💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.49K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
በአላህ ፍቃድ አዲስ የምንጀምረው ኪታብ
100 ሀዲስ ለሂፍዝ (ለሽምደዳ)

t.me/SadatKemalAbuMeryem/2650
Audio
♻️ሰምተናል ታዘናል

🔺አጭር ምክር

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Audio
♻️👇 እስልምና ለሴት ልጅ የሰጣት ትልቅ ቦታ በተመለከተ‼️

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
⇨ ወዷ እህቴ ሆይ ሷሊሃ ሴት ምክር ሲሰጧት የምትቀበል
⇨ሲያስታዉሷት የምታስታዉስ
⇨ከስህተቷ በፍጥነት ተመላሽ
⇨ጌታዎን ማሃርታ የምጠይቅ
⇨ለሙስሊም ህብርተሰብ ሰነ—ስርዓቷ ያማር
⇨ለሁሉ አዛኝ ናት እና እኔም አንችም ከሷ ያደርገን ዘንድ አላህን እለምነዎለሁ

➡️ለሱናዋ እህቴ

✍ام فلان
📌《ከተውሒድ ትሩፋት》

🔻ከበባድ ወንጀሎችን መጠንቀቅ ጥቃቅን ወንጀሎችን እንደሚያሰርዘው ሁሉ ሺርክን በመጠንቀቅ ተውሒድን ማጠንከርም ከበባድ ወንጀሎችን ያስምራል
ከእሳትም አድኖ ጀነት ያስገባል
ነቢዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ብለዋል
🔻" አንድን ግለ-ሰብ አላህ የቂያማ ቀን እፊቱ አቁሞት ስፋታቸው የሰው ዓይን እይታው የሚያበቃበት ያክል የሆኑ 99 በወንጀል የተሞሉ መዝገቦችን ዘርግፎለት ከዚህ ውስጥ የምታስተባብለው ነገር አለን? ብሎ ይጠይቀዋል ግለ-ሰቡም በፍፅም የለም ብሎ ሲመልስ ከቅጣቴ የምትድንበት ምክንያት ወይም አንዲት እንኳ መልካም ስራስ አለህን ብሎ ይጠይቀዋል እሱም የለኝም ይላል!
አላህም፥ አለህ እንጂ እኔ ዘንድም አትበደልም በማለት አንዲትን
🔹(أشهد أن لا إله إلا الله وأشهد أن محمدا رسول الله )
🔻የሚል ፅሁፍ ያለባትን ብጣሽ ወረቀት አውጥቶ ይሰጠዋል እሷና የመጥፎ ስራ መዝገቦቸቹ ሚዛን ላይ ሲቀመጡ ላኢላሀ ኢለሏህ ሚዛን በመድፋቷ የመጥፎ ስራ መዝገቦቹ ወደ ላይ ይበራሉ"

📑ቲርሚዚይ ዘግበውታል

✍𝐔𝐬𝐭𝐚𝐳 𝐀𝐡𝐦𝐞𝐝 𝐒𝐡𝐚𝐤𝐡 𝐀𝐝𝐞𝐦 (𝑯𝒂𝒇𝒊𝒛𝒆𝒉𝒖𝒍𝒍𝒂𝒉)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➦ብቻዬን ነኝ ብለህ አትረበሽ
የመጣኸዉም የምትሄደዉም ለብቻህ ነዉና አብሮህ የመጣ የለም እዚህም ዱንያ ላይ ኖረህ ስትሞት አብሮህ ብቸኝነትህን ተጋርቶ የሚወዳጅህ የለም ብቻህን መጣህ ብቻህን ትጓዛለህ ብቻህን ትወጣለህ የራስህ ጉዳይ ነዉና!!
ስለዚህ

قال إبراهيم بن أدهم رحمه الله تعالى :

⇘ኢብራሂም ኢብኑ አድኸም የተባለዉ አሊም እንዲህ ይላል

مالي وللناس ❕
➲እኔ ከሰዎች ምን አለኝ ??
(ምን አገናኘኝ)

كنت في بطن أمي وحدي ،

⇘በእርግጥም በእናቴ ሆድ ውስጥ ብቻዬን ነበርኩኝ
وخرجت إلي الدنيا وحدي ،

⇘ከእናቴም ሆድ ወደ ዱንያ የወጣሁት ብቻዬን ነዉ
وأموت وحدي ،

⇘ምሞተዉ ለብቻዬ ነዉ
وأدخل قبري وحدي

⇘ቀብር ምገባዉ ብቻዬን ነዉ
وأسأل وحدي ،

⇘ቀብር ዉስጥ ምጠየቀዉ ብቻዬን ነዉ
وابعث من قبري وحدي ،

⇘ከቀብሬ ምቀሰቀሰዉ ለብቻዬ ነዉ
وأحاسب وحدي ،

⇘አላህ ፊት ሂሳቤን ምተሳሰበዉ ብቻዬን ነዉ
فإن دخلت الجنة دخلت وحدي ،

⇘ጀነት ከገባዉ ምገባዉ ብቻዬን ነዉ

وإن دخلت النار دخلت وحدي ❗

⇘እሳትም አላህ ካስገባኝ ምገባዉ ብቸቻዬን ነዉ
ففي هذه المواطن لا ينفعني أحد ،

⇘በነዚህ ሁሉ ቦታዎች ላይ ማንም ሰዉ ምንም አይጠቅመኝም ( ምወጣቸዉ ብቻየዬን ነዉ
☜ فمالي وللناس .

⇘ከሰዎች ምን አለኝ ምን አገናኘኝ
ይለናል ይህ ታላቅ አሊም

⇘እኔም የዚህ አሊም ንግግር ይዤ እኔ ከሰዎች ምን አለኝ ምን አገናኘኝ እላለው

እናንተስ ? ...

📚إيقاظ الهمم لإبن عجيبة (1/ 176)

⇘ሰዎችን ስትወድም ስትጠላም ለአላህ ብለህ ይሁን አላህ ካልወሰነ በስተቀር ሊጠቅሙህም ሊጎዱህም አይችሉምና!!!!
☆ قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله تعالى:


" ‏كُلُّ Ů…َا لَا ŮŠŮŽŮ†ŮŮŽŘšŮ ŮŮŮŠ Ř§Ů„Ř˘ŘŽŮŘąŮŽŘŠ ŮŮŽŮ‡ŮŮˆ بَاطِل، وإن كَانَ لَذَّة حَاضِرة، فإنَّهَا تَزُول وتَعد بِلا نَفعٍ يَبقَى، فهي بَاطِل بَهَذا الاعتِبَار ".


[جَامِعُ المَسائِل لإبنِ تَيْميِّة(١/ ٤٤)]
☆ ሸህ አል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ፣ ራሂመሁላህ እዲህ አለ


“በመጨረሻው ዓለም የማይጠቅም ነገር ሁሉ ዋጋ ቢስ ነው ፣ እናም የአሁኑ ደስታ ከሆነ ያኔ ያልፋል እናም ምንም ፋይዳ እንደሌለው ተደርጎ ይቆጠራል ፣ በዚህ ግምት ባዶ ነው።”#ምንጭ ⬇️
[جَامِعُ المَسائِل لإبنِ تَيْميِّة(١/ ٤٤)]

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎የአባት ምክር ለሴት ልጁ!

➻አቡልአስወድ አዱኣሊ ሴት ልጁን ሲመክር እንዲህ አለ:–

➻" ቅናትን ተጠንቀቂ እነሆ እሱ የፍቺ ቁልፍ ነው፣ በመሸላለም ላይ አደራ [ ከሽልማቶች ሁሉ ሽልማት ኩል ነው]፣ በሽቶም ኣደራ [ከሽቶዎች ሁሉ ሽቶ ውዱእን ኣሟልቶ ማድረግ ነው]።

[ዑዩን ኣላአኽባር– ኢብኑ ቁተይባህ 4/76
]
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#በሶስት_ነገሮች_ወደ_ዕሣት___!!

‏قال الإمام ابن القيم رحمه الله:

دخل الناس النار من ثلاثة أبواب:
1️⃣باب شبهة
أَوْرَثَت شَكّاً في دين الله
2️⃣ وباب شهوة
أَوْرَثَت تقديمَ الهوى على طاعتهِ
3️⃣ وباب غضب
أَوْرَثَت العدوان على خَلْقِه .

ዒብኑል ቀይም አሏህ ይዘንላቸው ይላሉ፡–

#ሰወች_በሶስት_በሮች_ወደ_እሳት_ይገባሉ።
①
#የጥርጣሬ_በር_ሲሆን……!!
በአሏህ እምነት ላይ ጥርጣሬን ይፈጥርባቸዋል።
②
#የስሜት_በር_ሲሆን___!!
አሏህን ከማምለክ ይልቅ ስሜት ማስቀደምን ያወርሳቸዋል።
③
#የቁጣ_በር_ሲሆን____!!
በፍጡራኖች ላይ ጥላቻን ያወርሳቸዋል።

من كتاب الفوائد لإبن القيّم ج١ ص٥٨


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
✅✅ ኡሱሉ ሰላሳ👉 ክፍል አራት④

🎙¶¶ አቡ አብደሏህ ኢብኑ~ኽይሩ//
Audio
🔺👇የሚዲያ አጠቃቀማችን ምን መምሰል አለበት❓
🔺👇ከሚዲያ ፈተና እራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን❓

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➡️ውዷ እህቴ መልካምነትሺ ታማኚነትሺ ለራስሺ!ሰዎች እንድቀርቡኝ & እንድወዱኝ ብለሺ እንዳታመሳስይ!!አስመሳይ የሙዕሚን ባህሪ ሳይሆን የሙናፊቅ ነውና ልብ በይ!!
Forwarded from Deleted Account
✔️ ሞትና ቀጣይ ሂደቶች

- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣

- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ

ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡

1- ልብሴን ያወልቃሉ፣

2- ያጥቡኛል፣

3- ይከፍኑኛል፣

4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣

5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣

6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣

7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡

ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡

8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል

- ቁልፎቼ 🔑🗝

- መጽሐፎቼ 📚

- ጫማዎቼ 👟

- ልብሦቼ 👖👔…..

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣

- የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣

- የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣

- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣

- ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣

- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤

- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል

- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤



ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …

በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ

1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ

2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣

3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣

የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ

ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!

1- መልክህ፣

2- ሀብትህ፣

4- ጤናህ፣

5- ልጅህ፣

6- ቪላህ፣

7- ዝናህ፣

8- ሚስትህ/ባልሽ

ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ

እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ

ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡

እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ

1- በግዴታዎች፣

2- በሱንና ነገሮች፣

3- በድብቅ መፅውት፣

4- መልካም ሥራ አብዛ፣

5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣

ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡

መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡
☘☘☘☘☘☘
"ውዷ _እህቴ"

⏭ትግስትን ሶብርን ስንቅሺ!
የአላህን ቃል ቁርአንን ጓደኛሺ!
ተወኩልን ተስፋሺ አድርገሺ ይዘሺ
"ኢልምን ከመፈለግ አትሰልቺ"!!
#ሴት_እህቶቻችን_ለሴት_እህቶቻችን_ሊጨነቁላቸው_ይገባል!

┈┈••••○○❁❁○○••••┈┈•
#ሸይኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ አልዋዲዒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–
"ይህ ኢስላማዊው ማህበረሰብ ሙስሊም እህቶቿን የጥፋትና የማጥፋት ተጣሪዎች እንዳይወስዷቸው (ወደጥፋት እንዳይነጥቋቸው) ዘንድ በጣም የሚያሳስባት ሴት ያስፈልገዋል!"
[📚 አልኢንቲሳር ሊሑቁቂ:’ልሙእሚናት ገፅ 6 📚]

የሚያሳዝነው የአጥፊዎቹ ተጠናክሮ መስራት ሳይሆን የአልሚዎቹ ማንቀላፋት ነው!

የነቃሽ እህቴ ሆይ ለሌላው ሙስሊም እህትሽ አስቢላት ኢስላምን በጥልቅ እንድትረዳ የበኩልሽን አስተዋፅኦ አበርክቺ! ቢያንስ መሰረታዊ የዲን እውቀት ይኖራት ዘንድ ጥረት አድርጊ! "ያወቀ ይነቃል" ነውበማሳወቅ ላይ በርቺ ተበራቺ!! አደራሽን ከእዝነት ከርህራሄ የመነጨ አካሄድን ተላበሺ ያኔ የሸፈተች እህትሽን ልብ መግዛት ትችያለሽ!!

አላህ ባለሽበት የኢስላም ገፅታን የምታስወቢ ሌሎች እህቶችሽን ለማቅናት የምትለፊ የዲን ጀግና ያድርገሽ!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#ሰለፎቻችን_የሴቶችን_ፈተና_ምን_ያክ_ይጠነቀቁ_ነበር!?? እንመልከት
፠በበይተል ማል ተቆጣጣሪ ተደርጌ ብሾም ታማኝ ሁኜ እገኛለሁ፤በሴት ልጅ ግን ነፍሴን አላምናትም። ዐጧዕ ረሂመሁሏህ
ምንጭ ሲየር አዕላም አንኑበላዕ 5/87-87
፠ሸይጧን በሴት ልጅ መቶ እስኪፈትን ድረስ ተስፋ አይቆርጥም።
ሰኢድ ኢብኑ ሙሰየብ
ምንጭ ሲየር አዕላም አንኑበላዕ 4/237
፠ሰኢድ ኢብኑ ሙሰየብ አንድ አይናቸው ጠፍቶ 84 አመት ሁኗቸው ይሄን ተናግረዋል፦
-እኔ ዘንድ እንደ ሴት ያለ አስፈሪ ነገር የለም።
-ሴት ልጅ ባንተ በኩል ከመጣች እስከምታልፍ ድረስ አይንህን ጨፍን። አነስ ረዲየሏሁ አንሀ
፠ሁመይድኢብኑ ሂላል እንዳወሩት፡ አስወድ ኢብኑ ኩልሱም የሚባል ሰው ነበር ከቤቱ ወጥቶ ጉዞ በሚጀምር ጊዜአይኑን ከእግሩ አይነቅለልም ነበር።አንዳንድ ሴቶች ፀጉራቸውን ገልጠው ተቀምጠው እሱ ካለፈ ባትሸፍኝ ችግር የለውም ሰውየው እኮ አስወድ ኢብኑ ኩልሱም ነው ይሉ ነበር። ምንጭ አዝ ዙህድ 256
፠ሀሳን ኢብኑ ሲናን ለኢድ ሶላት ወጥተው ሲመለሱ ባለቤታቸው"ዛሬ ስንት ቆነጃጂት ሴቶችን ተመለከትክ?"አለቻቸው።ይሄንኑ ጥያቄ ስትደጋግምባቸው"ወየውልሽ ከቤቴ ወጥቼ እስክመለስ ድረስአውራ ጣቴን እንጂ አላየሁም" አሏት።ምንጭ አል ወረዕ ሊብኒ አቢ ዱንያ
፠ወደ መጥፎ ነገር (ባጢል) መመልከት ማዘውተር ሀቅን ከማወቅ ይከለክላል።ኢብራሂም ኢብኑ አድሀም ምንጭ ሂልየቱል አውልያዕ 2/8
አሏህ ከሚጠቀሙት ያድርገን።

✍كوني سلفية على الجادة
▪️قال ابن القيم رحمه الله تعالى:

((إن في القلب قسوة لا يذيبها إلا ذكر الله تعالى، فينبغي للعبد أن يداوي قسوة قلبه بذكر الله. ))

📙 [الوابل صيب(١٠٧)]

🔺ልብ ውስጥ አሏህን ማስታወስ እንጂ የማያቀልጣት ድርቀት አለች

አንድ ሰው ልቡን አሏህን በማስታወስ ሊያክም ይገባል
ወጣቶች እንደሚተናኮሏትና እንዳስቸገሯት በመናገር
ለወንድሟ አቤት ያለችውን እህት! ኢስላማዊ አልባሳት መሸጫ ወስዶ ለፊትና የማያጋልጥ ኢስላማዊ ልብስ ገዛላትና መልበስ ጀመረች። ከተወሰነ ጊዜ በኃላ አሁንም ወጣቶቹ ያስቸግሩሻል? በማለት ጠየቃት። የእህቱ ምላሽ፤ "በአላህ ይሁንብኝ ይህንን ልብስ ከገዛህልኝ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ያከብረኛል" የሚል ነበር። ወንድሟ ይህን ሲሰማ እንዲህ አላት « የሚፈታተን ልብስ በመልበስ አንቺ ነበርሽ ማለት ነው የምትለክፊያቸው። እነሱ ቢሆኑ ኖሮ የጨዋ ልብስ ከለበስሽ በኃላም ማስቸገራቸውን ይቀጥሉ ነበር»።

[ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ اﻟﻨَّﺒِﻲُّ ﻗُﻞ ﻷَِّﺯْﻭَاﺟِﻚَ ﻭَﺑَﻨَﺎﺗِﻚَ ﻭَﻧِﺴَﺎءِ اﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﻳُﺪْﻧِﻴﻦَ ﻋَﻠَﻴْﻬِﻦَّ ﻣِﻦ ﺟَﻼَﺑِﻴﺒِﻬِﻦَّ ۚ ﺫَٰﻟِﻚَ ﺃَﺩْﻧَﻰٰ ﺃَﻥ ﻳُﻌْﺮَﻓْﻦَ ﻓَﻼَ ﻳُﺆْﺫَﻳْﻦَ ۗ ﻭَﻛَﺎﻥَ اﻟﻠَّﻪُ ﻏَﻔُﻮﺭًا ﺭَّﺣِﻴﻤًﺎ] الأحزاب 59

«አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» አል አህዛብ 59

አላህ ሆይ! እህቶቻችንን የፊትና ምክኒያት ከመሆን ጠብቃቸው። ከሸይጣን ወታደሮች ሁሉ ሰትራቸው። የትክክለኛ ሒጃብን ውበት አሳያቸው። በሀያእ አስጊጣቸው!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w