💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
#የወለጋ_ላይ_ግፍ__!!
----------------------------
በዘር ፖለቲካ ወገኔ ሲታረድ፡
ዶልዷማ ጀገራ ባጥንቱ ሲሞረድ፡
የሚሰራው በደል ያሳዝናል በጣም፡
ከዘረኝነት ማጥ ለምን አንወጣም!?
-------------------------------------------
ፍትህ ለሌለበት ይሔ ዝቃጭ ስልጣን፡
ስንት ወገን ጨርሶ ስንት ነፍስ አሳጣን፡
ምን አይነት ጋኔን ነው ምን አይነትስ ሰይጣን፡
ሰው እያስገደለ ደሙን የሚያስጠጣን፡
ያ አሏህ በዕዝነትህ ከዚህ መከራ አውጣን??
---------------------------------------------------
ባልሰማ ባላየው በማያውቀው ስሌት፡
የመከራን ቁና ሲሰፍሩበት ቀን ሌት፡
ለመንግስት አካላት ይህ ነው ትልቅ ቅሌት፡
እንመራለን ብለው ሀላፊነት ወስደው፡
ተመርጠናል ብለው ስልጣኒቱን ለምደው፡
በምን ምክንያት ነው ወገኔ የሚያልቀው፡
በዚህ ዘግናኝ ድርጊት ማን ነው የሚፀድቀው?
---------------------------------------------------
ግልፁን ይነገረን ምን ይሆን ትርጉሙ፡
ሀቁን ተናገሩ በቃ አታልጎምጉሙ፡
ፍጠኑ ቸኩሉ ፀፅሞ አትለግሙ፡
ወገን በወለጋ የሚፈሰው ደሙ፡
ለዚህች ሀገር እድገት ያስፈልጋል አፅሙ!?
አወ ወስኑና እውነቱን ንገሩን፡
ሰላምን በመንሳት ሁሌ አታስፈራሩን፡
--------------------------------------------
በዘረኝነት ማጥ ህዝባችን ሲረግፍ፡
መቼ ነው ማቆሚያው የወለጋ ላይ ግፍ፡
----------------------------------------------
በኑረዲን አል አረቢ 1443
---------------------------------------------
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
Audio
✅ አዲስ የኪታብ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖➖

📚አቂደቱ አህሊሱነቲ ወልጀማኣ

【ክፍል፦ ②】

🎙አቡአብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
سورة المجادلة
<unknown>
➛መልካም ቀን

➧እንደ ቁረአን ልብን የሚያረጋጋ ምንም ነገር የለም! የሱን ፍቅር መሰጠት መታደል ነው።
የሙሓመድ አወል መንዙማ ( 9 )
Abu Useymin
➡️ ተከታታይ ሙሐደራ
➛➛➛➛➛➛➛

▪የሙሐመድ አወል መንዙማ!!

➲የሽርክ ስንኞቹ ከራሱ ድምፅ ጋር!

➡️ ክፍል ዘጠኝ

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➧https://t.me/abuUseyminabdurehman/7270

https://t.me/https_Asselefya1
➘የትዳር አጋር የታክሲ ጉዞ አይደለም!!
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧ረጂም ዉጣ ዉረዶች የሚታለፉበት፣ የእድሜ ልክ ጓደኛ፣ የልጆቼ አባት ነው።
ስለሆነም የአንድ ሰው ዐቂዳው መስተካከል ብቻ ለትዳር በቂ መስፈርት ተደርጎ አይቆጠርም
።

➲መንሀጁ ካማረ፣ ሰለፊይ ከሆነ፣ ኡስታዝ ከሆነ በሚል አጉል እይታ ትዳር ዉስጥ እየተዘፈቃችሁ እንዳትሸወዱ። የትዳር አጋርን በምንመርጥበት ወቅት ለስነምግባሩ የምንሰጠው ዋጋ ለዐቂዳው ከምንሰጠው ዋጋ አይነስ።

⇢ስለጠየቅ እሺ ማለት፣ ኡስታዝ ነኝ ስላለ በቶሎ መረታት፣ ቤተሰብን አለማማከር፣ ቤተሰቦች ከተቃወሙም በቃ በሸሪዓ ፍርድ ቤት እናድርገው በሚል መዘፈቅ በተለዬ መልኩ ሴቶችን ይጎዳል።

➛እናም እህቶቼ ጥምረታችን በማስተዋል ላይ የተመሰረተ ይሁን ለማለት ያክል ነው። አወ ትዳርን የመሰለ በዱኒያ ላይ ምንም ነገር እንደሌለ አውቃለሁ ግን እሱም ደስታን ማጣጣም የሚቻለው አላህ ሷሊህ የሆነ ትዳርን ከሰጠን ነው። ምርጫችንን እናስተካክል ምክሩ ለእኔም ለአንቺም ውዷ እህቴ ነው!!
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
027 ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
♦️አዲስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

▪️كتاب منهاج الفرقة الناجية والطائفة المنصورة

➲ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ

▪️ክፍል ሀያ ሰባት
〰〰〰〰〰

♦️የኪታቧን PDF ለማገኘት
➴➴➘➘➷➷➴➴➘➘➷
https://t.me/https_Asselefya1/3725

🎙ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/https_Asselefya1
➲እስኪ እራሳችንን እንፈትሺ ቆንጆ የተውሂድ ጥያቄ ነው ሞክሩት ሊኩን በመጫን ግቡና ሞክሩ

👇👇👇👇👇👇👇👇
إختبروا عقيدتكم https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSedvbsOON6bNmGlj2LkcRNoy3Xxi079Yt-ehRM0Oi_bCpmT5g/viewform?vc=0&c=0&w=1&flr=0&fbclid=IwAR3N-NYB56160z_FJAM144qRcK6i_jBMDcfoS3ym9yOns45We235UuIQki8
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
🎀ከጥሩ ባል መገለጫዎች በጥቂቱ ፡-🎀 ➧በሁሉም ነገር አላህን ይፈራል ➧ከሚስቱ ጋር በጥሩ ስነ-ምግባር ይኗኗራል ➧በተቻለው ያክል ቃሉን ይሞላል ➧ለሚስትና ለልጆቹ መልካም አርዓያ ይሆናል ➧ንግግርና ተግባሩ አንድ ነው (አታላይ አይደለም) ➧ሚስቱን ያከብራል ለሷ ያለውንም ፍቅር ይገልጻል ➧ሸሪዓ የሰጣትን ሐቅ ይጠብቃል ➧ዘመድና ቤተሰቦቿን ያከብራል ➧በሆነ ባልሆነው አይጨቃጨቅም ➧ትርፍ ቃል…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
➲🎀ከጥሩ ሚስት መገለጫዎች🌸💎
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧የትም ብትሆን አላህን ትፈራለች፣ በሁሉም ነገር የነቢዩን ሱና ትከተላለች

➧ባሏ ያዘዛትን በሙሉ -ከዲን ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ- ትታዘዛለች

➧ከሷ ጥሩን ነገር እንጂ እንዳያይ፣ እንዳይሰማና እንዳያሸት ጥረት ታደርጋለች

➧ቤትና ንብረቱን እንዲሁም
ቤተ-ሰቦቹን ትጠብቃለች

➧እሱ የማይፈልገውን ሰው
አትጠጋም አታስጠጋምም


➧ባሏን ሳታሳውቅ ሱና ጾም አትጾምም
ከቤትም አትወጣም


➧የባሏንና የቤቷን ሚስጥር
በሚገባ ትጠብቃለች


➧ባሏን በመልካም ነገር ላይ
ታግዛለች ሲሰንፍ ታበረታታዋለች፣
ሲረሳ ታስታውሳለች


➧ሐላል ከስብ እንዲከስብ ሐራምን እንዲርቅ ዘወትር ትገፋፋዋለች፣ለእሷና
ለቤቱ ብሎ ዲኑ የማይፈቅደውን
ስራ እንዳይሰራም ታሳስበዋለች


➧ደስታና ሃዘኑን ትጋራለች፥
እርሱ ሐሳብና ጭንቀት ውስጥ ሆኖም እሷ አትስቅም፣ እሱ ማረፍና መደሰት በሚፈልግበት ወቅት ላይም እሷ በተቃራኒው ተከፍታ አታስከፋውም

➧በሚያደርግላት ነገር በሙሉ
ይብዛም ይነስ ታመሰግነዋለች

➧ቤቷን እያቀዘቀች የሰው ቤት አታሞቅም ቤቷንም እያፈረሰች የሰው ቤትአትገነባም!

➧ አላህ የሰጣትን ልጆች በኢስላም ስርዓት ቀርጻ ታሳድጋለች ትልቁ የእሷ
ስራም ይህ እንደሆነ በማወቅ በስራዋ ትኮራለች
! ልጅም ያጣች እንደሆነ ታግሳ ተስፋ ሳትቆርጥ ጌታዋን ትለምናለች
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
✅ አዲስ የኪታብ ቂርአት
➖➖➖➖➖➖➖➖

📚አቂደቱ አህሊሱነቲ ወልጀማኣ

【ክፍል፦ ⓷】

🎙አቡአብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
◾️ሸህ ሷሊህ አልፈውዛን "አላህ ይጠብቃቸው" እንዲህ ብለዋል።

✅ ዱአ ካደረጉ በኋላ ፊትን ማበስ በሸሪአችን ያልፀደቀ መሰረት የሌለው ተግባር ነው።

📕[إغاثة اللهفان 27-06-1438 هـ]
➾ፍቅር...

➛ፍቅር ማለት በትንሽ ፊደሎች የተዋቀረ ነገር ግን ትርጉሙ ሰፊ የሆነ ሳያስፈቅድ በልብ ውስጥ ሰርፆ የሚገባ የራሱ የሆነ ግፊት ያለው የፈጣሪ ፀጋ ነው።

➛ፍቅር ማለት ላፈቀሩት ሰው መኖር ማለት ነው። ፍቅር ከቃላት ድርደራ በላይ ተግባራዊ ገለፃን የሚሻ ልዩ ገፀ በረከት ነው።

➛ፍቅር መስዋዕትነትን የሚጠይቅ ላፈቀሩት ሰው ራስን አሳልፎ እስከመስጠት የሚደርስ የሀይል ባለቤት ነው።


➛ፍቅርን በቃል መግለፁ ቀላል ነው ፍቅርን መኖር ግን ከባድ እና ትዕግስትን የመፈታተን ልምድ ያለው ነው።

➛ እውነተኛ አፍቃሪ የሚያፈቅረው ሰው 75% ስህተት ቢኖርበትም 25% መልካምነቱን ብቻ የሚያሳይ ልዩ መነፀር ያለው ነው።


➛ፍቅርን የሚዘምሩ ብዙዎች ናቸው የሚኖሩት ግን ጥቂቶች ናቸው።

➛እውነተኛ አፍቃሪ ፍቅርን በመስጠት የሚሽቀዳደም እንጂ ለመቀበል ሁሌ የሚጓጓ አይደለም።


➛በፍቅር ዐለም ውስጥ መሸነፍ በራሱ ማሸነፍ ነው።ለፍቅር መሸነፍህን ከውርደት የምትቆጥር ከሆነ ለአቅመ ፍቅር አልደረስክም ማለት ነው
።

➛ስለ ፍቅር በመሸነፍ ውስጥ ትልቅ የሆነ ማሸነፍ አለ።

➛እውነተኛ ፍቅር መቀመጫው ልብ ላይ እንጂ ምላስ ላይ አይደለምና የምላስ አፍቃሪ ሆነክ የልብ አፍቃሪዎችን እንዳትጎዳ ተጠንቀቅ!...


➛ብቻ ፍቅርን መግለፅ ከባድ ነውና አፍቅራችሁ ተረዱት።

✍️አላህ ሆይ ፍቅርን ከሚያወሩት ብቻ ሳይሆን ከሚኖሩት ከእውነተኛ አፍቃሪዎች አድርገን።

✍️@ተነካክቶ የተወሰዴ!!

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
🖋ከሚስትም ጠላት አለ‼️
➛➛➛➛➛➛➛➛➛


✍️ሀያሉ አምላካችን የዚህች የቅርቢቱ ዐለም ህይወታችን የተሟላ እንዲሆን ከጎምዛዛና ስልቹ የብቸኝነት እስር ቤት ወጥተን ጣፋጭ የሆነ በመተሳሰብና በመተጋገዝ ላይ የተመሰረተ የሰመረ ህይወት እንዲኖረን ትዳር እንድንመሰርት አዞናል ። ይህም ህይወት ፍሬ አፍሮቶ በልጆች ደምቆ ለቀጣዩ ዐለም የስኬት ህይወት የሚያዘጋጅ እንዲሆን የምታገባት የትዳር አጋርህ አላህን የምትፈራ በኢማን የተዋበች በቁርኣን ያጌጠች በሐዲስ ተኮትኩታ በሱና የታነፀች መሆን እንድትችል መልፋት ይኖርብሃል ። የዚህ አይነትዋ ሚስት የልጆችህ እናት ናት ። ሀላፊነታቸውን ትወስዳለች አንተ ወደ አኼራ ብትሄድም እሷ ልጆችህን ለቁም ነገር ታበቃለች ። አባታችን አላህ ይዘንለት እንዲሉ ትጥራለች ይህ የሚሆነው ግን አንተ በሷ ላይ ከምርጫህ ጀምሮ እስከ መጨረሻው በምትከፍለው ዋጋ ነው ። በተቃራኒው በዲኗ ላይ ካረዳሀት በዱንያዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ ካቶከርክ የቸልታህ ውጤት የሷ ጠላትነት ሊሆን ይችላል ። ለዚህ ነው አላህ ከሚስቶች ውስጥ ጠላት የሚሆኑ እንዳሉ እንዲህ በማለት የነገረን :–

" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ وَأَوْلَادِكُمْ عَدُوًّا لَّكُمْ فَاحْذَرُوهُمْ ۚ وَإِن تَعْفُوا وَتَصْفَحُوا وَتَغْفِرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيم ٌ"
التغابن ( 14 )

" እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! ከሚስቶቻችሁና ከልጆቻችሁ (ከአላህ መንገድ በማስተጓጎል) ለናንተ ጠላቶች የኾኑ አልሉ ፤ ስለዚህ ተጠንቀቋቸው ፤ ይቅርታ ብታደርጉ ብታልፏቸውም ብተምሩዋቸውም አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው።

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1