💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
📍ዉዷ የሱናዋ እህቴ!!

የኔ እህት ስደት አትጥሊዉ ስደት ብዙ መጥፎ ነገሮች መከራ ችግሮች ቢኖሩትም ጥሩ መልካም ደስ የሚሉም ነገሮች አሉበት።በጥቅሉ በሂወትሽ ዉስጥ ትልቅ ትምህርት ቤት ነዉ ስደት!
ከምንም በላይ ትክክለኛ መነሀጂ ይዘሺ ሺርክና ቢዲዓ እርቀሽ ተዉሒድና ሱና አጥብቀሺ መያዝሽ በዛዉ መፀናትሽ ይሄ ትልቅ ነገር ነዉ።አልሐምዱሊላህ በይ! የአንቺ ጓደኞች ስደት ያልመጡ ተዉሒድ እና ሱና አያቁ ሁለየ ከአላህ ዉጭ ባለ ነገር ተንጠልጥለዉ፣ጥላሞት እየፈሩ፣ጥቁር ድመት እየፈሩ፣እንቅፍት ሲመታቸዉ አይቀናኝም ብለዉ ከወጡበት ሀጃ የሚመለሱ ስንቶች ናቸዉ??አንችን ግን አላህ መርጦሽ ይሄን ዉብ እስልምናን አሳዉቆሻል በስደት ሰበብ! አልሐምዱሊላህ በይ አይክፍሽ ስደት በመሄድሽ አይዞሺ ሀሳብሺ ሙሉ አድርጎ አዛኙ ጌታ በሰላም ለሀገርሺ ያብቃሺ!!

✍️

http://t.me/https_Asselefya1
📍ትዳር በመዘግየቱ ምንም አይክፍሽ!

ሲጀመር የወጣሺበት አላማ አሳክተሽ እስክትመለሽ ትዳር ከራስሽ ባታስገቢዉ መልካም ነዉ።ትዳር ካሰብሽም ሀገርሽ ስትደርሺ!የሩቅ ነገር እያየነዉ ነዉ። ለሳምንት ለወር ነዉ ነገሩ!አላህ ከዚህ ጠብቆሽ መዘግየቱ ተደሰቺ ልብሽ ሳይሰበር በon line ሰላም ሀገር መመለስሽ ጥሩ ነገር ነዉ።እስኪ ከጎንሺ ያሉት ተመልከች በon line አግብተዉ የፈቱ፣አዉርተዉ የተዉ፣ስንት አሉ ልባቸዉ የተሰበረ ከስደቱ ብሶት ሌላ ጭማሪ በትዳር ስም ብሶት በሀዘን የተንገላቱ ስንት ናቸዉ። ታድያ ከእነዚህ ትምህርት አትወስጂም ወይ! ከዚህ ፈተና ጌታሺ የጠበቀሺንም አመስግኝ! ስለባል አታስቢ አብሽሪ አንቺ ጥሩ ሚስት ለመሆን ራስሺን ሁለየ አስተካክሊ ጥሩ ሚስት ሆኖ ለመገኘት ጣሪ ከዛ አታስቢ አላህ ከነ መፈጠሩ የማታቂዉ የሱን ዉድ ባሪያ ይወፍቅሻል ከዛም በደስታ ሁለየ ትኖሪያለሽ ያም ጌታሺ የሰጠሺ ዉድ ሰዉ የልብሽ መርጊያ የአይንሽ ማረፊያ ሁኖ ሁለየ ወደሺዉ ሀቁ ጠብቀሽ ትኖሪያሽ! እናም አደራሺን በሶብር! የትዕግስት ፍሬዉ ጣፍጭ ነዉ።የጌታሺ ዉሳኔ እስኪደርስ ጥንቁቅ ሁነሺ ኑሪ!ሸሪዓዊ እዉቀት በመፈለግ ላይ ራስሽን ቢዚ አድርጊ ወላጆችሽን በመንከባከብ ላይ በርቺ! አላህ ከአንቺ ጋር ይሁን.......!

✍️

http://t.me/https_Asselefya1
📍ትግልሽን ቀጥይ!!

ድንጋይ ባገኘ ቁጥር የሚቀመጥ ሰው
ረጅም መንገድ ተጉዞ ካሰበበት ግብ
ሊደርስ አይችልም ዓላማሽ ሆነ ምኞትሽ
ከግብ እንዲደርስ መልፋት መጣር ነዉያለብሽ።

📍ከፍ ያለ ቦታ ሚፈልግ ሰዉ
በደምብ ይለፋል የተለመደ ዉጤትየፈለገ ሰዉ በትንሹ ይለፋል!ስለዚህ ህይወትሽንና ቤተሰብሽን
አልፎ ዲንሽን ሀገርሽን ሚጠቅም ትልቅ
ዓላማ ይኑርሽ ለአላማሽ ታማኝ ሁኚ ስሪለት ድከሚለት!!


📍ገናነሽ ወጣት ነሽ ትደርሻለሽ!!
ገና ብዙ መስራት ትችያለሽ ለሁሉም
እጅ አትስጪ የመሸበቻ ሰአትሽ ሳይደርስ ለምን በሀሳብ እየተናወጥሽ ትደክሚያለሽ ትሸብቻለሽ!?

📍በቃ ትክክለኛ ሰው ሆነሽ ተጓዥ እንጂ
አሏህ ካንችጋ ነው አትወድቂም ብቻ
አሏህ ሚወደው መንገድ ይሁን ጉዞሽ!


📍ሚዛናዊ ሀቀኛ ሁኚ ለጉዞሽ ማማር
ዋነኛው ነውና  አሏህ የሚወደውን ስኬትም ትጎናፀፊያለሽ
       
منقول
http://t.me/https_Asselefya1
📍ኡኽታ!

ቤተሰቤ ከሽርክ አልወጣ አለ ብለሽ 1የ ሁለተየ ተናግረሺ ሀገር ለቀሺ አትሂጂ ሳትሰለቺ ደጋግመሽ ምከሪ ይቀየራሉ ኢንሻ አላህ! ማለቴ እስኪ ራስሺ እንደት እንደተለወጥሽ ዘወር ብለሽ እይዉ በ1ንድ በ2ኦዶወ በመስማት ነዉዴ ያደግሺበት የሽርክ እሞነት የለቀቀሽ እና የተዉሒድ እምነት የገባሺ በጭራሽ አይደለም ብዙ ሰምተሽ ነዉ ከተለያዬ ኡስታዞች አንደበት ማለት ነዉ ስለዚህ አንችም በተለያዬ ሂክማዎቸ እየተጠቀምሺ ሳትሰለቺ ቤተሰብሽ ምከሪ! በአንደየ በሁለተየ ምክር እንቢ አሉ ብሎ ሀገር ለቆ መሄድ ሀቂቃ በደል ነዉ በሽርካችሁ ሙቱ ማለትኮ ነዉ እ እንደት ያስችላል.......

✍️

http://t.me/https_Asselefya1
📍የኔ እህት

ስደት ካለሽ እዛ ያሉ ሰዎች የሚሉሽ ነገር አትስሚ እነሱ አይቀየሩም እሺ አይሉም የሚሉሽ ነገር አትስሚ በጭራሽ ይሄ ነገር ተስፍ የሚያስቆርጥሽ ጭራሽ ተስፍ እንዳትቆርጭ ቆራጥ ጀግና ሁኝ እቀይራቸዋለሁ ብለሽ ራስሽን አሳምኝ እነሱን ማሸነፊያሽ(ማሳመኛሽ)እዉቀት ነዉ እና አሁን ጠንክረሽ ተማሪ መረጃዎችሽን በደንብ ስብስቢ ሂድያ ሰጭዉ አላህ ነዉ አንች ብቻ ጠንከር ብለሽ ሰበቦችን በጥሩ ስነ ምግባር አድርሻቸዉ! አይዞን የማይቀየር የለም እኛም ከእነሱዉ ተወልደን አብረን ሸሆቹ እያልን አድገን ተቀይረናል እነሱም የማይቀየሩበት ምክንያት የለም። ብቻ እሺ አይሉኝም የሚል ነገር ቅንጭላትሽ ዉስጥ እንዳታስቀምጪ! በአላህ ፍቃድ ሰበብ አደርሳለሁ ይቀየራሉ የምትለዋ በጭንቅላትሽ ይዘሺ ሞክሪ! አይዞን💪

✍️
http://t.me/https_Asselefya1
የነብዩላህ ኑህ የተውሂድ ተጋድሎ

ተከታታይ ደርስ እለቃለሁ አብረን እንከታተል
የቀደምቶቻችን የተዉሒድ ተጋድሎ እየሰማን እኛም እንጠነክራለን!


✍️
𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ማን ነህ በዚህ ዘመን የነበርክ…¡
አባቶቻችን ይዘንጡባት ነበር በግዜው ቶሎ አያልቅም ይቆያል እደውም በዚህ ኑሮ ውድነት ወንዶች ብትጠቀሙት አሪፍ ነው!!

«ከዚሁ ከ ኮሜንት ሰፈር ያገኘሁት ነው»
ነፃ ካልወጡ ነፃ አውጪዎች ተጠንቀቂ!
~
የፊታችን ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው አሉ፡፡ ወይ ፈረንጅ! አመቱን በሙሉ እኮ “የምንትስ ቀን” እያሉ ሊዘጉት ነው፡፡ ፈረንጅ ሲስል የሚስለው ሌላው ክፍል ነጩ ሰው “የግብረ ሰዶማውያን ቀን” ብሎ ቢጀምር ያለምንም ማመንታት ይከተላል፡፡ አሁንም ስላለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ብቻ ማርች ስምንትን ለሴቷ ሰጧት አሉ፡፡ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት!!”
እለቱን ሳስታውስ አንድ ነጭ አስተማሪ ስለ ሴቶች “መብት” እንቅስቃሴ እያወራ የተናገረው ነገር ከአመታት በኋላ ትዝ አለኝ፡፡ የሴቶችን መብት ካፋጠኑ ነገሮች አንዱ ብስክሌት ነው ነበር ያለው፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ይደንቀኝ ነበርና ኢንተርኔት ገብቼ ሳስስ ለካንስ ሀሳቡ የሱ ብቻ አይደለም፡፡ ይሄ ነገር ሰዎቹ ምን ያክል ቂ ሎ ች እንደሆኑ እና ነፃነት ሲሉም ግርማ ሞገስ ያለውን አለባበሷን ማስጣል እና በቤት እመቤትነቷ እንድትሸፍት ማድረግ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ብቻ አላማቸው የሴቶችን መብት ማክበር እንዳልሆነ ከሙስሊም ሴቶች አንፃር ያላቸው አተያይና ፖሊሲ በተጨባጭ አይን ላለው ሁሉ እያሳየ ነው፡፡ እርቃንነትን እስከ ጥግ እየፈቀዱ ሙስሊሟን ግን አለባበሷን ምክኒያት በማድረግ፣ ከትምህርት ገበታ፣ ከስራ ቦታ ማፈናቀሉን ተያይዘውታል፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ ስለ ሴቶች መብት የሚያቀነቅኑት፡፡ ከባህልም ከሞራልም ያፈነ ገጡ አለባበሶች ላይ ትንፍሽ ሳይሉ ለሙስሊሟ ሲሆን ግን በየመንገዱ ይጎነትላሉ፡፡ አልፈውም ህገ-ደንብ ያወጣሉ፡፡ ፖሊሲ ያረቃሉ፡፡ ከዚያም አያፍሩም ስለ ሴቶች መብት ይደሰኩራሉ፡፡ “የምትለብሺውን እኔ ካልመረጥኩልሽ” ከማለት በላይ ምን አፈና አለ?!!
እህቴ ሆይ! ተጠንቀቂ!! ብዙዎቹ የሴቶች “ነፃ አውጪዎች” የሰይጣን ተልእኮ አራማጅ የሆኑ የሀሰት ጥሩ ንባዎች ናቸው፡፡ እውነት ተቆርቁሮልሽ እንዳይመስልሽ፡፡ ቢሆንማ ለእርቃን እሩብ ጉዳይ መሆንን ፈቅዶ መልበስሽን ለምን ይቃወምሻል?! እውነት ለመብትሽ ተሟጋች ከሆነ ስትራቆቺ ገልፍጦ ስትለብሺ ለምን ደሙ ይፈላል?! ለምንስ በየመንገዱ ይጎነትላል?! ለምንስ ከየተቋሙ ያባርራል?! እመኚኝ “ነፃ ውጪ” የሚለው በየጎዳናው በነፃነት በነፃ ወይም በርካሽ እንዲያገኚሽ ነው፡፡ አስተውይ! ልብስሽን ስለጣልሽ ነፃ አትወጭም፡፡ ነፃ መሆን ልብስ በመጣል ከሆነ ነፃ ሰዎች ማለት እብ - ዶች ናቸው፡፡ የሚጮኸው ስለ ክቡር ማንነትሽ ሳይሆን ስለ እርቃን ገላሽ ነው፡፡ የነቁበት ነቅተውበት እየተመለሱ ነው፡፡ ይሄውና በምዕራቡ አለም ከሚሰልሙት ውስጥ 80% ሴቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች ለሀጫቸው የሚዝረበረብለትን የምዕራቡን “ነፃነት” ሸሽተው ወደ ኢስላም “ጭቆና” ይጎርፉ ይዘዋል፡፡ በጊዜ ንቂ፡፡ ብልጥ ማለት በሌሎች ላይ ከደረሰው ቀድሞ የሚማር ነው፡፡ ምሳሌሽን በትክክል ምረጪ፡፡ በአኢሻ ስብእና እያፈርሽ አሊሻን  መሆን ካማረሽ ግን ግፊበት፡፡ ጀሀነምን የሚቋቋም ገላ ካለሽ መንገዱን ጨርቅ ያርግልሽ፡፡
ንቂ! ያለበለዚያ ይሄ በስጋዊ ፍላጎት የታወረው “ጠበቃሽ” የኮንዶም ማስታወቂያ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ! ያለበለዚያ ይሄ ካንገት በታች እንጂ ካንገት በላይ የሌለው ርካ ሽ በ ድ ን ከምንም በታች አርክሶሽ የሱ ርካሽ ሸቀጥ ማሻሻጫ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ! ሙስሊም ወንድምሽ ስለበደለሽ በኢስላም ላይ ብታምጪ ኢስላምን ቅንጣት ታክል አትጎጂውም፡፡ ብቻ በዱንያም ላታተርፊ ሁለቱንም አገር የከሰርሽ ከሁለት ያጣሽ ትሆኛለሽ፡፡ እራስሽን ሁኚ፡፡ የገደል ማሚቶ አትሁኚ፡፡ ሌሎች ስለሳሉ አትሳይ ስላነጠሱም አታነጥሺ፡፡ የተፈጠርሺው ለክቡር አላማ ነው፡፡ አላማ ቢስ አትሁኚ፡፡ ያለበለዚያ ኮምፓስ እንደሌለው መርከብ ዋለሽ ዋለሽ አስከፊ ፍፃሜ ላይ ትደርሻለሽ፡፡
ተጠንቀቂ!! ከሸሪዐው አጥር ውጭ ያለ የመብት ጥያቄ አትጠይቂ፡፡ የፈጠረሽ ጌታ አንቺ እራስሽን ከምታውቂው በላይ ያውቅሻል፡፡ ላንቺም ከተኩላው “እንባ ጠባቂ” ቀርቶ ከራስሽም በላይ ያዝንልሻል፡፡ ደግሞም አትዘንጊ፡፡ ህይወት ማለት የአኺራ ህይወት ነው፡፡ አላህ አድሎሽ ሰማንያ ዘጠና አመት ብትኖሪ እንኳ በጊዜ ከኢስላም ባቡር ውስጥ ካልተሳፈርሽ ሲመሽ ይቆጭሻል፡፡ ምን ብትኖሪ ህይወትሽ መጨረሻ አለው፣ ሞት፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ዘላለማዊ ህይወት፡፡ የዛሬው ቅቤ አንጓች “እንባ ጠባቂ” ተኩላ ግን የአኺራ ምንነቱም አይገባውም፡፡ ለዚያ ቀርቶ ለዱንያ እንኳ ጤነኛ ህልም የለውም፡፡ ለአኺራማ እንኳን ላንቺ ለራሱም አይሆንም፡፡ የአህያ ባል ከጂብ አያስጥልም፡፡ ለናቱ፣ ለሚስቱ፣ ለልጁ፣ ለእህቱ የማይሆን ሰካ - ራም ነፃ ያወጣኛል ብለሽ ከገመትሽ የመጨረሻ ቂ ል ነሽ፡፡ እሱ እራሱ በስሜቱ የሚገዛ የስሜት ባሪያ ሆኖ በየትኛው ሞራሉ ነው አንቺን ነፃ የሚያወጣሽ?! ቀድሞ ነገር ምን ሲደረግ ለሰካ - ራም ጆሮሽን ሰጥተሽ?! ቦታ ከሰጠሽውማ የአለም እዝነት የሆኑትን ነብይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠላትሽ እንደሆኑ ቀስ እያለ እያዋዛ ያሰርፅብሻል፡፡ በጊዜ ካልነቃሽ መውጣት ከማትችይበት የስሜት አሮንቃ ውስጥ ይነክርሻል፡፡ በደጋሚ ምላሱ ጭንቅላትሽ ላይ ተብትቦብሽ የስሜት ባሪያ ሆነሽ ረክሰሽ፣ ከማንም በላይ ብቁና ንቁ የሆንሽ ይመስልሻል፡፡  ተቆርቋሪ መስሎ ስለቀረበ እንዳያታልልሽ፡፡ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ሐያእሽ ባለመሟጠጡ በግልፅ ባታወጪው እንኳ ውስጥሽ ለኢስላም ይደፈርሳል፡፡ ለነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ያለሽ ክብርም ምናልባት ካልጠፋ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ግን እስቲ እኔ ልጠይቅሽ፡ እውነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላንቺ ስለማይቆረቆሩ ነው ከመቶ ሺ በላይ  ሶሐቦቻቸው በተሰበሰቡበት ታላቅ ቀንና ታላቅ ቦታ ላይ “የሴቶችን ነገር አደራ” እያሉ አዋጅ ያሰሙት? እርግጥ ነው ብዙ በደል አለብሽ፡፡ ግን አስተውይ ከበደሎቹ ሁሉ የከፋው ዘላለማዊ ክብር የሚያጎናፅፍሽን ኢስላምሽን እንዳታውቂ መደረግሽ ነው፡፡ እናም እልሻለሁ፡ በኢስላም ከኢስላም መብትሽን ፈልጊ፡፡ ለወዳኛው ህይወትሽም ትጊ፡፡ የተኩላ ሰለባ እንዳትሆኚ ንቂ፡፡ የአላህ ሰላም ላንቺ ይሁን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር)
=

የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁለት ሚስቶችን በአንድ ፍራሽ ይዞ መታኛት ይፈቀዳልን (ፍርዱስ ምንድን ነው)??

🎙العلامة ابن عثيمين رحمه الله
አድ-ዱሩሱል ሙሂመህ ሊዓመቲል-ኡመህ.apk
94.9 MB
🎁 አዲስ አፕልኬሽን ተለቀቀ 🎁

📚 አድ'ዱሩሱል ሙሂማህ | الدروس المهمة

| ሙሉ ደርስ ያለ ኔት

📲 አዲስ አፕ በአዲስ አቀራረብ

⊙ ሙሉ ደርስ በድምፅ
⊙ የኪታቡ pdf
⊙ ማስታወሻ መያዣ
ሁሉንም በአንድ የያዘ ምርጥ አፕ!

| | የኪታቡ አዘጋጅ :- ሰማሐቲ ሸይኽ ዐብዱል-ዐዚዝ ብን ዐብዲላህ ብን ባዝ -ረሒመሁሏህ-

| 🎙 | አቅራቢ:- ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም -ሐፊዞሁሏህ-

| 🎧 | ከክፍል 01 እስከ ክፍል 07 ሙሉ ደርስ

_
📥  የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/4181
-
ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ!
#ሼር በሚደረግ ለብዙሃን ይደረሰ ዘንድ የበኩሉን አሰተዋጽኦ ያድርጉ!

በቅርቡ ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎችን ይጠብቁ።
إن شاء الله

https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam
ለሴት ልጅሽ ጥሩ ምሳሌ ለመሆን ሳትዘጋጂ ወደ ትዳር አትግቢ፥ ካልሆነ ያንቺው አይነት ምድር አበላሽ ልጅ ታፈሪያለሽ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ለልጆቻችን ለአካዳሚ ትምህርታቸው የምንሰጠውን ትኩረት ሩቡን ያክል ለዲን ትምህርታቸው ትኩረት ብንሰጥ ጅህልና በተቀረፈ ወይም በተቃለለ ነበር"

https://t.me/https_Asselefya1
በሂወታችን መጥፉ ነገር ሲከሰት ለምን ተከሰተ አንበል ይልቅ ከዛ ክስተት ተምረን ወደፊት ያለዉ ሒወታችን እናስተካክል!!

©ሸጋ ለይል ቤተሰቦች!

✍️
"የማይታመን ነገር!
የባንክ አካውንት ያለው ሶሓቢይ እንዳለ ታውቃላቹህ?"

ተገርሜ ላስገርማቹህ!
👇👇👇
https://youtu.be/3EKi9lYW1fM