💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ቀ.ውሱ ወሊይ አሕመደል በደዊይ
~

በሙስሊሙ ዓለም ስማቸው ከገነኑ የሱፊያ ወልዮች ውስጥ አንዱ አሕመደል በደዊይ ነው። በደዊይ በያመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ቀብሩን ይጎበኛል። ያገራችን ሱፍዮች:-
"አሕመደል በደው
ጠላታችንን ገደል ሰደደው!"
እያሉ የሚመፃደቁበት ታላቅ ወሊያቸው ነው።
ምን አይነት ሰው ነበር? ብዙ ፀሐፊዎች ቀ.ውስ እንደነበር ሲገልፁ ሌሎች ደግሞ እብ.ድ እብ.ድ የሚጫወት የበኑ ዑበይድ ሺዐዎች ሰላይ ነበር ይላሉ። የዐብዱሶመድ ዘይኑዲን አልአሕመዲይን ምስክርነት ላስቀምጥ። እንዲህ ይላል ስለ በደዊይ፦
وأقام على سطح الدار لا يفارقه ليلًا ولا نهارًا، وإذا عرض له الحال يصيح صياحًا متصلًا، وتزيَّى أحمد البدوي بزي المجاذيب، وظل ضاربًا اللثامين على وجهه، وكان إذا لبس ثوبًا أو عمامة لا يخلعها لغسل حتى تذوب، فيبدلونها بغيرها
"በቤቱ ጣራ ላይ ኑሮውን አደረገ። ሌትም ቀንም ከሱ አይለይም። ሓሉ ሲነሳበት ረጅም ጩኸት ይጮሃል። አሕመደል በደዊይ የወፈ -ፌዎችን ገፅታ የተላበሰ ነበር። ፊቱ ላይ መከናነቢያ እንዳደረገ ነበር የሚቆየው። ቀሚስ ወይም ጥምጣም ሲለብስ ላዩ ላይ (ቆሻሻው) እስከሚቀልጥ ድረስ አያወልቀውም ነበር። ከዚያ ሰዎች በሌላ የሚቀይሩለት።" [አሰዪዱል በደዊይ ዲራሳህ ነቕዲያህ፡ 15]

ሲዩጢይ (911 ሂ.) እና አልሙናዊይም (1031 ሂ.) ቀደም ብለው ይህንን እውነታ ገልፀውታል። [ሑስኑል ሙሓዶራ፣ ሲዩጢይ፡ 1/522] [አልከዋኪቡ ዱሪያህ፣ መናዊይ፡ 2/388]

ታዋቂው የታሪክ ፀሐፊ አልመቅሪዚይ (845 ሂ.) ደግሞ በአንድ ወቅት ጁሙዐ ቀን ኹጥባ ተጠናቆ ሶላት ሊሰገድ ኢቃማ ከተደረገ በኋላ አሕመደል በደዊይ ተነስቶ ህዝብ እያየው ሃፍረተ ገላውን ገልጦ ልብሱ ላይ፣ የመስጂዱ ምንጣፍ ላይ ሽንቱን እንደሸና ፅፈዋል። ሶላት የለ፣ ምን የለ። [ዱረሩል ዑቁድ፡ 3/77]

በ"ዳኢረቱል መዓሪፊል ኢስላሚያህ" ላይ ደግሞ እንዲህ የሚል እናገኛለን፦
وكان يمكث طوال نهاره وليله قائمًا شاخصًا ببصره إلى السماء، وقد انقلب سواد عينيه بحمرة تتوقد كالجمر، وكان يمكث الأربعين يومًا وأكثر لا يأكل ولا يشرب ولا ينام
"ቀንና ሌቱን ሙሉ አይኑን ወደ ሰማይ ገልብጦ ነበር የሚቆየው። የአይኑ ጥቁሩ ክፍል እንደ ፍም የሚንቀለቀል ቀይ ሆኖ ተቀይሮ ነበር። አርባ ቀን ሳይበላ፣ ሳይጠጣ፣ ሳይተኛ ይቆያል።" [ቅፅ 2፣ ገፅ፡ 476]
በደዊይ ብዙ ወዳጆቹ እንደሚሉት የአእምሮ ህመምተኛ ከሆነ ወሊይ ሳይሆን "መርፉዐል ቀለም" ነው። ነብያችን ﷺ "ቀለም ተነስቶላቸዋል" ማለትም ተጠያቂዎች አይደሉም ካሏቸው ውስጥ አንዱ ያበ'ደ ሰው ነውና። ሰውየው አንዳንዶች እንደሚሉት ለበኑ ዑበይድ የሚሰልል ሺ0 ከነበረ አላህ የስራውን ይስጠው። ብቻ ሱፍዮች ድንበር የሚያልፉበት ይሄ ሰው ሻል ቢል ሶላት የማይሰግድ፣ መስጂድ ውስጥ የሚሸና እብ.ድ ነው። በሱፍያው ዓለም ብዙ ቀውስ ወሊዮች ስላሉ ይሄ ብዙም የሚገርም አይደለም።

ማሳሰቢያ፦
ምንጭ ጠቅሼ ነው የፃፍኩት።
* ምስሉ በግብፅ ጠንጣ ከተማ ውስጥ የሚገኝ በአመት ሁለት ጊዜ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚሰባሰብበት ዶሪሕ (ቀብር) ነው።

( Ibnu Munewor ፣ ረጀብ 06/1445 (ጥር 08/ 2016))
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

* የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
ዛሬ ወደት ነሺ .... እንዳትደነግጡ ከሚድያ አንስቼ ነዉ ምን ልነግራችሁ መሰላችሁ ስንመጣ አየሩ ላይ ያለችዉ የምትሞቀዉ ፎጣ ነች ምነዉ ይዣት በወረድኩኝ ብዬ አሁን ትዝ አለችኝ ለካ ይዞ መዉረድ አይቻልም ህእ



=
እኛ ስንመጣ ነበረዴ በሉ !? ግን ይኖራል ያኔማ እኛ ስንመጣ ልጅነት+ፍርሀቱ ከቤተሰብ መለየቱ ዉስጣችን በጭንቀት ሞልቶ አየሩ ላይ ምን እንዳለ አስተካክለን ሳናይ የወረድን አለን .... ምን ልላችሁ ነዉ አሁን ስትሄዱ ነቃ ብላችሁ ጓዝ ሳታበዙ ቅልጥፍ ብላችሁ አየሩ ጎብኘት እያደረጋችሁ ሂዱ ማለቴ ነዉ ... 🕶 ሲሆን ከሀገር ዉጭ እየወሰዴ የሚያዝናና ሀቢብ ይወፍቃችሁ ! አሚን በሉ!

~
ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ።
~

ገንዘብ አልፈልግም የምትሉ ሴቶችኮ ትገርሙኛላችሁ የምር ባፈልጉ ነበር ግን ትፈልጋላችሁ እዉነቷ እናዉራ ከተባለ ገንዘብ ፍለጋ አይደል ወይ በሰዉ ሀገር ሰዉ ቤት ከሰዉ በታች ዝቅ ብለን የነሱ ቆሻሻ የምናነሳዉ !? ገንዘብ ካለ በሸቃልነት ሳይሆን ማዳም ሁነሺ ከሀቢቦ ጋር የተለያዩ ሀገሮች እየሄድሺ ትዝናኒያለሽ በቃ ሞልቀቅ ዘና ብለሺ ትኖሪያለሽ አለቀ። አላህ በሀላል ከስቦች ሀብታም ያድርገን አሚን !

=

t.me/https_Asselefya1
አትሸማቀቁ አዋቂ የተቀመጠው ያላወቀን ለማሳወቅ ነው። ብሳሳትስ ብላችሁ ሰውነታችሁ እስከሚኮማተር፤ሊያልባችሁ እስከሚቀርብ ድረስ አትጠበቡ።አስተማሪ የተቀመጠው እርሱን ስህተት ለማረም ነው።

የጻፍኩት እየተማሩ ሳለ የተማሩትን አስተማሪ ዘንድ ሲያሰሙ እሳሳት ይሆን ወይስ እያሉ ለሚሸማቀቁ ከልክ በላይ በፍርሃት ለ*ሚ*ዋ*ጡ ተማሪዎች ነው።በተለይም ለ Online ተማሪዎች።

አስተማሪዎች ሆይ! ተማሪን መንከባከብ፣ማበረታታት፣ተስፋ መስጠት ልማዳችሁ ይሁን።

አቡ ዑበይዳ፦ t.me/AbuOubeida
ለሰዎች መልካም/ቅን መሆንሺን ቀጥይበት እነሱ ግን ለኔ እኔ እንደምሆንላቸዉ ይሆኑልኛል ብለሺ አታስቢ ! ብዙ ሰዉ ለራሱ ጥቅም እንጅ ለሰዉ ግድ የለዉም። ግን አንቺ ቀጥይበት መልካምነትሺ/ቅንነትሺ አብሽሪ አንድ ቀን ታገኚዋለሽ የመልካምነትሽ ዋጋ ጠንክሪ ስልሺ ነዉ ኡኽታ.....!!

=
ባል እና ዋይፋይ ቀረብ ሲሉ ነዉ
ባል እና ሚስት ሲራራቁ ጥርጣሬ አለመተማመን ጭቅጭቅ በብር መጣላት በር ይከፍታል ክክ
ምርጧ ሴት
~
መልካም ሴት ማለት በጋብቻ አማካኝነት ክብሯን እንድትጠብቅ፣ ልጅም እንድትሰጥና እናትም እንድትሆን እድሉን የሰጣትን ጌታ ታመሰግናለች። በመቀጠልም ባሏን አመስጋኝ ነች።

~
t.me/yesunawakonjobetwuhidyabebech
ከሚስት ሀቆች

⓵ መህሯን መክፈል

ሴቷ ከመህሩ በፈቃዷ ወዳ እስካልሰጠች ድረስ የሷ ብቻ መብት በመሆኑ ለባልም ሆነ ለሌላ አካል ከሱ አንዳችን መውሰድ አይፈቀድላቸውም።
(وَآتُوا النِّسَاءَ صَدُقَاتِهِنَّ نِحْلَةً فَإِنْ طِبْنَ لَكُمْ عَنْ شَيْءٍ مِنْهُ نَفْسًا فَكُلُوهُ هَنِيئًا مَرِيئًا) [النساء:4]

"ሴቶችንም መህሮቻቸውን በደስታ ስጡ፡፡
ለእናንተም ከእርሱ አንዳችን ነገር ነፍሶቻቸው ቢለግሱ መልካም ምስጉን ሲኾን ብሉት፡፡"

{ኒሳእ 4}

=

t.me/https_Asselefya1
ከባል ሀቆች
~
❶ እሱን መታዘዝ

እንደሚታወቀው እስልምና ወንዶችን በሴቶች ላይ የበላይ ጠባቂ ሲያደርጋቸው በትዳር ህይወት ውስጥ ደግሞ ባልን የቤተሰብ ሀላፊና አስተዳዳሪ አድርጎታል።
     

በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመንሽው ሚስት ሆይ! ዱንያ ለአኼራ የምንዘጋጅበት ሀገር በመሆኑ ይህ ዝግጅትሽም የተሟላና ያማረ መጨረሻ እንዲኖረው ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ የባለቤትሽን ሀቅ ጠንቅቀሽ ማወቅሽና  መተግበርሽ ነው። እሱ በወንጀል እስካላዘዘሽ ድረስ ውስጥሽ ወደደውም አልወደደውም ትዕዛዙን በአግባቡ መፈፀም ከባል ሀቆች አንዱ ነው።

ሁሌም ጉዞሽ ስኬታማ እንዲሆን ቅንጣት የማይፈይድሽን የነ እከሌ አስተያየትና ፍልስፍና በመተው ለአለም እዝነት ተደርገው የተላኩትን ነብይ ወርቃማ ንግግሮች ላይ ብቻ ትኩረት ልትሰጪ ይገባል።

ረሱል صلى الله عليه وسلم የጥሩን ሴት መገለጫ ሲጠቅሱ "ባሏን ታዛዥ" የሚለውን አካተዋል።ስለዚህ በሳቸው አንደበት ከተመሰከረላቸው የምርጦች ምርጥ ለመሆንና ባልሽ ዘንድም ተፈቃሪ ለመሆን ኒያሽን አስተካክለሽ፣ የአላህን ምንዳ በመሻትና የሱንም እገዛ በመለመን የባለቤትሽን ትዕዛዛት በቻልሽው አቅም ለመተግበር ጣሪ።

አማኝ ሴቶች ለባላቸው ታዛዥ መሆን እንዳለባቸው ከሚያወሱ ሀዲሶች፦

"አንዲት ሴት አምስት ወቅት ሶላቷን ከሰገደች የረመዳንን ወር ከጾመች ብልቷን ከሀራም ከጠበቀችና ባለቤቷን ከታዘዘች በፈለግሽው የጀነት በር ግቢ ትባላለች።"
በዚህ ሀዲስ 3ቱ ተግባር ላይ ወንዶችም የታዘዙበት ሲሆን አንዱ ብቻ አንቺ የተነጠልሽበት ነው።


ውዷ እህቴ! ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ የሚገኘውን ውዷን ሀገር ጀነትን ከሚወርሱት እንጂ (አላህ ይጠብቅሽና)እንደ ብዙዎቹ ሴቶች የጀነትን በር በራሳቸው ላይ ከሚዘጉት ሴቶች ላለመሆን (አላህ ይወፍቅሽና)ክቡሩን ባልሽን ታዘዢ።


منقول
http://t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዘና እያላችሁ በአይናችሁ በእግራችንማ የት ተገኚቶ...🕶

↳ያልፍል አብሽሩ↲

=
አህለን ወሳህለን ቤት ቤትኩም እንግዶችዬ🕶
⁌በመጀመሪያው የግንኙነት ለሊት ምን ማድረግ ይገባል!!⁍
    

ጥያቄ፡
☞በጋብቻ ቀን ለሊት ለባልና ሚስት ሱናው ምንድነው? ከነብዩ የተገኙ ዱዓዎችንና ስራዎችን እንድትጠቅሱልን እንፈልጋለን፡

መልስ፡

⁍ባል ከሚስት ጋር በሚገናኝበት ለሊት ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ነገሮች ውስጥ፦

☞ለሷ ክንፉን ዝቅ አድርጎ(ተረጋግቶና) ጭርታን በሚያስወግድ መልኩ ወደሷ መግባት አለበት። ምክንያቱም በዚህ ሰአት ጭንቀትና ፍርሀት እሷ ዘንድ ይኖራልና።

☞ሯሷን ይዞ የሚታወቀውን ዱዓ ያድርግ
"አላህ ሆይ!
ከኸይር ነገሯና በእሱ ላይ እሷን የፈጠርክበትን ኸይር እጠይቅሀለሁ፡ ከሸሯና በእሱ ላይ እሷን ከፈጠርክበት ሸር በአንተ እጠበቃለሁ"፡ ይህንን በግልጽ (ድምጹን ከፍ አርጎ) ይበል፡ ምናልባት ሰግታ "ምንድነው? በኔ ላይ ሸር አለ?"  ትላለች ብሎ ካልፈራ በስተቀር፡ ይህን ከፈራ እጁን ልሡ ላይ አስቀምጦና ድምጹን ዝቅ አርጎ መቅራት በቂ ነው።

☞ሁለተኛው የአላህ መልእክተኛ  -- አንድ ሰው ከባለቤቱ ጋር ግንኙነት ሲያደርግ  እንዲል ያነሳሱበትን ዚክር ይበልአንዳቹህ ወደሚስቱ ሲመጣ "በአላህ ስም! አላህ ሆይ እኛን ከሸይጧን ጠብቀን፡ የምትሰጠንንም ከሸይጧን ጠብቅ" ካለ በመካከላቸውም ልጅ ከተቀደረ ሸይጧን መቼም አይጎዳው !!

«ይሄ ልጆችን ከማስተካከያ ሰበቦች ነው። ቀለል ያለም ሰበብ ነው።»

↷ልክ እንደዚሁ መገንዘብና ማወቁ ከሚያስፈልግ ነገሮች… ግንኙነት እስካረጉ ድረስ የዘር ፈሳሽ ባይፈስም በሁለቱም በኩል ገላን መታጠብ ግድ ይላል።ከፊሎች በተቃራኒው መታጠብ ግድ የሚለው የዘር ፈሳሽ ሲፈስ ነው ብለው ያስባሉ ይሄ እሳቤ ስህተት ነው።ምክንያቱም ነብዩ --   <በአራት ቅርንጫፎቿ መሀል ከተቀመጠና ግንኙነት ከፈፀመ የዘር ፈሳሽ ባይፈስም ትጥበት ግድ ሆኗል> ብለዋልና።

↳በዚህም ከሁለት በአንዱ ትጥበት ግድ ይላል፡ ወይ የዘር ፈሳሽ በመውጣት ወይም በግንኙነት። የዘር ፈሳሽ የወጣው በመሳሳም ቢሆን በመተቃቀፍም ቢሆን ወይ በስሜት በማየትም ሆነ በመነጋገር በየትኛውም ቢሆን መታጠብ ግድ ነው።ግንኙነት ተደርጎም የዘር ፈሳሽ ባይወጣም መታጠብ እንዲሁ ግድ ነው።

↳ብዙ ሰዎች ግንኙነት ፈፅመው በወቅቱም የዘር ፈሳሽ ካልወጣ እንደማይታጠቡና በዚህም ብዙ ወራት እንዳለፉ (ምን ማድረግ እንዳለባቸው) ይጠይቁናል። የዚህ ምክንያቱ የሚያገባ ሰው በጋብቻ ወቅት ምን ማድረግ እንደሚገባና ምን ግዴታ እንደሆነ አይጠይቅም። ብዙዎቹም ሰዎች እንደዚህ አይነት ትምህርቶችን በወጣቶች መካከል አያሰራጩም።
    
لِلشَّــيْخ العَلّامـَـة/ مُحَـمَّد بـنُ صَـالِح العُثَـيْمِين -رَحِــمَهُ الله-

منقول
=
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1
PTT-20200730-WA0003.opus
254.3 KB
ዉብ ቲላዋ ተጋበዙልኝ

~

ቁርአን ማንበብና እንዲሁም በትኩረት ማዳመጥ ትልቅ ኢባዳ ነው!
سورۃ الغاشيۃ
Abu Useymin
ደገምኳችሁ ተጋበዙ ምሺታችሁ ደመቅ ይበል !
~

🎙አቡ ዑሰይሚን
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
የምሺቱ ስጦታዬ ዉሰዱ = t.me/https_Asselefya1
ጓደኛ ቤተሰብ ወደ ሀገር ስትልኩ የመሸኛ ፕሮፍይል ስትሰሩ አየር ስትፈልጉ ወደ ቤታችሁ ጎራ ብላችሁ ዉሰዱ ስላችሁ...

=

http://t.me/https_Asselefya1