💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
اسمــ؏ وتدبــر : وَلِمــَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّـہِ جَنَّتَانِ _ فَبــِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَــا تُكَذِّبَانِ _ ذَوَاتَا أَفْنـانٍ ...
➧አመስጋኝ ሚስት ሁኚ !!

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:-(
ባሏ በተቸረው) ባለመብቃቃት ባሏን የማታመሰግንን ሴት አላህ ወደ እርሷ (በእዝነት አይኑ) አያይም።

((አልባኒ በተርጚቡ ሰሂህ ቁ(1944) ሰሂህ ብለውታል))።
➭ደሀ ማለት ገንዘብ የሌለው ሳይሆን አደብ የሌለው ነው!
➛አንተም
         ➛አንችም


✍️አንተም
ላጤው ቶሎ አግባና ቅመሰው ያን ሀሴት፡
አልያ ግን ፀጥ በል አታውራ ስለ ሴት፡
✍️አንችም
ክብርሽን ጠብቂ ሀላሉን ድፈሪው፡
ፊትና እንዳይፈጠር በሚድያ አታውሪው፡
✍️አንተም
ሴትን ልጂ አታማር መርጊያህ ነችና እርሷ፡
ላንተ ክብር ሲባል ሀላል ሆኗል ነፍሷ፡
✍️አንችም
በየደረሽበት ወንድን አታብጠልጥይ፡
ሀሜቱን ተይና በሀላሉ ቀጥይ፡
✍️አንተም
ቢጤህን ካገኘህ በል ወስንና አግባ፡
ብቅ ጥልቅ እያልክ ሰው ግራ አታጋባ፡
✍️አንችም
የሌለሽን ውበት ተኳኩለሽ ወጥተሽ፡
የማይሆን አትስሪ በሽቶ ተሻተሽ፡
✍️አንተም
ይችንም ያችንም ተው ግራ አታጋባ፡
አንዷን ፅደቅባት በል ወስነህ አግባ፡
✍️አንችም
ክብርሽን ጠብቂ ታማኝ ሁኝ ላመነሽ፡
ሽማግሌ ልኮ ወዶ ለለመነሽ፡
✍️አንተም
የሁሉን ሴት ስም አታጥፋ፡
ሚስጥርክን አታውጣ ይፋ፡
ሰው ሁኖ ፍፁም የለም፡
ሁሉም ሴት መጥፎ አይደለም፡
✍️አንችም
የሴትነት ክብር ይኑርሽ፡
ወንዱ ሁሉ እንዳከብርሽ፡
ስርዐት አትለፊ፡
ወንድን ሁሉ አትበይ ቀጣፊ፡
ቁጥብ ሁኝ አደብ ይኑርሽ፡
ሁሉም ወንድ እንድፈልግሽ፡
✍️ሁላችንም

እንድንወጋገዝ አይደለም ኢስላም የሚያስተምረን፡
አመስግነን እንቀበል ጥፋታችን ከተነገረን፡
ይቅር አይጠቅምም ለኛ በፆታ መወጋገዙ፡
ሙስሊሞች ሆነን ሲያበቃ በሆድ ቂም አታርግዙ፡

በማህበራዊ ሚዲያ የነውር ወሬ አትበትኑ፡
ፍላጎታችሁ ላይሞላ የጠላት መሣቂያ አትሁኑ፡
ሁላችንም እናጠፋለን በቃ በዚህ እንስማማ፡
ወንዱ ሴትን አያውግዝ ሴቱም ወንዱን አይማ፡
ጥፋት እንፈፅማለን ከስህተት የሚያገል የለም፡
የሰውነት መገለጫ ነው ማንም ፍፁም አይደለም፡

ሴቷ ወንዱን አትፈትኝ ወንዱም ሴቷን አትንካ፡
ፍላጎት ካደረብህ ወስነህ ያዛት በኒካ፡
ከዚህ ውጭ ያለው ቅርርብ የለውምና በረካ፡


ለማንም ለምንም ቢሆን ሚስጥርሽን አትናገሪ፡
መቻልን ልማድ አድርጊ ታገሽ ፊትና አትፍጠሪ
፡

አንተም ክብርህን ጠብቅ በቃ ሀሌ አትልከስከስ፡
አንዴ ስህተት ከሰራህ ወስን ላለመመለስ፡


እባካችሁ እንንቃ አንነቋቆር  በፆታ ፡
ሁሌ ነገር አትስሩ በጧት ሆነ በማታ፡
እየተመለከተን ነው ሀያሉ የአለም ጌታ፡


✍️በኑረዲን_አል_አረቢ


https://t.me/nuredinal_arebi
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
➧እኔ የምወደው
〰️〰️〰️〰️〰️〰️

እኔ የምወደው የምሳሳለት
ጥሩ ፍቅር የለው ስለዲን እውቀት
መማር የማይሳለች ምንም እመይታክት
ይለፋል ይደክማል ሁል ጊዜ ይማራል
ባወቀው ለመስረት በጣሙን ይጥራል
ብዙ ከመናገር መስራትን ይመርጣል
አይቀርም በፍጹም ውጤቱን ያገኛል

እኔ የምወደው ሁሌ የማስበው እስላምን በቅጡ የተገነዘበው
ኢማንን ለማግኘት ሁሌ የምጥረው
እንዲህ አይነቱ ነው እኔ የምወደው
ፍፁም በቃኝ ሳይል ምንም ሳያሰልስ


የትውስት ነፍሱን ለጌታው እስኪመልስ
ይለፋል ይደክማል በጣሙን ይጥራል


አላህን በመፍራት እጅግ ይታገላል
ከእሳት ለማምለጥ ሁል ግዜ ይለፋል
ለጀነት አገሩ ስንቅን ያዘጋጃል

እኔ  የምወደው ሁሌ የማከብረው
የሙእሚኖች ወንድም የሙእሚን መሪ ነው
አላህ የሰራውን ተፈጥሮ የሚያደንቅ
በራሱ የማይኮራ እማይመፀደቅ

<ሀዛ ኸልቁሏህ >>ብሎ የሚደነቅ
በአለማዊ ነገር ልቡ ያልቀለጠ
ለጠፊዋ አለም ያልተቅበጠበጠ


እኔ የምወደው ልቤ የሚያስበው
ለሙእሚኖች ወንድም መሆን የሚችለው
አንድነት በፅኑ የሚያሳስበው
ፈጥኖ የማይጓዝ ቀስ ብሎ ሚያስብ
በብልጭልጭ ነገር ከቶ እማይሳብ
በትግስት በሰብር ኢማንን ተላብሶ
ሐቅን ያገኛታል ሁሉንም ደርምሶ
ቢድዐን አይሰራ ሁሉንም አግበስብሶ
ሱናን ለመተግበር ሁሉንም አዳርሶ
ሁሌም የሚጥር ነው መልሶ መላልሶ
የአሏህን ስራ ተፈጥሮን አፍቃሪ
ትንሽ ትልቅ ሳይል ሁሉንም አክባሪ


እኔ ምናፍቀው ዱንያ ወል አኼራ
<<በላኢላሃ ኢለላህ>> ልቡ የሚያበራ
ሶላቱን ይሰግዳል ከጀመዓ ጋራ
ለአንድ ጌታው ፍቅሩ የተጣራ
የዱንያ ላይ ጀግና የጀነት ሙሹራ
ሁሌም የማይጠፋው ከአሊሞች ጎራ ዘወትር የሚገልፅ ፍቅሩን በኢባዳ መሆኑ የገባው ለዱኒያ እንግዳ


እኔ  የምወደው ዘወትር እማከብረው
<ላቱሽሪኩ ቢላህ> በልቡ ያለን ነው
የእስልምና ፍቅር በህሊናው ሰርፆ
በአምላኩ ፍቅር ልቦናው ታንፆ
ለመኖር ይጥራል ህይወቱን አድሶ
የቤተሰቡን ሀቅ ለመሙላት የሚጥር
በበላይነቱ ምንም የማይፎክር
ስለዲን ጉደይ ሁሌ የሚያስተምር
ስስት ብሎ ነገር ምንም ያልነካካው
የሱ መታወቂያ መለገስ መስጠት ነው


ሁሌ ትዝ የሚለኝ የሚወደው ልቤ
ምንም የማልረሳው የሚያልመው ቀልቤ


በቃ እሱን ነው እሱን ነው ሁሌ እማልመው
ያንን የአላህ ሰው
እንደዚህ አይነቱ ከመጣማ
በፍፁም አልመልሰውም


@رحيمة ا/دغا

✍️ከላጤዎች ሰፈር የተገኘ¡
⇛«እኔ ነኝ ከሁሉ የተጎዳሁት፤ የኔ ይብሳል!» ብንልም በጥልቀት ሲታይ ግን ሁላችንም ተመሳሳይ ነን፣ሁላችንም የጎደለን ነን፣
ሁላችንም የተጎዳን ነን፣ጤና ያለው ገንዘብ የሌለው፣ ገንዘብ ያለው ጤና የሌለው፣ትዳር ያለው ልጅ የሌለው፣ ልጅ ያለው አስተዋሽ የሌለው ፣ወላጅ ያለው ተንከባካቢ የሌለው ፣
በዚህ መልኩ ጉድልድል ያልን ነን።

☞የሞላለት ማንም የለም። ስለ ሁሉም የአላህ ክፍፍል ማመስገን አለብን። ብናመሰግን የሚጨመርልን እንጁ የሚቀነስብን ነገር የለም።
~አልሐምዱ ሊላህ~
t.me/AbuSufiyan_Albenan
Audio
☑️ አዲስ ለወጣቶች ምክር

👉ሞክሮ ያየው ሰው ምክር!!

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
አሁን ወቅት እራስሺን አጠንክረሺ መጠንከር የሚያዋጣሺ እከሌ ያግዘኛል ብለሺ አትንጠልጠይ በራስሽ ቀጥ ብለሺ በጌታሺ ታግዘሺ የያዝሺዉ አላማ ግብ ምቺ!

✍️
ሙሓደራ_ሺርክ
አቡ ረይስ ኢብኑ ኢማም
"አዲስ ~ሙሓደራ"
〰️〰️〰️〰️〰️〰️

👉ሺርክ…

➛018 ቀበሌ አምባገር ወረባቦ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/7019
t.me/abu_reyyis_arreyyis/7019
➧ከስደት መልስ የእህቶች ደስታ እንደማየት የሚያስደስት የለም እዚህ አብረን ስንኖር የነበረች እህቴ ሀገር ገብታ አላህ መንታ ልጆች ሰጥቶ ልቧ በደስታ ሞላዉ አልሀምዱሊላህ!!

➛ለሁላችንም መንታ መንታዉ ይወፍቀን ከስደት መልስ የስደት ኑሮ በቃ ብሎ በሀገራችን ሪዝቃችን ይክፈትልን ያረብ!



✍️
የሌላን ሰዉ  ሕይወት በፍፁም አትኑሪ
የራስሺ ሕይወት ብቻ ኑሪ  የራስሺ አላማ እና ራእይ ብቻ ተከተይ!!


✍️
☞በነገራችን ላይ…«ለሰዎች ፊት አትስጥ ትናቃለህ!»የሚለው የቂሎች አባባል እንደሆነ ጠንቅቄ አምናለሁ! ይልቁንስ ሰው ስታከብረው ያከብርሃል፣ፊት ስትነሳውም ይነሰሃል። ኮስታራ ስለሆንክ የምትከበር፣በጣም ዝምተኛ ስለሆንክ የምትሰማ የሚመስልህ ከሆነ ተሳስተሃል!
⇛ኡስታዙም ሆነ አስተማሪው ከ ተማሪዎቹ ጋር ቆፍጣና፣ዝምተኛ ስለሆነ አይከበርም። ይልቁንስ ተማሪዎች እንድሸሹትና መጠየቅ የሚፈልጉትን ጥያቄ እንዳይጠይቁት ማሳቀቅና ማጨናነቅ ነው ብየ አምናለሁ።እና ሁሉንም በልኩ እንያዘው ለማለት ነው¡)

t.me/AbuSufiyan_Albenan
𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
☞በነገራችን ላይ…«ለሰዎች ፊት አትስጥ ትናቃለህ!»የሚለው የቂሎች አባባል እንደሆነ ጠንቅቄ አምናለሁ! ይልቁንስ ሰው ስታከብረው ያከብርሃል፣ፊት ስትነሳውም ይነሰሃል። ኮስታራ ስለሆንክ የምትከበር፣በጣም ዝምተኛ ስለሆንክ የምትሰማ የሚመስልህ ከሆነ ተሳስተሃል! ⇛ኡስታዙም ሆነ አስተማሪው ከ ተማሪዎቹ ጋር ቆፍጣና፣ዝምተኛ ስለሆነ አይከበርም። ይልቁንስ ተማሪዎች እንድሸሹትና መጠየቅ የሚፈልጉትን ጥያቄ እንዳይጠይቁት…
ሀቂቃ ልክ ብለሀል ሰዉ አንተ እንዳደረከዉ ነዉ የሚሆን ስለዚህ ኮሽተር የሚባልበት ኮሽተር ሳቅ የሚባልበት ሳቅ ዝም የሚባልበት ዝም የሚወራበት ማዉራት ሁሉን ድንበር ባላለፈ መልኩ ብናደርገዉ መልካም ነዉ እላለሁ እንደኔ!!

✍️
አላማ ይኑርሽ አላማ ካለሽ
የብዙዎች ምኞት ትሆኛለሽ!
አትቸኩይ ትደርሻለሽ.........!

✍️
➲ምክር ለእህቶች !!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️

🖋𝑨𝒃𝒅𝒖𝒔𝒆𝒍𝒂𝒎

➲ፌስ ቡክ ላይ የማይለፈለፈውን ትለፈልፉና የማይፓሰተውን ትፓስቱና ሴትን የማይመጥናት ወይም ባለጌዎችን ወደ እናንተው የሚስብ ነገር እየሰራችሁ ። ቆየት ብላችሁ እባካችሁ ወንዶች አላህ ፍሩ በውስጥ መሾመር አትምጡብን  የምትሉ ሴቶች ጤነኛ ናችሁ?  ለምን እናንተ አላህን አትፈሩም? ለምን አደብ አይኖራችሁም? ሲጀመር እራሳችሁ እራሳችሁን ለፊትና እየዳረጋችሁ ከዛ ኡኡኡ ትላላችሁ አጂብ ። በር ክፍት ከሆነ እብድ መግባቱ አይቀሬ ነው"! ነገር ግን በሩ በዝጊያና የተከበረ ከሆነ ማንም አይቀርበውም ። የእናንተም እደዙሁ በሚዲያ ላይ አደብ ካላችሁ ማንም በውስጥ አያጨናንቃችሁም ። ደግሞ ለባለጌዎች ብዙ መፍትሄ አለ። ብሎክ ማድረግ አለ ማዋራት ። ግን የእናንተ ፌቢ ላይ መጮህ የሴት ልጅ ተግባር አይደለም""!!

➧ሒጃብ አካልን እንደሚሰትር ሁሉ መልካም ተግባርና አደብ ማንነትን ያስከብራል"! ሒጃባችን ከብዙ ነገር ይጠብቀናል ፣ ብዙ ሰላምንም ያጎናፅፈናል ። አምላካችን አላህ ሒጃብን  ከባለጌዎች እንደምንሰተርበትም ይነግረናል ። ባለጌዎች ሙሉ አካሏን ሸፍና የምትሄደውን ሴት ፈፅሞ አይቀርቧትም  ። እንዲያውም ለእርሷ መንገድ ይለቃሉ ። ትከበራለች ።

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

[ ሱረቱ አል- አሕዛብ - 59 ]
አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

👉ሱብሃን አላህ ። ሒጃብ አካላችንን እንደምናስከብርበት ሁሉ መልካም አኽላቅ ( አደብ) ማንነታችንን ያስከብራል ። ሀያዕ ከሌለውን ደግሞ አደብም አይኖረንም "! 

አሏህ ከአደበኞች ያድርገ!!

➛ኮፒ ከዚሁ ሰፈር የተገኘ!
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ምክር ለእህቶች !! 〰️〰️〰️〰️〰️〰️ 🖋𝑨𝒃𝒅𝒖𝒔𝒆𝒍𝒂𝒎 ➲ፌስ ቡክ ላይ የማይለፈለፈውን ትለፈልፉና የማይፓሰተውን ትፓስቱና ሴትን የማይመጥናት ወይም ባለጌዎችን ወደ እናንተው የሚስብ ነገር እየሰራችሁ ። ቆየት ብላችሁ እባካችሁ ወንዶች አላህ ፍሩ በውስጥ መሾመር አትምጡብን  የምትሉ ሴቶች ጤነኛ ናችሁ?  ለምን እናንተ አላህን አትፈሩም? ለምን አደብ አይኖራችሁም? ሲጀመር እራሳችሁ እራሳችሁን ለፊትና…
ተመከሩበት ሀቂቃ fb ተጠቃሚዎች
እኔ እሱ ሰፈር ከለቀቅኩ ቆይቻለሁ ወደዛም አልመለስ ቴሌግራምዬ ትኑር በቂዬ ናት!

በቴሌግራም ራሱ የምንለቀዉ ነገር ልብ እያልን ከፕሮፍይላችን ጭምር በደንብ ትኩረት ሰጥተን እንጠቀም!!እኛ ራሳችን ከጠበቅን ማንም አይነካን!!

✍️