💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝የሙናፊቆች ባህሪያት❞ ➖〰➖〰➖〰➖ «ክፍል  ⓼» {የሙናፊቆች ልዩ ባህሪ} ☞ሙናፊቆች የማያዉቁትን ያወራሉ፣ሲናገሩ ይዋሻሉ፣ የተከለከሉትን ይተገብራሉ፣ያጠፍሉ ይጠፍሉ፣ በአላህ ላይ ያምፃሉ፣ሰይጣንን ይታዘዛሉ፣ነገር ይሰራሉ፣ሙስሊሙን  ያጣላሉ፣በዉሸት ይመሰክራሉ፣መጥፉ ቃል ይናገራሉ፣ሰዉ ያማሉ። ☛ሙናፊቆች ሙእሚን ጥላታቸዉ፣ካፊር ወዳጃቸዉ፣ ሰይጣን ኋላፊያቸዉ ነዉ።ሙናፊቆች ደረቅ ነዉ ልባቸዉ፣ቆሻሻ ነዉ…
❝የሙናፊቆች ባህሪያት❞
➖〰➖〰➖〰➖

«ክፍል  ⓽»

【የሙናፊቆች ባህሪ በቁርአን ዉስጥ ከባለፈ የቀጠለ..1】

ሁለተኛ ዉምሳሌ፦እዉነትና ዉሸቱ፣እምነትና ክህደቱ፣ቀንና ሌሊቱ፣ነጭና ጥቁሩ፣ሰማይና ምድሩ፣ ተቀላቅሎበት መለየት ተስኖት የሚይዘዉን  የሚጨብጠዉ ጠፍቶ እንደሚደናበር ደንባራ ነዉ።

◂ قال تعالى : { أَوۡ كَصَیِّبࣲ مِّنَ ٱلسَّمَاۤءِ فِیهِ ظُلُمَـٰتࣱ وَرَعۡدࣱ وَبَرۡقࣱ یَجۡعَلُونَ أَصَـٰبِعَهُمۡ فِیۤ ءَاذَانِهِم مِّنَ ٱلصَّوَ ٰ⁠عِقِ حَذَرَ ٱلۡمَوۡتِۚ وَٱللَّهُ مُحِیطُۢ بِٱلۡكَـٰفِرِینَ } { یَكَادُ ٱلۡبَرۡقُ یَخۡطَفُ أَبۡصَـٰرَهُمۡۖ كُلَّمَاۤ أَضَاۤءَ لَهُم مَّشَوۡا۟ فِیهِ وَإِذَاۤ أَظۡلَمَ عَلَیۡهِمۡ قَامُوا۟ۚ وَلَوۡ شَاۤءَ ٱللَّهُ لَذَهَبَ بِسَمۡعِهِمۡ وَأَبۡصَـٰرِهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَیۡءࣲ قَدِیرࣱ }

➲አላህ እንድህ ይላል፦ወይም ምሳሌቸዉ  ከሰማይ እንደወረደ ዝናብ[ባለቤቶች] ነዉ። በርሱ በዳመናዉ ዉስጥ ጨለማዎች ነጓድጓድም ብልጭታም ያሉበት ሲሆን ከመብረቆቹ  ሞትን ለመፍራት ጣቶቻቸዉን በጆሮቸዉ ዉስጥ እንደሚያደርጉ ቢጤ ነዉ። አላህም  ከሀድዎችን ከባቢ ነዉ። ብልጭታዉ አይኖቻቸዉን ሊነጥቅ ይቀርባል ለነርሱ ባበራላቸዉ ቁጥር በርሱ ዉስጥ ይሄዳሉ በነሱም ላይ ባጨለመ ግዜ ይቆማሉ አላህም ባሻ ኖሮ መስሜቸዉንና ማያዎቻቸዉን  በወሰደ ነበር። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነዉና። (አልበቀራህ:19_20)

በቁርአን ዉስጥ ከተጠቀሱ ባህሪዎቻቸዉ ዉስጥ ጥቂቱን እንመልከት፦

1▸ ምድር ላይ ማጥፍትና ማበላሸት፦ የማስመሰያዉና የስሜቱ በሽታ ልባቸዉን አፍኖ ገሎታል። መጥፉ ፍላጎታቸዉ ሀሳባቸዉን አበላሽቶታል።ብልሽቱ በወረርሽኝ መልኩ ተንሰራፍቷል  ሃኪሞት መደሀኒት አጥተዉለት ወደ ጥፍት ቀርቧል።

▪قال تعالى:{ وَإِذَا قِیلَ لَهُمۡ لَا تُفۡسِدُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ قَالُوۤا۟ إِنَّمَا نَحۡنُ مُصۡلِحُونَ } { أَلَاۤ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡمُفۡسِدُونَ وَلَـٰكِن لَّا یَشۡعُرُونَ }

◄ አላህ እንድህ ይላል፦ ለእነርሱም በምድር ላይ አታበላሹ በተባሉ ግዜ አሳማሪዎች ብቻ ነን ይላሉ። ንቁ እነሱ አጥፊዎች እነሱዉ ናቸዉ ግን አያዉቁም። (አል_በቀራህ :11_12)


2▸ ወደ እስልምና ሲጠሩ ማሾፍና ማላገጥ፦ በቁርአን እና በሱና ላይ በማሾፍ እምቢተኝነታቸዉን አሳይተዋል ።እነሱ ዘንድ ባለዉ እዉቀት በመደሰት ትእቢታቸዉን ገልፀዋል። ጠፊ የሆነችዉን ንግድ ለመፈለግ ባህርን ስንጥቀዋል፣ጋራን ወጥተዋል፣ ቁልቁለትን ወርደዋል።ጥርጣሬቸዉ የቅዠትን  ማዕበል ያማታቸዋል። የጭንቀትን  ማቅ ያለብሳቸዋል።

▪قال تعالى:{ وَإِذَا قِیلَ لَهُمۡ ءَامِنُوا۟ كَمَاۤ ءَامَنَ ٱلنَّاسُ قَالُوۤا۟ أَنُؤۡمِنُ كَمَاۤ ءَامَنَ ٱلسُّفَهَاۤءُۗ أَلَاۤ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلسُّفَهَاۤءُ وَلَـٰكِن لَّا یَعۡلَمُونَ }

➲አላህ እንድህ ይላል፦ ለእነርሱም ሰዎች እንዳመኑ እመኑ በተባሉ ግዜ ቂሎች(ሞኞች) እንዳመኑ እናምናለን? ይላሉ {አዋጅ}  ንቁ!እነሱ ቂሎች እነሱ ናቸዉ ግን አያዉቁም። (አል በቀራህ:13)

ሙናፊቆች  ነጭና ጥቁር ሁለት ፊት ያላቸዉ ሲሆኑ አማኞች የሚያታልሉባቸዉ እና ቢጤዎቻቸዉን የሚቀላቀሉበት ነዉ። እንደዚሁም  ሁለት ምላስ ሲኖራቸዉ፦አንዱ አማኞችን አምነናል በማለት የሚስማሙበትና ሁለተኛዉ  በልባቸዉ የተደበቀዉን ክህደት  የሚያንፀባርቁበት ነዉ።

▪قال تعالى:{ وَإِذَا لَقُوا۟ ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ قَالُوۤا۟ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَوۡا۟ إِلَىٰ شَیَـٰطِینِهِمۡ قَالُوۤا۟ إِنَّا مَعَكُمۡ إِنَّمَا نَحۡنُ مُسۡتَهۡزِءُونَ }

▸አላህ እንድህ ይላል፦ እነዚያ ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ አምነናል ይላሉ ወደ ሰይጣኖቻቸዉ ባገለሉ  ጊዜ እኛ ከናተ ጋር ነን(በርሱ) ተሳላቂዎች ብቻ ነን ይላሉ። <አል_ በቀራህ :14>

📔ይጥላል ኢንሻ አላህ........

⇊↶⇣⇣↶⇊↶⇣⇣↶⇊↶⇣⇣↶⇊↶
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
~ሁሉ አማረሽ እትሁኑ እእ ልበሱ በቃ ሰጠኋችሁ¡
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝የሙናፊቆች ባህሪያት❞ ➖〰➖〰➖〰➖ «ክፍል  ⓽» 【የሙናፊቆች ባህሪ በቁርአን ዉስጥ ከባለፈ የቀጠለ..1】 ሁለተኛ ዉምሳሌ፦እዉነትና ዉሸቱ፣እምነትና ክህደቱ፣ቀንና ሌሊቱ፣ነጭና ጥቁሩ፣ሰማይና ምድሩ፣ ተቀላቅሎበት መለየት ተስኖት የሚይዘዉን  የሚጨብጠዉ ጠፍቶ እንደሚደናበር ደንባራ ነዉ። ◂ قال تعالى : { أَوۡ كَصَیِّبࣲ مِّنَ ٱلسَّمَاۤءِ فِیهِ ظُلُمَـٰتࣱ وَرَعۡدࣱ…
❝የሙናፊቆች ባህሪያት ❞
➖〰➖〰➖〰➖〰

«ክፍል  ⓾»

【የሙናፊቆች ባህሪያት በቁርአን ዉስጥ ከባለፈ የቀጠለ...... 2】

3▸ ንግግርን ማሳመር ፣ወግን ማጣፈጥ፣በክርክር መርታት፦

۞قال تعالى:{ وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن یُعۡجِبُكَ قَوۡلُهُۥ فِی ٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَا وَیُشۡهِدُ ٱللَّهَ عَلَىٰ مَا فِی قَلۡبِهِۦ وَهُوَ أَلَدُّ ٱلۡخِصَامِ }

☞አላህ እንድህ ይላል፦ከሰዎችም ዉስጥ እርሱ ክርክር ብርቱ ሲሆን በቅርቢቱ ሕይወት ንግግሩ የሚደንቅህና በልቡ ዉስጥ ባለዉ ነገር ላይ አላህን የሚያስመሰክስ ሰዉ አልለ።(አልበቀራህ :204)

4▸ንግግራቸዉ ያማልላል፣ግዝፈታቸዉ ያምራል፦

۞قال تعالى:{ ۞ وَإِذَا رَأَیۡتَهُمۡ تُعۡجِبُكَ أَجۡسَامُهُمۡۖ وَإِن یَقُولُوا۟ تَسۡمَعۡ لِقَوۡلِهِمۡۖ كَأَنَّهُمۡ خُشُبࣱ مُّسَنَّدَةࣱۖ یَحۡسَبُونَ كُلَّ صَیۡحَةٍ عَلَیۡهِمۡۚ هُمُ ٱلۡعَدُوُّ فَٱحۡذَرۡهُمۡۚ قَـٰتَلَهُمُ ٱللَّهُۖ أَنَّىٰ یُؤۡفَكُونَ }

☞አላህ እንድህ ይላል፦ባየሀቸዉ  ጊዜ አካሎቻቸዉ(ግዙፍነታቸዉ)ያስደንቁሀል።ቢናገሩም ለንግግራቸዉ ታዳምጣለህ፣ከዕዉቀት ባዶ በመሆን። እነርሱ ልክ በግድግዳ የተጠጉ ግንዶችን ይመስላሉ። ጩኸትን ሁሉ በእነርሱ ላይ ነዉ ብለዉ ያስባሉ። እነርሱ ጠላቶች ናቸዉና ተጠንቀቃቸዉ።  አላህ ይጋደላቸዉ (ከእምነት እንደት ይመለሳሉ!(አል_ሙናፊቁን :4)

☛ሙናፊቆች ንግግራቸዉ ማራኪ ነዉ፣ግዝፈታቸዉ ያማረ ነዉ፣ልባቸዉ  ቆሻሻ ነዉ።

5▸ምድስን ማበላሸት አዝመራን ማድረቅ እንስሳትን ማጥፍት፦

۞قال تعالى:{ وَإِذَا تَوَلَّىٰ سَعَىٰ فِی ٱلۡأَرۡضِ لِیُفۡسِدَ فِیهَا وَیُهۡلِكَ ٱلۡحَرۡثَ وَٱلنَّسۡلَۚ وَٱللَّهُ لَا یُحِبُّ ٱلۡفَسَادَ }

☞አላህ እንድህ ይላል፦ካንተ በዞረም ግዜ በምድር ላይ በዉስጧ ሊያበላሽና አዝመራንና እንስሳዎችን ሊያጠፍ ይሮጣል። አላትም ማበላሸትን አይወድም።( አል_በቀራህ፡205)

☛የሙናፊቆች ጥርጣሬ የለበሰ የእምነቱ ብርሀን ይበጣበጣል። የተንኮላቸዉን ነበልባል ያቀጣጠለ ከአሳማሚ ቅጣት ላይ ይጥሉታል።  የማመሳሰያቸዉን ነጥብ የሰማ በጆሮዉና በልቡ ግርዶሽ ይጥላል።

۞قال تعالى:{ أَلَاۤ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡمُفۡسِدُونَ وَلَـٰكِن لَّا یَشۡعُرُونَ }

☞አላህ እንድህ ይላል፦ንቁ! እነርሱ አጥፊዎች እነርሱዉ ናቸዉ፣ግን አያዉቁም። (አል_በቀራህ 12)

6▸በመፎ ያዛሉ፤ከመልካም ነገር ይከለክላሉ፤ ለመመፀዎት ይሳሳሉ፤አላህን ይረሳሉ፤እርስ በርሳቸዉ ይስማማሉ። 

۞قال تعالى:{ ٱلۡمُنَـٰفِقُونَ وَٱلۡمُنَـٰفِقَـٰتُ بَعۡضُهُم مِّنۢ بَعۡضࣲۚ یَأۡمُرُونَ بِٱلۡمُنكَرِ وَیَنۡهَوۡنَ عَنِ ٱلۡمَعۡرُوفِ وَیَقۡبِضُونَ أَیۡدِیَهُمۡۚ نَسُوا۟ ٱللَّهَ فَنَسِیَهُمۡۚ إِنَّ ٱلۡمُنَـٰفِقِینَ هُمُ ٱلۡفَـٰسِقُونَ } { وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡمُنَـٰفِقِینَ وَٱلۡمُنَـٰفِقَـٰتِ وَٱلۡكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَـٰلِدِینَ فِیهَاۚ هِیَ حَسۡبُهُمۡۚ وَلَعَنَهُمُ ٱللَّهُۖ وَلَهُمۡ عَذَابࣱ مُّقِیمࣱ }

☛አላህ እንድህ ይላል፦ የወንድና የሴት ሙናፊቆች ከፊሎቻቸዉ ከከፊሉ ናቸዉ።በመጥፎ ያዛሉ ከመልካም ነገር ይከለክላሉ። እጆቻቸዉንም ከመመፀዎት ይሰበስባሉ።  አላህን ረሱ። ስለዚህ (እርሱን)ተዋቸዉ።ሙናፍቃን አመፀኞች እነርሱ ናቸዉ። የወንድናየሴት ሙናፊቆችን፣ከሐድዎችንም አላህ የገሀነብ እሳት በዉስጧ ዘዉታሪዎች ሲሆኑ (ሊያስገባቸዉ)ቃል ገብቶላቸዋል። እርሷ በቂያቸዉ ናት። አላት ረግሟቸዋል።ለእነርሱም ዘዉታሪ ቅጣት አላቸዉ። {አል-ተዉባህ :67_68}

📔ይቀጥላል  ኢንሻ አላህ.........


📝አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰዉ ያደርጋልና!

          <ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ>
  ↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
ምንም ቢሆን ለናተ ጥንካሬ ጉልበት የሚሆኗችሁ ሰዎች እንጂ ለመድከም ሰበብ ከሚሆኑ ሰዎች አትወዳጁ!!
=
t.me/https_Asselefya1
Audio
❝አዲስ የአቂዳ ኪታብ ቂርአት❞
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️


☞የኪታብ ርዕስ፦ሚን ኡሱሊ አቂደቲ አህሊ ሱነቲ ወልጀመዓ!!

❂ ክፍል   13

📜የኪታብ 𝐏𝐝𝐟 ⇩⇩
t.me/https_Asselefya1/11411

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

  ⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇙⇙⇙⇙⇙⇙
    t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
ወንድ ልጅ የሚያፈቅርሽ ከሆነ ምንም አጣብቂኝ ውስጥ ቢሆን ድምፅሽን ሳይሰማ አይውልም አያድርም ከዛ ውጭ  በሳምንት እየመጣ ናፍቀሽኛል እወድሻለሁ ቢልሽ ውሸት ።

t.me/SileTidarEnmekaker
➮ወዳጅ መስሎ የቀረበን ሁሉ የሚወደን አይደለም ።አንዳንድ አዳኞች ወዳጅ መስለው ቀርበው ደካማ ጎናችንን ካወቁ በኋላ ሊያጠቁን ይችላሉ ።

=