💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
✍️አንዳደየ የሚድያዉ ትዳር ሲታይ
የገጠር ትዳር ይሻላል!
ገጠር ከጂህልና ዉጭ
በጥሩ የሚኖሩ በሀያዕ ተሞልተዉ!
ሴቶቹ ባላቸዉ ቀና ብለዉ ሳያዩ በስሙ እ
ራሱ አይጠሩም የሀያዕ ጥጉ ማለት ነዉ።

✍️የሚድያዉ ግን እዉቀቱ ኖሮ!አኗኗራቸዉ
ቅጥ የለዉ። ባላቸዉ እንደ ተራ ሰዉ የሚያዪ ክብር የለ
።መቆጣት መገላመጡ መከራ! ተጋቡ ሲባል ትንሺ ሳይቆይ ተፍቱ!

አላሁመ ሙስተዓን!

👉🐎በዚች ተጋብተዉ ብዙ አመት ይኖራሉገጠር!
👉🚗በዚች ተጋብተዉ ወር ሳይሞላ ይፍታሉአወቅን የሚሉት ሰፈር!

👉ገርሞ ይገርማል ላጤዎችዬ አላህዬ መልካሙ ይግጠማችሁ ትዳር ገብቶ ከመዉጣት ይጠብቃችሁ!!


https://t.me/https_Asselefya1
ወንድ ልጂ ለወደዳት ሴት የማይሆነዉ የለም!
እሷን የሚያገኝበት መንገድ የማይሄድበት የለም
!

ገጠርኳኮ እንቢ ካሉ ቤተሰብ እሷም እንቢ ካለች
ከመንገድ ሰርቋት የሚጠፍ ክክ!

አላህዬ ሆይ ለላጤ እህቶቼ የሚወዳቸዉን ሷሊሁ
ወፍቅልኝ! አሚን በሉ!
አንዳንዱ ሰው ለዱንያው የሚጨነቀውን ያክል ለዲኑ አይጨነቅም ‼️

ለዱንያችን የምንጨነቀውን ያክል ለዲናችን ብንጨነጨነቅ የትናየት በደረስን ነበር ‼️

ለዱንያህ ከምትጨነቀው በላይ ለዲንህ ተጨነቅ ዱንያንም አኼራንም አትራፊ ትሆን ዘንድ ፡፡

https://t.me/https_Asselefya1
💧ዋ የኔ ነገ...ር...💦

    አቡሁረይራ ሞት በመጣባቸው ግዜ በጣም አለቀሱ አጠገባቸው ያሉ ሰዎች ምን ያስለቅሳቹሃል አሏቸው እሳቸው "የምያስለቅሰኝማ የሚጓዘው መንገድ ርቀቱ... የያዝኩት ስንቄ ማነሱ ነዉ" ነበር ያሉት።

የሸይኻችን ንግግር ምንኛ አማረ?
   ሁሉም ይጓዛታል ያቺን የሩቅ ጉዞ
   የሌለው ባዶ እጁን ያለው ስንቁን ይዞ


https://t.me/https_Asselefya1
721947881561089
اللهم اجعل القرآن ربيع قلوبنا ونور صدورنا وجلاء همنا وذهاب غمنا يارب

➧የምሺቱ ዉብ ቲላዋ ግብዣ

https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ 🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ?! ➫➫➫➫➫➫➫➫ ➲ክፍል አራት ➤በክፍል 3 ዳሰሳችን ላይ የተወሰኑ የመልካም ጓደኛን ባህሪ አይተን ነበር በአላህ ፍቃድ በዝህኛውም ክፍል የተወሰኑትን እንመለከታለን ። ❹➛ባንተ ምንም ምቀኝነት የለለው !! ➲ማለትም ብዙን ሰዎች ትመለከታለህ ወንድሜ ሆይ ያንተን ማግኘት ሲመለከቱ ባንተ ላይ ምቀኝነት ይዟቸው እንዳለ የሚዘገኩክ ብዙዎች ናቸው : …
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ

🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ ?!
➫➫➫➫➫➫➫➫

➲ክፍል አምስት


➤በአላህ ፍቃድ ከክፍል 4 የቀጠለው ክፍላችን ይሆናል የመልካምን ጓደኛ ባህሪ እያየን ነበር እንቀጥላለን ኢንሻ አላህ ።

➑➛ሓራም ነገር ላይ ከወደቅክ በቁርአን እና በሓዲስ የሚገስፅህ
!!

➲በአሁን ግዜ ኣላህ ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር ይህንን ባህሪ ያለው ጓደኛ ያለው በጣም አናሳ እና የተመናመነ ነው ይህ ግልፅ ነው ምክኒያቱም ከሰዎች ዘንድ የዲን ግንዛቤ በጣም ስለተመናመነ ።


➤ወንድሜ ሆይ አንተ ላይ አንድ ስህተት ሲያይ ከመምከሩ በፊት የሚሸሽህ ከሆነ ይሄ ችግር አለበት እወቅ ምክኒያቱም ሊመክርህ ይገባው ነበር በቁርአን በሓዲስ ካልቻለ ደግሞ በሰዎች ቢያስመክርህ ጥሩ ነበር ።


➲ግን ዘሎ የሚያኮርፍህ እና የሚርቅህ ከሆነ ይህ ታዲያ ምኑን ጓደኛ ተባለ ስለዝህ ይህንን ባህሪዉንም እይ እወቅ ልብ በል ከመከረህም ምርጥ ተመካሪ ለአላክ ብሎ የተመለሰ ምርጥ ጓደኛ ሁንለት ኸይር ።


❾➛ለአላህ ብሎ የወደደክ ላንተም ዱዓህ የሚያደርግልህ

➤ለአላህ ብሎ መዋደድ ታላቅ ምንዳን ያስገኛል አላህ ዘንድ ነገ በቂያም ቀን ሰዎች በፀሀይ ሲቃጠሉ በወንጀላቸው ልክ ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሰዎች ግን አላህ ከዓርሽ ጥላ ስር ያደርጋቸዋል አላህ ይወፍቀን ለሁላችንም ።

➲ይህንንም ታላቅ ምንዳ አውቆ የወደደህ እና የቀረበህ ለአላህ ብሎ ማለት ነው ለአኼራው ብሎ በጀነትም ጎረቤት እንዲያደርጋችሁ በመመኘት።

➤ በተጨማሪም ላንተ አላህ በዱንያም በአኼራህም መልካምን ነገር እንዲገጥምክ ሁሌም በዱዓው የማይረሳህ ወንድም ነው ጓደኛህ ማለት እንጅ የሚረሳህ አይደለም ።

➲ አንተን ሲቀርብህ ለገንዘብህ ለብርህ ለክብርህ ለዝናህ ብሎ ሳይሆን ለአላህ ብሎ መሆን አለበት ለዱንያዊ ጥቅሞችማ የቀረበህ ሰው ጥቅሙ ስትቋረጥበት ትቶህ ነው የሚሄደውና አስተውል ወንድሜ ።

➓➛በዘርህ ግንድ የማይጠመጠም ሲወድህ ለተውሂድህ ለሱናህ የሆነ !!

➤አንዳንድ ሰዎች አንድን ሰው ሲወዱ ከዘሩ ጋር ይሆናል ይህ ደግሞ የጃሂልያ አስተሳሰብ ነው ወደ ጥንብ ወደሆነችው #ዘረኝነት ይመራልና ይህንን ሰው ጓደኛ እንዳታደርግ ምንም ጥቅም የለውም ጉዳት ብቻ እንጅ ።

➲ለዘሩ ብቻ ብሎ ከቀረበህ እሱን ተውና ከሌላ ዘር የሆነውን የሱና ወንድምህን ተጎዳኝ እሱ ነው የሚጠቅምክ ወንድሜ እንጅ የኔ ጎሳየ ብሎ ለጎሳህ ብቻ ብሎ ከቀረበህ ምንም አይጠቅምም ።

➤ስለዝህ በዘር ግንድ መተሳሰር ጥሩ ቢሆንም ግን ግን ግን ወደ ጎጠኝነትና ወደ ዘረኝነት ካመራ
#ጥንብ ይሆናል አንድ የተከበረ ሙስሊም ሁሌም ጦሀራ የሚያደርግ ሙስሊም ይህንን ጥንብ ዘረኝነት ሊሸከም አይገባም ።

➧ክፍል ስድስት ይቀጥላል ኢንሻ አላህ.........✍️

✍️አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
▪️በቁርአን ልብ ሰላም ደስታ እርካታ ታገኛለች!

👉የምሽቱ ግብዣዬ በሰላም እደሩ!!

➧ወደ ቻናላችን  ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷

https://t.me/https_Asselefya1
متن أصول الثلاثة۵
Abu Useymin
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖

📚ኪታብ ኡሱሉ ሰላሳ

            ➧ክፍል 
❺

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1

@abuUseyminabdurehman
➧ለምን ትሸፋፈኛለሽ ብለው ከጠየቁሽ እንዲህ በያቸው " ውድ ስለሆንኩኝ"።

▪️ምክንያቱ ውድ ነገር ይደበቃል እርካሽ ነገር ግን ተገላልጦ በየቦታው ይታያል ምክንያቱም ዋጋ የለውምና።

▪️አንቺ ግን እህቴ ውድ ነሽ ለዚያም ነው አላህ እንድትሸፈኝ ያዘዘሽ ክብርሽን ከፍ ሊያደርገው።

➘እናም እህቴ ይሄንን ውብ እና ውድ አካልሽን ለምን ለማንም እያሳየሽ እራስሽን ታረክሻለሽ??

➧ቆንጆ እንደሆን ሰው እንዲነግርሽና ውበትሽን እንዲያደንቁልሽ ከሆነ...የሰው ሙገሳ አያስፈልግሽም ቆንጅዬ እንደሆንሽ ለማወቅ ምክንያቱም ከፍ ያለው አላህ ውብ እንደሆንሽ እንዲህ በማለት በተከበረ ቃሉ ይነግርሻል፦

لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي أَحْسَنِ تَقْوِيمٍ
ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው፡፡ (ሱረቱ አል-ቲን: 4)

አስከትሎም እንዲህ ይላል፦
ثُمَّ رَدَدْنَاهُ أَسْفَلَ سَافِلِينَ
ከዚያም (ከፊሉን) ከዝቅተኞች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው፡፡ (ሱረቱ አል-ቲን: 5)

ቀጥሎም እንዲህ ይላል፦
إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَلَهُمْ أَجْرٌ غَيْرُ مَمْنُونٍ
ግን እነዚያ ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት ለእነርሱ ተቆራጭ ያልኾነ ምንዳ አልላቸው፡፡ (ሱረቱ አል-ቲን: 6)


➘ውዷ እህቴ ሆይ ለውጫዊ ውበትሽ ብዙም አትጨነቂ ግና ለውስጣዊ ውበትሽ አብዝተሽ ተጨነቂ፤ የልብ ውበት በጊዜ አትወሰንም ሁሌም እንዳበበች ትቆያለች ግና ዛሬ የፈካው  ውበትሽ ነገ ይረግፍና ምንም ዋጋ ሌላት የጠወለገች አበባ ያስመስልሻል።

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘                 
https://t.me/https_Asselefya1
[[ ቆሜ ብቀርስ !!!]]

➧ምንም ብከጅልም ቢፈልግም ነብሴ
ብቸኝነት መምረጥ ባልፈልግ ለራሴ
ለሁለት ሀገር ህይወት ስኬትን ፈልጌ
እራሴ ለመስጠት ውስጤንም ሸሽጌ
መቆይትን ብመርጥ ባለጌን ጠልቼ
ለዲኑ ማይሆነው ከርፋፋውን ትቼ
መኖር ይሻለኛል ካገሬ ውጥቼ!!

➧ከእሡ ባልሻልም ጠልተውት አይኖቼ
ሁል ጊዜ ለሽሽት እራሴን ሠጥቼ
መኖርን ለመድኩት ከእሡ ተጣልቼ
ማነው እሡ በዲኑ ደነዙ
ቀን ማታ በጫቱ እንደው መደንዘዙ
ከእሡ መኖሩ ብዙ ነው መዘዙ
ባገሬ የሞላው እንደሡ አይነቱ
እኔ ምፈልገው አይደለማ ከንቱ!!

➧ጉድለቴ ቢሞላ አልሠጠውም እጄን
ብሩ ቢትረፈረፍ አያየውም አይኔን
ለትዳር ብቻ አይደል የኔ መፈጠሬ
ሙሉነት ባይሠማው አካሌ ደምስሬ
ጌታዬን ካገኘው ይበቃኛል ለኔ
እንዳንተ አይነቱ አይፈልግም ጎኔ
!!

ስለተመቸኝ ተነካክቶ የተወሰዴ ነዉ።

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
የሴቶች መክፈር ምን አበዛው ??
Abu Useymin
↪️ አድስ ሙሓደራ
➥➥➥➥➥➥➥

▪️የሴቶች መክፈር ምን አበዛዉ!?

👉ድናቸዉ ጠንቅቀዉ አለመማራቸዉ!

👉ሴቶች የካፊር ጓደኛ አድርገዉ መያዛቸዉ
!

ሌሎችም በርካታ ነጥቦች ተዳሰዉበታል!

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
➧https://t.me/abuUseyminabdurehman/8802
▪️ያን ሰለፍይ ጀግና

የለውም ጥርጥር በኢስላም ጎዳና፡
በአሏህ ያመነው ከልቡ ነውና፡

በደሊል የቆመው በሀቁ እንደፀና፡
ጥሩልኝ ያንን ሰው ያን ሰለፍይ ጀግና፡
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ 🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ ?! ➫➫➫➫➫➫➫➫ ➲ክፍል አምስት ➤በአላህ ፍቃድ ከክፍል 4 የቀጠለው ክፍላችን ይሆናል የመልካምን ጓደኛ ባህሪ እያየን ነበር እንቀጥላለን ኢንሻ አላህ ። ➑➛ሓራም ነገር ላይ ከወደቅክ በቁርአን እና በሓዲስ የሚገስፅህ !! ➲በአሁን ግዜ ኣላህ ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር ይህንን ባህሪ ያለው ጓደኛ ያለው በጣም አናሳ እና የተመናመነ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
✍️አድስ ተከታታይ ፁሁፍ

🖋ያንተ ጓደኛህ ማነዉ?!
➬➬➬➬➬➬➬

➲ክፍል ስድስት

➤በአላህ ፍቃድ ባለፉት ክፍሎቻችን ላይ የመልካም ጓደኛን የተወሰኑ ባህሪዎችን ለማየት ሞክረን ነበር ዛሬም የምንቀጥል ይሆናል ኢንሻ አላህ ።

❶❶➛ሚስጥርህን የሚጠብቅ !!

➤ጓደኛ ተብሎ ሚስጥርህን ካልጠበቀ ይሄ ጓደኛ አይባልም ጓደኛ ማለት ከርሱ ጋር ሆንክም ብቻክን ሆንክ ሚስጥርህን የሚጠብቅ ማለት ነው እንጅ ሚስጥህን ካልጠበቀማ ይሄ ጓደኛ ሊባልም አይችልም ወንድሜ።

➲ሚስጥርህን ከንግግርም ሊሆን ይችላል ከሌላም ነገር እንዲሁም ዓይብህን የሚሸፍንልክ መሆን አለበት ያንተን ጉድለትህን እና ሚስጥህን በየአደባባዩ የሚያሰራጭ መሆን የለበትም ።

➤ልብ በል እንዲህ አይነት ጓደኛ የሰይጣን ባልደረባ ነውና ተጠንቀቀው ምን አይነት ካልከኝ ያንተን ሚስጥር የማይጠብቅና ያንተ ዓይብ በየአደባባዩ የሚናገር ስለዝህ ተገንዘብ ጓደኛህ ማነው ??

➲ሰው ጓደኛህ ሁኖ እንደገና እንኳ ብትጋጨው በፍፁም ሚስጥሩን ልታወጣበት አይገባም ያዝለት ዓይቡን ሸፍንለት አላህ ያንተንም በአኼራህ ይሸፍንልካልና ።

⓬➛ከምዕራባዊያን ፋሽን የራቀ !!

➤በተለይ በአሁን ግዜ በምዕራባዊያን ፋሽን ያልተለከፈ ጓደኛ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው አላህ ሲገጥምህ ነውና ይህንን ጓደኛ አጥብቀህ ያዘው የነዝህን ፋሽን የማይከተልም ከሆነ ።

➲የምዕራባዊያንን ፋሽን ተከታይ ከሆነ ለሱና ያለው ቦታ በጣም አናሳ ስለሚሆን እሱ በተለከፈበት በሽታ አንተንም እንዳያስታትምምክ እንዳያጣብቅብክ ራቀው አደገኛ #ቫይረስ ነውና ይህ በሽታ ።

➲ ሱናን ሳይከተል በምዕራባዊያን ፋሽን ተጠምዶ እነዝህን ከተገበረ ፦

➧ ልብሱን ከቦጫጨቀ !
➧ ፁጉሩን እንደ አውራ ዶሮ ከቆለለ !
➧ሱሪዉን ከጎተተ !
➧ ሀፍረተ ገላውን እየገለጠ ከሄደ !
➧ ሴቶችን የሚጨብጥ ከሆነ !
➧ሱና ተከታይ የሆኑ ሰዎች ላይ ካፌዘ !

➬እናም የመሳሰሉ ባህሪ ካለበት ተወው ወንድሜ ላንተ ምንም አይጠቅምክም ከቻልክ ምክረው ።

❶❸ ➛አርቆ አሳቢ መሆን አለበት !!

➤ይህ ማለት እንዳንድ ሰዎች ለነገ ምን አለኝ የሚለውን እና ለወደፊት ምን ሰርቻለሁ ምን ስንቅ ይዣለሁ የሚለውን ነጥብ እንዳለ የረሱ ብዙ ናቸውና ተንቀቅ በል ለነገ ሀሳቢ መሆን አለበት ወንድሜ።

➲ ለነገ ማሰብ ማለት ያገኘነውን ሁሉንም እናጥፋ እናባክን ለነገ አላህ አለ እያለ ወደ ገንዘብን ማባከን የሚመራህ እናም ከዝህ በከፋ መልኩ ደግሞ ለአኼራው ምን እንዳስቀደመ የማያውቅ ከሆነ ነው ።


▪አላህ እንዲህ ይላል ፦
" እናተ ያመናችሁ ሰዎች አላህ ፍሩ ሁሉም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት " ።

➤ይህ የአምላካችን ቃል ነው እንግዲህ አላህ እንዳለው ያስቀደማችሁትን እዩ እያለን ነውና ለነገ ምን እንዳስቀደምን ካላወቅን አደጋ ነውና ጓደኛ ተብሎ ራሱን ከረሳ ሰውም መሆን አይጠበቅብንም ።

➧ክፍል ሰባት ይቀጥላል ኢንሻ አላህ.........✍️

✍️አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/abuUseyminabdurehman
https://t.me/https_Asselefya1