💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Video message
‏
۞ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى
النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا
عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
۞

https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል 1⃣1⃣0⃣➰
〰〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Forwarded from Ibnu Muhammedzeyn
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አላህ በሚሰጠን ኒዕማ(ፀጋ) እንደምትሐስዱን(እንደምትመቃኙን) ቀድሞ ቁርኣን ነግሮናል።

{وَدَّ كَثِيرٌ مِّنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَوْ يَرُدُّونَكُم مِّن بَعْدِ إِيمَانِكُمْ كُفَّارًا حَسَدًا مِّنْ عِندِ أَنفُسِهِم مِّن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ الْحَقُّ}
«ከመጽሐፉ ባለቤቶች ብዙዎች እውነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በኾነው ምቀኝነት ከእምነታችሁ በኋላ ከሓዲዎች አድርገው ሊመልሱዋችሁ ተመኙ፡፡»[በቀራ 109]

እሄው ሌት ተቀን እኛን ለመመለስ ትጥራላችሁ ትደራጃላችሁ ትለፋላችሁ ግን ደስ የሚለው ብዙዎች ከናንተ ሀይማኖት ነው ወደኛ ሀይማኖት የሚመለሱት‼️

አላህ በሚያወርድልን ኒዕማ እንደምትመቃኙና እንደምጠሉ ገና ሳታሳውቁን በስተፊት ቁርኣን ቀድሞ አሳውቆናል።

{مَّا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَلَا الْمُشْرِكِينَ أَن يُنَزَّلَ عَلَيْكُم مِّنْ خَيْرٍ مِّن رَّبِّكُمْ}

«እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶችና ከአጋሪዎቹም የካዱት በናንተ ላይ ከጌታችሁ የኾነ መልካም ነገር መወረዱን አይወዱም፡፡»[በቀራ 105]

ያው በምቀኝነት (ልክ እንዳንተ) ፊታችሁ ይገረጣል እንጅ በአማኞች ላይ ሌት ተቀን በዝችም ሆና በዛንኛው አለም የአላህ እዘነትና ፀጋ ከመውረድ አይቋረጥም። በቁጭት ሙቱ‼️
ደግሞ "ጋኒን ተሰብስቦ ይስቅባቸዋል ብዬ…" እያለ ያፊዛል አመድ በዱቂት ይስቃል ነው እንጅ ነገሩ ከናንተ በላይ ጋኒን አለ እንዴ!? እሄ ሳቃችሁ እኮ የሰይጣ ስብስብ ሁላ ‼️

እርኩስ የሳት ማገዶ እንኳን እኛ አንተም በእጅህ የጠረብከውን እንጨት አምልከህ እፀድቃለሁ ብለሃል……

⊰✿◇✿⊱•
✍ t.me/IbnuMuhammedzeyn
Audio
✅የጀግና ሴቶች ተምሳሌት!!
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

➛ታላላቅ ሴቶች በኢስላም ያበረከቱት ታሪክ!

➛ሴቶች ሸሪአን ማወቅ ምናክል አንገብጋቢና አሳሳቢ እንደሆነ ከሌሎች ቁም ነገሮች ጋር የተዳሰሰበት ምክር!

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
حفظه الله

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
▪ሴቶች ሆይ!!


▪እናንተ የልጆቻችሁ ታላቅ አስተማሪ ናችሁና እናንተ ከምንም በፊት ተውሂድን ተማሩ።

▪ ምንም የሌለው ምንም መስጠት አይችልም እንደሚባለው ፣ አንቺ የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ተውሂድን ካላወቅሽ ለልጆችሽ ምንም መስጠት አትችይም።

▪ሴቶች ሆይ! ልጆቻችሁን በልጅነታቸው ተውሂድን አስተምሩ ።


▪ወጣቶች ሆይ! ከምንም እውቀት በፊት የተውሂድ እውቀት ይቀድማልና ቅድሚያ ስጡት።


➰ተውሂድ እና ሽርክ

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧ማስታወሻ 2/3/4ተኛሚስት ለመሆን 👉 ከመጣደፍሽ በፊት ካንች በፊት የነበረችዉን እህትሽን አያያዙን አጣሪ ከገቡ ቡኋላ ማለቃቀስ ማፊ ፍይዳ። 👉እናማ አትሩጪ አጣሪ!ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታልና! 👉ገብተሺ ሂወትሺ አበላሽተሺ ከመዉጣትሺ በፊት አገባብሺ አስተካክይ እህቱ! 👉ልብ በሉ ሴቶች!!
👉ተጨማሪ ስላገቡ ብቻ ዘላለም ፀንቶ የሚኖር የሚመስላቸዉ ሞኞች አሉ ያላገቡ እህቶቻቸዉ በምላሳቸዉ በአሽሙር የሚወጉ እረ ተዉ ምን አልባች ያንች ትዳር ፈርሶ እሷ አግብታ በትዳሯ ፀንታ ልትኖር ትችላለች ይህ የአሏህ ስራ ነዉና!!

👉እናማ ስላገባችሁ ብቻ አትኮፈሱ እንደዉም ይህን ትልቅ ነኢማ ለለገሳቸዉ አላህ እያመሰገናችሁ ራሳችሁ ዝቅ አድርጉ ላላገቡ እህቶች አላህ እድወፍቃቸዉ ዱዓ አድርጉ!!

👉ዝም ብላችሁ አትንቦጣረሩ አማኝ አይንጠባረርም
ሁለየ ተናናሺ ነዉ!!!
016 ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
♦️አዲስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

▪️كتاب منهاج الفرقة الناجية والطائفة المنصورة

➲ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ

▪️ክፍል አስራ ስድስት
〰〰〰〰〰

♦️የኪታቧን PDF ለማገኘት
➴➴➘➘➷➷➴➴➘➘➷
https://t.me/https_Asselefya1/3725

🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/https_Asselefya1
▪በላጭ_ሴት!!
➬➬➬➬➬

➧በተውሒድ በሱና የማትደራደር፡
ፈገግታ የሞላት የማትዞር መንደር፡
ዘመድ ጎረቤቷን ወዳጂና አክባሪ፡
የሀላል ንጉሷን የእውነት አፍቃሪ፡
ሀቅ ላይ የፀናች ጥንቁቅ እንስት የምር፡
የውበት አለቃ ሲያዋት የምታምር፡


➧ሰለፍይ ኮከብ ያች ኒቃቢስቷ፡
መንሀጂና አቂዳ የህነው ርስቷ፡
በመልካምነቷ ሁሉም ሰው የሚያፍራት፡
አሏህ በችሮታው አሟልቶ የሰራት፡
ስትጓዝ በአደብ ሳብ ያለ ቁመቷ፡
ሀያዕ የለበሰች በወጣትነቷ፡


➧ብልጥ አርቆ አሳቢ አስተዋይ የሆነች፡
ሚስትነት የገባት መልካም ሴት ይህች ነች፡
የወንድን ልጂ ህይወት ምትሞላው ሀሴት፡
የዘላለም ንግስት ይህች ነች በላጭ ሴት፡

✍️በኑረዲን_አል_አረቢ حفظه الله

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧ከተውሂድ አርማዎች ➛➛➛➛➛➛➛➛ ➭ክፍል አስራ አንድ ➲3⃣ኛው አንኳር ነጥብ ተውሒድን ማረጋገጥና ማሟላት ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➧ተውሒድን ማረጋገጥ ከፍተኛና የላቀ ደረጃ አለው፡፡ ረሡል صلى الله عليه وسلم በታወቀው ሐዲሳቸው የተውሒድ ባለቤቶች ያለምንም ሒሳብ እና ቅጣት ጀነት እንደሚገቡ አውስተዋል፡፡ ▪️وعن ابن عباس وغيره رضي الله عنهم قال صلى…
➲ከተውሂድ አርማዎች
➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧ክፍል አስራ ሁለት
➻➻➻➻➻➻➻

➲እነዚህ በሁለቱም ክፍል ያሉ ተውሂድን አረጋጋጭ ሰዎች - ሙቅተሲድና በመልካም ተሸቀዳዳሚዎች - የትንሳኤ ቀን ያለምንም ሂሳብና ቅጣት ጀነትን ይገባሉ፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

▪️ثُمَّ أَوْرَثْنَا الْكِتَابَ الَّذِينَ اصْطَفَيْنَا مِنْ عِبَادِنَا ۖ فَمِنْهُمْ ظَالِمٌ لِّنَفْسِهِ وَمِنْهُم مُّقْتَصِدٌ وَمِنْهُمْ سَابِقٌ بِالْخَيْرَاتِ بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَضْلُ الْكَبِيرُ

➧“ከዚያም እነዚያን ከባሮቻችን የመረጥናቸውን መጽሐፉን አወረስናቸው፡፡ከእነርሱም ነፍሱን በዳይ አልለ። ከእነርሱም መካከለኛ አልለ፡፡ከእነሱም በአላህ ፈቃድ በበጎ ስራዎች ቀዳሚ አልለ፡፡ ያ (ማውረስ) ፤ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው፡፡” (ፋጢር፡32)

➲ሶስቱም ክፍሎች - ነፍሱን በዳይ ፣ሙቅተሲድ (መካከለኛዎች) እና በመልካም ተሸቀዳዳሚዎች - ዘውታሪ የሆኑ ገነቶችን ይገባሉ፡፡ ሙቅተሲድ እና በመልካም ተሸቀዳዳሚዎች፡ ያለምንም ሂሳብ ጀነት ይገባሉ፡፡

➧ከሽርክ በታች በሆኑ ወንጀሎች ነፍሳቸውን በዳዮች ደግሞ ጀነትን ይገባሉ፡፡ ነገር ግን ነፍሳቸውን የበደሉት ልክ እንደ ሙቅተሲድና በመልካም ቀዳሚዎች ያለምንም ሂሳብና ቅጣት መጀመሪያ ጀነትን አይገቡም፡፡ ይልቁንም ለቅጣትና ለሂሳብ ይቀርባሉ፡፡ በአላህ መሽአ ውስጥ ናቸው፡፡ አላህ ከፈለገ ቀጥቶ ጀነት ያስገባቸዋል ወይም ምህረት
ያደርግላቸዋል፡፡

➧አራተኛው አንኳር ነጥብ የተውሒድ አፍራሽና አጉዳዮች
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➲ተውሒድ የራሱ የሆነ አፍራሽና አጉዳይ አለው፡፡ የተውሒድ አፍራሾች ስራን የሚያሰርዙ ሀይማኖቱን በአጠቃላይ የሚያበላሹ ናቸው፡፡ እነርሱም በአላህ መካድ፣ማጋራትና ጥርት ያሉ ንፍቅናዎች ናቸው፡፡ የክህደት ፣ የማጋራት እና የትልቁ ንፍቅና አይነቶች ከመሰረቱ ተውሂድን ያፈርሱታል ፣ ይንዱታል፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጹ የሚከተለውን ተናግሯል፡

▪️وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ

➧“ብታጋራ ስራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሃዲዎቹ ትሆናለህ ማለት
ወደ አንተም ወደእነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል
፡፡” (አዝ ዙመር:65)

➲የተውሒድ አጉዳዮች፡ ማለት ደግሞ ተውሒድን ሙሉ በሙሉ የማያበላሽ የማይንድ ነገር ግን የሚቀንስ ነው፡፡ ከነዚህ መካከል ትንሹ ክህደትና ተግባራዊ የሆነው ንፍቅና ናቸው ፡፡

▪️የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በሚከተለው ሐዲስ ተናግረዋል፡-

▪️"آية المنافق ثلاث: إذا حدث كذب ، وإذا وعد أخلف ، وإذا اؤتمن خان"

“የመናፍቃን ምልክት ሶስት ናቸው፡ ሲያወራ ይዋሻል ፣ ቃል ሲገባ ያፈርሳል ፣ ሲያምኑት ይከዳል” ቡኻሪ፡ 33 ሙስሊም፡59

➧ይህ ተውሒድን የሚቀንስ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች ከባሪያው ላይ ከተገኙ ተውሒዱን እና ኢማኑን ያጎድሉታል፡፡ ትንሹ ማጋራት ፣ ማጋራትን ሳያስብ በአንደበቱ የማጋራት ቃላትን መናገር ተውሂድን ይቀንሳል፡፡ ነገር ግን ማጋራትን አስቦ ከሆነ ተውሒዱን ሙሉ በሙሉ ከሚያፈርሱት ትልቁ ማጋራት ውስጥ የሚገባ ይሆናል፡፡

በዚህ ምክንያት እያንዳንዱ አማኝ ሙሉ በሙሉ አፍራሽም ይሁን አጉዳይ ነገሮችን በመራቅ ተውሒዱን መጠበቅ ፣መንከባከብ ይኖርበታል፡፡

▪️ሸይኽ ዓብዱረህማን ብን ሀሰን - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

((የተውሒድ ተቃራኒ ሽርክ መሆኑን እወቅ፡፡ እነርሱም ሶስት አይነቶች ሲሆኑ ትልቁ ማጋራት ፣ ትንሹ ማጋራት እና ድብቁ ማጋራት ናቸው፡፡

▪️ለትልቁ ማጋራት መረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው፡

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا

“አላህ በርሱ የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡” አን ኒሳእ፡116

▪️لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

“አልመሲህም አለ፡- “የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን
ተገዙ፡፡” እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም
አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡”
አል ማኢዳህ፡72

➛ይህ አይነቱ ማጋራት አራት አይነት ክፍሎች አሉት የሚለውን በቀጣይ ክፍል እናየዋለን።
◉
◉
◉✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል


تأليف: فضيلة الشيخ عبدالرزاق بن عبد المحسن البدر

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】

🖊ام فاروق

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➧ልብ ትዝጋለች ፣ ብረት እንደሚዝገው ሁሉ ማፅጃዋ አሏህን ማውሳትና ቁርኣን መቅራት ናቸው ።
አሏህ ሆይ የአንተን ውዴታ ወፍቀን!✍

▪️صباح الخير اذكار صباح የጧት ዚክርን እንዳረሱ ባረከላህ ፊኩም

🌹መልካም ቀን🌹☕️
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ማስታወቂያ
~
ረመዷን ሊገባ ሲል ተቋርጦ የነበረው አንፎ አካባቢ የሚሰጠው ደርስ ኢንሻአላህ የፊታችን እሁድ ይጀምራል።
.
መልእክቱን አሰራጩልን ባረከላሁ ፊኩም።
▪️سٌئل أحد السلف : كيف أصبحت؟

قال : أصبحنا وبنا من نعم الله
‏ما لا نحصيه مع ك؍ع؊ ما نعصيه فما ندري أيهما نشكر ؟! أجميل ما ظَهر أم قبيح ما ستع

[ الشكر ] لابن أبي الدنيا (٦٦/١).

➲ከሰለፎች ለአንዱ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ ፦እንዴት አነጋህ ?


እንዲህ አለ :- «ከምናምፀው በበለጠ ብዙ የአላህ ኒዕማ ላይ የትኛውን እንደምናመሰግን አላውቅም አላህ የሚወደው ግልፁ ወይስ በሚሰትረው ድብቅ መጥፎ

☞︎︎︎አሽሹክር ሊብኒ አቢ ዱንያ ( 1/66 )
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
سورة المائدة
Abu Useymin
🌅የማለዳ ማራኪ ቲላዋ ግባዣ!
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛

📚سورة المائدة كامله!

◉ቁርአን ማንበብና እንዲሁም በትኩረት ማዳመጥ ትልቅ ኢባዳ ነው!


🎙በአቡ ዑሰይሚን حفظه الله

➧https://t.me/abuUseyminabdurehman/6650

https://t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمني الله وإياه:-

[ وَاَللَّهُ يُحِبُّ الْكَلَامَ بِعِلْمِِ وَعَدْلٍ وَيَكْرَهُ الْكَلَامَ بِجَهْلِِ وَظُلْمٍ ]


«አላህ በፍትሀዊነትና በእዉቀት ላይ የተመሰረተ የሆነን ንግግር ይወዳል ፡፡ የበደለኝነትና የድንቁርና የሆነን ንግግር ደግሞ ይጠላል አይወድም »

【مجموع الفتاوى ( ٩٦/١٦) 】


https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል 1⃣1⃣1⃣➰
〰〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
መረጃ አይናቅም ሸር እንደራረግ አደራ!!

👉#ደሴ_ላይ_የታሰሩ_ዑስታዞቻችን__!!

ወደ ሌላ ቦታ ሊዘዋወሩ እንደሆነ መረጃወች እየወጡ ነው

ዛሬ ከ5:00 በኋላ ሊጠይቁ የሔዱ ወንድሞቻችን በተላላኪ ካልሆነ ፊት ለፊት መገናኘት አትችሉም ተብለው ተመልሰዋል።

በመሆኑም የግፍ አስረኞቻችን እስካሁን ለምን እንደታሰሩ ያላወቁ ከመሆኑም በላይ ከታሰሩበት ሰአት ጀምሮ ምንም የተባሉት ነገር እንደሌለ ተናግረው አሁን ግን ወደ ሌላ ቦታ ሊወስዷቸው እንደሆነ መረጃወች ያመላክታሉ።

#አብሽሩ_ጀግኖቻችን__!!
---------------------------------
በሀቅ ላይ ቆሞ በሰለፎች አሰር፡
መሞትም ክብር ነው እንኳንስ መታሰር፡

#ለማለት_ተገድጃለሁ_ኑረዲን__!

http://t.me/nuredinal_arebi

ያኢላሂ አንተው ጠብቃቸው !
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የመልካም ሚስት ስብዕና ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ ➭ለባሏ ደስታን የምትፈጥር ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➲"አይኔንም አልጨፍንም" ማለት ይቅር ብለኸኝ በእኔ ደስተኛ እስከምትሆን፣ ይሄንንም በዓይኔ አይቼ እስከማረጋግጥ ድረስ ለእንቅልፍም እራሴን አላዘጋጅም አልተኛም ለማለት ነው። በጣም የሚያሳዝነው ግን አንዳንድ ሴት ባሏ አንድ፣ ሁለት ወይም ሶስት ለሊት ከዚያም አልፎ ሳምንታትና ወር ድረስ በእርሷ…
➧የመልካም ሚስት ስብዕና
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➧ባሏን አፍቃሪ
➻➻➻➻➻➻

▪️تزوّجوا الودود الولود ، فإني مكاثِرٌبكم الأمم يوم القيامة

➲"አፍቃሪ እና ወላድ የሆነችን ሴት አግቡ፣ ምክንያቱም እኔ የቂያማ ዕለት (ከሌሎቹ) ሕዝቦች ጋ እፎካከርባችኃለሁና።

ስለሆነም አንዲት ሚስት ልጆችን ለመውለድ ጥረት ማድረግና ለዚህም የሚያስፈልጉ ሰበቦችንም ማድረስ ይጠበቅባታል። እንድሁም ልጆችን ኮትኩቶ ማሳደግ፣ በመልካም ባህሪ አንፃ ማብቃት፣ መጠበቅና መከባከብ ላይ ከፍተኛ ጥረትና ትግል ማድረግ ይገባታል።

➧ይህንንም ስትፍፅም ከአላህ የምታገኘውን ምንዳ እያሰበች መሆን አለበት በማህበረሰቡ ዘንድ መልካም የሆኑ ልጆች የለውጥ አርዓያ የሆኑ (አስተካካይ) ዱአቶች (ተጣሪዎች) እንድፈጠሩ ምክንያት ለመሆን እቅድ መሆን ይገባል። ይሄንን አላማ ወደ ትዳር ከገባችበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።

➲እንድህ በማለት በእራሷና በአላህ መካከል (ቃል ትግባ) ምን አልባትም አላህ የቅን ጎዳና መሪ ወይም የሙስሊም ምሁራንና ልሂቃን ወይም ወደ መልካም የሚጣሩ (ዱዓት) በሆኑ ልጆች ያከብረኝና ያልቀኝ ይሆናል። በዚህም መልካምና ታላቅ እሳቤዋ እንድሁም ልጆቿን በአግባቡ በመንከባከቧና በመጠበቋ ለዚህም በሰጠችው ትኩረት ታላቅ ምንዳ ይፃፍላታል።

➧ አል ሙዋቲየቱ المُوَاتِيَةُ
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛

➲"አል ሙዋቲየቱ" ማለት ዐመለ መጥፎ (ግርጭርጭ) እና ልበ ደረቅ (ጨካኝና ግትር) ያልሆነች ማለት ነው። ይልቁኑ እርሷ ታጋሺና ቻይ (ገር እና ለስላሳ) ባሏን የምታዳምጥና የምትታዘዝ፣ መልካም ምላሺ የምትሰጥ፣ ትዕቢተኛ ወይም እብርሪተኛ ያልሆነች፣ የማትጠባረር፣ በባሏ ላይ ራሷን የማትሰቃቅል( ከፍ ከፍ የማታደርግ) እንድሁም ባሏን የማታምፅና በእርሱ ላይ የበላይነት የማይሰማት ናት።

➧ አል ሙዋሲየቱ المُوَاسِيَةُ
➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻

➲ "አል ሙዋሲየቱ" ማለት ባሏን የምትመክር (የምታፅናና) እና ከባሏ ጎን የምትቆም ማለት ነው። በመልካም ተግባርና አላህን በመታዘዝ ላይ ረዳት የምትሆን ናት። ደስታና ስኬትን በሚያስገኝ ነገር ላይ ሁሉ አለኝታው የሆነች ናት።

➧አላህን ከፈሩ "إِذَا اتَّقَيْنَ اللَّه"
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➠አላህን ከፈሩ" ሲባል እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ መገለጫ ባህሪያት አንዲትን ሴት የሚጠቅማት ልዕለ ሀያልና ከፍ ያለውን አላህን ከፈራችና ከተጠነቀቀች ብቻ ነው ። አፍቃሪ፣ ወላድ፣ ቻይ እና ታጋሺ እንዲሁም ባሏን አፅናኝና አጋዥ ብትሆን እንኳ በእነዚህ ነገሮች የዱኒያ ጥቅምን ብቻ የምትፈልግና አላህን የምትፈራ ከሆነች እነዚህ ባህሪያት ምንም አይጠቅሟትም።

➛ይልቁኑ እነዚህ ባህሪያትና መልካም መገለጫዎች የሚጠቅሟት የአላህን ውደታ ፈልጋ የተላበሰቻቸውና ለአላህ ያላትን ፍራቻ ተግባራዊ ለማድረግ (በፍፁምነት ለማሟላት) ፈልጋ የታገለችና የጣረች ከሆነ ብቻ ነው።
◉
◉
◉
◉✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

➧የመልካም ሚስት ስብዕና ከሚለው ከአብዱረዛቅ ቢን ዐብዱልሙሕሲን አልበድር ኪታብ የተወሰደች!

🖊ام فاروق
➧ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1