💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
فتن ة النساء 🎊
➲የሴቶች ፊትና

🍃للشيخ صالح الفوزان حفظه الله

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
""ፈልጓት እህቴን""
በብዙወች መሀል ለአይን የተጋርደች
ፌትናንም በመፍራት ጥግ የተደበቀች
እራሷን በሀያእ በተቅዋ አብዝታ ያነፀች
ተዉሂድን ለማንገስ ቀጥ ብላ የቆመች

ሁለገብነትን ያልተዳፈርች
ከወሬ ዛዛታ አብዝታ የራቀች
ሸሪዓ በሚያዘዉ ቀጥ ብላ የሄደች
በጥብቅ ፈልጓት ታስፈልገናለች

Copy
✅🔺የትእግስት ደረጃዎች 🔺✅

♻️➰وللإنسان عند المصائب أربع مقامات:
♻️➰የሰው ልጅ ሙሲባ በሚደርስበት ጊዜ አራት ሁኔታዎች አሉት
1⃣ "جزع"؛ وهو حرام.
🔺#መበሳጨት፦ ይህ #ሀራም (ክልክል) ነው
2⃣ "صبر"؛ وهو واجب.
🔺#መታገስ፦ ይህ ደሞ #ግዴታ ነው
3⃣ "رضا"؛ مستحب.
🔺#ወዶ_መቀበል፦ ይህ ደሞ #የተወደደ ነው
4⃣ "شكر"؛ وهو أحسن وأطيب.
🔺#ማመስገን፦ ይህ ግን ከሌላው #የተሻለና_ያማረ ነው

📚 قول المفيد شرح كتاب التوحيد (٦٥١)

✅🔻 ትእግስተኝነትህና በቀደር ያለህ እምነት የሚለካው ሙሲባ (ፈተና) በሚደርስብህ ሰአት ነውና በደረሰብህ ነገር አላህን የማመስገንና ወዶ የመቀበል ደረጃ ላይ እንኳ ባትደርስ ሶብር ማድረግን ግን ሊያቅትህ አይገባም። የደረሰብህ አደጋ (ሙሲባ) ምንም ይሁን ምንም ከመበሳጨትና የሶብር ተቃራኒ የሆነን ተግባር ከመፈፀም ግን በእጅጉ ልትርቅ ይገባል። ምክንያቱም ይህ ተግባርህ በቀደር ላይ ያለህን እምነት ሙሉ ለሙሉ ሊያስወግድብህ ወይም ሊያዳክምብህ ይችላልና ተጠንቀቅ።

✍ኢብኑ ኸይሩ
〖حكم ما يسمى #بالطبق_الخيري〗

❍لفضيلة الشيخ /صالح بن فوزان بن عبد الله الفوزان - وفقه الله -

السُّـــ↶ــؤَال :

● أحسن الله إليكم صاحب الفضيلة، يقول: ما حكم الطبق الخيري الذي تقوم به جمعية تحفيظ القرآن بقصد جمع التبرعات؟

الجَــ↶ـــوَابُ :

● هذا من العبث لأنه تلاعب بالأموال الذي يريد الخير يتصدق بدون طبق أو بدون هذا الإجراءات الملتوية الصعبة الذي يريد الخير الباب مفتوح ليتصدق بما فيه خير للمحتاجين بدون طبق خيري أو طبق شهري ما أدري كيف هذه كله من اللعب والعبث نعم وإضاعة الوقت نعم .

🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸


📌الــمَصْـدَر مِـنْ هُنـ↶ـا

📥🔊http://www.alfawzan.af.org.sa/sites/default/files/3085.mp3

https://t.me/g4448
➲ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሀንበል (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ እኔም ዝም ካልኩ አንተም ዝም ካልክ አላዋቂው ማህበረሰብ እንደት መጥፎውን ከጡሩው መለየት ይችላል?!
مجمو؏ الفتاوى [231/28
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Photo
➲አግብታ የፈታች አልያም ባል የሞተባት ሴት ክብር!
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅

☞አላህን እንፍራ!
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅

➲አንዲት በሰሓቦች ዘመን የነበረች ሴት ባሏ የሞተ አልያም የፈታት ግዜ ሰሓቦች እሷን ለመንከባከብና ለመደገፍ ክብር በተላበሰ መልኩ ይቻኮሉ ነበር።

➲ የሰሓቦችን ታሪክ ብናገላብጥ አንዲት ሰሓቢይ ሴት አራት ሰሓቦችን በተለያየ ግዜ እንዳገባች እንረዳለን። አንዱ ሲሞት ሌላውን እያገባች ተከብራ ኖራለች። እሷን የመሰሉ ሴቶችን በንቀትና በጉድለት በፍፁም አይመለከቷቸውም ነበር።

➲ዐቲካ የምትባልን ሴት ተመልከት! የአቡ በክር ልጅ አገባት በጣም ታፈቅረው ነበር እሱም በቃላት ሊገለፅ በማይችል መልኩ ይወዳታል ከግዜያት ቡኃላ ሸሂድ ሆኖ ሞተ። ከዛም ታላቁ ሰሓቢይ ዑመር አልፋሩቅ አገባትና እሱም ሸሂድ ሆኖ ሞተ። ከዛም እሷን ለማግባትና ለማክበር የመልእክተኛው ሓዋሪይ የሚባለው ታላቁ ሰሓባ ዙበይር ኢብኑል ዓዋም ተቻኮለ፤ አገባትም። ከጥቂት ግዜ ቡኃላም ሸሂድ ሆኖ ሞተ። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ሰዎች ሲሞቱ "በባሎቿ ላይ ሙሲባ የምታመጣ" አልተባለችም። እንደውም "ሸሂድ መሆን የፈለገ ዐቲካን ያግባ!" ተብሏል።

➲የአስማዕ ቢንት ዑመይስን ታሪክ እናገላብጥ። የመጨረሻ ባሏ ታላቁ ጀግና ፈረሰኛው ሰሓቢይ ዐሊይ ኢብን አቢ ጧሊብ ነበር። ከሌሎች ባሎቿ የወለደቻቸውን ልጆች ያጫውት የሷን ጣፋጭ ንግግርና የልጆቿን ጨዋታ በመስማት በደስታ ፈገግ ይል ነበር። በቀደሙ ባሎቿ በፍፁም ቅናት አይሰማውም። "በቀደሙ ባሎችሽ ላይ ስሞቷ ብታሰሚ እቆጣሻለው! በፍፁም በመጥፎ ስታነሺያቸው እንዳልሰማ እነሱ ወዳጆቼ ናቸው።" ይላት ነበር።
(ሁሉንም አላህ ስራቸውን ይውደድ!)

➲የትኛዋም ሰሓቢያ ሌላ ባል ስታገባ የመጀመሪያ ባሏን እያወሳች በክህደት አልተጠረጠረችም።

➲የአላህ መልእክተኛም ከእናታችን ዐይሻ በስተቀር ድንግል ሴት አላገቡም። መጀመሪያ ትዳርን የመሰረቱትም ከሳቸው በፊት ትዳርን ከምታውቀው ከእናታችን ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ጋር ነበር።

➲የተፈታችን አልያም ባል የሞተባትን ሴት ማግባት እንዲሁም ከአንድ በላይ ማግባት ስነ ምግባርን የሚጥስ፣ ክብርን የሚነካና የሚጠየፉት የወረደ ተግባር ቢሆን ቀድሞውንም ኢስላም ይከለክለዋል። ስነ ምግባርን፣ ልቅናንና እውነተኛ ሰብኣዊነትን ያስተማረን ኢስላም ነውና!

➲የተፈታች ሴት በፍፁም የውድቀት ምልክት አይደለችም። አላህን ከፈራች ከፍቺውም ቡኃላ አላህ ከችሮታው ያብቃቃታል። የተሻለ የህይወት መስመር ያበጅላታል።

➲ከመጀመሪያ ባልሽ የተሻለ መልካም የትዳር አጋር አላህ ሊሰጥሽ ይከጀላል። መጪው ቀናት በአላህ ፈቃድ መልካም ብስራትና ተስፋ ይዞ ብቅ ይላል። አንገትሽን አትድፊ!

☞እኛም የደረሰባቸውን ሀዘን ለመጠገን መሯሯጥ ይገባናል። በብዛት የሚያጋጥማቸውን ሞራላዊና ማህበረሰባዊ ተፅእኖ በመልካም ለመግፈፍ መታተር ይጠበቅብናል።

➲በክፉ ከሚመለከቷቸው የሰው አውሬዎች ልንከላከላቸውና በደካማ ጎናቸው ለማጥቃት ካሰፈሰፉ ዋልጌዎች ልንጠብቃቸው የበኩላችንን ጥረት ማረግ አለብን።

➲በሚያሳዝን ሁኔታ በአሁን ወቅት አግብታ የፈታችን ሴት ለማግባት የሚያስብ የሷን መብት ልክ እንደ አሮጌና ያገለገለ መኪና አስመስሎ ፕሮፖዛል የሚያቀርብ አለ።

➲ይህ በሴቶች መብት ላይ ግፍና በደል ነው።

🌸አሏህን ልንፈራ ይገባል!

➲ባል የሞተባት አልያም የፈታች እህትና ልጅ ቢኖረህ ለሷ የምትመኘውን ለሎችም እህቶችን መመኘት አለብህ። ስሜት ካወረው ፅልመት ተላቀህ ሰብኣዊነት የተሞላ ኢስላሚዊ መንፈስ ይኑርህ።

➲ቁምነገሩ ያንተ ወንዳ ወንድነትና ስብእና እንጂ የሷ የቀደመ ትዳር ተፅእኖ አይደለም።

➲በብልሀትና በስነምግባር የተሞላህ መሆንህ በአላህ ፈቃድና ችሮታ ያለፈ ህይወቷን አስረስቶ ስኬታማ ትዳርን በሀሴት ይለግሳታል።

➲ኋላ ቀር የሆኑ አባባሎች ጠፍረው አይከርችሙህ። መመሪያህ ኢስላም ብቻ ይሁን።

🔵በሙስሊም እህቶቻችን ላይ አላህን እንፍራ!

📋ከተወሰነ ማብራሪያ ጋር የተተረጎመ!

✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የኢኽላስ ምዕራፍ
Sadat
የኢኽላስ ምዕራፍ
تَفْسِيرُ سُورَةِ الْإِخْلَاصِ
ድፍረቱ ይኖርሃልን??

ውዱ ወንድማችን Ibnu Munewor ሐፊዘሁላህ «ተቅዋ» በተሰኘው ሙሃደራው ላይ ከተናገው ንግግር ለሁላችንም አንድ ጥያቄ ጠይቆን ነበር ...

እንዲህ ብሎ: –

«..... ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ቢድዓ ገና ከፊታቸው በሌለበት ነበር ጠዋት ማታ (ስለቢድዓ አስከፊነት) የሚቀጠቅጡት።
فيما رواه جابر ابن عبد الله رضي الله عنه ....
”كان رسول الله صلى الله عليه وسلم اذا خطب احمرت ايناه ....

(ጃቢር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳወራው) :–
« መልእክተኛው صلى الله عليه وسلم ኹጥባ ሲያደርጉ ..... (ምንድን ነበሩ?)
‘احمرت ايناه’
አይኖቻቸው ይቀሉ ነበር።
‘وعلا صوته‘
ድምፃቸው ከፍ ይል ነበር።
‘واشتدت غدبه‘
ቁጣቸው ይከፋ፣ ይበረታ ነበር። አለ።

ሱብሓነላህ! (....)

’كانه منذر جيش‘
ልክ ሰራዊት እንደሚያስጠነቅቁ
’صبحكم ومساكم‘
ማታ መጣባችሁ፣ ጠዋት መጣባችሁ።
ግዙፍ ሰራዊት የሚጨርስ፣ የሚያጭድ እየመጣ ነው ያለው። ጠዋት ነው የሚደርሰው። ነገ ጠዋት። ነገ ማታ። እያሉ የሚያስፈራሩ (የሆነ) አስፈሪ የሆነ አቀራረብ ነበር የነበራቸው።

ተመልከቱ! እንዲህ አይነት አስፈሪ የሆነ አቀራረብ ይዘው ግን የሚያስፈራሩት ስለምንድን ነበር? ...
የተለመደውን ኹጥባ ‘ኢነል ሐምደ ሊላህ ..’ ብለው ከጨረሱ በኋላ ...

وخير الهدى هدى محمد (صلى الله عليه وسلم) ...
#‏وشع_الاُمور_محدثاتها ،

ከነገር ሁሉ ክፉ ማለት መጤዎች ናቸው። አሉ (በዲን ውስጥ) ። በዲን ውስጥ ክፉ ማለት መጤዎች ናቸው።
ልብ ይበሉ! እንደዛ እየተቆጡ፣ እንደዛ አይናቸው ቀልቶ፣ ድምፃቸው በርትቶ፣ ቁጣቸው ከፍቶ እየተናገሩ እያለ ...
«መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ነው።» እያልክ ልትናገር ድፍረቱ ይኖርሃልን ከፊታቸው ብትሆን???

ይኖርሃል እንደዚህ አይነት (ድፍረት)??

ፍፁም ሊሆን አይችልም!! ....»
منقول
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
✅ በምላስ የወጋኸው ሰው ቁስል በቀላሉ አይድንምና ተጠንቀቅ

🔹قـ✑ـال الٳمـام سفيان الثوري رحمــه اللـہ تعالـﮯ
♻️ኢማም ሱፍያን አሰውርይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

◐ لو رميـت رجــلا بســهم كان أحــبّ إلـيّ من أن أرميه بلساني ، لأن رمي اللسان لا يڪاد يخطىء.
🔺👇አንድን ሰው በምላሴ (በመጥፎ ንግግር) ከምወጋው ጦር ወርውሬ ብወጋው እመርጣለሁ። ምክንያቱም ጦር ወርውሬ ምናልባትም ልስተው እችላለሁ በመላሴ ከሆነ ግን በፍፁም ልስተው አልችልምና።
📚 المنتقى من مكارم الأخلاق (137/141)

منقول
●قال جندب البجلي رضي الله عنه:

◄◉مَثَلُ الَّذِي يَعِظُ وَيَنْسَى نَفْسَهُ مَثَلُ الْمِصْبَاحِ يُضِيءُ لِغَيْرِهِ وَيُحْرِقُ نَفْسَهُ.


➩◉ሌሎችን ➷እየመከረ እየገሰፀ ➷እራሱን የሚዘነጋ ሰው ➷ምሳሌው እራሱን ➷እያቃጠለ ለሌላ ➷እንደሚያበራ መብራት ➷ነው‼️

📚((صحيح/ابن أبي شيبة))
Audio
♦️هل نحن من الصادقين ؟

📌እኛ እውነተኞች ነን?

➡️من لم يكن صادقا مع الخالق لم يكن صادقا مع المخلوق

♦️ከፈጣሪ ጋር እውነተኛ ያልሆነ ከፉጡር ጋር እውነተኛ አይሆንም

🎙አቡ አዩብ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
<<አንድ ሴት በኢስላማዊ አደብ ከኖረች የተከበረና በላጭ ኑሮን ትኖራለች፡ በተለይም በህብረተሰቡ ውስጥ የተከበሩና የበላጮችን ኑሮ (ትኖራለች)።

➲ከተፈተነችና ከፊትና ከሸርና ከፈሳድ ተጣሪዎች ጋር አብራ ከቀጠለች ግን ራሷም ትጠፋለች ለሌሎች መጥፋትም ሰበብ ትሆናለች፡፡

➲አንድ ቀን ይህን የዱንያ ህይወት እንደምትተወው ታስታውስ፡ በውብ አካሏ ከነፈታኝ መልኳ ከወንድ ሚፈትን መጋጌጧ ጋር በሷ ላይ አንድ ቀን ይመጣል…

🔗 ወደጉድጓድ የምትገባበት
🔗 አፈር በሷ ላይ ሚደፋበት
🔗 ምስጦች የሚበሏት
🔗 ክብሯና ውበቷ ጥሏት ሚሄድበት
🔗 በዚህ ጉድጓድ በስራዋ ትያዛለች፡ በዱንያ ላይ ያሳለፈችው ተይዞ!

➲ ከሷ በፊት ህንጻ ውስጥ የሚኖሩ ሴቶች ነበሩ፡ ከዛም በቀብር ውስጥ መርጊያቸው ሆነ!

🌸ሙስሊም ሴት አላህን ትፍራው! ለዚህ ቀንም ትዘጋጅ!>>

📚 ሸይኽ አብዱረዛቅ አልበድር (ሀፊዘሁላህ)

🖋hijab
u Sohih

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w