💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
➪ባል ለሚስቱ - ሲበላ ያብላት፡ ሲለብስም ያልብሳት፡ ፊቱዋን እንዳይመታ፡እርሱዋንም ሆነ የምትሰራውንም ምግብ እንዳያጥላላ፡ ማኩረፍ ካለበት ቤት ውስጥ እንጂ ውጭ እንዳያኮርፋት።

ረሱል ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
ምንጭ፦ ሶሒህ ኢብኑ ማጀህ (1850)

✍︎ℎ𝑢𝑠𝑒𝑛 𝐴ℎ𝑚𝑒𝑑
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሙሓደራ 096 ዒስቲቃማ
Ustaz Kedir Ahmed
ሙሀደራ 096

ኢስቲቃማህ

ለኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች በኢብኑ አባስ መድረሳ ሲማሩ ለነበሩት ብርቅዬ ተማሪዎች የተሰናባች ምክር

🎙በኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
MyTone -(ibnu munewr )mohammed ahmed
MP3Cutter
ከኢብኑ ሙነወር ወሳኝ #ሙሐደራዎች

ክፍል ❽

ርዕስ  â†ˇâ‡Łâ†ś
ምክር ለወጣቶች
part "B"

🎙 በኡስታዝ #ኢብኑ_ሙነወር ሀፊዘሁሏህ

➽ ወጣቶች በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ አላቸው። ለማህበረሰብ ለውጥ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ። ለዛም ነው ወጣቶች ሲስተካከሉ ሁሉም ማህበረሰብ ይለወጣል ወጣቶች ሲበላሹ ሁሉም ማህበረሰብ ይበላሻል የሚባለው ይህ በብዛት ተከሳች ነው።


➲ በመሆኑም ለወጣቶች መለወጥ ትክክለኛ ሚና የሚኖረው እስልምና ነው።

➽ ኡስታዝ ያቀረበው ምክር ሁሉም ወጣት ሰምቶ ሊለወጥበት የሚገባ ነው።

➚ በርካታ #ጠቃሚ ትምህርቶችን #ከሙሐደራው ይከታተሉ!!!
✅ قال شيخ الإسلام ابن تيمية -رحمه الله تعالى- :

✅ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል።

📌《"والنَّاس إذا تعاونوا على الإثم و العدوان أبغض بعضهم بعضاً"》
♻️🔺ሰዎች እርስ በራሳቸው በወንጀልና በመጥፎ ነገር ላይ ከተባበሩ ከፊሉ ከፊሉን ይጠላል።


[ مجموع الفتاوى(١٢٨/١٥)]
Audio
🔺✅ የጀግና ሴቶች ተምሳሌት ✅🔺

👉 ታላላቅ ሴቶች በኢስላም ያበረከቱት ታሪክ
👉 ሴቶች ሸሪአን ማወቅ ምናክል አንገብጋቢና አሳሳቢ እንደሆነ ከሌሎች ቁም ነገሮች ጋር የተዳሰሰበት ምክር

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Photo
➲፝"በመጀመሪያው ቀን ትውውቅ እንዴት ልገመግመው?

➲ዕድሜዬ 22 ነው፤ የመጨረሻ ዓመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ነኝ፡፡ ከአንድ ወጣት በቤተሰቦቹ በኩል የትዳር ጥያቄ ቀረበልኝ:: እናቱ ወደደችኝ እና ለእናቴ ጥያቄዎን አቀረበች፤ አባቱ እና አባቴ ተነጋግረው የሁለታችንም ቤተሰቦች በተገኙበት እንድንተያይ እና እንድንተዋወቅ ቀጠሮ ያዙልን።

➲ከልጁ ጋር ምንም የቀደመ ትዉዉቅ የለንም፤ ተያይተን አናውቅም፡፡ ምናልባት ስንተያይ የምርጫውን አይነት ሴት እንዳልሆን ወይንም እርሱ እኔ የማልወደው ዐይነት ወንድ እንዳይሆን ፍርሃት አለኝ። ቤተሰቦቼ ቀጠሮው ለመተዋወቅ ያህል ብቻ እንደሆነ እና ሌሎች እርምጃዎች የሚኖሩት በሁለታችንም በኩል ሙሉ መፈቃቀድ ሲኖር ብቻ እንደሆነ አስረድተውኛል።

ጥያቄዬ የሚከተለው ነው ፤
➛በመጀመሪያ ትውውቅ የምርጫዬን ዓይነት እንደሆነ እንዴት ልገመግመው እችላለሁ?

➛ስብዕናውን ለመረዳት እና አስተሳሰቡን ለማወቅስ ምን መጠየቅ ወይም መናገር አለብኝ?

➲የተሳሳተ ምርጫ ላይ ወድቄ የስሜት ጉዳት እንዳይደርስብኝ መጠንቀቅ እፈልጋለውና እባካችሁ ምክር ለግሱኝ።

➦ምላሽ:-ከሁሉም በፊት ከአላህ ጋር ያለሽ ትስስር በጣም ጠንካራ ይሁን፤ ከአላህጋር ያለሽ ትስስር ጠንካራ ከሆነ እና ዘወትር ዱዓ ካልተለየሽ የጉዳዬችሽ ፍጻሜ ሁሉ ያማረ እንደሚሆን አያጠራጥርም። አላህ እርሱን ታዛዦችን ወደ መልካም መንገዶች ይመራል፡፡

ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺘَّﻖِ اﻟﻠَّﻪَ ﻳَﺠْﻌَﻞ ﻟَّﻪُ ﻣِﻦْ ﺃَﻣْﺮِﻩِ ﻳُﺴْﺮًا
«አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን ያደርግለታል» ጦላቅ 4

➲ውዷ እህታችን!
በጥያቄሽ ላይ እንደቀረበው አይነት የህይወት መንገድን የሚያስቀይሩ መንታ መንገዶች ሲገጥሙን ምርጫን ወደ አላህ ማስጠጋት መልካም መሸሸጊያ ነው፡፡ ፍርሃትና ስጋትን ሁሉ ያጠፋል፡፡ አላህ ትክክለኛውን ምርጫ እንዲያሳይሽ ከብዙ እና ብርቱ ዱዓ ጋር ደጋግመሽ [እስቲኻራ] አድርጊ፡፡

➲ትዳር ላሠቡ ሁለት ጥንዶች የመጀመሪያ ትውውቅ እና መተያየት በመሀላቸው መፈቃቀድ እና ተቀራራቢ የነፍስ ፍሰት መኖሩን ለመፈተሽ ወይም ለማወቅ የሚጠቅም ነው፡፡ በዚህ ሂደት ዐይን በሚያየው አካላዊ ገፅታ አሊያም በንግግርና በውይይት መጣጣምና መፈቃቀድ ሊፈጠር ይችላል፡፡

➦በዚህ የመጀመሪያ ትውውቅ ወቅት አላህ ከአንቺ ጋር ሁሌም እንደሆነ አስቢ፤ ራስሽን ብቻ ሁኚ፤ ምን መናገር ወይም መጠየቅ እንዳለብሽ በማሰብ ስሜትሽን አትረብሺ፡፡ እነዚህ ነጥቦች ወደ ለትክክለኛው ምርጫ ያግዙሻል፡፡

➦ነገር ግን ይህ ሰው ትክክለኛ ምርጫ መሆኑን ለማረጋገጥ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆኑ መንገዶች መሠረታዊ የሆኑ በርካታ ወሳኝ ነጥቦችን መመርመር እና ማጣራት ያስፈልግሻል፡፡

➊) ለእምነቱ ያለው ትኩረት ምን ያህል ነው? ሰላት በህይወቱ ውስጥ ምን ቦታ አለው?ከሰዓት ከመዘውተር እና ከሁኔታ አንፃር በትክክል ሰላቱን ይጠብቃል?

➟ትክክለኛውን የትዳር አጋር ለማግኘት እነዚህ ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ማግኘት አለባቸው፡፡ ሰላቱን የሚጠብቅ ሰው ከአላህ ጋር ዘወትር የተሳሰረ ነው ፤ ከአላህገር የተሣሠረ ሰው አብሮ ከሚኖረው ሰው ጋር መልካም ግንኙነት እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

➋) ለወላጆቹ ምን ያህል መልካም ነው? ለወላጆቹስ በጎ ነውን? ይህን ጥያቄ ቀጥሎ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ለወላጆቹ መልካም ከሆነ አላህን የሚፈራ እና የአላህን ውዴታ የሚፈልግ ሰው ለመሆኑ አንድ ማስረጃ ነው፡፡

➛ከነዚህ ምላሾች በመነሣት ከዚህ ሰው ጋር የህይወት ጥምረት መፍጠር እምነት የሚጣልበት መሆኑን እና አለመሆኑን መገምገም ይቻላል፡፡

❸) ከወንድሞቹ ፣ ከእህቶቹ ፣ ከጓደኞቹ፣ ከስራ ባልደረቦቹ አንዲሁም በዙሪያው ከሚገኙ ሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል? ተወዳጅ ሰው ነው? ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማ እና ያልተረበሸ ነው?
ለሰዎች ያለው አቀራረብ ለዛ አለው?

➬የእነዚህ ጥያቄዎች ምላሾች ደግሞ የማህበራዊ ግንኙነቱን ስኬታማነት ያሳያሉ፡፡

➯) የህይወት ታሪኩ ምን ይመስላል? ቢያንስ ስለዚህ አጭር ነገር ማወቅ የኀላ ማንነቱን ለማወቅ ጠቃሚ ነው። ዕውቀት በመፈለግ ባሳለፈባቸው ትምህርት ቤቶች ፣ ሪዝቅ በመፈለግ ባሳለፈባቸው የስራ ቦታዎች እንዲሁም ኑሮውን ባሳለፈበት መንደር ትቶት ያለፈውን የህይወት ጠረን ጥሩ ይሁን መጥፎ ማሽተት ያስፈልጋል፡፡

➪መልካም ሽታ የመልካም ስነምግባር ውጤት ሲሆን መጥፎ ሽታ የመጥፎ ስነምግባር ውጤት ነው፡፡

➎) ተቀዳሚ ምልከታሽ ዲን ይሁን ፤ ገንዘብን ወይንም ማህበራዊ ክብርን ከዲን አታስቀድሚ፤ የነብዩ /የአላህ ሠላም እና ሰላት በእርሳቸው ላይ ይሁን/ የምክር ቃል ይህን ይላል፦
قال النبي صلى الله عليه وسلم: إذا أتاكم من ترضون دينه وخلقه فانكحوه

«እምነቱን እና ስነምግባሩን የወደዳችሁት ሰው የትዳር ጥያቄ ሲያቀርብ ተቀበሉት»

➧አደራ የምንልሽ ቤተሰቦችሽ የትዳር ጥያቄ ያቀረበውን ሰው አስመልክቶ የሚሰጡትን አስተያየት ቦታ እንዳትነፍጊው ነው። አስተያየታቸው በህይወት ተሞክሮዎች የተፈተሸ በመሆኑ ጠቃሚነቱ አያጠራጥርም፡፡
የምታማክሪዉን ሰው ልታውቂ ይገባል። በእድሜ ላንቺ እኩያ ወይም ካንቺ ያነሱ ያልበሰሉ ወጣቶችን ካማከርሽ፤ ቁሳዊ መመዘኛን ተጠቅመው ወይም ከቅናት ስሜት በመነሳት የማይበጅሽን ሀሳብ ሊለግሱሽ ስለሚችሉ ተጠንቀቂ።

➨ሁልጊዜም ለአላህ ትእዛዛትና ገደቦች ጥንቁቅ ሁኝ፡፡ አላህን መፍራት ያማረ ፍፃሜ የሚገኝበት ብቸኛ መንገድ ነው።

ﻭَاﻟْﻌَﺎﻗِﺒَﺔُ ﻟِﻠﺘَّﻘْﻮَﻯٰ

«መልካም መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት!» ጣሀ 132
ነሲሓ መጽሔት ቅጽ Vol1 ቁጥር 1
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#ለምን__እናትህን??
<===================>
ዘጠኝ ወር አርግዛ በመከራ ወልዳህ፡
ባለ ውለታህን ደፍረህ እየከዳህ፡
እርሷን ለመሳደብ እየተሰናዳህ፡
እናትህን ሳይሆን ራስህን ጎዳህ፡
<=======\\\==========>
እናም እንድህ አልኩኝ!!
ከውስጤ እያፈርኩኝ!!
<~~~~~~~~~~~>
አይቻልም እንጂ ቢቻልማ ኖሮ፡
መሳደብ እንዲያቆም እናቱን አዙሮ፡
ውለታዋን ቆጥሮ እንድኖር አክብሮ፡
ምጥ ማሳየት ነበር ባለጌን ዘንድሮ፡
<=======\\===========>
የመፈጠር ሰበብ የኑሮ ሻማህን?
ከማንም አብልጣ ተንከባካቢህን?
ላንተ በመጨነቅ አርቆ አሳቢህን?
ደፍረህ መሳደብህ ለምን እናትህን!!!
#ለምን!!? #ለምን!!? #ለምን!!?
<=======\\\==========>
#በኑረዲን_አል_አረቢ
<===================>
http://t.me/nuredinal_arebi
Audio
✅✅ ወሀብዮች እነማን ናቸው ✅✅

👉 ወሀብይ ሲሉ ማንን ነው የፈለጉበት
👉 እውነት ወሀብይ የሚባል ቡድን አለ?
👉 በዚህ ዙሪያ ለሚቀጥፉት ቅጥፈትና ውሸት አስመልክቶ የተዳሰሰበት ምክር

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎አንዲት እናት ለሴት ልጇ ፦

➛"ስትራመጂ እግርሽ የት ላይ እንደሚያርፍ እያስተዋልሽ ተራመጂ።" ስትል መከረቻት።

💎ልጅትዋም፦

➛"ማማ! አንቺም ስትራመጂ ጥንቃቄ አድርጊ! እኔ እንደሆን ያንቺን እርምጃ ነው የምከተለው።" ብላ መለሰችላት።

➛ለልጆች መስተካከል ምክንያት ከሚሆኑት ነገሮች ዋናው የእናት መስተካከል ነው!

➛እራስሽን አስተካክዪ ልጆችሽ አንችን አርዓያ አድርገው ይከተሉሻልና።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Photo
#በአሏህ_ሁላችንም_እናንብበው??
<========================>
#እህቴ_እባክሽን??
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አሏህ በችሎታው ውብ አድርጎ ፈጥሮሽ፡
ተሸፋፈኝ ብሎ በጀነት አብስሮሽ፡
እየተገላለጥሽ አንች ወንጀል አምሮሽ፡
አድስ መጤ ክስተት ስልጣኔ አስክሮሽ፡
አይነ አፋርነትን እርግፍ አርገሽ ተውሽው፡
በለስላሳ ድምፅሽ ስንቱን ረበሽው??
ስንቱን ጀግና ወጣት ስንቴ አንበረከክሽው??
<==========\\\\============>
ነግሬሽ ነበረ ባትሰሚኝም እንኳ፡
ሳሙና ነው ብዬ የቆንጆ ልጂ መልኳ፡
ሀያዕ ያጣች ጊዜ ያበቃል ታሪኳ፡
ውሀ ላይ እንዳለ እንደ ሽንቁር ታንኳ፡
ግን ይህንን ምክሬን ያኔ አልሰማሽኝም፡
የቀናሁኝ መስሎሽ መርሀባ አላልሽኝም፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
#ነግሬሽ_ነበረ፤
ውበት ደም ግባትሽ ሁሉን እንደሚስብ፡
የወንድ ልጅን አይን ከተበተነበት እንደሚሰበስብ፡
#ነግሬሽ_ነበረ፤
ትንሽ ስትስቂልን ብዙ እንደምናስብ፡
#ነግሬሽ_ነበረ፤
ባንች ትንሽ ስህተት ብዙ እንደምንከስብ፡
<===========\\\=============>
#ነግሬሽ_ነበረ...
ሴት ልጅ ስታማርጥ ለራሷም ምራጭ ናት፡
#በክብር_ነው_እንጂ...
በመውለድ አይደለም የሚኮነው እናት፡
#ነግሬሽ_ነበረ፤
ክብረ-ቢስ ህይወቶች ጣፍጠው አይቀጥሉም፡
ወላጂ ከብትም አለ፤
የወለዱ ሁሉ እናቶች አይደሉም፡
#ፀንቶ_የሚቆመው_ሆኖ_የማይሟሟ፡
#ነግሬሽ_ነበረ_እናትነት_ስሟ፡
ከክብሯ ነው እንጂ ከልጇ እንዳልወጣ፡
ብትወልድም ምንም ነች ሴት ክብሯን ስታጣ።
<============\\\=============>
#ነግሬሽ_ነበረ
ሴት ክብሯን ስትጥል እድሜዋ ይሄዳል፡
አደብ በማጣቷ ክብር ሴትነቷ ፈጥኖ ይዋረዳል፡
#የወንድ_ልጅ_ቤቱ...
የሴት ልጅ ውበት ነው ካየበት ይለምዳል።
ስለዚህ ነቃ በይ ፊትናን አታራግቢ፡
በየሚዲያው ላይ ፈረስ አትጋልቢ፡
ሀያዑ ነው ክብርሽ እህት ተዐደቢ፡
ብሎ የሚልሽን ያ ሁቢ ያ ቀልቢ፡
በል እራቀኝ በይው ፈፅመሽ በረቢ፡
።።።።።።።።።።።።።።።፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
#ነግሬሽ_ነበረ፤
ሀሳብሽ ሀሳቤን ሁሌ እንደማይበልጠው፡
#ቁንጅናም_ይረክሳል፤
ብቻውን ይቀራል ሁሉም ከመረጠው፡
።።።።።።።።
ብነግርሽ ብነግርሽ ባትሰሚኝም ቅሉ፡
"ሰደበኝ" በማለት ታወሪያለሽ አሉ፡
#ግንክ_ሀቅ_ነው፤
እውነቶች ውሽት ፊት ስድብ ይመስላሉ፡
እኔ ግን ልምከርሽ የወንድምነቴን፡
አሁን አርማለሁ ያለፈ መክሊቴን፡
ከተሞክሮዬ ልምከርሽ እህቴን፡
አወ እነግርሻለሁ ዛሬም ሳልታበይ፡
ነግሪያት ነበር ስል አንቺ "ሰደበኝ"በይ፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
#ግን_እነግርሻለሁ‼
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ውበቷ አይመችም፡
ሁሉም ያፈቅራታል አንዱም ጋር የለችም፡
በአንች እየተፈተን እኛም አንገት ደፋን፡
ወላሒ ወቢላህ መላ ቅጡ ጠፋን፡
መንሀጂ ተረድተናል ጀግና ነን ብንልም፡
በሴት ግን ዝንጉ ነን ፈፅሞ አንችልም፡
#ስለሆነም___??
ወንድን አትፈትኝ ጠብቂው ክብርሽን፡
በሀያዕ ድመቂ እህቴ እባክሽን፡
<========\\\============>
#በኑረዲን_አል_አረቢ
http://t.me/nuredinal_arebi
Audio
🍃• ولنعم دار المتقين •🍃

▫️ القارئ ؛ #عبدالعزيز_الأحمد

• ‏الجنة امنية الصالحين ومأوى أف،د؊ العابدين
‏كم دمعت لها العيون وأحترقت لها القلوب ،
‏ جعلنا الله ووالدينا من اهلها