💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
👉እዉን ቁርአን የአላህ ንግግር አይደለምን      ክፍል  ➄ ➴⇘በነገራችን ላይ ይሄ በቁርአን ላይ ያላቸዉ እምነት ቁርአን  ፍጡር ነው”  ከሚለው የሙዕተዚላ እምነት ጋር አንድ ነው። እንደሚታወቀው ጂብሪልም ይሁን ሙሐመድ ፍጡሮች ናቸው። የፍጡር ንግግር ፍጡር ነው። ስለዚህ ይሄ በእጃችን ላይ ያለው ቁርኣን ፍጡር ነው ማለት ነው፣ እንደነሱ እሳቤ። ታዲያ ይሄ እነ ኢማሙ አሕመድን…
👉እዉን ቁርአን የአላህ ንግግር አይደለምን
  


ክፍል  ➅ የመጨረሻ

በይሀቂይ ረሒመሁላህ እንደሚሉት “ከዚህ የተለየ በሶሐባም በታቢዒዮችም ዘመን ከአንድም ሰው አልተገኘም።” [አልአስማእ ወሲፋት፡ ቁ. 562] ለዚህ ደግሞ “ከሰባ አመት በፊት የመልእክተኛውን صلى الله عليه وسلم ሶሐቦችና ከነሱም በታች ያሉትን ‘አላህ ፈጣሪ ነው። ከሱ ሌላ ያለ ፍጡር ነው፣ ቁርኣን ሲቀር። ቁርኣኑ የአላህ ንግግር ነው። ከሱ ወጥቷል፤ ወደሱም ይመለሳል’ እያሉ አግኝቻለሁ” የሚለው የታዋቂው ታቢዒይ ዐምር ብኑ ዲናር ንግግር ዋቢ መሆን ይችላል። ከሱፍያን ብኑ ዑየይናህ እና ከአቡበክር ብኑ ዐያሽም ተመሳሳይ ንግግር ተገኝቷል። [ሙኽተሶሩል ዑሉው፡ 164፣ 166]

በርካታ ቀደምት የኢስላም ሊቃውንት “ቁርኣን ፍጡር ነው አንልም” በማለታቸው
ሳቢያ ግድያ፣ ስቃይና እንግልት አስተናግደዋል። ቁርኣንና ሐዲሥን በሶሐቦች ግንዛቤ በመታገዝም ፈተናውን በፅናት ተወጥተዋል። ይህም ጉዳዩ ምን ያክል ቀላል እንዳልሆነ ነው የሚያሳየን። አንድ ድንቅ ምሳሌ እንውሰድማ።
በጊዜው በርካታ የሱና ዑለማዎችን ሲያንገላታ የነበረው ኸሊፋው አልዋሢቅ ወህኒ ካጎራቸው ሰዎች ውስጥ አንድ ሽማግሌ ትዝ ይሉትና “ያንን ሽማግሌ አምጡልኝ” ይላል። እጆቻቸው እንደታሰሩ ቀረቡ። ከፊቱ ሲቆሙ ሰላምታ አቀረቡለት። ኸሊፋው አልመለሰም።

ሽማግሌው፡ የሙእሚኖች መሪ ሆይ! የአላህንም የመልእክተኛውንም صلى الله عليه وسلم አስተምህሮት በኔ ላይ ተግባራዊ
አላደረግክም። የላቀው አላህ፡ በሰላምታ  በተከበራችሁም ጊዜ ከርሷ ይበልጥ ባማረው (ሰላምታ) አክብሩ። ወይም (እሷኑ)  መልሷት ይላል። ነብዩም صلى الله عليه وسلم ሰላምታን በመመለስ አዘዋል” አሉት።

ኸሊፋው፡ ወዐለይከ ሰላም” ካለ በኋላ ፈታኝ አድርጎ ያዘጋጀውን ኢብኑ አቢ ዱኣድን፡
“ጠይቀው!” በማለት ሽማግሌውን እንዲፈትን
አዘዘው።


ሽማግሌው፡ “የሙእሚኖች መሪ ሆይ! እኔ የተጠፈርኩ እስረኛ ነኝ። በእስር ላይ ውሃ ተከልክዬ በተየሙም ነው የምሰግደው። የታሰርኩበት ይፈታልኝ ዘንድ እዘዝልኝ። ውዱእ የማደርግበት ውሃም እዘዝልኝና አድርጌ ልስገድ። ከዚያ በኋላ ጠይቀኝ” አሉት። የታሰሩበት እንዲፈታላቸው አዘዘ። ውሃም አዘዘላቸውና ውዱእ አድርገው ሰገዱ። ከዚያም ለፈታኙ ኢብኑ አቢ ዱኣድ “ጠይቀው!” አለ። ሽማግሌው ግን የዋዛ አልነበሩም። “ጥያቄ ለኔ ይሁን። መልስእንዲሰጠኝ እዘዘው” አሉት።

ኸሊፋው“ጠይቅ” አላቸው።

ሽማግሌው፡ እድሉን ሲያገኙ ኢብኑ አቢ ዱኣድን አጣደፉት። “እስኪ ንገረኝ። ይሄ
‘ቁርኣን ፍጡር ነው’ እያላችሁ ሰዎችን የምትጣሩበት ጉዳይ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የተጣሩበት ጉዳይ ነውን?” አሉት።
ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ።

ሸይኹ፡ “ጥሩ። ከሳቸውስ በኋላ አቡበክር ሲዲቅ የተጣሩበት ነገር ነውን?” አሉት። ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ። (አይደለም ማለቱ ወዶ አይደለም። “አዎ” ካለ የከፋ መፋጠጥ
ስለሚከተለው ነው።)


ሸይኹ፡ “ጥሩ። ከነሱስ በኋላ ዑመር ብኑል ኸጧብ የተጣሩበት ነገር ነውን?”  አሉት። ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ።

ሸይኹ፡ “መልካም። ከነሱስ በኋላ ዑሥማን ብኑ ዐፋን የተጣሩበት ነገር ነውን?” አሉት። ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ።

ሸይኹ፡ “መልካም። ከነሱስ በኋላ ዐልይ ብኑ አቢ ጧሊብ የተጣሩበት ነገር ነውን?”  ሲሉት ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ።

ሸይኹ፡ “የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ያልተጣሩበት ነገር፣ አቡ በክርም፣ ዑመርም፣ ዑሥማንም፣ ዐልይም - ረዲየላሁ ዐንሁም - ያልተጣሩበትን ነገር አንተትጣራበታለህን?

መቼም ‘ያውቁት ነበር’ ወይ ደግሞ ‘አያውቁትም ነበር’ ከማለት ውጭ ምርጫ የለህም። ‘ያውቁት ነበር ግን ሳይጣሩበት ዝም ብለዋል’ ካልክ እኛንም አንተንም እነሱን የበቃቸው ዝምታ ይበቃናል። ‘አይ አያውቁትም ነበር እኔ ግን አወቅኩት’  ካልክ አንተ ውዳቂ የውዳቂ ልጅ! አንድን ነገር ነብዩ صلى الله عليه وسلم እና ቅን ምትኮቻቸው - ረዲየላሁ ዐንሁም - ሳያውቁት አንተናባልደረቦችህልታውቁት ነውን?” አሉት።

ኸሊፋውአፉን በልብሱ በማፈን እየሳቀ ተነሳ። ከዚያም እንዲህ አለ፦ “እውነቱን
ነው። ወይ ‘ያውቁት ነበር’ ወይ ደግሞ
‘አያውቁትም ነበር’ ከማለት ውጭ ሌላ ምርጫ የለም።
ያውቁት ነበር ግን ሳይጣሩበት ዝም ብለዋል’ ካልክ እኛንም አንተንም እነሱን የበቃቸው ዝምታ ይበቃናል። ‘አይ አያውቁትም ነበር እኔ ግን አወቅኩት’ ካልክ አንተ ውዳቂ የውዳቂ ልጅ! አንድን ነገር ነብዩ صلى الله عليه وسلم እና ቅን ምትኮቻቸው - ረዲየላሁ ዐንሁም - ሳያውቁት አንተና ባልደረቦችህ ልታውቁት ነው?” አለ።[አሸሪዐህ፡ 53-54]

ልክ እንዲሁ ቁርኣን የአላህ ንግግር መሆኑን የሚያስተባብሉ ጠማሞችን እንዲሁም የአላህን መገለጫዎች (ሲፋት) የሚያራቁቱ የጀህሚያ ወራሾችን የሰለፎቹን ግንዛሬ በመጠቀም መፈናፈኛ ማሳጣት ይገባል። ይሄ ርእስ እጅግ በርካታ ህዝብ የተፈተነበት ጉዳይ በመሆኑ በምትችሉት ሁሉ በማሰራጨት የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በአላህ ስም እጠይቃለሁ። ወሶለላሁ ወሰለም ዐላ ነቢይና ወኣሊሂ ወሶሕቢሂ ወሰለም። ተፈፀመ።

✍️ተፃፈ በኢብኑ ሙነወር እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 2005 ላይ ተፅፎ ዛሬ ሚያዚያ 14/2015 በመጠኑ ተነካክቶ የወጣ።


       ↶✍️↶  أم عثيمين بنت أراغاو الولوية
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
👉ከኩሽና ርቆ እንዲች ያለች ቦታ ቂርአት ናፍቆናል......✍️ ጀሊሉ ነጃ በለን ከኩሽና....!

https://t.me/https_Asselefya1
➬ አላህ ሰለፍያህ ባል ከወፈቀሽ.........

𝐓𝐞 ≈ https://t.me/https_Asselefya1
"ኡስታዝ" ነው የሚለው እና ፀባዩ " ሸጋ" ነው የሚሉት ነገሮች የሚለያዩ ነገሮች ናቸው። ሁለቱም ባንድ ላይ ላይገኙ ይችላሉና አጣርተሽ ግቢ ለማለት ያክል ነው።
منقول
🌿✍️
قال الإمام ابن القيم رحمه الله :

‏من كثرت همومُه وغمومه
‏فلكثر من قـول :  ‏لا حـول ولا قـوة إلا باللـه.
‏ زاد المعاد 183/4

🍁 ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-
" ጭንቀቱና ትካዜው የበዛ ሰው ላ ሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂ : የሚለውን ዚክር ያብዛ "
ዛዱል መዓድ ( 4/183 )

𝐓𝐞~ t.me/https_Asselefya1
✍️ حياءُ المرأةِ حياتُها !

✮ የሴት ልጅ ሀያዕ አይናፋርነቷ ሂወቷ ነው።
መስፈርት ካልተሟላ 100አመት ቢሰጠዉ ኡማዉ አንድ ማድረግ አይቻልም!
ወንድም ሳዳት ከማል حفظه الله
👉መስፈርቱ ካልሟላ 100 አመት ቢሰጠውም ኡማውን አንድ ማድረግ አይችልም፡፡

🎙በወንድም ሳዳት ከማል حفظه الله

http://t.me/https_Asselefya1
እህቴ ቂርአት ከበደኝ ብለሺ ከቂርአትቦታ እንዳትርቂ ጠበቅ አድርገሺ ያዢዉ አይዞሺ ታሸንፊዋለሺ!!የምን ተስፍ መቁረጥ  ቀርተሺ ያለፍሺዉን እንደት እንዳፍለሺዉ ዘወር ብለሺ አስቢና  ከዛ የጀመርሺዉን  ጠበቅ አድርገሺ ያዢዉ አይዞሺ ዉዷ!! ✍️𝐔𝐦𝐮 𝐔𝐬𝐞𝐲𝐦𝐢𝐧

𝐓𝐞 ~ t.me/https_Asselefya1
➬በቲክቶክ ወጥቶ መጨፈር ጀግንነት ሳይሆን ጂልነት ነዉ እህቴ ይቅርብሽ ጭፈራ አያዋጣሺም የዛሬ አድናቂሽ አጨብጫቢሽ ነገ አላህ ፊት አይጠቅምሺም ተመለሽ እቴዋ ወደ ጌታሽ ይብቃሽ መጃጃሉ✍️
↷በቲክ ቶክ ለተሸወዱ አጭር ምክር↶
አቡ አብዲላህ «ኢብኑ ኸይሩ»
በቲክ ቶክ ለተሸወዱት አጭር ምክር ↶

You tube
☞Tik tok
☞subscribe

ሰበር ዜና በማለት ጊዜያችሁን አትግደሉ
!!

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ


⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/10700
☞አላህ አልቀደረልንም ብለን በዉዴታ የምንቀበለው ነገር እንጂ አለፈን ብለን የምንቆጭበት ዕድል የለም።ጌታዬ ሆይ እኛ የጓጓንለትን ሳይሆን አንተ የተሻለ ነው ያልከዉን ነገር ስጠን።
~t.me/AbuSufiyan_Albenan
አንዳዴ........

ድክሞ ይለናል¡ አማን እደሩ! የነገ ሰዉ ይበለን የተለያዩ ነገሮች የምንለጥፍ ይሆናል¡

ጫት አስካሪዉ
ሸይኽ አቡ አማር አወል አህመድ
🍁 ጫት አስካሪዉ......

🎙ሸይኽ አቡ አማር አወል አሕመድ

↷↷↷↷↷⇊🍃⇊↶↶↶↶
http://t.me/https_Asselefya1
«ውዷ―እህቴ»

ትዕግስትን( ሶብርን) ስንቅሽ!
የአላህን ቃል ቁርዓንን ጓደኛሽ!
ተወኩልን ተስፋሽ አድርገሽ ይዘሽ!ـ
"ዒልምን ከመፈለግ አትሰልች።


(فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ۝)
النحل:﴿٤٣﴾


« የማታውቁም ብትኾኑ የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡»

(አል  ነህል: 43)

የማታውቂውን ነገር ጠይቂ እወቂ
አትፍሪ ተማሪ በተውሒድ በሱና ተበሰሪ
በእምነትሽ አልባሣት ኩሪ ጠንካሪ እንስት ሁኚ!!


➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
ባልሽ ያገባሽ አዛኝ፣ ትሁት፣ ሲከፋዉ አፅናኝ፣ የደስታዉ ዶክተር እንድትሆኝለት እንጅ ፌደራል ፖሊስ ሆነሽ ሲወጣ ሲገባ ቁም ተራመደ አሳርፍ 100 ዉረድ 200 እያልሽ ፊትሽን እንደ ደርግ አኮሳትረሽ እንደክረምት ደመና አጥቁረሽ እንድትጠብቂዉ አይደለምና ተጠንቀቂ። 

ሴቶች እ👆 እኔ አላልኩም ኮፒ ነዉ!!

🍁t.me/https_Asselefya1