💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ለባል ፊት አትስጡ ይላሉ አሉኮ¡ ደሞ
ታድያ ጀርባዉን ሰጥቶሺ ፊት የምሰጠዉ ጋር ይሄድልሻላ¡¡ ማ የሚጎዳ!?

ተዉጂ ጎበዝ እየተዛዘንን እ¡
ምክርም ከሆነ የሚጠቅም ምክሩ ዝም ብላችሁ አትቀባጥሩ ጥሩ አይደለም!!

✍️
⭕️👉ለኒቃብ ለባሾች……

ኒቃብ ለብሳ ሁለት አይኗን ከገለጠችው ይልቅ አንድ አይን ብቻ የምትገልጠው ትሻላለች። አንድ አይኗ ከገለጠችው ይልቅ ሁለቱም አይኗ የሸፈነችው ትሻላለች። ምክንያቱም የበለጠ አስተር ስለሆነ። አንዳንድ እህቶች አይን በመክፈት ሰበብ ቅንድባቸው፣ የጉንጫቸው የተወሰነ ክፍል፣ ከአፍንጫቸው በኩል ዝቅ ብሎ ከጎን በኩል ደግሞ ከአይናቸው አልፎ የፊታቸው ግማሽ አልያም ሩቡን የሚያሳዩ አሉ። አንዳንዶች አይናቸው ኩል ቀብተው ሁለት አይናቸው በማስዋብ ፊቷ ሙሉ ለሙሉ ከገለጠችው በላይ የሚፈትኑ አሉ። ሁለቱም አይን መሸፈን በላጭ ከመሆኑ ጋር መስፈርቱ በጠበቀ መልኩ አይኗን መግለጥ ከፈለገች ኩል ሳትቀባና ምንም አይነት ውበት ሳይኖረው መሆን አለበት። ነገሩ እጅግ ጥንቃቄ ይፈልጋል። ሙሉ አካላችሁን ሰትሩ። አይናችሁም እንደዚሁ። ሸፍናችሁ ማየት እየቻላችሁ አይናችሁ አትግለጡ። አንዳንዶች ፊት ላይ ጣል የሚደረግ ትንሽዬ ኒቃብ መሳይ ነገር በማሰር ጎምበስ ቢሉ ጉንጫቸው ሁሉ ይታያል። ትንሽዬ ንፋስ ወይም የራሷ ትንፋሽ አወዛውዞ ይገልጠዋል። በኒቃብ ዙሪያ ተሳሁል ወይም መዘናጋት አያስፈልግም። በኒቃብ ላይ የሚታይ ትንሽ ክፍተት እየሰፋ ኒቃቡን እስከማውለቅ ያደርሳል። ክብራችሁ ኒቃባችሁ ስር ነውና እጅግ ልትሳሱለት ይገባል። በኒቃብሽ ስር የተደበቅሽ አልማዝ ሁኚ።

ሸሪአዊ መስፈርቱን ያሟላ ኒቃብ ለሚለብሱ እህቶቻችን አላህ ይጠብቃቸው። ከተኮለኞች ሴራ አላህ ያርቃቸው። አብሽሩ በኒቃብ ላይ ፅኑ። ዛሬ በኒቃባችሁ ሰበብ የሚደርስባችሁ ችግርና አዛ ነገ አላህ ፊት ትልቅ ምንዳ ሆኖ ነው የምታገኙት።

   ➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
✍️ኸይር ኸይሩ አሠማን በኸይሩ ላይ አጠንክረን!
Forwarded from قَنَاةُ:أبِي رَسْلَانِ السَلَفي (أبو رسلان إدريس السلفي)
እውቀትን አሏህ ዘንድ ሰላምን ታገኝ ዘንድ አስበህ ተማር እውቀትን ስትፈልግ ለክብር፣ለስልጣን፣ለልቅናም ሆነ ለምስክር ወረቀት ብለህ አትማር።
ምክንያቱም ባንተ ላይ የሚፈራው በጅህልናህ/ባለማወቅህ እንዳትጠፋ ነው እንጅማ ዲኑ አሏህ እሱን በመጠበቅ ላይ ዋስትናውን ወስዷል።።።።ባንተ ወይም በሌላ ሰው ይረዳል ዲኑ

#الشيخ صالح العصيمي حفظه الله

قَنَاةُ:أبِي رَسْلَانْ السَلَفي
رحم الله عبدا قال بالحق، واتبع الأثر، وتمسك بالسنة، واقتدى بالصالحين



https://t.me/abuhamudasselefy/1769
Audio
"ጣፍጭ  ቲላዋ ተጋበዙ"

➧ከቁርአን ጋር እንኑር!

ደግ አደራችሁ...........☕️
ያ ረብ!
⇛የኔ ባልኾነ ነገር ላይ ልቤን አታንጠልጥልብኝ፣ዓይኔም የኔ ያልኾነን አይከጅል፣በማላገኘው ነገር ላይ ሀሳቤ አይበታተን።


ኮፒ ... ከአቡ ሱፍያን
አባት የመጀመርያም የመጨረሻም የሆነ ብቸኛ ልጁን ሊድር ድል ያለ ሰርግ ደግሶ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቹን ጠርቶ የምሳ ግብዣውን እየተዟዟረ ይመለከታል።

‹‹ማን ቀረ ማን መጣ›› የሚለውን በትኩረት እየተመለከተ ሳለ የቅርብ የግድግዳ ጎረቤቱን ከእይታው ያጣዋል። ግራ በመጋባት እየተዟዟረ ቢመለከትም ጎረቤቱንም ሆነ የጎረቤቱን ልጆች ሊያይ አልቻለም።

‹‹የልብ ወዳጄ በዛሬ ቀን እንዴት ከጎኔ ይጠፋል›› እያለ በንዴት ስሜት በመብሰልሰል ላይ ሳለ ድንገት የጎረቤቱ ልጅ ብቅ አለ ና በፍጥነት ትንሽ ምግብ ቀማምሶ ትቶ ወጣ።

ይህን ትዕይንት የተመለከተው ደጋሽ በንዴት ተብከነከነ። የአባቱ በደስታው ግዜ አለመገኘት ሳያንሰው ልጁ መጥቶ በምግቡ አላግጦ መውጣቱ አበሳጨው።

በዚህ መሀል የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ ሊጀምሩ መኪናቸውን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ ምግቡን ቀማምሶ በፍጥነት የወጣው የጎረቤቱ ልጅ ሙሽራውን ለማጀብ ከግቢ መኪናውን ይዞ ይወጣል።

አባት ተበሳጨ፣ ንዴቱን መቆጣጠር ቢያቅተው በቁጣ መንፈስ ተሞልቶ ወደ ጎረቤቱ ልጅ በመሄድ፦‹‹አባትህ ጎረቤቴ ሁኖ ደስታዬ ላይ አልተገኘም፣ ታላላቅ ወንድሞችህም እንደዝያው፤:ታድያ አንተ ምን አስበህ ነው በምግብ አላግጠህ ትተህ የወጣኸው? አሁን ተመለስ ያንተን አጃቢነት አንፈልግም›› ብሎ መለሰው። ልጁም እቤቱ ገባ፤ ሰርገኛዎችም ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት አቀኑ።

በመጨረሻም አጃቢዎች ሙሽሮችን ይዘው ወደ ቤት በመግባት የደስታቸው ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ቀኑ ሲጨልም ሁሉም ተበታትኖ ሰርግ ቤቱ በሙሽሪት እና በሙሽራው ጭር አለ።

አባት አሁንም በጎረቤቶቹ ንዴት እየተብሰለሰለ ነው። ድንገት ከመሸ ያለ ወትሮው የጎረቤቱ ጊቢ ተከፈተ። የሙሽራው አባት እየተመለከተ ነው።

የጎረቤቱ ልጆች በትከሻቸው አስክሬን ተሸክመው ከቤታቸው ሲወጡም ተመለከተ። ፍፁም ዝግታ እና እርጋታም በሚስተዋልበት እርምጃ ልጆቹም ይራመዱ ጀመር።

የሙሽራው አባት ጠጋ አለ። ፦‹‹ምንድነው? የማንን አስክሬን ነው የተሸከማችሁት ›› ሲልም ጠየቃቸው።

‹‹አባታችን ጠዋት ሙቶ ነው፤ ሲሞትም በሱ ለቅሶ ምክንያት ያንተ ደስታ እንዳይጓደል መሞቱን ከሰርግህ በፊት ለማንም እንዳንናገር እና ድምፅ አውጥተን እንዳናለቅስ ተናዞልን ነበር። ለዝያ ነው ድግሱ ላይ መገኘት ያልቻልነው። ›› በማለት ጀናዛ የተሸከሙ ልጆች ጉዳያቸውን አስረዱ።

ደጋሽ ተፀፀተ፦‹‹ወላሂ እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህን የማድረግ አቅም አይኖረኝም ነበር›› ሲልም የፀፀት እንባ ያነባ ጀመር።

በህይወታችን ችላ ያሉ እየመሰሉ በቁስላቸው ደስታችንን ላለማበላሸት ሲሉ ከአከባቢያችን የሚርቁ ሰዎችን አላህ ይዘንላቸው።
▼ በሆነ አጋጣሚ መምከር ያሰብኳችሁ የታናሻችሁ ምክር ቢጤ ነች!

= abu mahir al assery
=
Forwarded from 💎أُخْتِي عَيْشِي مَعَ الكِتٰابْ وَالسُّنَّة💎
📌 ሴቶችዬ ሰሞኑን ወንዶች ሸክዋ እያቀረቡ ነው አሉ ለምን በሉኝማ!

የአሁን ዘመን ሴቶች የምግብ ሞያ የላቸውም እያሉን ነው ውነትም የለንም እንዴ እንደሚሉት?

💦ለማንኛዉም ውዷ እህቴ ሞያ ሊኖርሽ ይገባል ሁሌም ጣፋጭና ግሩም የሆኑ ምግቦችን መስራት ልመጂ አስበሽ ይቺ ሞያላትም ስትባይ!

ደግሞ እኮ ወንዶችዬ ሆዳቸውን ይወዳሉ አሉ ወንዶች እየተሳደብኩኝ አደለም ይህ ነው ውነታው ሆዳቹ ሲጎል አትወዱም ።

ስለዚህ እህቴ ዲን እንደምትማሪው ሁሉ ከጐን መያንም ልመጂ በንፅህና እና በምግብ ሞያሽ የተመሰከረልሽ እንቁ እንስት ሁኝ እልሻለሁ ።
አላወራም ብዬ የተዉኩት እርዕስ ዛሬ ልታስወሩኝ ነዉ.......እ

1ዷ ሚስት እጃችሁ ሳታስገቡ ስለ 2ኛ 3ኛ 4ኛ የምዘምሩ ወንዶች ግን ጤናችሁ ያሰጋል!?

እረ ተዉ broዎች ቀስ እያላችሁ እደጉ እ!?

ካነሳሁ አይቀር ልጨምር 2 አግብተዉ ሁለቱም ሚስቶቻቸዉ ቤታቸዉ ቁጭ አድርገዉ የሚያኖሩ ጀግና እንዳሉ ሰማሁ እንደ እናንተ አይነቶቹ በሺ ይወለዱ አቦ¡¡

ግን አንድም ሳትይዙ ሌላ የምዘምሩ እባካችሁ ቀስ ብላችሁ እደጉ¡¡ አትረብሹ ¡¡


✍️
ክብር ! በዚህ ፍች በበዛበት ዘመን ጠንክረዉ እየሰሩ ሚስቶቻቸዉ በደንብ ተንከባክበዉ ለሚያኖሩ ጀግና ወንዶች!!

አንተ ጀግና ነህ ወንድሜ በርታልኝ
እነዚህ ህፃኖች ገና ሳይደርሱ በስመ ተዓዱድ ስም ሊያስጠፉ ቢፍጨረጨሩም አንተ በተግባር የያዝከዉ ወንድሜ በርታልኝ ክብር ይገባካል!!


✍️
በተደጋጋሚ ስትጠይቁ ለነበራችሁ!

ሁሉም መፅሀፎች ታትመው  በዑካዝ የቴሌግራም ግሩፕ እና በአል ተውባ መክተባ ይገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Awolseisd
0913604751

የቴሌግራም አድራሻችንን ተቀላቀሉ
https://t.me/Okazcom
🌸🍃

ما زادَك مثلُ زادِك، وأعظمه: التَّقوى،،
قال الله تعالى:

﴿وَتَزَوَّدُوا۟ فَإِنَّ خَیۡرَ ٱلزَّادِ ٱلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُونِ یَـٰۤأُو۟لِی ٱلۡأَلۡبَـٰبِ﴾

📓 الشيخ صالح العصيمي حفظه الله
ስራ እየሰራች ቁርአን መስማት ሙሐደራ መስማት ኹጥባ መስማት የኪታብ ደርስ መስማት የለመዴች ነፍስ ያ ሲቀርባት ወደ መጃጃል መሳነፍ ትሄዳለች ያ ሱብሃን አላህ!

ከራሴ ተሞክሮ ነዉ ገርሞኝ ሰሞን ኤርፎኔ ተበላሽቶ ስራ ስጨርስጂ ስራ ላይ ለመስማት አልችልም ነበር ያች ደካማ ነፍሴ ግን የለመደችዉ ሲቀር ወደ..............¡

👉🎧👈አልበረክት ያለን ቢኖር ስደት ይሄ ነዉ እዳ ፍብሪካዉ ራሱ ለ3ቀን የሚሰራ ልበል እ!?

👉እናም የለመድነዉ እንዳይቋረጥ ሳይበላሽ ቶሎ ቶሎ እየገዛን እናስቀምጥ እላችሁ አለሁ¡

አላህ ሆይ ነፍሳችን በመልካም ላይ ጥመድልን!ከመራሀት ቡኋላ አታዘንብልብን!ቀጥ አድርገን በትዕዛዝህ ላይ!አንተ እስከምንገናኝ!!

✍️