💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ

📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች

📌በመልካም ስነምግባር መዋብ
📌 (التحلي بالأخلاق المشروعة)

🔹እውነተኝነት 🔹ጥቡቅነት
🔹ቸርነት 🔹አይናፋርነት
🔹ጀግንነት 🔹አማናን መወጣት
🔹ቃል ኪዳንን መሙላትና ሌሎችም

《ክፍል 1⃣9⃣

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
ማግባትህ ካልቀረ ሰለፍይዋን አግባ


↪️ እውነተኛ ሰለፍይ የሆነችን ሴት ያገባ ወንድ ምንኛ ታደለ❗️

♻️ስማማ ወንድሜ
🔻🔻🔻🔻🔻🔻
🔹ሽቶህ የፈረንሳይ ቢሆን
🔹ጫማህ ከጣሊያን ቢገዛ
🔹ሰአትህ የስዊዘርላንድ ቢሆን
🔹መኪናህ ከጀርመን ቢመጣ
ሚስትህ ሰለፍይና ጣሊበል ኢልም ካልሆነች የህይወትን ደስታና ጣእም ሙሉውን አታገኝም።

ለዛም ነው አንዳንዶቹ "ሰለፍይ የሆነችን ሚስት ያላገባ ወንድ ሁሌም ላጤ ነው" የሚሉት።

↪️ ሰለፍይዋን በማግባትህ ከምታገኛቸው ጥቅሞች ውስጥ በትንሹ

◾️በዲንህ እንድትበረታ፣ ለአሔራህ እንድትለፋና በሱና ላይ እንድትጠናከር ታግዝሀለች።
◾️ሁሉ ነገሯ ያንተ ብቻ ነው። ካንተ ውጪ ማንም አይጨብጣትም፣ አያያትም፣ አይነካትም።
◾️የተለያዩ ቁሳ ቁሶችና ያላስፈላጊ ወጪ በመጠየቅ ብርህት አታባክንም።
◾️አጉል መዝናኛ፣ ትርፍ የሌለወወ ሽርሽርና ቅጥ ያጣ ደስታ በሚል ጊዜህን አትገልብህም።
◾️የትም ብትሄድና ከሷ ብትርቅ በልጆችህ፣ በገንዘብህና በፍራሽህ ጉዳይ ላይ ምንም ስጋት አይገባህም።
◾️ህመምህ ህመሟ፣ ጭንቅህ ጭንቋ፣ ስቃይህ ስቃይዋ፣ ደስታህ ደስታዋ አድርጋ ስለምታስብ ሁሌም ትሳሳልሀለች።
◾️ለልብህ መርጊያ፣ ለአይንህ ማረፊያ እንዲሁም ለቀልብህ ደስታ ትሆነሀለች።

💢 ይህች ናት ሰለፍይዋ እወቃት


↪️ የሰለፍይ ሴት እጅግ ብዙ መገለጫና ባህርይ ቢኖራትም ከነዚህ ውስጥ በመጠኑ ልጠቁምህ

➲የማትጠራጠር ሁሌም በእርግጠኝነት የተሞላች
➲ሀሜት አታውቅም ምላሷን ጠባቂ ናት
➲ቶሎ አትናደድም ነገራቶችን በርጋት ምትቃኝ ናት
➲ትርፍና የማይጠቅም ከሆነ ነገር ሁሉ ትርቃለች
➲አዛኝ ናት ጭካኔን አታውቅም
➲ሩህሩህ ናት ደንዳና አይደለችም
➲ለእውቀት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች መሀይምነትን ትጠላለች
➲ባወቀችው ነገር ትሰራለች ሰዎችም በአደቡ ትመክራለች
➲ስነምግባሯ ያማረ ነው ጋጠወጥ አይደለችም
➲ጥቡቅ ናት የፈለገ ሁሉ አያገኛትም
➲ርካሽ ቦታ አትገኝም ክብሯን ትጠብቃለች
➲ባላት የምትብቃቃ ናት ሌሎችን አሻግራ አትመለከትም
➲ለዱንያ ብዙም አትጨነቅ በጌታዋ የምትተማመን ነች
➲እራሷን ጠባቂ ናት አትዝረከረክም
➲ንግግር አታበዛም ቁጥብ ናት
➲እውነተኛ ናት ውሸትን አትወድም
➲ጌታዋን ታወሳለች ዝንጉ አይደለችም
➲ዙረት አታበዛም በቤቷ ረጊ ናት
➲ለማንም አትገላለጥም ለባሏ ካልሆነ በቀር
➲ባሏን አክባሪ ናት አታዋርደውም
➲ሚስጥሩን ጠባቂ ናት ለማንም አሳልፋ አትሰጥም
➲የተረጋጋች ናት ቸኳላ አይደለችም
➲ጊዜዋ በኢባዳ እንጂ በወሬ በፊልም በድራማ አትገልም
➲ሰዎች ይናፍቋታል እንጂ መቸም አይሰለቿትም
➲በውይይት የምታምን እንጂ ግትር አይደለችም
➲ሰውን አክባሪ እንጂ ፈሪ አይደለችም
➲ሽርክ ቢድአና ኹራፋትን በጭራሽ አትቀርብም
➲በኒቃቧ ተሸፋኝ ናት ሰውን አትፈትንም
➲የአላህን ውሳኔ ወዳ ሶብር ታደርጋለች እንጂ አትበሳጭም
➲የባሏን ትእዛዝ ታከብራለች በፍፁም አታምፀውም
➲ለሰዎች መልካምን እንጂ መጥፎ አትመኝም
➲ለሌሎች ዱአ ታደርጋለች እንጂ አትመቀኝም
➲በተራ ምክንያት ትዳሯን ገደል አትከትም
➲ይቅር ባይና ሆደ ሰፊ ናት ቂም አትይዝም
➲አርቆ አሳቢ ናት ስሜታዊና ቅፅበታዊ አይደለችም
➲መነጫነጭ፣ መነታረክ፣ መኮሳተር፣ መከራከር አቶድም
➲በዲኗ ጉዳይ ከማንምና በምንም አትደራደርም
🔺ለወንድ ብላ ሀይማኖቷን አትቀይርም
🔺ለዱንያ ብላ ሱናዋን አትሸጥም
🔺ለትዳር ብላ ከመንሀጇ አትንሸራተትም
🔺ለስሜቷ ስትል ዲኗን አታሰድብም
🔺ለጥቅማ ጥቅም ስትል ክብሯን አሳልፋ አትሰጥም

▶️ ይህች ናት አግባ የምልህ

📝ልብ በል📝
💢ትዳር ከተስተካከለ እዚህ ምድር ላይ ካሉ ኒእማዎችና ፀጋዎች ውስጥ አንዱና ዋና ከሚባሉት የሚመደብ ሲሆን በተቃራኒው ከሆነ ደሞ ህይወትህ ምስቅልቅሉ የሚያወጣና ደስታን የሚነሳ ስለሆነ ከማግባትህ በፊት ማን ማግባት እንዳለብህ ቆም ብለህ አስብ።

↪️ አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል።
【ٱلْخَبِيثَٰتُ لِلْخَبِيثِينَ】
💎መጥፎ ሴቶች ለመጥፎ ወንዶች የተገቡ ናቸው።
【وَٱلْخَبِيثُونَ لِلْخَبِيثَٰتِ】
💎መጥፎ ወንዶች ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡
【وَٱلطَّيِّبَٰتُ لِلطَّيِّبِينَ】
💎ጥሩዎቹ ሴቶች ለጥሩዎቹ ወንዶች የተገቡ ናቸው።
【 وَٱلطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَٰتِ】
💎ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች የሚገቡ ናቸው፡፡
📚ሱረቱ ኑር (26)

↪️ ለዚህም ነው በተጨማሪ ውዱ ነብያችን እንዲህ ያሉት፦
【"فاظفر بذات الدين تربت يداك"】
የዲን ባለ ቤቷን ምረጥ። እጅህ አፈር አፋሽ ይሁንን

👉 በአላህ ፍቃድ
ስለወንዶቹ
ይቀጥላል።

t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1670
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1670
بسم الله الرحمن الرحيم


ዛሬም እንዴ ጥንቱ መላዕክትና ጂን የሚያመልክ አለ
●●●●●●●●●●●●●●●●●●

🔺አላህ እንዲ ይላል፦
↪️ሁሉንም በሚሰበስባቸውና ከዚያም ለመላእክቱ፡
እነዚህ እናንተን ነበር የሚገዙት? በሚላቸው
ቀን አውሳ]። [መላዕክቱም]፡ ጥራት ይገባህ ከነሱ ይልቅ ረዳታችን አንተው ነህ።
ይልቁንም ጂንን ነበር የሚያመልኩት።
አብዛኞቻቸው በእነሱ አማኞች ናቸው ይላሉ"።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
[ሰበእ፡40-41]


↪️እነሆም ከሰዎች የሆኑ ወንዶች
በወንድ ጅኖች ይጠበቁ ነበር።
መሼበርንም ጨመሯቸው።[ አል ጂን፡5]


🔻ዛሬም ተመሳሳይ እውነታ አለ።
አዲስ ቤት ሰርተው ሲገቡ የአካባቢው
➡️"ቆሌ" እንዳይጣላቸው ለመጠበቅ
ደም የሚያፈሱ አሉ።

🔺ከህመም ለመጠበቅ የተለያዩ መልክና
ስያሜዎች ያሏቸው ዶሮዎችን በላያቸው ላይ
አዙረው የሚለቁ ኋላም በቃላቸው
የሚያርዱ ሰዎች በሀገራችን በብዛት አሉ።

🔹በመንገድ ላይ ሲጓዙ አስፈሪ አካባቢ
ሲደርሱ ወይም ከፍ ያለ ዛፍ ሲያገኙ
ከስሩ ለበረካው ተቀምጠው የአካባቢውን
ቆሌና አድባር ከስጋት እንዲጠብቃቸው
የሚለማመጡ ብዙ ናቸው።

ታዲያ የሚያስቡትን አማን፣ የሚያልሙትን
ጤና ሊያገኙ ቀርቶ ሁሌ በስጋት ነው
የሚኖሩት። ሁሌ ምርኮኛ ሆነው ነው
የሚቀሩት።
♻️♻️♻️♻️♻️
um fulan


https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ

📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች

📌(እስላማዊ በሆኑ አደቦች ማጌጥ)
📌 (التأدب بأداب الإسلامية)

🔹ሰላምታን ማብዛት
🔹ያስነጠሰን ማስደሰት
🔹የተቸገረን መርዳት
🔹የአበላል ስነስርአት
🔹የታመመን መጠየቅ
🔹የቤትና የመስጅድ አደቦችና ሌሎችም ተወስቶበታል

《ክፍል 2⃣0⃣

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ

📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች

📌(ከሽርክና ሌላ ወንጀሎች መጠንቀቅ)
📌 (التحذير من الشرك وأنواع المعاصي)

🔹ሽርክ 🔹የየቲም ገንዘብ መብላት
🔹ሀሜት 🔹ሰውን ዝሙተኛ ማለት
🔹ሲህር 🔹ዝምድናን መቁረጥ
🔹ወለድ 🔹ሰዎችን መበደል
♻️የትልቁና የትልቁ ወንጀሎች ልዩነት


《ክፍል 2⃣1⃣

🎙አቡ አብደሏህ


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
خذ_عقيدتك_من_الكتاب_والسنة_እምነትህን_ከቁርዓን_እና_ከትክክለኛ_ሀዲስ_ያዝ_v1_89_mod.apk
88.1 MB
የኹዝ አቂደተከ ሚነል ኪታቢ ወሱና ሶሂሀ ሙሉ ቂርአት ያለኔት


📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
🎙በአቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
🔹🔹

💢በአቂዳና በተውሂድ ጉዳይ ወሳኝ ቂርአት ስለሆነ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ይድርጉት

الدال على الخير كفاعله

t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1696
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1696
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ

📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች


ሙታንን ማዘጋጀት መስገድና መቅረብ
تجهيز الميت والصلاة عليه ودفنه

🔹አንድ ሰው ሲሞት የሚደረግ ጥንቃቄ
🔹ለሞት የቀረበ ሰው ተልቂን ማስደረግ

♻️ሞትና ለሞት መዘጋጀት በሚል ርእስ አጭር ምክር

《ክፍል 2⃣2⃣

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
‏طوبى لمن خرج من الدنيا وليس لأحد عليه حق.

لفضيلة الشيخ: فلاح مندكار -رحمه الله
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦

“ሲያነጋ በእኔ ላይ አስር ጊዜ ሰላዋት ያወረደ፤ ሲያመሽም አስር ጊዜ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የቂያማ (ትንሳኤ) ቀን ምልጃዬ (ሸፈዓዬ) ታገኘዋለች።”

📚 ጦብራኒ ዘግውታል አልባኒ ተርጊብ ወተርሂብ (1/273) ላይ ሶሂህ ብለውታል።
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
🔁 سورة الكهف 🔁
🔺ማራኪ የሱረቱል ከህፍ ቂርአት
🎙القارئ محمد صديق المنشاوي
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#ራሳችንን_እንፈትሽ
#ሙእሚን_ነን_ወይስ_ሙናፊቅ!!?
------------------------------------------
=}>ራስህን ሙእሚን ነኝ ወይስ ሙናፊቅ ነኝ ብለህ መጠየቅ ከፈለክ; «ሰላቴን ወቅቱን ጠብቄ እየሰገድኩኝ ነኝ ወይ?» ብለህ ጠይቅ። በተለይ ደግሞ «የሱብሂ» ሰላት።
ስርዓቷን ጠብቀው ከሚሰግዷት ቤተሰቦቿ ከሆንክ፦ አብሽር አንተ ሙእሚን ነህ። በአንተና በጀነት መሃል መሞትህን እንጂ ሌላ የለም!!

=}> የሱብሂ ሰላትህን ያበላሸሃት ከሆንክ ግን; በፍጥነት ነፍስህን አድናት።
ምክንያቱም የሱብሂ ሰላትን ማበላሸት ከንፍቅና ምልክቶች ነው [በአላህ እንጠበቃለን።]!!

-----ከሀዲያኖች የውጭ ጠላት ሲኾኑ; ሙናፊቆች ግን ድብቅና ውስጣዊ ጠላቶች ናቸው። እነርሱም አደጋቸው የከፋና ጉዳታቸውም የበረታ ናቸው። ምክንያቱም ከሙስሊሞች ጋ ተቀላቅለው ሁኔታቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉ።
[ابن عثيمين رحمه الله تعالى]
شرح الممتع 27/2
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

👑ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
አዲስ ሙሓደ

ላ ኢላሀ ኢለሏህ لَاإِلَهَ إِلَّا الَّٰله

🔸የ ላዒላሓ ኢለሏህ ትርጉም
🔸የ ላዒላሓ ኢለሏህ መስፈርቶች
🔸የ ላዒላሓ ኢለሏህ አፍራሾች


ቦረና 014 ቀበሌ ደገር

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/2108
t.me/abu_reyyis_arreyyis/2108
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ

📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች

📌(የሙታን አስተጣጠብና አከፋፈን ሁኔታ)
📌 (صفة غسل الميت وتكفينه)

🔹ሙታንን እንዴት ማጠብ እንዳለብን
🔹የወንድና የሴት የአከፋፈን ሁኔታ
🔹የህፃን ልጅ አከፋፈን ሁኔታ

ክፍል 2⃣3⃣

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ



https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
«⇘የወንዶች ልብ ውስጥ ተቅዋ የሞተ ጊዜ የሴቶችም ሃያእ ያኔ ይጠፋል»‼️

⇘አባት ልጁን ካላደበ፣ወንድም እህቱን ካልመከረ፣ባል ሚስቱን ካልተቆጣጠር ይሄኔ ነው መጥፋቱ

⇘``የሷብቻ መታገል፣ሃያእ ለማድረግ መፈለጓ፣ በሂጃብ መሸፈኗ፣ ጌታዋን ለመፍራት መጣጣሯ መች ከምትፈልገው ያደርሳትና

⇘በአከባቢዋ ያሉ ወንዶች ካልተስተካከሉ ብቻዋን ብትጥር በተኩላዎች መነከሷ እንዴት ይቀርና

⇘ሸይኽ አብድረዛቅ አልበድር {ሃፊዘሁላህ} እንዲህ ይላሉ፦

⇘ሰንትና ስንት መልካም ሴቶች በመጥፎ ወንዶች ተበላሹ

⇘ስንት ሴቶች ሙኡሚኖች፣ መልካሞች፣ የተሸፈኑ፣ የተከበሩ፣ በትቅዋና፣በኢማን፣በጥሩነት መካከል መልካምነትን የፈለጉ

⇘ተኩላዎች ይገጥሟቸዋል ከተኩሎች የሆኑ ያበላሿቸዋል በምላሳቸው፣ በሰልክ መስመሮች በተለያዩ ኢንተርኔቶች፣ፈታኝ በሆኑ ንግግሮች፣ በተለያዩ አነጋገሮች ያበላሿቸዋል ክብሯቸውንና ብልጭነታቸው ይነፍጓቸዋል።
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሐቅን መደበቅ ከባድ አደጋ አለው!!

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

إِنَّ الَّذِينَ يَكْتُمُونَ مَا أَنزَلْنَا مِنَ الْبَيِّنَاتِ وَالْهُدَىٰ مِن بَعْدِ مَا بَيَّنَّاهُ لِلنَّاسِ فِي الْكِتَابِ ۙ أُولَٰئِكَ يَلْعَنُهُمُ اللَّهُ وَيَلْعَنُهُمُ اللَّاعِنُونَ

«እነዚያ ከአንቀፆችና ከቅን መምሪያ ያወረድነውን ለሰዎች በመጽሐፉ ከገለጽነው በኋላ የሚደብቁ፤ እነዚያ አላህ ይረግማቸዋል፤ ረጋሚዎችም ሁሉ ይረግሟቸዋል፡፡»
አል-በቀረህ 159

ሸይኽ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ) ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል:- “ይህ ጉዳይ በቢድዐ ሰዎች ላይ ብቻ የሚገደብ አይደለም፣ ይልቅ ስለ ቢድዐና ስለ ቢድዐ ሰዎች ዝም ያለንም ሰው በውግዘትና በቅጣት ያካተዋል። ምክንያቱም ግዴታው ለሰዎች የቢድዐንና የቢድዐ ሰዎችን አደጋ ግልፅ ማድረግና ማብራራት ነው። ይህ በጥፋት ሰዎች ላይ በእውቀት የተመሰረተን መልስ የመስጠቱ ስራ በዚህን ጊዜ በኢስላማዊ ቤተ-መፅሃፍቶች (በመፅሃፍ ደረጃ) በርክቶ ይታያል፣ ሁሉም ለቀጥተኛው መንገድ የሚከላከሉ ናቸው። በዲን ላይ "የአስተሳሰብ ነፃነት፣ የመናገር ነፃነት" ብለው ከሚያራግቡት ያስጠነቅቃሉ። ይህን አስተሳሰብ የሚያራግብ የለም ሀቅ የሚደብቅ ጠማማ ካልሆነ በስተቀር!።

እኛ በመናገራችን ሀቅን ፈልገንበት ነው እንጂ ሰዎችን ያለ አግባብ መተቸትና መናገር ፈልገንበት አይደለም!። ፍላጎታችን ሀቅን ግልፅ ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ አላህ ዑለማዎችን ያሸከማቸው የሆነ አማና ነው!። ከጥፋት ሰዎች ዝም ማለት አይፈቀድም!። ነገር ግን እጅግ በጣም ከሚያሳዝነው ነገር፣ እውቀት ያለው ሰው ተነስቶ በሚያጠፉ ሰዎች ላይ መልስ መስጠት ሲጀምር "ይህ ይቸኩላል…" እና ሌሎችንም መሰል ሰዎችን በሚረብሹባቸው ቃላት ይናገሩታል። ይህ የእውቀት ባለ ቤቶችን የጥመት ሰባኪያንን ተንኮል ግልፅ ከማድረግ ፈፅሞ ሊያግዳቸው አይገባም!።”
[ኢትሃፉል ቃሪ ሸርህ አስ-ሱና በርበሃሪ 1/48]

ይህ ሸይኹ የጠቀሱት በአጥፊዎች ላይ ምላሽ በሚሰጡ ዓሊሞች የተለያዩ ቃላቶችን መርጦ የመወረፉ እውነታ ዛሬ ላይ በሀገራችንም በሁለቱ ጆሯችን የምንሰማው ተጨባጭ ነው!!።

✍🏻 ኢብን ሽፋ: ረጀብ 11/1442 ዓ.ሂ