💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
የአሕባሾች መንዙማ ➀➂
ÂŤ Abu Useymin Âť
❝ የአሕባሾች መንዙማ በቁርአን በሀዲስ ሚዛን ....!? ❞

👉⭕️የአህባሾች የሽርክ መንዙማ!!

👉🎙 ከራሳቸው ድምፅ ጋር ዳሰሳ!!

     🔖👉ክፍል  ①➂

🎙በአብዱረሕማን አቡ ዑሰይሚን

t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/https_Asselefya1
«ክብር አለኝ ላንች»

ኢኽላስ እየጠፋ ቀን ሰግደን ሌት ፁመን፡
ፊትናና ማስመሰል በበዛበት ዘመን፡
እድለኝነት ነው ለኢስላም መታመን፡


በስደት ምድር ላይ ወይ በገጠር ጎጆ፡
ድንን በመማር  ላይ ለፀናችው ቆንጆ፡
ክብር አለኝ ላንች ለኢልሟ ኮረጆ፡


የቲክቶክ አካውንት ሳትመሰርች፡
በምላስ አለንጋ ሰው ሳትነርች፡
በአደብ ላይ ያለሽ እህቴ ሆይ በርች፡


በነገራም ሴቶች ወሬ ሳትረች፡
ተውሒድ አቂዳሽ ላይ ለምትበረች፡
በአሏህ ይሁንብኝ ክብር አለኝ ላንች፡


     ✍️ኑረዲን አል አረቢ

http://t.me/nuredinal_arebi
🛑👉 ትዳርን ካንድም ሁለት ጊዜ ሞክረው ያልተሳካላቸው አልያም ትዳር ለመያዝ በተሳሳተ መንገድ ተጉዘው ብዙ ጥረት አድርገው የተበላሸባቸው ወይም ከመሰረቱ ለትዳር ያላቸው አመለካከት የተበላሸና የተሳሳተ ለትዳር ምንም ቦታ የሌላቸው አንዳንዶች ትዳርን ስቃይ የተሞላበት እስር ቤት አስመስለው የሚያቀርቡልሽና ተልካሻ ምክንያት እየጠቀሱ ትዳርን እንድትፈሪ አልያም ከትዳር እንድትሸሺ አልፎም ለትዳር መጥፎ አመለካከት እንዲኖርሽ የሚያደርጉ የመሀይማን ንግግር ትተሽ የነዚህ እንቁ የሱና ኡለማዎች ንግግር በደምብ አዳምጪ።

🛑👉 እህቴዋ ትዳር አለም ነው ወደ ትዳር ሩጪ። የነሱ ህይወት አንቺ አትኖሪውም። ለነሱ የገጠማቸው ፈተና ሁሉ ላንቺ አይገጥምም። ተገቢው ጥንቃቄ ከማድረግሽ ጋር ወደ ትዳር አምሪ። ከነሱ ትምህርት ውሰጂ እንጂ በፍፁም እንዳትከተይ። ሞዴልሽ በትዳር ላይ የገፋፍሽ ነብዩን እንጂ እነዚህን አታድርጊ። ትዳር ሪዝቅ ነው። የሁሉም ሪዝቅ ደግሞ ይለያያል። ጎረቤት ድሀ ስለሆነና ስለቸገረው አንቺም ድሀ ትሆኛለሽ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ትዳርም እንዲሁ ነው። አላህ ከመልካሙ ጋር እንዲገጥምሽ አበክረሽ ለምኚ። በትዳር ላይ ችለተኛ አትሁኚ። ለትዳር ተገቢው ቦታና ክብር ስጪ። የሴት ልጅ ክብሯ ትዳር ውስጥ ነው። እድሜ ቆሞ አይጠብቅሽም። እናት አባትሽ ቤት ደልቶሽ ሁሉ ነገር ተሟልቶልሽ ከምትኖሪ እየቸገረሽም ቢሆን ሷሊህ ልጆች ወልደሽ እየሳምሽ ትዳር ውስጥ መሆንና መሰተርን ምረጪ።

🛑👉 ከዚህ የከፋው ደግሞ የሱና ሰው እንዳታገቢ እውቀት ያለው ተጠንቀቂ ጃሂልም ቢሆን የሚያከብርሽን አግቢ እያሉ የሚዘባርቁ አልያም ወደዚህ የሚያግደመድሙት አደራ አደራ በመቶ ሜትር ከተቻለም ከዛ በላይ ራቂያቸው። አንዳንዶችማ በግልፅ አፋቸው ሞልተው ላንቺ ውዴታ ይኑረው ያክብርሽ እንጂ የሱና ሰው ባይሆንም ብታገቢው ችግር የለውም የሚሉ ገልቱዎች አልጠፋም። እነዚህ ትዳር ውስጥ ከሚገኘው ከአሄራው ይልቅ የዱንያው ጥቅም የሚያስበልጡ ናቸው። እህቴ ከሱና ሰው ውጪ ማንንም አታግቢ። እውቀት ያለው እያለ ጃሂል አትምረጪ። አስተምሬ እመልሰዋለሁ። ቀስ ብዬ እቀይረዋለሁ ብለሽ ያልሆነ ቦታ እንዳትወድቂ። በአጭር ጊዜ ቀይሮሽ ነው ቁጭ የሚለው። ብዙ የሱና እህቶች እመልሰዋለሁ እቀይረዋለሁ በሚል የቢድአ ሰው አግብተው አልያም ስለዲኑ ምንም የማያውቅ ጃሂል ላይ ወድቀው ትዳሩ ስቃይ የሆባቸው ብዙዎች አሉ። አይተውት ነገር ትዳር ነው በዛ ላይ ወልደዋል። አይፈቱ ነገር ለፍች የሚጠየቁት ብር ብዙ ነው በዛ ላይ ፍቹ በሱ እጅ ነው። ታግሰው አይኖሩት ስቃይ ነው። አላህ ይጠብቅሽ ከንዲህ አይነቱ ትዳር።

🛑👉 ጃሂል አልያም ሙብተዲእ አግብተሽ ከምትነፍሪና ዘርሽ ከምታበላሺ አደራ ቢበድልሽ እንኳ ሱንዩን አግቢ። በሱ ላይ ታገሺ። ዱንያዊ ፍላጎትሽ ባያሟላና ባያስደስትሽ እንኳ አሄራሽ አያበላሽብሽም። ስትወጪ ስትገቢ በቤትሽ የሱና ሽታ ታሸቻለሽ። ቤተሰብ ጓደኛ ዘመድ አዝማድ ቢመጣ አታፍሪም። ጫት የለ ነሺዳ መንዙማ ዘፈን የለ ፊልም የለ ወንድና ሴት ቅልቅል የለ መገላለጥ የለ። እንደው ለዚህ ስትይ ከሱና ሰው ውጪ ማንም እንዳታገቢ። ቤትሽ በቢድአና በሁራፋት የሞላ ሆኖ የተደላደለ ህይወት ከምኖሪ ከሽርክ ከቢድአና ከሑራፋት የፀዳ ሆኖ አንዳንድ ነገር እየጎደለሽም ቢሆን እየሶበርሽ የሱና ህይወት ብትኖሪ ላንቺ የተሻለ ነው።

🛑👉 አንዳንዶቹ ደፍረው የሱና ሰው አታግቢ ላይሉሽ ይችላሉ። ነገር ግን አንዳንድ የሱና ሰዎች አይብ በመጥቀስ እንድትጠያቸው ያደርጋሉ። ስንትና ስንት በሱና ላይ ያሉ የሰመረ ትዳር የሚመሩ ብዙዎች እያሉ እገሌና እገሊት አታይም እንዴ እያሉ አንድ ሁለት ያልተሳካ ትዳር ይጠቅሳሉ። ደፍረው እውቀት ያለውን ትተሽ ጃሂል አግቢ ላይሉሽ ይችላሉ። ነገር ግን የነሱ መጥፎነት በመጥቀስ እንድትጠያቸው ያደርጋሉ። ስልታቸው ብዙ ቢሆንም አደራ ተጠንቀቂያቸው። እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አይነት ብሂላቸው ወደ ጎን ተይው።

🛑👉 ደግሞ በሁሉ ነገር የተዋጣለትና ሁሉ ነገር ያሟላ ትዳር አትጠብቂ። ትዳር ውስጥ ብዙ ችግርና ፈተና አለ። በሶብርና በትእግስት ግን ሁሉም ያልፋል። ትዳር ማለት ያንዱን ጉድለት ሌላው የሚደፍንበት የጋራ መድረክ እንጂ ሁሉ ነገር ያሟላና የተስተካከለ ቤት ማለት አይደለም። በሁለት ባለትዳሮች መካከል የጠበቀ ግኑኝነት፣ የረዘመ ወዳጅነትና የሚያስቀና ፍቅር በመካከላቸው የሚኖረው ሁሉ ነገር ስለተሟላላቸው አይደለም። ምንም አይነት ግጭት፣ ስህተት ወይም ቅራኔ በመካከላቸው ስለማይኖር አይደለም። ሚስጥሩ የፈለገ ነገር ቢፈጠር በመተሳሰብ፣ በመነጋገር፣ በመተላለፍ፣ በመመካከር፣ በመተዛዘንና ይቅርታ በመባባል ችግራቸውን ስለሚፈቱና የአንዱ ችግር አንዱ ስለሚሸፍን ነው። ዋናው  ያንዱን አይብ ሌላው ስለሚሰትር ነው። ስለዚህ ትዳርን አትፍሪ። ተገቢውን ሰበቡ አድርሺ። ከዛ በኋላ በጌታሽ ተመኪ።

🔖 አላህ ለሁሉም ላላገቡ ሙስሊም ወንድም እህቶቻችን ያማረና የሰመረ ትዳር ይወፍቃቸው። ያገቡትም ትዳራቸው ይባርክላቸው ለኡማው የሚጠቅም ሷሊህ ልጅም ይስጣቸው።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
«ወላጂ ምን ያድርግሽ?»
➖➖➖➖➖➖➖➖

ተይ ልጄ ቀስ በይ እያሉ ሲመክሩሽ፣
አልሰማም አልሽና በሚድያ ሰክርሽ፣
ሙግት ትይዧለሽ አገባለሁ ብለሽ፣
በንግግር ብቻ ወንድ ልጅን አምነሽ፣
የወላጅን ልፋት እደቀላል አይተሽ፣

ቤተሰብ ለልጁ እደመይሳሳ አድርገሽ፣
ከለከሉኝ ብለሽ ደግሞ ታለቅሻለሽ፣
ይገርማል እህቴ ምነዉ ሶብር አጣሽ፣
የወጣሽበትን አላማ ዘነጋሸ?፣
የስደት እንግልት ድካሙን እረሳሽ፣

በተለይ በተለይ ገጠር የተወለድሽ፣
የአባትን ስቃይ መከራዉን ያየሽ፣
የእናትን ለቅሶ ዱዓዋን የሰማሽ፣
ተይ አታስከፊያቸዉ እህቴ ልንገርሽ፣

ዛሬ ብትማሪም ዛሬ ያወቅሽ መስሎሽ፣
ዘመናዉይነት ስልጣኔ መስሎሽ፣
ድምፅ መቀያየር ከተሜነት መስሎሽ፣
የተጓሺዉ ስደት ቤተሰብ ካስረሳሽ፣


✍️ሶላሁዲን አቡ ዑበይዳህ

𝐓𝐞 « t.me/selahudin_Islamic_knowlages
አንቺ ክብርሽ ጠብቀሽ እስከተቀመጥሽ ድረስ
ማንም መጥቶ ባንቺ ክብር ላይ ሊረማመድ አይችልም።


=
t.me/https_Asselefya1
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ብለዋል፦

«الڪذب علـى الشخـص حـرام ڪلـه سـواء ڪـان الرجـل مسلمـا أو ڪافـرا بـرا
أو فاجـرا لڪن الافتراء على المؤمن أشد».
"በአንድ ሰው ላይ መዋሸት ሰውየው ሙስሊምም ሆነ ከ.ሃ. ዲ ፣ ደግም ሆነ አመፀኛ ሐራም ነው። በአማኝ ላይ መቅጠፍ ግን የከፋ ነው።"
Ibnu Munewor
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

* የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
▪️من أول من أحدث بدعة المولد النبوي؟
🎙️الشيخ محمد بن صالح العثيمين رحمه الله

@yesunawakonjobetwuhidyabebech
✍️የቱ ጋር ነዉ ክብርሽ?!
➬➫➬➫➬➫➬➫➬

የወጣሽበትን አላማ ዘንግተሽ፣
የልፈት እንግልት ዉጤቱ ሳይገባሽ፣
በሚድያዉ አልም አብደሽ እየሰከርሽ፣
ያን የወንድ አልጫ ሂደሽ እያባበልሽ፣
ተግባሩ ሳታይ ወይ አንች ሳይገባሽ፣
ለጥሎሽ አታስብ እኔ እጥላለሁ አልሽ፣?!

በስደቱ አለም ላይ እዛዉ እያገባሽ፣
ዘወር በይ እያለ መልሶ ሲፈታሽ፣
ክብሬን አጣሁ አትበይ ክብርሽን እያጣሽ፣
ያ ሜስኬን አባትሽ ተይ ልጄ እያለሽ፣
እኔ ከወደድኩት ምን አገባዉ እያልሽ፣

ተግባሩን ሳታይ በድምፁ እየሰከርሽ፣
ክብሬን አጣሁ አትበይ ክብርሽን እያጣሽ፣
መቶ ሲጠይቅሽ ያንች ክብር ሁኖ፣
በቁጥብነትሽ በራሱ ተማምኖ፣
አሏህ ሲፈቅድ ብለሽ ከዘጋሽ ከበርሽ፣
ያ ነዉ ያንች ክብር የሴትነት ወግሽ፣

  
«ግን ካልሆነ እህቴ ..!!»

የለለሽን ነገር ጨምረሽ ጨማምርሽ፣
እሱን ለማማለል ድምፅ ከቀያየርሽ፣
እመኝኝ እህቴ አንች ነሽ የከሰርሽ፣
ያልሆንሽዉን ሁነሽ ለምን ትቀርቢያለሽ፣
አንችዉ በር ከፍተሽ ይኸ እኮ ትያለሽ፣

ሚድያ ላይ ማግባት ብዙ ሁኖ ዉሸት
ተግባሩ ሳይታይ ቡሓላ መፀፀት


        
«እናማ ልምከርሽ..!!»

የወጣሽበትን አላማ አስበሽ፣
ላንች እሚጨነቁ ቤተሰብን ናፍቀሽ፣
የተማርሽዉን ድን ተግባር ላይ አዉለሽ፣
የተከበርሽ እንስት ቁጥብ እቁ ሁነሽ፣

ሀገር ስትገቢ ክብርሽን ጠብቀሽ፣
ላንች የታዘዘ ጀግና ታገኛለሽ፣
ወይም ከጠበቀ በተግባር ታያልሽ፣


      
«ካልሆነ ግናማ...!!»

በስደት አለም ላይ ፈጥነሽ እያገባሽ፣
ሳምንት እየቆየ መልሶ ከፈታሽ፣
ክብሬን አጣሁ አትበይ ክብርሽን እያጣሽ፣


✍️ሶላሁድን አቡ ዑበይዳህ

𝐓𝐞 « t.me/selahudin_Islamic_knowlages
SadatKemal Abu Meryem
Video
yes !

እማማ ኢክራም አላህ ይህ ወንድማችን ሰበብ አድርጎ ወደ ድንሽ እንደምትመለሽ ተስፍ አደርጋለሁ ¡ በጣም ነበር ያሳዘንሺኝ የምሰሪያቸዉ ስራዎችሽ.....¡

ኢላሂ ሌሎችም ብዙ መንገድህ የጣሱ ባሮችህ አሉ አንተ መልሳቸዉ .....!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
~ኡስታዝ ሳዳት ከማል ይቅር ባይ ነህና አላህ ይቅር ይበልህ!

አህሉ ሱናዎች ከሚታወቁበት ገፀ-ባህሪዎች መካከል «ይቅር» ባይነታቸው አንዱ ነው።

|•| የእይታህ አድማስ በሰፋ ቁጥር…ከበደል ትርቃለህ፣ ለበደለህ ምክንያት ትፈልግለታለህ፣ ባንተ ላይ ላጠፋብህ ጀሊሉ ያዝንለት ዘንድ ዱዓ ታደርግለታለህ፣ ሥምህን በክፉ ያነሳን የአላህን ይቅርታ ትለምንለታለህ። ይህ ነው የ ሱና ሰዎች መገለጫቸው!

«ይቅርታ የጠየቀህን ሰው በፈገግታ ተቀበለው»
ይሉ ነበር አህነፍ ቢን ቀይስ―
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
የመስጂድ ውስጥ ልመና
~
ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
ﺃﺻﻞ اﻟﺴﺆاﻝ ﻣﺤﺮﻡ ﻓﻲ اﻟﻤﺴﺠﺪ ﻭﺧﺎﺭﺝ اﻟﻤﺴﺠﺪ ﺇﻻ ﻟﻀﺮﻭﺭﺓ ، ﻓﺈﻥ ﻛﺎﻧﺖ ﺿﺮﻭﺭﺓ ﻭﺳﺄﻝ ﻓﻲ اﻟﻤﺴﺠﺪ ﻭﻟﻢ ﻳﺆﺫ ﺃﺣﺪاً ﻛﺘﺨﻄﻴﻪ ﺭﻗﺎﺏ اﻟﻨﺎﺱ ، ﻭﻟﻢ ﻳﻜﺬﺏ ﻓﻴﻤﺎ ﻳﺮﻭﻳﻪ ﻭﻳﺬﻛﺮ ﻣﻦ ﺣﺎﻟﻪ ﻭﻟﻢ ﻳﺠﻬﺮ ﺟﻬﺮاً ﻳﻀﺮ اﻟﻨﺎﺱ ﻣﺜﻞ ﺃﻥ ﻳﺴﺄﻝ ﻭاﻟﺨﻄﻴﺐ ﻳﺨﻄﺐ ، ﺃﻭ ﻭﻫﻢ ﻳﺴﻤﻌﻮﻥ ﻋﻠﻤﺎً ﻳﺸﻐﻠﻬﻢ ﺑﻪ ﻭﻧﺤﻮ ﺫﻟﻚ ﺟﺎﺯ .
"ልመና በመሰረቱ በመስጂድም ውስጥ ይሁን ከመስጂድ ውጭ ለአስገዳጅ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር አይፈቀድም። አስገዳጅ ሁኔታ ኖሮ መስጂድ ውስጥ ቢለምን
- ማንንም ካላስቸገረ - የሰዎችን ጫንቃዎች መረማመድን ይመስል፣
- በሚያወራው ላይ ካልዋሸ ፣ ማለትም ያለበትን ሁኔታ ብቻ ከጠቀሰ፣
- ሰዎችን በሚጎዳ ጩኸት ካልጮኸ - ለምሳሌ ኸጢቡ ኹጥባ ላይ እያለ መለመንን ይመስል፣ ወይም ዒልም እያደመጡ ካልረበሻቸው ፣ ወዘተ
(መለመን) ይቻላል።"
[ጊዛኡል አልባብ፣ አሰፋሪኒይ፡ 2/267]

Ibnu Munewor

=
▸ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

▸ የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
አል ካፊያ ሸሪዓዊ ሩቃ ቤት

ሸሪዓውንና ሱናን በጠበቀ መልኩ የቁርአን ህክምና የሚሰጥበት አል ካፊያ ሩቃ ቤት በመምጣት በአሏህ ፍቃድ ሰበብ እንሆነዎታለን።

አድራሻ  ኮ/ቻ ቀበሌ 08 ድልድዩን ተሻግሮ ሁለተኛው ቅያስ ገባ ብሎ። ወይም ከሩሃማ መስጂድ በቀኝ በኩል ዝቅ ብሎ

ስልክ ቁጥር ➴➴➴
0960243692~ 0915508640

ለማንኛውም ጥያቄ➴➴➴
@abureyyis ~ @abureyyis

ቴሌግራም ግሩፕ ➘➘➘➘➘➘
https://t.me/al_kafia_ruqyeh_bet
https://t.me/al_kafia_ruqyeh_bet
⇘የሱና ወንድምህን ክብሩን እወቅለት!!! ⇙
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
☛በአሏህ ዲን ላይ መዋደድ በተውሒድ በሱና መዋደድ በመንሓጅ መዋደድ ከዓርሺ ጥላ ስር ከሚሆኑ ሰዎች መካከል እንድንሆን የሚያደርግ ትልቅ ዒባዳ ነው።

☛ስለ ሱና ወንድምህ ክብር ምን ያክል ታውቃለህ ? እሱንስ ምን ያክል ሓቁን እየተወጣህ ነው ??

☞የሱና ወንድምህን ከቻልክ እገዘው ካልቻልክ ግን እባክህን እባክህን ጋሬጣ አትሁንበት ክፍተት ካየህበት በአቅምህ ያክል ክፍተቱን ሙላለት !! ።

☛እንኳን የሱና ወንድምህን አይደለም ለማንኛውንም ሰው ጋሬጣ መሆን አይፈቀድም ስህተት ላይ ካለ እረመው ቀስ ብለህ !!

☞ለሰው መልካም መሆን ትልቅ ደረጃ እንዳለው ሁላ ለሰው መጥፎ መሆን ምቀኛ መሆን ደግሞ ትልቅ ወንጀል ነው  !!

☛መቼም የሰው ልጅ ከስህተት አይፀዳምና በሱና ወንድምህ ላይ ስህተት ካገኘህበት ምከረው በአደባባይ ከማውጣቱ ይሁን  ከማውጣትህ በፊት!!

☞ከዝህ ውጭ ሳይጠሩ ሰርግ እንደሚሄዱ ሰዎች ሳይበላህ እያከክ የግል ሂወቱ ውስጥ እየገባህ ያለ ሙያህ አታቡካ ሊጡን ታበላሻለህና !!!

☛የሱና ወንድም ክብሩን ምን ያክል አውቀናል ግን ወገን  ?? የሱና ወንድም ሲያዝን በቻልከው ያክል ማገዝ እሱን ማበረታታት ሲገባህ እንዴት እንዴት ለሹ ጋሬጣ ትሆናለህ ? ?

☞ለሱና ወንድም ክብር ይኑረን የሱ ደስታ የኛም ደስታ ነው ፣ የሱ ትካዜ የኛም ትካዜ ነው ትክክለኛው ውዴታ ከሆነ ።

« الله في عون العبد ما کان العبد في عون أخیه »
ውዱ ነብያችንﷺ  ብለው ይሉናል ፦

" አሏህ አንድን ባሪያ እንዳገዘው ነው ይህ ባሪያ ወንድሙን ባገዘ ቁጥር "

☛የሱና ወንድምህን ማገዝ ችግሮቹን ተባብረህ መፍታትህ አሏህ ዘንድ ትልቅ ደረጃን ያስገኝልሀል ፤  በተጨማሪም ያላችሁ ውዴታም እንዲጨምር ያደርጋል ከዝህ በላይ ምን ፈለግክ ? !!

ከአርቴፊሻል ወንድምነት አሏህ ይጠብቀን በስ !!

✍ወንድምህ አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

𝐓𝐞« t.me/abuUseyminabdurehman