💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
እኔ የምላችሁ ዉስጥ ሳይገናን ከላይ መመሳሰል ምንድነዉ ጥቅሙ ? በአካል ዉሻ እና ድመት በሚድያ ላይ እጅና ጓንት የሚኮነዉስ ለምንድነዉ እስኪ አስረዱኝ እ? እስከ መቼ ማስመሰል ?

=
«ጨው ዉሃ ሊቀዳ ሄዶ በዛው ሟምቶ ቀረ!»

"መቀየር ከማትችለው ሰው ጋር አትታገል እራስህን እንዳታጣ! አስተውል።
منقول
=
القارئ علي الحذيفي فأوحينا إليه أن اصنع الفلك بأعيننا ووحينا فإذا…
💭🌸خدمة تلاوات🎧
ቁርአንን አስተካክሎ ማንበብ ትልቅ የአላህ ኒእማ ነው። ጥረት ከተደረገ እንደ ቁርአን ቀላል ነገር የለም።

«ከቁርአን ጋር እንኑር

=
t.me/https_Asselefya1
عجبا!!


عجبا لمن اتقى حر الصيف في الدنيا كيف لا يتقي باجتناب الذنوب حر جهنم يوم القيامة

«በዚህ አለም ላይ የበጋን ሙቀት የሚፈራ ሰው እንዴት ከሀጢያት በመራቅ በቂያማ ቀን የጀሀነምን ሙቀት አይፈራም»

=
t.me/nuredinal_arebi
Forwarded from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے (لَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق)
አንዲት የ Pakistan ተወላጅ የሆነች እህት በኒካኋ ቀን መህሯን ኪታቦች እንዲገዛላት በጠየቀችው መሰረት ትላንት መህሯን ተረክባለች!
----

اللهم بارك

©ከTweeter
t.me/abdu_rheman_aman
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲አድስ ተከታታይ ፅሁፍ    ▱▰▱▰▱▰▱▰ ➭ፋጡማ ቢንት ሙሀመድ ረዲየላህ አንሃ ክፍል ❶ 👑ፋጢማን ያስደሰተ አላህን እንዳስደሰተ ነው። እሷን ያስቆጣ አላህን እንዳስቆጣ ነው አባቷ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የሙሃመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና የኸድጃ ረ.ዐንሃ አምስተኛ ልጅ የሆነችው ፋጢማህ ረዲየሏሁ አንሃ አባቷ ከሁሉ ነገር ተለይተው ወደ መካ ተራራ በመዝለቅ ስለ ፍጥረተ አለሙ ማሰላሰል (መመራመርና…
ፋጡማ ቢንት ሙሀመድ  ረድየላሁ አንሃ
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

           ክፍል
ሁለት

አንድ ወቅት ገና አስር አመት ሳይሞላት አባቷን ተከትላ ወደ መስጅደል ሀራም (ካዐባ)ሄደች ከዚያም አባቷ ሂጅር በተባለው ስፍራ ላይ በመቆም ወደ ከዕባ ዞረው ፀሎት ሲያደርጉ ከጎናቸው ቆመች። የነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ግንባር ቀደም ጥላት የነበሩ የቁረይሺ ጉግ ማንጉጎች በእርሳቸው ላይ ጥቃትን ለመፈፀም በቦታው ተሰበሰቡ። ከእነርሱም ውስጥ አቡ ጀህል፣ ኢብኑ ሂሻም፣ ዑቅባህ ኢብን አቢ ሙዐይጥ፣ ኡመያህ ኢብኑ ኸለፍና እንዲሁም ሸይባና ኡትባህ ይገኙበታል።

እነዚህ ሰዎች በነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ጥቃት ለማድረስ ወደ እርሳቸው ተጠጉ ተንኮሉን ሲያስተባብር የነበረው አቡ ጀህልም ወዳጆቹን ማንኛችሁ ናችሁ የከብት የግመል አንጀት አምጥታችሁ በሙሃመድ ላይ የምትጥሉት? ሲል ጠየቀ። በተኮለኚነቱ የሚታወቅ የነበረው ዑቅባ ኢብን አቢ ሙአይጥም ጥያቄውን ፈጥኖ በመቀበል ፀያፍ የሆነውን ስራ ለመተግበር አንጀት ፍለጋ ተፈተለከ።

ሺታው አፍንጫ የሚበጥስ ቆሻሻ በማምጣትም ነብዩ ሰላሁ አለይሂ ወሰለም ስጁድ ላይ በነበሩቀት ጊዜ በላያቸው ወረወረው። ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ወዳጅ (ሰሀባ )የነበረው አብደላህ ኢብኑ መስኡድ ረዲየላሁ አንሁ በቦታው ቢኖርም በእነዚህ በከተማይቱ ሹማምንት ላይ ምንም አይነት እርምጃ መውሰድ አልቻለም። ታዲያ ፋጡማ ረ.አንሃአባቷን ጥላቶቻቸው በዚያ ስሜት በሚጎዳ ሁኔታ ሲያጠቋቸው ስታይ ምን ይሰማታል? እንደዚሁም ይህቺ አስር አመት እንኳን ያልሞላት ልጃገረድ ምንስ ልታደርግ ይቻላታል? አዎ ትንሿ ፋጡማህ ረ.አንሃ ለፈጣሪያቸው ሱጁድ እያደረጉ መሬት ላይ እንደተደፉ በነበሩበት አባቷ ላይ የተጣለውን ቆሻሻ በማሶገድ በቁጣና በልበ ሙሉነት ዲርጊቱን የፈፀሙትን የቁረይሺ ወራዶች መሳደብ ጀመረች።

እነርሱም በእርሷ ላይ አንድትም ቃል ትንፍሺ አላሉም። ታላቁ ነብይም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከሱጁዳቸው በመነሳት ሰላታቸውን ከጨረሱ በኃላ "ጌታየ ሆይ!" ቁረይሾችን የእጃቸውን ስጣቸው ሲሉ አላህን ለመኑት። ይሄን እርግማን ሶስት ጊዜ ደጋገሙት በኃላ በማስተካከል እንድህ አሉ "ኡትባህን፣ ዑቅባህን፣ አቡ ጀህልንና ሸይባን የእጃቸውን ስጣቸው" እነዚህ ሁሉ ብዙም ሳይቆይ በበድር ጦርነት ላይ ተገድለዋል

በአንድ ወቅት ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፋጡማህን ረዲየላሁ አንሃ አስከትለው ከዕባን በመዞር ላይ ሳሉ የቁረይሺ ወረበሎች ከበቧቸው በልብሳቸው ለማነቅ ተያያዟቸው በዚህን ጊዜ ፋጡማ ረ.አንሃ ሰዎች ለእርዳታ እንዲደርሱላቸው በእሪታ ተጣራች። ጩኸቱን የሰሙት አቡበከርም ረ.አንሁ በስፍራው ፈጥኖ በመድረስ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን ለማስለቀቅ ቻሉ። በቁጣም ለመሆኑ አንድ ሰው ፈጣሪየ አላህ ነው በማለቱ ትገድላላችሁን?!በማለት ወቀሳ ሰነዘሩባቸው።ወረበሎቹ ለአቡበከርም አልተመለሱም። ይልቁን ከጭንቅላታቸውና ከፊታቸው ላይ ደም እስከሚፈስ ደበደቧቸው።



✍️የፋሩቅ እናት

ኢንሻአላህ ይቀጥላል
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➧ሓያትህ መርፌ ቢሆን እንኳን ሪዝቅህ ክር ሆኖ ይመጣል እንጂ አይስትህም!! ልብህን አረጋጋው በጌታህ ላይ የቂን ይኑርህ...!
«የሂጃብ አላማ አለዉ ዋና እና ትልቁ አላህን መታዘዝ ነዉ 2ኛ ደረጃ የአላህን ዉደታ እና ደስታ ማግኘት ነዉ። ሌላኛዉ  ደረጃ የሂጃብ አላማ ፊትናን መከላከል ነዉ። ሌላኛዉ አላማ ወጣቱን ዲኑ ላይ ቀጥ እንድል መርዳት እና ማገዝ ነዉ። ሒጃብ ስታደርግ  ለራሷ ብቻ ሳይሆን የምታስበዉ ወይም ልታስብ የሚገባት  ለወንድሟም ጭምር ነዉ  ኢማኑ ላይ ድክመት ያለበት ወንድ  የተገላለጠችን ሴት ሲያይ አይኑን ሰበር ማድረግ አይችልም ። ሙሉ ሒጃብ ያደረገች ሴት በሚያይበት ጊዜ አይኑን ሰበር ያደርጋል ሌሎች ላይ አይኑ ለመስበር በር ይከፍትለታል ትምህርት ይሆነዋል።»

🎧ከደርስ የተወሰዴ!
=

t.me/https_Asselefya1
«ቁርአን የህይወት ብርሃን፣ ለአማኞች ፈዉስና ክብር፣ ለሰዉ ልጆች በሙሉ የሁለት አለም ስኬት ፣መንገዶችን ማሳያና ለህይወት አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ የሚያብራራ፣ህጉን ለተከተሉ የቂያም ቀን መስካሪ እንደሆነ በርካታ የቁርአን አንቀፆችና ነብያዊ ሐዲሶች ተብራርተዋል።

«وَنُنَزِّلُ مِنَ ٱلۡقُرۡءَانِ مَا هُوَ شِفَاۤءࣱ وَرَحۡمَةࣱ لِّلۡمُؤۡمِنِینَ وَلَا یَزِیدُ ٱلظَّـٰلِمِینَ إِلَّا خَسَارࣰا »


«ለአማኞች ፈዉስና እዝነት የሆነን ቁርኣን እናወርዳለን፣በእርሱ በመካድ እራሳቸዉን ለበደሉ ኪሳራን እንጅ ሌላ ምንም አይጨምርላቸዉም።» «አል ኢስራእ 82»

​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
http://t.me/https_Asselefya1
መልካም ጓደኛ
➫➫➫➫➫➫

ሁለት ውብ የሂወት ኡደቶችን ይለግሰሀል… "አንደኛው እዚህ ዱንያ ላይ ሲሆን" "ሁለተኛው ደግሞ ጀነት ውስጥ ይሆናል"

መልካም ጓደኞች «ወደ አሏህ መንገድ… ይጠሩሀል…» «ከጠፋህባቸው… ይፈልጉሀል…» ከተዘናጋህ… አስታውሱሀል»

«…በዱአቸው ውስጥ…ያካቱሀል»
«ልክ እንደ ከዋክብቶች… መርከብህ መንገድ ከሳተች…ይመሩሀል
…» «ነገ ከአሏህ አርሽ ስር…ኢንሸአላህ…ይጠብቁሀል…» «ጀነት ውስጥ ፈልገውህ ካጡህ…

አሏህን ወደነሱ እንዲቀላቅልህ ይለምኑልሀል» "አሏህ ሶሊሆቹን አድርጎ ከሶሊሆቹ ያወዳጀን ከሶሊሆቹ ጓደኞቻችን አይነጥለን በያሉበት ይጠብቅልን "


ያአላህ ምንኛ መታደል ነው እንደዚህ አይነት ጓደኛ ማገኘት አላህ ይወፍቀን እኛንም መልካሞች ያድርገን!!
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
" የሰው ልጅ ደካማ ከመሆኑ የተነሳ

አንድ ቃል ታስደስተዋለች
አንዷ ደግሞ እንዲያዝን ታደርገዋለች

( وَخُلِقَ ٱلْإِنسَٰنُ ضَعِيفًۭا )
" ሰውም ደካማ ሆኖ ተፈጠረ ፡፡"
[ኒሳእ 28]
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❞ الواسطة بين الحق والخلق ❝ «አል ዋሲጠህ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ» 【መግቢያ ከባለፈ የቀጠለ ❸】 ⭞ ይች የተከበረች አያህ(አንቀፀ) የምታመለክተዉ ወደ አላህ ለመድረስ ብቸኛዉ መንገድ ትክክለኛ የሆነ እምነት ከዚያም በደነገገዉ መሰረት አላህን ማምለክ ነዉ። ይች አያህ አምልኮን ከእምነት ያስቀደመችዉ በአላህ ዉደታ ለመጎናፀፍ ጀነቱን ለማግኘት የመልካም ስራ አስፈላጊነትና አንገብጋቢ…
الواسطة بين الحق والخلق


✍️አል ዋሲጠህ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ

      【መግቢያ ከባለፈ የቀጠለ ❹】

🌹 ዑመር  ኢብኑል ኸጧብ የነብዩን ዛት ትተዉ በዓባስ ዱዓእ ተወሱል ከማድረጋቸዉ ዉጭ ሌላ በአንብቢያዎችና በደጋጎች ዛት ተወሱል ማድረግ  እንደማይቻል መረጃ ባይኖር ኑሮ በነዚህ ሰዎች  ላይ ምላሽ ይበቃ ነበር።

📚 ኢማሙ አቡ ሐኒፋ  የተናገሩት  ንግግር ምንኛ ያማረ ነዉ፦ አላህን በአላህ እንጅ መጠየቅ እጠላለሁ። (አዱሩል ሙኽታር ከሌሎችም  የሐነፍያህ ኪታቦች ላይ ይገኛል።

🎀በጠቀስናቸዉ ዘዋት ወደ አላህ አዳራሽ መያዝ የሚቻል ቢሆን ኑሮ ከብዛታቸዉ ጋር  የቁርአን የሐዲስ መልእክት በዛታቸዉ ተወሱል የሚቻል መሆኑን ይዘዉ ይመጡ ነበር !

📝3ኛ፦ከሙስሊሞች ዉስጥ ይህችን ወሳኢጥ ሪሳላህ ናት ብሎ የተረዳ አለ። እርሷንም ማድረስ ፣ማስተማር ኮትኩቶ ማሳደግ ናት (ይላል)።  የጉዳዩን የበላይነት  የሰዉ ልጅ ለእርሷ ያለዉን ፈላጊነት አገኘ። ሸሪዓን ለማግኘት  በወሕይ ለመብራት ትልቅ ወሳኢጥ ከባዱ ወሳኢል አድርገዉ ለመያዝ ወደ መልእክተኛዉ ሮጡ  የህይወታየዉንም ታሪክ ቁርአንን እንደሚማሩ ይማራሉ። በዚህ ላይ አርማቸዉ የአላህ ጥሪ ነዉ።

«قَدۡ جَاۤءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورࣱ وَكِتَـٰبࣱ مُّبِینࣱ } { یَهۡدِی بِهِ ٱللَّهُ مَنِ ٱتَّبَعَ رِضۡوَ ٰ⁠نَهُۥ سُبُلَ ٱلسَّلَـٰمِ وَیُخۡرِجُهُم مِّنَ ٱلظُّلُمَـٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ بِإِذۡنِهِۦ وَیَهۡدِیهِمۡ إِلَىٰ صِرَ ٰ⁠طࣲ مُّسۡتَقِیمࣲ »
«ከአላህ ዘንድ  ብርሃንና ገላጭ መፀሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ ። አላህ ዉደታዉን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገዶች በእርሱ ይመራቸዋል። ወደ ቀጥተኛም መንገድ ይመራቸዋል። «አል ማኢዳህ:15-16»


📝ይህቺ  ቡዲን(ፊርቃ)፦ ባሳለፍነዉ ሐዲስ  የተጠቀሰችና በጀነት የተበሰረች ቡድን እርሷ (በዱኒያህ ከጥመት በአኼራ ከእሳት )ነፃ ወጭዋ ናት። በጣም የሚያመዉ ነገር የዚች ቡዲን መንገድ በሾሃማና  በዳገታማ የተሞላ መሆኑ ነዉ። ምክንያቱም ትክክለኛ እስልምና እንግዳ ሁኗል። ብዙሓኑ ሙስሊም እርቆታል። በፈጠራዎች እና በስህተቶች ቀይረዉታል። ይህ ችግር የቆየ በመሆኑ የአስተካካዮች ሚና አደገኛ እና አድካሚ ነዉ።


📝 ኢንሻ አላህ ይቀጥላል ....📝

  ──────⊹⊱✫⊰⊹──────
http://t.me/https_Asselefya1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM