💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
♻️🔺የትዳር አስፈላጊነት🔺♻️

🔺ላጤነት በእስልምና ቦታ የለውም


🎙አቡ አብደላህ ኢብኑ ኸይሩ
እናታችን ዓኢሻ (ረድየላሁ አንሀ) እንዲህ ትለናለች፦

➢ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተቀበሩት በቤታቸው ውስጥ ነበር እንዲሁም አባቷም አቡበከር (ረድየላሁ አንሁ) ከእርሳቸው ጋር አብሮ ነበር የተቀበረው። ማለትም በእናታችን ዓኢሻ ቤት ማለት ነው።

➢« ሁለቱም ሞተው ከተቀበሩ በኋላ እዛ ቤት እገባ ነበር ስገባም ሂጃቤን ባልተሟላ መልኩ ሳልለብስ ነበር
«እዚህ ቤት ውስጥ የተቀበሩት አባቴና ባሌ ናቸው ሌላ ሰው የለም» እልም ነበር።

➢በአላህ ይሁንብኝ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ አብሯቸው ከነሱ ጋር ከተቀበረ በኋላ ግን እዛ ቦታ ላይ አንድም ቀን ሂጃቤን በትክክል ለብሼ (ፊቴን ተሸፍኜ) ቢሆን እንጂ ገብቼ አላውቅም። ምክንያቱም ዑመር ረድየላሁ አንሁ (አጅነብይ በመሆኑ) ሀያዕ አደርጋለው ። »

(አህመድ ዘግበውታል )

💎https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
በአላህ ዲን ላይ መጽናት
በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን
👆👆👆
#በአላህ ዲን ላይ መጽናት

🔶በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን በስልጢ ወረዳ ቅበት ከተማ በኑር መስጅድ የተደረገ ሙሐደራ።

🎙 በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻟﻔﻀﻴﻞ ﺑﻦ ﻋﻴﺎﺽ ﻣﻦ
ﻋﻈﻢ ﺻﺎﺣﺐ ﺑﺪﻋﺔ ﻓﻘﺪ ﺃﻋﺎﻥ
ﻋﻠﻰ ﻫﺪﻡ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﻭﻣﻦ ﺗﺒﺴﻢ
ﻓﻲ ﻭﺟﻪ ﻣﺒﺘﺪﻉ ﻓﻘﺪ ﺍﺳﺘﺨﻒ
ﺑﻤﺎ ﺃﻧﺰﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﺰ ﻭ ﺟﻞ ﻋﻠﻰ
ﻣﺤﻤﺪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭ ﺳﻠﻢ
ﻭﻣﻦ ﺯﻭﺝ ﻛﺮﻳﻤﺘﻪ ﻣﺒﺘﺪﻉ ﻓﻘﺪ
ﻗﻄﻊ ﺭﺣﻤﻬﺎ ﻭﻣﻦ ﺗﺒﻊ ﺟﻨﺎﺯﺓ
ﻣﺒﺘﺪﻉ ﻟﻢ ﻳﺰﻝ ﻓﻲ ﺳﺨﻂ ﺍﻟﻠﻪ
ﺣﺘﻰ ﻳﺮﺟﻊ
ፉዶይል ኢብኑዒያድ አሏህ ይዘንላቸው እንዲህ ይላሉ
የቢድአ ባለቤትን ያከበረ እስልምናን በማፍረስ ላይ ተባብሯል ። ሙብተዲእ ፊት የሳቀ አሏህ በነብዩ ያወረደውን ቁርአንን አቃሏል ። ጥሩ ልጁን ለሙብተዲእ የዳረ ዝምድናዋን ቆርጧል ። የሙብተዲእን ጀናዛ የተከተለ እስከሚመለስ ድረስ በአሏህ ቁጣ ውስጥ ነው

ምንጭ_ሸርሁ_ሱና_ኢማም_በርበሃሪ_139
ከኢኽወኖች ጋር መተሻሸት መጨረሻው የሰለፎችን ግንዛቤ ወደ ጎን በማድረግ እንደፖለቲከኞች በስሜት ሰክሮ የሚናገሩትን አለማወቅ ያደርሳል።

በሰሞኑ ከኢብኑ መስኡድ ሴንተር ደጋፊዎች የታዘብነው ይህንኑ ነው። አንዳንዶች ታላላቅ ስመጥር አሊሞችን አሁን ላይ ካሉበት የስሜት ሞቅታ ጋር ስላልተጣጣመላቸው ሲተቿቸው እየየን ነው። አንዳንዶች ወረድ ብለው ከቀርደዊ እና ከዶ/ር ጀይላን ትምህርት እንወስዳለን የሚሉም አይተናል። አንዳንዶች የኢኽዋን መንሃጅ ትክክለኛ ነው ብለው በብዕራቸው የሚሰብኩ ሰዎችን መፅሀፍ እየገዙ ለሰው ሲሰጡም አይተናል።
ሰው መደገፍ የመጨረሻው ግብ አብሮ ቁልቁል መዝቀጥ ይለሀል እንደዚህ ነው።




ለዚህም ነው ሰለፎቻችን ከቢድዓ ሰዎች ጋር አትቀማመጡ እያሉ አበክረው የመከሩን።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
➚➶➚ የልዩነት ትልቁ መፍትሔ

በኮምቦልቻ ከተማ አንሷር
መስጂድ እየተሰጠ ከሚገኘው
ኮርስ የተቀነጨበ


ኮርሱ የሚቀጥል በመሆኑ በአካባቢው ያላችሁ ሰዎች ትጠቀሙበት ዘንድ እመክራለሁ

🎙 በሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ ሀፊዘሁሏህ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤

"ወሏሂ ይቅርብህ"

በወንድማችሁ አቡ ሳራህ
===============>
➷➘➷➘
ወንድሜ አቡ ሳራህ ኸድር ከነዚህ ሰዎች ጋር በኮሚቴነት ሰርቷል። ከማንም በላይ ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። እንቅስቃሴዎቻቸውን ሁሉ ከሁላችንም በላይ ያውቃል።

በመሆኑም ያንን ለሴረኞች ጠበቃ የሆነውን ሰው አድርሱለት
"ወላሂ ይቅርበት"
"ወላሂ ይቅርበት"
"ወላሂ ይቅርበት"
قال تعلى: ولا تكونوا من المشركين ➊➌ من الذين فرقو دينهم وكانوا شيعا كل حزب بمالديحم فرحون ➋➌

وقال صلى الله عليه وسلم: من مات وهو يدعو من دون الله ندا دحل النار.
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ሙሓደራ 095 የ አላሀ እዝነት ለ ሙእሚኖች እጅግ ቅርብ ነው.mp3
Ustaz Kedir Ahmed
ሙሓደራ 095

በመርከዝ ኢብኑ አባስ በዛሬው እለት የተደረገ ሙሓደራ

የአሏህ እዝነት ለሙዕሚኖች እጅግ ቅርብ ነው

🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል_ከሚሴ (ሐፊዘሁሏህ ተዓላ)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➪ሴት ልጅ የራሷን ውበትና የቤቷን ጽዳት ስትጠብቅ ባለቤቷን ከማስደሰትም አልፎ ትዳራቸው የስኬት ቁልፍ ይሆናል !!!
(233 عشر النصحة النساء)
Forwarded from Deleted Account
የተጠው'ዉዕ ሶላት ትርጓሜ
የተጠው’ዉዕ ሶላት
ግዴታ ያለሆነና መስገዱ የተደነገገ ሶላት ነው፡፡

የተጠው’ዉዕ ሶላት ትሩፋት
1 - የተጠው’ዉዕ ሶላት አላህ አገልጋይ ባሪያውን እንዲወደው ምክንያት ይሆናል፡፡ በሐዲስ አልቁድሲ እንደተመለከተው አላህ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ባሪያዬ እስክወደው ድረስ በነዋፍል (ግዴታ ያልሆኑ ተጨማሪ ዕባዳዎች በማከናወን) ወደኔ መቅረቡን ይቀጥላል፤ከወደድኩት ደግሞ የሚያይበት ማያው፣የሚሰማበት መስሚያው፣የሚሰነዝርበት እጅ እና የሚጓዝበት እግር እሆንለታለሁ፡፡ ከለመነኝ በእርግጥ እሰጠዋለሁ፤ከኔ መጠጊያና መጠበቂያ ከፈለገም በእርግጥ እጠብቀዋለሁ፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ]

2 - የተጠው’ዉዕ ሶላት በግዴታ ሶላቶች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ጉድለቶችን ያካክሳል፡፡ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በትንሣኤ ቀን ከሥራዎቻቸው ውስጥ ሰዎች በመጀመሪያ የሚጠየቁበት ሶላት ነው፡፡ ጌታችን እርሱ የበለጠውን የሚያውቅ እየሆነ ለመላእኮች እንዲህ ይላል፡- ‹የባሪያዬን ሶላት አሟልቶት ወይም አጉድሎ ሰግዶ እንደሆነ እዩለት› ይላል፡፡ የተሟላ ከሆነ (ምንዳው) የተሟላ ሆኖ ይጻፍለታል፡፡ የጎደለ ነገር ካለ ደግሞ ባሪያዬ የተጠው’ዉዕ ሶላት እንዳለው እዩለትና ተጠው’ዉዕ ካለው ‹‹ለባሪያዬ የግዴታ ሶላቱን ከተጠው’ዉዑ አሟሉለት› ይላል፡፡ የተቀሩት ሥራዎችም በዚሁ ዓይነት ይወሰዳሉ፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ]

3 - የተጠው’ዉዕ ሶላትን እቤት መስገድ ተመራጭ ነው

የጀማዓ ሶላት የተደነገገለት እንደ ተራዊሕ ያለው ሲቀር፣የተጠው’ዉዕ ሶላትን ከመስጊድ ይልቅ እቤት መስገድ ብልጫ አለው፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ከግዴታ ሶላት በስተቀር ያንድ ሰው በላጩ ሶላት እቤቱ የሚሰግደው ነው፡፡›› [በቡኻሪ የተዘገበ] ብለዋል፡፡

የተጠው’ዉዕ ሶላት ዓይነቶች
የተጠው’ዉዕ ሶላት ብዙ ዓይነቶች ያሉት ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው ፡-

አንደኛ- የግዴታ ሶላት ቀዳሚና ተከታይ ሱንናዎች (ረዋትብ) [ረዋትብ (ነጠላው ራትብ) ቋሚና የጸና ነገር ማለት ነው፡፡ ]
የፈርድ ሶላቶችን የሚከተሉ ረዋትብ ሲሆኑ የጸኑ ሱንናዎች ናቸው፡፡

የረዋትብ ሱንና በአጠቃላይ አስር ወይም አስራ ሁለት ረክዓዎች ናቸው፡፡ እነሱም ፡-

- ከፈጅር ሶላት በፊት ሁለት ረክዓ፤

- ሁለት ወይም አራት ረክዓ ከዙህር በፊትና ሁለት ረክዓ ከዙህር በኋላ፤

- ሁለት ረክዓ ከመግሪብ በኋላ፤

- ሁለት ረክዓ ከዕሻእ በኋላ ናቸው፡፡ እብን ዑመር ባስተላለፉት መሰረት፡- ‹‹ከነቢዩ ﷺ የያዝኩት አስር ረክዓዎችን ነው፡፡ ሁለት ረክዓ ከዙህር በፊት፣ሁለት ረክዓ ከዙህር በኋላ፣ሁለት ረክዓ ከመግሪብ በኋላ በቤታቸው፣ሁለት ረክዓ ከዕሻእ በኋላ በቤታቸውና ከሱብሕ ሶላት በፊት ሁለት ረክዓ ናቸው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብለዋል፡፡

ከዙህር በፊት አራት ረክዓ ከማለታቸው ውጭ ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ዘገባ ከዓእሻ (ረዐ) ተላልፏል፡፡ [በሙስሊም የተዘገበ]

ቀዳማይ ሱንና  የፈርድ ሶላት ደህራይ ሱንና
ሁለት ረክዓ የሱብሕ ሶላት -------
አራት ረክዓ የዙህር ሶላት ሁለት ረክዓ
------- የዐስር ሶላት -------
------- የመግሪብ ሶላት ሁለት ረክዓ
------- የዕሻእ ሶላት ሁለት ረክዓ
ከረዋትብ ሱንናዎች ሁሉ በላጩና ነቢዩ ﷺ ከጉዞ ውጭና ተጓዥም ሆነው አዘውትረው የሰገዱት ሁለቱ የሱብሕ ቀዳሚ ሱንና ሶላት ነው፡፡ ዓእሻ (ረዐ) ባስተላለፉት መሰረት ፡- ‹‹ነቢዩ ﷺ ከነዋፍል ውስጥ ከሁለቱ የፈጅር ረክዓዎች ይበልጥ አጥብቀው ይፈጽሙት የነበረ ሌላ ምንም አልነበረም፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብለዋል፡፡

ዋጅቦቹን ካለማጓደል ጋር ረክዓዎቹን ቀለል አድርጎ መስገድ ሱንና ነው፡፡

ዓእሻ (ረዐ) ባስተላለፉት መሰረት፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሁለቱን የፈጅር ሱንና ረክዓዎች ከሱብሕ ሶላት በፊት ሰገዱና ፋቲሓን ቀርተውበታል ወይ? ብዬ እስከምጠራጠር ድረስ ያሳጥሩ ነበር፡፡›› [በቡኻሪና የተዘገበ] ብለዋል፡፡

የፈጅርን ሱንና ካመለጠ ሰግዶ መተካት የተፈቀደ ነው፡፡
1 - ከሱብሕ ሶላት በኋላ፤ቀይስ ብን ዐምር ባስተላለፉት መሰረት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከሱብሕ ሶላት በኋላ የሚሰግድ ሰው አይተው፡- ‹‹የሱብሕ ሶላት ሁለት ረክዓ ነው›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ] ሲሉት ፡- ‹‹ከበፊቱ ያለውን ሁለት ረክዓ አልሰገድኩምና ነው አሁን የሰገድኳቸው›› አላቸው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዝምታ አለፉት ብለዋል፡፡

2 - ጸሐይ ከወጣች በኋላ፤ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹የፈጅርን ሁለት ረክዓዎች ያልሰገደ ሰው ጸሐይ ከወጣች በኋላ ይስገዳቸው፡፡›› [በትርምዚ የተዘገበ] ብለዋልና፡፡

ጠቃሚ ነጥቦች
- ከዙህር በፊት አራት ረክዓ መስገድ ያለው ትሩፋት በሐዲስ ተረጋግጧል፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ከዙህር በፊት አራት፣ከዙህር በኋላም አራት የሰገደን ሰው አላህ (ገላውን) በእሳት ላይ እርም አድርጓል፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ] ብለዋል፡፡

- ሙአክ’ከድ (የጸኑ) ካልሆኑ የተወደዱ (ሙስተሐብ) ሱንናዎች መካከል ከዐስር በፊት አራት ረክዓዎችን መስገድ አንዱ ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹ከዙህር በፊት አራት፣ከዙህር በኋላም አራት የሰገደን ሰው አላህ (ገላውን) በእሳት ላይ እርም አድርጓል፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ] ብለዋልና፡፡

- ከዐስር፣ከመግሪብና ከዕሻእ ሶላት በፊት ሱንናነቱ ያልጸና ሶላት መስገድ ተንግጓል፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹በየሁለቱ አዛኖች መካከል ሶላት አለ - ሦስት ጊዜ ደጋግመው በሦስተኛው ላይ - ለፈለገ ሰው፡፡›› [በቡኻሪና ሙስሊም የተዘገበ] ብለዋል፡፡ ሁለት አዛኖች ማለት በየአዛኑና እቃማ መካከል ማለት ነው፡፡

- አንድ ሰው በእንቅልፍ ወይም በመርሳት ምክንት ያመለጠውን ሶላት፣መስገድ በተጠላበት ወቅትም ቢሆን ሰግዶ መተካት የተፈቀደ ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ የዙህርን ደህራይ ሱንና ሳይሰግዱ ቀርተው ከዐስር ሶላት በኋላ መስገዳቸው ተረጋግጧል፡፡

ሁለተኛ- የውትር ሶላት
የውትር ድንጋጌና ትሩፋቱ
ውትር የጠበቀ ጽኑ ሱንና ነው፡፡ ነቢዩ ﷺ ፡- ‹‹አላህ ውትር (አንድ) ነው፤ውትርን (ኢተጋማሽን) ይወዳልና የቁርኣን ባለቤቶች ሆይ! ውትርን ስገዱ፡፡›› [በአቡ ዳዉድ የተዘገበ] ብለዋል፡፡ ነቢዩ ﷺ በሐዷርም ሆነ በሰፈር (እቤት እያሉም ሆነ በመንገደኝነት ጉዞ ላይ እያሉ) የውትር ሶላትን ተጠባብቀው ይሰግዱ ነበር፡፡

የውትር ሶላት አሰጋገድ
1 - የውትር ሶላት አነስተኛ ረክዓ አንድ ሲሆን ከፍተኛው ቁጥር አስራ አንድ ወይም አስራ ሦስት ረክዓ ነው፡፡ የሚሰገደው በሁለት-ሁለት ረክዓ ሆኖ በማጠቃለያው አንድ ረክዓ ብቻ ይሰገዳል፡፡

2 - ዝቅተኛው የምሉእነት ቁጥሩ ሦስት ረክዓ ሲሆን፣ሁለት ረክዓ ተሰግዶ በሰላምታ ካበቃ በኋላ አንድ ነጠላ ረክዓ ይሰገዳል፡፡ ሦስቱንም አገናኝቶ በአንድ ተሸሁድ ብቻ መስገድም ይቻላል፡፡

በመጀመሪያው ረክዓ ከፋቲሓ በኋላ ሱረቱል አዕላን፣ በሁለተኛው ሱረቱል ካፍሩንን፣በሦስተኛው ሱረቱል እኽላስን መቅራት ሱንና ነው፡፡

ኡበይይ ብን ከዕብ ባስተላለፉት መሰረት ፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ ﷺ በውትር የመጀመሪያው ረክዓ ‹ሰብ’ብሕ እስመ ረብብከል አዕላ›፣በሁለተኛው ‹ቁል ያ አይ’ዩሀል ካፍሩን››፣በሦስተኛው ‹ቁል ሁወል’ሏሁ አሐድ› ይቀሩ ነበር፡፡›› [በነሳኢ የተዘገበ] ብለዋል፡፡

የውትር ሶላት ወቅት
ከዕሻእ ሶላት በኋላ እስከ ጎሕ መቅደድ ድረስ ነው፡፡ በሌሊቱ የመጨረሻ ሲሶ መስገዱ በላጭ ነው፡፡ ከጃቢር በተላለፈው ሐዲስ ነቢዩ ﷺ ‹‹በሌሊቱ መጨረሻ ላይ አልነቃም ብሎ የፈራ ሰው ውትርን በሌሊቱ መጀመሪያ ላይ ይስገድ፡፡›› [በሙስሊም የተዘገበ]
🔸ሸይኽ ኢብን ባዝ ተጠየቁ :- ሙቅ ውሃን በምናፈስበት ጊዜ ቢስሚላህ እንላለንን፣ ይህም ጂን ቦታው ላይ ይኖራል ብሎ በመፍራት ነው
መልስ፡
"አዎን! ቢስሚላህ ይበል ምን አልባት ቦታው ላይ ጂን ካለ እንዲነቃ ለማድረግ ነው" ከዛም ሽይኹ እንዲህ አሉ" በርግጥም በአንድ ወቅት አንድን ሰው ጂን ይዞት በሚቀራበት ቦታ ተገኝቼ ነበር
#ሩቃ የሚያደርገው ሰው በሰውየው ላይ ለተደበቀው ጂኒ "ለምን ያዝከው "አለው
#ጂንውም "የሞቀ ውሃ በአንዱ ልጄ ላይ ደፋና ገደለው "አለ
#የሚቀራው ሰውዬ ደግሞ "እሱ ልጅህ በቦታው መኖሩን ስላላወቀ ነው" አለው
#ጂኒው ደግሞ "ለምን ቢስሚላህ አይልም ነበር እንዲያሳውቀው(እንዲያነቃው)"
#ሽይኽ ዘይድ አል መድኸሊ ረሂምሁሏህ እንዲህ አሉ ፡
"ለማንኛውም የሞቀ ውሃ በፍሳሽ ትቦዎችም ይሁን በመሬት ላይ አይደፋም ምክኛቱም መሬት በነዋሪዎች የተሞላች ነች ምናልባትም በጂኖች አለም ወይም በትንንሽ ፍጡሮች ላይ ያርፋል በዚህም ለበቀል ይነሳሱና ይይዙታል።ስለዚህ አንድ ሰው የሞቀን ውሃ መድፋት ከፈለገ በቀዝቃዛ ውሃ ቅዝቃዘው የማያስቸግር እስኪሆን ያብርደውከዛም ከፈለገ የፍሳሽ ትቦዎች ውስጥ ከፈለገ መሬት ላይ ያፍሠው" ንግግራቸው እዚህ ጋር አለቀ ረሂመሁሏህ.
፟፟======================
#ጉዳዩ አደገኛ ነው ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ ለወንድሞቻችሁ ለእህቶቻችሁ ለእናቶቻችሁ አድርሱላቸው ስንትና ስንት እህቶች በዚህ ሰበብ ችግር ውስጥ ይገባሉ ፓስታ የቀቀሉበትን ውሃ አውጥተው በመድፋት ስለዚህ አድርሱላቸው!
..🖋Bin Muhammed
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ትንሽ ምክር ቢጤ በተለይ ለእህቶቼ‼

ቁጥብ፣እንቁና ጥንቁቅ ሁኚ እህቴ።።።።።።
የአሏህን ቅጣትና ወንጀል በተጨማሪ እራሳችሁን ለአደጋ ያጋልጣችሇል እሱም።።።።እሱም ይሄ ሲህር የሚባል ተንኮልና ምቀኝነት ነው።።።።።።።

ፎቷችሁን ሚድያ ለሚድያ ስትበትኑ ለዚህ ትጋለጣላችሁና ቁጥብ ጥንቁቅ ሁኑ።።።።።።።።።

አንድ በጣም አሳሳኝና ውስጥ የሚነካ ታሪክና አጋጣሚ ልንገራችሁ፣

አንድት የከለላ ልጅ ነበረችና ኒቃቢስት ነች ነገር ግን ሲህር ተሰርቶባት ካፊር አግብታ አገኘሇት።።።።ከሚገርመው ደግሞ ካፌ ከፍተው ስሟን ወደ ካፊር ስም ቀይራ ግን ካፌ ስንገባ ኒቃብ ሳታወልቅ ነበር ያገኛናት።ለምን ስትባል መቼም አላወልቅም አይነት ነው የተናገረችው እምነቷን ግን ከመልቀቋ ጋር።።።።።።።

እና ጥንቃቄ ያሻል።።።።።
በተለይ ሱንይና ሰለፍይ እህቶቼ ራሳችሁን ጠብቁ አትዝረክረኩ ተጠንቀቁ ሰበብ አትርሱ ብዙ كلاب الناس من وراء حجابكم መኖሩን አትርሱ።
من الكافرين ومن في قلبه مرض من المسلمين‼
ግልባጭ ለወንድሞቼም፣፣፣፣፣።።።።
نسأل الله السلامة والعافية

اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عنا‼

✍ወንድም አቡ ሪሳላን
የ ዒልም አስፈላጊነት
ወንድማችን መሐመድ ሲራጅ
አጠር ያለ ሙሀደራ

➡️የኢልም አስፈላጊነት

ከኡስታዝ ከድር አህመድ የፈለቁ እንቁ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ የሆነው

🎙ወንድማችን ሙሀመድ ሲራጅ

በመርከዝ ኢብኑ አባስ የተደረገ ሙሀደራ



https://t.me/UstazKedirAhmed01OnlyChannal8990/5334
መጠኑ ወይም መልኩ ይለያያል እንጂ ብዙዎቻችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የዘረኝነት በሽታ ይንፀባረቅብናል። ለዚያም ነው ነብያችን ﷺ ይህንን በዘር መጎረር ወይም በዘር ማነወርን ህዝባቸው ውስጥ በተጨባጭ የሚኖር የጃሂሊያው ዘመን መገለጫ እንደሆነ መጠቆማቸው። እናም አላህ የጠበቀው ሲቀር ክፉ በሆነ የዘር በሽታ ላይ የሚወድቀው ብዙ ነው። እራሳችንን በየጊዜው እየተከታተልን ካልገታን ሌሎችን በዘራቸው ምክንያት የምንጠላበት፣ የምናነውርበት፣ አለፍ ሲልም የምናጠቃበት ሁኔታ ይኖራል። በሌላ በኩል ደግሞ በዘር ለሚዛመደን መጥፎ ሰው ወይም ካፊር እንኳ ቢሆን ብዙ ርቀት ሄደን ከሙስሊሞች በላይ የምንቆረቆርበት፣ የምንወግንበት ሁኔታም ይገጥማል። ይሄ እምነታችንን አደጋ ላይ የሚጥል ክፉ በሽታ ስለሆነ ውስጣችንን ልንፈትሽና ልናስተካክል ይገባናል። ማንንም ቢሆን በዘሩ ምክንያት ብቻ በተለየ ልንወደው ወይም ልንጠላው አይገባም። አላህን መፍራት ካልታከለበት ዘራችን ስሙኒ ታክል ከሌሎች ከፍ አያደርገንም። እንደሚታወቀው ሰውን አንዱን ከሌላው ከፍ የሚያደርገው ተቅዋው ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል:–

(یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقۡنَـٰكُم مِّن ذَكَرࣲ وَأُنثَىٰ وَجَعَلۡنَـٰكُمۡ شُعُوبࣰا وَقَبَاۤىِٕلَ لِتَعَارَفُوۤا۟ۚ إِنَّ أَكۡرَمَكُمۡ عِندَ ٱللَّهِ أَتۡقَىٰكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِیمٌ خَبِیرࣱ)
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡" [አልሑጁራት: 13]

በዚህ አጋጣሚ ማስታወስ የምፈልገው በወቅታዊው የፖለቲካ ትኩሳት የተነሳ በአንዳንድ አካባቢዎች ትግሬዎችን በዘራቸው ሰበብ የማጥቃት ነገር እንዳለ እየተወራ ነውና ለእንዲህ አይነቱ ጥፋት አስተዋፅኦ እንዳናደርግ ልንጠነቀቅ ይገባል። ፖለቲካው ሌላ ነው። ከፖለቲካው ጋር ፈፅሞ ንክኪ የሌላቸውን ሰዎች አንድ ላይ በዘር መስፈሪያ ከሰፈሩ በኋላ አብሮ መጨፍለቅ ፍርደ ገምድልነት ነው። እንዲህ አይነቱን አካሄድ እምነታችን በጥብቅ ይኮንነዋል። ለአስተዋይ ህሊናም የሚጎረብጥ ነው። ስለዚህ በሚመለከተንም በማይመለከተንም ውስጥ ዘው እያልን እየገባን ሌሎችን እንዳንጎዳ፣ ቅስማቸውን እንዳንሰብር ልንጠነቀቅ ይገባል። አላህ ከፈተና ይጠብቀን።
የ ሀዳዲዮች አዲስ ስትራቴጂ

አንገብጋቢ መልዕክት
=============>

ወዳጆቼ !!!

በተለይ ቻናልና ግሩፕ ያላችሁ እህት ወንድሞቼ ይህን መልዕክት በደንብ ተረዱልኝ

===/~~~\===/~~~\===/~=>

በሀገራችን መንሃጃቸውን በውሸት ለማስፋፋት የሚንቀሳቀሱ ብዙ ቡድኖች አሉ። ከነዚህም መካከል ሀጃዊራዎች ወይም ሀዳዲዮችን የተኩ የሆኑ አካላት በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

እናም ውድ እህት ወንድሞቼ እነዚህ ሰዎች የሱና ሰው መስለው በመቅረብ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቻናሎችንና ግሩፖችን በመክፈት አድ (Add) አድርጉ
በሌላ በኩልም ቻናሌን አስተዋውቁ እያሉ በመናገር ቻናሎቻቸውና ግሩፖቻቸው ብዙ ሰው ከሆነ ቡኋላ ያንን ግልፅ ሂዝቢያነታቸውን ይሰብኩበታል።

በመሆኑም የማታውቁት ግሩፕ ላይ ማንንም አድ አታድርጉ!!!

አስተዋውቁልን የሚሏችሁን ቻናል ሁሉ አታስተዋውቁ!!!

#ጥንቃቄ_ያስፈልጋል


✍ አቡ ዒምራን
‏☆ قَالَ العَلّامَة صالِح الفَوْزَان حَفِظَه اللهُ تَعالَى:

" أثبتَ اللهُ الأمنَ لمَنْ لَمْ يُشْرك، والذي لمْ يُشْرك يكونُ مُوحدا، فدلّ على أنّ مِن فضائل التوحيد استقرار الأمن ".

[القول المفيد(صـ٣٧)]

ኮፒ የተደረገ