💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
አህለን ወሳህለን ቤት ቤትኩም እንግዶችዬ🕶
⁌በመጀመሪያው የግንኙነት ለሊት ምን ማድረግ ይገባል!!⁍
    

ጥያቄ፡
☞በጋብቻ ቀን ለሊት ለባልና ሚስት ሱናው ምንድነው? ከነብዩ የተገኙ ዱዓዎችንና ስራዎችን እንድትጠቅሱልን እንፈልጋለን፡

መልስ፡

⁍ባል ከሚስት ጋር በሚገናኝበት ለሊት ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ነገሮች ውስጥ፦

☞ለሷ ክንፉን ዝቅ አድርጎ(ተረጋግቶና) ጭርታን በሚያስወግድ መልኩ ወደሷ መግባት አለበት። ምክንያቱም በዚህ ሰአት ጭንቀትና ፍርሀት እሷ ዘንድ ይኖራልና።

☞ሯሷን ይዞ የሚታወቀውን ዱዓ ያድርግ
"አላህ ሆይ!
ከኸይር ነገሯና በእሱ ላይ እሷን የፈጠርክበትን ኸይር እጠይቅሀለሁ፡ ከሸሯና በእሱ ላይ እሷን ከፈጠርክበት ሸር በአንተ እጠበቃለሁ"፡ ይህንን በግልጽ (ድምጹን ከፍ አርጎ) ይበል፡ ምናልባት ሰግታ "ምንድነው? በኔ ላይ ሸር አለ?"  ትላለች ብሎ ካልፈራ በስተቀር፡ ይህን ከፈራ እጁን ልሡ ላይ አስቀምጦና ድምጹን ዝቅ አርጎ መቅራት በቂ ነው።

☞ሁለተኛው የአላህ መልእክተኛ  -- አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር ግንኙነት ሲያደርግ  እንዲል ያነሳሱበትን ዚክር ይበልአንዳቹህ ወደሚስቱ ሲመጣ "በአላህ ስም! አላህ ሆይ እኛን ከሸይጧን ጠብቀን፡ የምትሰጠንንም ከሸይጧን ጠብቅ" ካለ በመካከላቸውም ልጅ ከተቀደረ ሸይጧን መቼም አይጎዳው !!

«ይሄ ልጆችን ከማስተካከያ ሰበቦች ነው። ቀለል ያለም ሰበብ ነው።»

↷ልክ እንደዚሁ መገንዘብና ማወቁ ከሚያስፈልግ ነገሮች… ግንኙነት እስካረጉ ድረስ የዘር ፈሳሽ ባይፈስም በሁለቱም በኩል ገላን መታጠብ ግድ ይላል።ከፊሎች በተቃራኒው መታጠብ ግድ የሚለው የዘር ፈሳሽ ሲፈስ ነው ብለው ያስባሉ ይሄ እሳቤ ስህተት ነው።ምክንያቱም ነብዩ --   <በአራት ቅርንጫፎቿ መሀል ከተቀመጠና ግንኙነት ከፈፀመ የዘር ፈሳሽ ባይፈስም ትጥበት ግድ ሆኗል> ብለዋልና።

↳በዚህም ከሁለት በአንዱ ትጥበት ግድ ይላል፡ ወይ የዘር ፈሳሽ በመውጣት ወይም በግንኙነት። የዘር ፈሳሽ የወጣው በመሳሳም ቢሆን በመተቃቀፍም ቢሆን ወይ በስሜት በማየትም ሆነ በመነጋገር በየትኛውም ቢሆን መታጠብ ግድ ነው።ግንኙነት ተደርጎም የዘር ፈሳሽ ባይወጣም መታጠብ እንዲሁ ግድ ነው።

↳ብዙ ሰዎች ግንኙነት ፈፅመው በወቅቱም የዘር ፈሳሽ ካልወጣ እንደማይታጠቡና በዚህም ብዙ ወራት እንዳለፉ (ምን ማድረግ እንዳለባቸው) ይጠይቁናል። የዚህ ምክንያቱ የሚያገባ ሰው በጋብቻ ወቅት ምን ማድረግ እንደሚገባና ምን ግዴታ እንደሆነ አይጠይቅም። ብዙዎቹም ሰዎች እንደዚህ አይነት ትምህርቶችን በወጣቶች መካከል አያሰራጩም።
    
لِلشَّــيْخ العَلّامـَـة/ مُحَـمَّد بـنُ صَـالِح العُثَـيْمِين -رَحِــمَهُ الله-

منقول
=
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1
PTT-20200730-WA0003.opus
254.3 KB
ዉብ ቲላዋ ተጋበዙልኝ

~

ቁርአን ማንበብና እንዲሁም በትኩረት ማዳመጥ ትልቅ ኢባዳ ነው!
سورۃ الغاشيۃ
Abu Useymin
ደገምኳችሁ ተጋበዙ ምሺታችሁ ደመቅ ይበል !
~

🎙አቡ ዑሰይሚን
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
የምሺቱ ስጦታዬ ዉሰዱ = t.me/https_Asselefya1
ጓደኛ ቤተሰብ ወደ ሀገር ስትልኩ የመሸኛ ፕሮፍይል ስትሰሩ አየር ስትፈልጉ ወደ ቤታችሁ ጎራ ብላችሁ ዉሰዱ ስላችሁ...

=

http://t.me/https_Asselefya1
ሁለየም እንደምልሺ አንድ ነገር ሳትሞክሪ አልችልም አትበይ ሞክሪ ትችያለሺ አንቺኮ ልዬ ፍጡር ነሽ ብዙ ነገር መስራት ትችያለሺ ሃቢቢቲ !! ደስ ከሚለኝ ነገር ሁሉንም መሞከር ነዉ እየሞክራችሁ የሞከረ መቻሉ ሰለማይቀር ጠንክሩ ማለቴ ነዉ ።

=
t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተፈጥሮ አየት አድርጉና በሉ እርፍ በሉልኝ
መልካም ለይል
.......🕶

=
Audio
تلاوة من سورة الكهف

🎙አቡ የህያ ኢድሪስ አህመድ

t.me/Abu_yehya/333
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጀግንነት ከፈለክ ከስደተኛዋ ተማር ይሄ ሁሉ እቃ መቀመጫዉ ቦታ አፀድታ መልሳ አስተካክላ ቤቱ ፏ የምታደርግ እነቁ እኮ ነች!!

ከዛም ቀኑ ሙሉ የደከመ ሰዉነቷ ተቋቁማ ቁጭ ብላ እንቅልፏ እያዳፍት ድኗ ትማራለች እዉነትም እንቁ ነች ጀግና 💪 ክፉ አይንካችሁ በርቱ ሂቢባቶቼ!

መልእክት አረብ ሀገር ብር የሚታፈስ የሚመስላችሁ እንድህ ወገብ ቁርጥ ብሎ ነዉ የሚገኝ !!

እድህ ያለ ቤት እስከ አሁን በስደት ስኖር አላጋጠመኝም ስራ ግን ብዙ እህቶች የምትኖሩት ነዉ አላህ ሀይልእና ቅዋዉ ይስጣችሁ እህቶቼ አይዞችሁ ያልፋል እሺ ጠንክሩ !!

=
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ15 በላይ የጋዝ ሲሊንደር የተሰረቀበት ሰው ስለ ሌባው ምን ሊል ይችላል??
በኢስላም የተኮተኮተ ስብእና ግን ምንም እንኳ በመሰረቁ ቀልቡ ቢሰበርም ግን ይህን ብሎታል!

"አላህ ይስጠውና ለምን እንደሆነ ባላውቅም 1 ፍሬ ሲሊንደር አስተርፎልናል... " ብሎ አስቀጥሎ:-

"አላህ እንዲመራው፣ ይቅር እንዲለው፣ በዱንያም በአኼራ ነውሩን እንዲሸፍንለት አላህን እለምነዋለሁ!!
ካላሰበው በኩልም ሲሳይን እንዲሰጠው እለምነዋለሁ!!
የመጨረሻው የስርቆት ገንዘቡ ያድርግለት!!
እንዲመራው እንዲምረው እለምነዋለሁ!!

አላህ ሆይ ባንተም በፍጡሮችህም ምስክርነት ይኸው ምሬዋለሁ...!!!"

ሱብሀናላህ አይገርም ግን ︎⁈⁉

ከኢስላም ውጪ ያለ ሰው ቢሆን ገንዘቡን ንብረቱን ለሰረቀበት ሰው ምን ሊለው ይችላል?? እንደው አልገረመውም ብለን ብናስብ ቢያንስ ቢያንስ ለበረካው "የበላኸው ሰውነት አይሁንህ..." የመሰለች ትንሽ እርግማን ቢጤ ጣል አያደርግም ብላቹ ታስባላቹ??

ማንምኮ ለሰረቀው ሰው እንዲ በምርቃትና በዱዓ አያንበሻብሽም ሙስሊም ሲቀር

الحمد لله على نعمة الإسلام


✍️መንቁል
🥀የእህታችን ጦይባ ኡሙ ዑበይዳህ የሺኝት ፕሮግራም 🥀

የሱና እህታችን ኡሙ ዑበይዳህ
ሀገር  ብንለያይ ቢያራርቀን ቦታ
ባለንበት ሁነን አለን በትዝታ
በድን በትስስር ጠንክረን እንበርታ!!

በሱና አሸብርቀሽ በሂጃብ ተዉበሽ
አብሽሪ የኛ እህት ኑሪ ቀጥ ብለሽ
ፅኚ በድንሽ ላይ  ፊትናም ቢበዛብሽ

አደራ የኛ እህት መጠንከር አለብሽ
የሱና ጥላት ፊቱን ቢያዞርብሽ
እንዳትጨነቂ ምንም እንዳይመስልሽ
በርችልን የኛ እህት መፅናት ነዉ ያለብሽ!!


በድንሽ ጠንክረሽ አውቀሽ አሳውቂ
የመጣው ቢመጣ እዳትጨነቂ፣
ሰወችም ይሉሻል አክራሪ አሸባሪ
አላህ ከኛ ጋር ነው ምንም እዳትፈሪ

አኼራን ረስተሽ ለዱንያ እዳታድሪ
በድንሽ ለመጣ አትደራደሪ፣
እናማ አህቴዋ አደራየ ይህ ነው
የተፈጠርንለት አላማ ተውሂድ ነው


ጉዟችን አድካሚ ቢሆንም መራራ
አላህ በእውቀቱ ነው ከእኛ ጋራ፣
ምንም አትስሚያቸው  ያወራ ቢያወራ

አንድ ላይ አይሆንም ስኳርና አቧራ
ይሄንንም ስልሽ አይደል ካንች አውቄ
ሁሉ እደሚገባሽ አውቃለው ጠንቅቄ፣


መልካም ጉዞ እንመኝልሻለን የኢብኑ ተይሚያ ጀመዓዎችሺ ኡሙ ዑበይዳህ ዉዷ እህታችን

=

t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed