💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ይላሉ፦

➧ሴቶች ሆይ ሰደቃ አብዝታችሁ ስጡ! አብዛኞቹ የጀሀነም እሳት ነዋሪዎች እናንተ ሁናችሁ አይቻችኋለሁና።

➧ጀሀነም ውስጥ የበዛንበት ምክንያቱ ምንድን ነው አንቱ የአሏህ መልዕክተኛ ብለው ጠየቁ፡ ከዛም ረሱል"እርግማን ስለምታበዙና የባላችሁን ውለታ ስለምትክዱ ብለው መለሱላቸው።


➻ሴቶችን ጀሀነም ውስጥ እንዲበዙ ያደረጋቸው ሁለት ምክንያቶች ፡

①እርግማን ስለሚያበዙ

② ከባላቸው ጋ ለአመታት የደስታን ህይወት አሳልፈው ልክ አንድ ቀን የሆነ ነገር ሳያሟላላት ሲቀር "አንተ ምን አድርገህልኝ ታውቃለህ ምናምን ብለው ያን ሁሉ በደስታ ያሳለፉትን ያን ሁሉ ውሌታውን በአንዲት ጉድለት ስለሚክዱ"እንዲሁም የባላቸውን ሀቅ ስለማያሟሉ በሚልም ተፈስሯል።

➧እንዳጠቃላይ ከነዚህና መሰል ተግባራቶች ራሳችንን በማራቅ ነፍሳችንን ከጀሀነም እሳት በአሏህ ፈቃድ እንታደግ ።

➧በዋናነት ጀሀነም ውስጥ የሴትች መብዛት ሰበብ እነዚህ ሁለት ነገሮች መሆናቸውን ረሱል ተናግረዋል።

🔹አሏህ ሁላችንንም ከጀሀነም እሳት ይጠብቀን አሚን።

📚ምንጭ ሶሂሁል ቡኻሪ (304)
↷⇣🌷⇣↷
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
اللهمّ إنّكَ عفوٌ كريمٌ تُحب العَفو فَاعفُ عنّا.
Audio
◾️ለይለተል ቀድር ይበልጥ በሚከጀልበት ቀን ላይ የተከሰተ አስተማሪና አስደናቂ ታሪክ

👉ሰምተን ልንተገብረው ይገባል
🔻ለሌሎችም ሼር እናድርገው

قالت عائشة رضي الله عنها للنبي ﷺ :أرأيت إن وافقت ليلة القدر ، ما أقول فيها؟ فقال ﷺ : قُولِي: اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌ تُحِبُّ العَفْوَ فَاعْفُ عَنِّي
[السلسلة الصحيحة (٣٣٣٧)]


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
እውነተኛ ዉበት እና የተሟላ ጌጥ የምትፈልጊ ከሆንሽ?

ይህን ቁንጅና እና ዉበት ልታንፀባረቂው ደግሞ የምትችይዉ በነዚህ ነገራቶች ላይ ሆነሽ ስትታይ ነው።

ኢማን ፣ተቅዋ በአሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ሸሪያ ፣ ድንጋጌዎች ህግጋትና ጥቆማዎችን በመተግበር የሱን ፊት ብቻ በመፈለግ ነው።

ይህ ነው ትክክለኛ ዉበትሽ
ይህ ነው ትክክለኛ ደስታሽ
ይህ ነው ለአንድ ሰው በዱኒያም በአኼራም ነፃ መውጫዉ።

الشيخ عبد الرزاق بن محسن البدر حفظه الله موعظة للنساء (ص/14)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
" اللَّهُـمَّ إِنَّـكَ عَفُـوٌ تُحِـبُّ الْعَفْـوَ فَـاعْفُ عَـنِّي "

" اللَّهُـمَّ إِنَّـكَ عَفُـوٌ تُحِـبُّ الْعَفْـوَ فَـاعْفُ عَـنِّي "

" اللَّهُـمَّ إِنَّـكَ عَفُـوٌ تُحِـبُّ الْعَفْـوَ فَـاعْفُ عَـنِّي "
«ምኞትሽን ያሳካልሽ»



➪ልታይ ልታይ በበዛበት የኢስላምን ስም እያጠፉ እርቃናቸውን የሚሄዱ ሴቶች በበዙበት አንቺ የፀሀዩን መክበድ ሳይበግርሽ በሙሉ ሂጃብ ♕︎ክብርሽና እምነትሽ ለጠበቅሽው እህቴ አላህ በዱንያም በአኼራ ያሰብሽውን ኸይር ያሳካልሽ💎🌹
የቦረናው ሸህ ክፍል 1
Sadat
➴የቦረናው ሸህ

~ክፍል1⃣

🎙Ūstâz Sâdãt Kĕmāl
(حفظه الله)
~
☟ ☟ ☟
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/3005
የቦረናው ሸህ ክፍል 2
Sadat
➴የቦረናው ሸህ

~ክፍል2⃣

🎙Ūstâz Sâdãt Kĕmāl
(حفظه الله)
~
☟ ☟ ☟
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ዘካውን ከሚገባው ሰው ዘንድ እንዲደርስ ከጣረ በኋላ የማይገባው ሰው ላይ እንደ ደረሰ የተረዳ ሰው ዳግም ማውጣት አይጠበቅበትም። ዘካውን ያብቃቃዋል። ምክንያቱም በሚችለው መጠን አላህን ፈርቷልና። አላህ ደግሞ ነፍስን ከአቅሟ በላይ አያስገድዳትም።
~ መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን፣ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ~
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
◾️ይህን ዱአ ከመደጋገም አንሰላች

🔻ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ደጋግመን ልንለው ይገባል።
《اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني》
{አሏህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ባይነትም ትወዳለህና ይቅር በለኝ!!}
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
...ከነፈሰው ጋር አትንፈስ። ማንም ተነስቶ በቀደደው አትፍሰስ። በትንሽ በትልቁ በሹብሀት አትልፈስፈስ። አትፍረክረክ። በማስረጃ አቋም ይዘህ በስሜት አትንበርከክ። መንገድ በሳተ ብዙሀን አትብረክረክ። ሁሌም #ለማስረጃ እጅ ስጥ። ትላንት ከያዝከው ሀቅ በልብወለድ አታፈንግጥ። ቀጥ!በል አትለዋወጥ።

ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሃፊዘሁሏህ
ከኢብኑ ሙነወር ወርቃማ ንግግሮች ውስጥ

"ወጣት ሆይ ወጣትነትህን ተጠቀም። እራስህን አድን።ሀላፊነትህን ተወጣ። #አርአያዎችህን ለይ። #ቀና_በል_በተውሂድ። ከሺርክ ሰፈር #አትልከስከስ። ወጣት ሆኖ ለሺርክ ጠበቃ ለተውሂድ ግን ጠላት ሲሆን ማየት ምነኛ ልብ የሚያደማ ነው ?!ምነኛ የሚያሳፍር ነው ??!"

📚 "ተውሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ" ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Photo
💎ሠለፎች የማንበብ ንጉሶች ብቻ ሳይሆኑ

➻የመገንዘብ
➻የማመንና
➻የመተግበርም ንግስትና ንጉሶች ናቸው

💎ሀፍሳ ቢንት ሲሪን አሏህ ይዘንላትና
ከታቢዒ እንስቶች መካከል ግንባር ቀደሟ
ሊቅና በኢባዳ የታወቀች ጥንቁቅ ሴት ናት።

➧በታሪኳ ላይ እንደሰፈረው አሮጊትም
ሆና እንኳ ፊቷን ትሸፍን ነበር።

➧ኣሲም ቢን አህወል (ረሂመሁሏህ) ስለ
ሀፍሳ የገጠመውን እንዲህ ይላል፦

➻«ወደ ሀፍሳ ቢንት ሲሪን ያለችበት ቤት
እንገባ ነበርና ስታየን በጅልባቧ ፊቷን
ትሸፈናለች።

➻አሏህ ይዘንልሽና አሏህኮ

☜( وَالْقَوَاعِدُ مِنَ النِّسَاءِ اللاَّتِي لاَ يَرْجُونَ
نِكَاحاً فَلَيْسَ عَلَيْهِنَّ جُنَاحٌ أَن يَضَعْنَ ثِيَابَهُنَّ
غَيْرَ مُتَبَرِّجَاتٍ بِزِينَةٍ )

➻«ከሴቶችም እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት
ተቀማጮች (ባልቴቶች) በጌጥ የተገለፁ
ሳይኾኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእነሱ
ላይ ኀጢአት የለባቸውም፡፡ » ብሏል ስንላት

➻ከዚያስ በኋላ ምንድነው ያለው
አለችን
☜ وَأَن يَسْتَعْفِفْنَ خَيْرٌ لَهُنَّ )

➻«ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ የተሻለ
ነው፡፡ » ብሏል አልናት

💎እሷም
«እሱም (የተሻለው) በሂጃብ መፅናት ነው።»
ኣለችን ይላል።

📚በይሀቂይ ዘግበውታል: (7 / 93)
__
💎ሠለፎቻችንን ሴቶቻቸውንም
ወንዶቻቸውንም አሏህ ይዘንላቸው።

➻ለዱንያም ለአኺራም ሀያታቸው ሁሌም
የተሻለውን አፈፃፀም ይመርጡ ነበር።

➴የተፈቀደላቸውን እንደሚወዱት ሁሉ
ምርጫ በተሰጣቸው ቦታም በላጩን ይመረኮዛሉ።

➻ሃፍሳ (ረሂመሀላህ) በጥልቅ
የተገነዘበችውና የተገበረችው የጌታችን
ቃል የሆነው መመሪያችን ሙሉ አንቀፁም
እንደሚከተለው ነው።

☜” وَالْقَوَاعِدُ مِنَ النِّسَاءِ اللَّاتِي لَا يَرْجُونَ
نِكَاحًا فَلَيْسَ عَلَيْهِنَّ جُنَاحٌ أَن يَضَعْنَ ثِيَابَهُنَّ
غَيْرَ مُتَبَرِّجَاتٍ بِزِينَةٍ ۖ وَأَن يَسْتَعْفِفْنَ خَيْرٌ
لَّهُنَّ ۗ وَاللَّـهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ “ النور ﴿٦٠﴾

➻«ከሴቶችም እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት
ተቀማጮች (ባልቴቶች) በጌጥ የተገለፁ
ሳይኾኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእነሱ
ላይ ኀጢአት የለባቸውም፡፡

➧ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ የተሻለ ነው።
አሏህ ሰሚም ዐዋቂም ነውና፡፡ »

【አል-ኑር: 60】
↷⇣🌹⇣↷
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w