርአን የሚያነብ ልጅ ለማፍራት የአንች ጥንካሬ ይፈልጋል ከአሁኑ ጠንክሪ አባቱ ከመምረጥ ጀምረሽ ማነሽ ብርቄ ¡

=
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«እዩት አንበሳውን»
«ሸይኽ ኢብኑ-ዑሰይሚን»

ሐቅን ለመናገር ሚንበር ላይ ሲወጣ፡
አንበሳ ይመስላል ከጫካ የመጣ፡
ህይወቱን የሰጠው ተውሒድ ለማስተማር፡
ተመልከቱትማ እዩን ይህን ማማር፡
ድምፁም ይጣፍጣል ከወለላው ከማር፡

ሽርክን አንኮታኩቶ ብዙ ኪታብ ፅፏል፡
ብርሀኑን ገልፆ እጂግ ፅልመት ገፏል፡
ከጨለማ መረብ ከም ትውልድ አትርፏል፡

ስህተት ለመልቀም ሁሌም አትደገስ፡
ተመልከት ውበቱን አስብ ግርማ-ሞገስ፡
ዱንያ ላይ እስካሉ እንደሱ ነው መንገስ፡
ሁሌ እንዳፈረሱ የቢዲዓን ፈንገስ፡

የውሒድ ችቦ አብሪ የድል ቀንድ ለኳሽ፡
የሒዝብያን ጂሬ በመረጃ ተኳሽ፡
ያለምንም ህፀፅ ያለ ድንበር ማለፍ፡
ይህ ሰው መምህር ነው መዘሀበ-ሰለፍ፡

በሰለፎች አቋም አምሮ እንደደመቀ፡
ቀደሩ ደርሶበት ዱንያን የለቀቀ፡
ተመልከት በሀይባ ሲነግስ ብቻውን፡
ፍቅሩ ልብ ይነጥቃል እዩት አንበሳውን፡

ሐቅን ለመናገር የማያመነታ፡
በእውቀት መድረክ ላይ ጠማማን የረታ፡
ፀባይን ያዋሰው የአለማት ጌታ፡

ጥበብ የተሰጠ ከረበል-አለሚን፡
ተውሒድ የወረሰ ከሙሀመድ አሚን፡
የሀረሙ አንበሳ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን፡

በኑረዲን አል አረብ

https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
بَارَكَ الله لَكُما، وَبَارَكَ عَلَيْكُما، وَجَمَعَ بَيْنَكُمَا فِي خَيْرٍ

😴 𝐔𝐦𝐮 𝐎𝐮𝐛𝐞𝐢𝐝𝐚 😴

🌸እኳንም ደስ አለሽ🌸


አልሀምዱሊላሂ ብየ ልጀምረዉ
የአለማቱ ጌታ ምስጋና ለሱነዉ
አላህ በራህመቱ እሱ  የወፈቀን
ከዝሙት አርቆ ሀላልን የሰጠን

አልሀምዱሊላህ እሱ  አስከበረን
ዉድቷ እህታቺን እኳን አደርሰሽ
የኢማንን ግማሽ ትዳርን ወፈቀሽ
የክብር ማማላይ ጌታቺን አስቀመጠሽ
ከብቸኛ ሂወት ንግስት አደረገሽ

ዘቡራ ኡመር የኛ ልዩ እህት
ትዳርሽን ያርገዉ ደስታ የሞላበት
መልካም ሷሊህ ልጂች እምታፈሩበት
አላህ ያዝልቃችሁ ከዱንያ እስከጀነት

እኳንም ደስ አለሽ እኛ ደስብሎናል
ከብቸኛ ሂወት አላህ  አዉጥቶሻል
የአይንሽ ማረፊያ ጀሊሉ  አድሎሻል
የክብር ማማላይ አሏህ   አዝልቆሻል

እህታቺን ዉብነሽ በጣም እምንወድሽ
ልክ እደሉል አንች እኮ  ዉድነሽ
አላህ ያዝልቅሽ እደህ ዉድ እደሆንሽ
በትዳርሽ ኑሪ ሁሌየም ተደስተሽ ።


    🌸አደራ የምልሽ 🌸


በተዉሂድ በሱና ሁልግዜም ደመቂ
ከመጥፎ ጓደኛ አደራ እህቴ እራቂ
በትዳርሽ መሀል ሸይጧን እድይገባ በደብ ተጠቀቂ

ባጋጣሚ ጉዳይ ክፍተት ቢኖርበት
እህቴ ሰትሪዉ አደራ እዳታወሪበት
ትዳርሽን ምሪ አደብ በተሞላበት


  🌸አደራ በሱናላይ 🌸


ሂወትሽ እዲያምር ትዳርሽ እድሰምር
ልክ እደጨረቀ ሁልግዜ እዲያምር
ትዳርሽ እዲያብብ ደግሞ እዲያፈራ
በሱና ላይ በርቺ እህቴ  አደራ


  🌸 እህት ተጠቀቂ 🌸


ከባልሽ አጠገብ ሌላዉ ከማዉራት
እህቴ እራቄ እዳይገባ ክፍተት
ያንቺ ባል ላቺ ልክ እደሉል ነዉ
ዉበቱም ያቺ እጂጉን  ልዩነዉ

ከወዶቹ ሁሉ ያቺባል ሉልነዉ
እናም አሞግሸዉ ፍቅርሽን ግለጪለት
እደምትዉጂዉ ሁልየም  አዉሪለት

መልካም ፅባዩን አዉ አናግሽለት
እህቴ አደራ በትዳርሽ መሀል እዳይገባ ክፍተት።


🌸ትዳር🌸


ትዳርሽ ላቺ አወ ሂጃብሽ ነዉ
የመደበቂያሽ የመከበሪያሽ ነዉ
ትዳርሽ ላቺ እህቴ ጌጥሽነዉ

እዳይደበዝዝ በደብ ተያሺዉ
እደ ደቤኔ እቁላል ከተከባከብሽዉ
ልዩ የሆነን ፍቅር ከሰጠሽዉ
ከሌሎች ወንዶቺ ጋር ካላወዳደርሽዉ
ልቡን በሙሉ ላቺነዉ እሚሰጠዉ
ወጥቶ እስተሚመለስ በጣምነዉ እሚጓጓዉ


🌸አቺ ብለሽ ታልሺዉ 🌸


ንዉሴ እኮነህ በጣም የምወድህ
እኔ ዘንድ አተ እጂጉን ልዩ ነህ
ላንተኮ በጭራሽ  አምሳያ የለለህ

የሂወት አጋሬ አበባየ  እኮ ነህ
ወጥተህ እስተምትመጣ ትናፍቀኛለህ
እደ እህል ዉሃ ጠምተህ ትርበኛለህ
ሀቢቢዋ ለኔ የምር   ልዩነህ ።


«ከኢብኑ ተይሚያ ጀመአ እህቶችሽ  ደስታሺ ደስታችን ነዉ መልካም የትዳር ዘመን እንመኝልሻለን» 🌸እንወድሻለን🌸

=
t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Audio
🔖ሴት ልጅ እቤቷ ውስጥ ሆና እስፓርት መስራት ትችላለች። ነገር ግን ጂም ቤት፣ የሴቶች እስፓርት ቤት መሄድ ግን አይፈቀድላትም። http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
ለጌታዋ የምትጠይቀው፣ እንዲሰጣት የምትፈልገው፣እንዲያስተካክልላት፣እንዲያሽራት፣ የልቧን መሻት እንዲፈፅምላት የምትከጅለው ብዙ ነበር። ግና« ያ ረብ» ብላ ከማልቀስ ውጪ ሌላ ቃላት ማውጣት አልቻለችም። የምወድሽዋ እንኳንም ጌታሽ ዘንድ አለቀስሽ። አብሽሪ! ሰላም ለልብሽ!

منقول
=
t.me/https_Asselefya1
በትልቅ የአላህ ፀጋ ዉስጥ ዋልን፣ እሱም የአላህ ሲትር ነው። አዛኙ አላህ ገመናችንን ሸፈነ። ሲትራችን ቢገለጥ ኖሮ ስንት ጉዳችን በወጣ።

ያ ረብ ከኔ ጋር ሁን።
منقول
=
ከዓኢሻህ - ረዲየላሁ ዐንሃ - በተላለፈ ዘገባ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

إِنَّمَا أَهْلَكَ الَّذِينَ مِنْ قبلكم أنهم كانوا إذا سرق فيهم الشريف، تَرَكُوهُ. وَإِذَا سَرَقَ فِيهِمُ الضَّعِيفُ أَقَامُوا عَلَيْهِ الْحَدَّ. وَإِنِّي، وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ! ‌لَوْ ‌أَنَّ ‌فَاطِمَةَ بِنْتَ مُحَمَّدٍ سَرَقَتْ لَقَطَعْتُ يَدَهَا)

“ከእናንተ በፊት የነበሩትን ያጠፋቸው ባላባት ሲያጠፋ ሲያልፉት፤ ደካማ ሲያጠፋ ግን ህጉን ተግባራዊ ያደርጉበት ነበር። ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ ብትሰርቅ እጇን እቆርጣት ነበር!” [አልቡኻሪይ: 3288] [ሙስሊም፡ 1688]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor